Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.7K subscribers
40.2K photos
309 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
#አህጉር_አቀፍ #የሰላም_ኮንፈረንስ‼️

አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ "የበለጸገች ሰላማዊና አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሀሳብ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ በተገኙበት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

በኮንፍረንሱ ላይ 22 የአፍሪካ አገራትና የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችን ጨምሮ ከ400 በላይ ሰዎች ይሳተፋሉ።

በመርሃግብሩ የሰላም ኤግዚቢሽን የዶክመንተሪ ዝግጅትና ውይይቶችን የሚካሄድ ሲሆን ተሳታፊዎች የመዲናዋን የኮሪደር ልማት አድዋ ሙዚየምንና የተለያዩ የሰላም ተቋማት ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ ህዳር 16 እና 17 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ መገለጹ ይታወሳል።

በኮንፍረንሱ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ ርዕሰ መስተዳድሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በማርቆስ በላይ

ህዳር 16 ቀን 2017 ዓም
👍6👎1
አፍሪካ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በንግድና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ጠንካራ አሰራሮችን ልትከተል ይገባል"
- ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ስላሴ
******
(ኢ ፕ ድ)

አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ የበለጸገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ስላሴ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ አፍሪካ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በንግድና በቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ጠንካራ አሰራሮችን ልትከተል ይገባል። አፍሪካ ያላትን አቅም ተጠቅማ ወደፊት መራመድ እንዳለባትም ጠቁመዋል።

አፍሪካ ለሚመጡ የሰላምና የብልጽግና ተግዳሮቶችና እድሎች እራሷን ማዘጋጀት አለባት ያሉት ፕሬዚዳንቱ አፍሪካ ዘላቂ ሰላም ለመገንባት በንግድና በቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ጠንካራ አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ኮንፈረንሱ የአፍሪካ ሰላምና ልማት የሚያበረታቱ ሀሳቦችን ለማፍለቅ እንደሚረዳ ጠቅሰው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ሰላምን ለማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

የተወሳሰቡ የሰላም ግንባታ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ተቋማትን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ የአየር ንብረት ለውጥ ስጋትን ለመቅረፍ ዘላቂ መፍትሄዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ለአህጉሪቱ ምሳሌ እንደሚሆን ገልጸዋል።

ኮንፍረንሱ ሰላምና ብልፅግናን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት እንደሚያበረታታ ያላቸውን እምነት በመግለጽ መተባበርና የጋራ ግቦች ለአፍሪካ እድገት ወሳኝ ናቸው ብለዋል።

በማርቆስ በላይ

ህዳር 16 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍6😁21
#የኢትዮጵያአየርመንገድ #ስታርአላያንስ

የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ 25 የአለማችን ግዙፍ አየር መንገዶች ሕብረት የሆነው “ስታር አላያንስ” የ2024 ምርጥ የአየር መንገዶች ህብረት በሚል ተሸልሟል፡፡

“ስታር አላያንስ” ውድድሩን ሲያሸነፍ ይህ ለ5ኛ ተከታታይ ዓመት መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የዘንድሮው የሽልማት አሰጣጥ መርሐግብር በፖርቹጋል ማዲዬራ መካሄዱንም ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ህዳር 16 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍10👏1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት #Instagram ገፅን ፎሎ፣ ላይክ፣ ሼር ያድርጉ‼️
https://www.instagram.com/agencyethiopianpress/
2🔥2👍1
ሲቪል ሰርቪሱ ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ መሆኑ ተጠቆመ
******
(ኢ ፕ ድ)

በአሁኑ ወቅት ያለው የሲቪል ሰርቪሱ ቁጥር ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ መሆኑን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ ዶ/ር አስታወቁ።

የቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው ነገሪ (ዶ/ር) በተለይም ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ በየመንግሥት መሥሪያ ቤቱ ያለው የሠራተኛ ቁጥር በጣም በርካታ ነው። ሀገሪቷ ከምትሸከመውና አገልግሎቱ ከሚፈልገው በላይ የበዛ ነው። ከአደረጃጀት አንጻር ሲታይም በአንድ መሥሪያ ቤት ውስጥ መዋቅሩ የሚሸከመው ብዙ የሰው ኃይልን ነው፤ በተሸከመ ቁጥር ደግሞ የሚያገኘው ጥቅም አናሳ ነው።

የመንግሥት ሠራተኞች የብዛታቸውን ያህል የሚሠሩት አገልግሎት የሚያረካ አይደለም ያሉት ዶ/ር ነገሪ፤ የተወሰኑ ይሠራሉ፤ ሌሎቹ ግን የተወሰኑ ሠራተኞች ሌሎቹ ግን የተወሰኑ ሠራተኞች በሠሩት ትከሻ ላይ ተንጠላጥለው.....
https://press.et/?p=141511

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ኢንታግራም https://www.instagram.com/agencyethiopianpress/
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍18😁3
በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ልዊሳ ፍራጎሶ እና በኢትዮጵያ የሮማኒያ አምባሳደር ጂሊያ ፓታቺ ጉብኝት
*****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ልዊሳ ፍራጎሶ እና በኢትዮጵያ የሮማኒያ አምባሳደር  ጂሊያ ፓታቺ ብርሃን የአይነስውራን 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።

በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ዘላቂ ለውጥን ለማምጣት መሰረት በማድረግ እየተተገበሩ ካሉ ፕሮጀክቶች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ጥራት ያለው ትምህርትን ተደራሽ ማድረግ አንዱ ነው።

በዚህ መሰረት ከተገነቡ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ብርሃን የአይነስውራን 2ኛ ደረጃ አዳሪ ትምህርት ቤትን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ በኢትዮጵያ ለፖርቹጋል አምባሳደር ልዊሳ ፍራጎሶ እና በኢትዮጵያ ለሮማኒያ አምባሳደር ጂሊያ ፓታቺ ማስጎብኘታቸውን በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

ኢንታግራም፣https://www.instagram.com/agencyethiopianpress/
👍2👎1