የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት‼️
ፓፓያ ለሀገር ውስጥ አቅርቦት በመዋሉ እንዲሁም ለውጭ ገበያ ባለው እምቅ አቅም የተነሳ በኢትዮዽያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ካላቸው የፍራፍሬ ዝርያዎች አንዱ ነው። የበለፀጉ የግብርና አሰራሮችን በመጠቀም አርሶአደሮች ከፍ ያለ ምርት እና የላቀ ትርፍ ሊያገኙ ይችላሉ። በፓፓያ ምርት ሥራ የተሰማሩ ሁሉ ጥረቶቻቸውን በእጥፍ በመጨመር እንዲተጉ ጥሪ አቀርባለሁ።

👍19❤2😁1
#አህጉር_አቀፍ #የሰላም_ኮንፈረንስ‼️
አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ "የበለጸገች ሰላማዊና አፍሪካን እንገንባ" በሚል መሪ ሀሳብ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ በተገኙበት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።
በኮንፍረንሱ ላይ 22 የአፍሪካ አገራትና የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችን ጨምሮ ከ400 በላይ ሰዎች ይሳተፋሉ።
በመርሃግብሩ የሰላም ኤግዚቢሽን የዶክመንተሪ ዝግጅትና ውይይቶችን የሚካሄድ ሲሆን ተሳታፊዎች የመዲናዋን የኮሪደር ልማት አድዋ ሙዚየምንና የተለያዩ የሰላም ተቋማት ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ ህዳር 16 እና 17 በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ መገለጹ ይታወሳል።
በኮንፍረንሱ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱዓለም፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ ርዕሰ መስተዳድሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በማርቆስ በላይ
ህዳር 16 ቀን 2017 ዓም

👍6👎1
አፍሪካ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በንግድና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ጠንካራ አሰራሮችን ልትከተል ይገባል"
- ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ስላሴ
******
(ኢ ፕ ድ)
አህጉር አቀፍ የሰላም ኮንፍረንስ የበለጸገችና ሰላማዊ አፍሪካን እንገንባ በሚል መሪ ሀሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ስላሴ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ አፍሪካ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ በንግድና በቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ጠንካራ አሰራሮችን ልትከተል ይገባል። አፍሪካ ያላትን አቅም ተጠቅማ ወደፊት መራመድ እንዳለባትም ጠቁመዋል።
አፍሪካ ለሚመጡ የሰላምና የብልጽግና ተግዳሮቶችና እድሎች እራሷን ማዘጋጀት አለባት ያሉት ፕሬዚዳንቱ አፍሪካ ዘላቂ ሰላም ለመገንባት በንግድና በቴክኖሎጂ ላይ ያተኮሩ ጠንካራ አሰራሮችን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ኮንፈረንሱ የአፍሪካ ሰላምና ልማት የሚያበረታቱ ሀሳቦችን ለማፍለቅ እንደሚረዳ ጠቅሰው የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ሰላምን ለማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
የተወሳሰቡ የሰላም ግንባታ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ተቋማትን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ የአየር ንብረት ለውጥ ስጋትን ለመቅረፍ ዘላቂ መፍትሄዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ለአህጉሪቱ ምሳሌ እንደሚሆን ገልጸዋል።
ኮንፍረንሱ ሰላምና ብልፅግናን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት እንደሚያበረታታ ያላቸውን እምነት በመግለጽ መተባበርና የጋራ ግቦች ለአፍሪካ እድገት ወሳኝ ናቸው ብለዋል።
በማርቆስ በላይ
ህዳር 16 ቀን 2017 ዓም
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et

👍6😁2❤1