Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መዳረሻዎች ቁጥር 140 መድረሱ ተገለጸ
**************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን 80ኛ የምስረታ በዓልን አስመልከቶ የትራንሰፖርትና ሎጂስቲክስና የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን በጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ እንደገለፁት፤ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከ114 አገራት ጋር የሁለትዮሽ የአየር ትራንስፖርት ስምምነት ተፈራርሟል።

በዚህም የአየር መንገዱ የበረራ መዳረሻዎች ቁጥር 140 ደርሷል ብለዋል::

ኢትጵያን ከተቀረው ዓለም ጋር በማገናኘት፣ ንግድና ቱሪዝምን በማቀላጠፍ ረገድ ለሚደረገው ሥራ የአቪዬሽን ባለስልጣን ድርሻ ትልቅ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የኢትዮጵያ የአየር ትራንስፖርት ጥራትና ደህንነቱ የጠበቀ እንዲሆን የባለስልጣኑ ሚና ትልቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት መሰረት በዓለም ላይ ጥራቱ የተጠበቀ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት ከሚሰጡ ጥቂት ሀገራት መካከል የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን አንዱ ነው ሲሉ ገልፀዋል::

የትራንሰፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ደኤታ አቶ ደንጌ ቦሩ በበኩላቸው፤ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን የምስረታ በአል ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2017 ዓ.ም በተለያዩ ፕሮግራሞች ያከብራል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ምስረታን የተቀላቀለችው የአየር ትራንስፖርት በተጀመረበት ጊዜ ነው ያሉት ሚኒስትር ድኤታው፤ ላለፉት 80 ዓመት በስኬት ቆይቷል ብለዋል።

ትልቅ አየር መንገድ በማቋቋም ዓለምን የማገናኘት ሥራ አየተሠራ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ ስኬት ጀርባ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬን ባለስልጣን ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።

ጥራቱና ደህነቱ የተረጋገጠ የአየር ትራንስፖርት እንዲኖር በማድረግ ረገድ የተጫወተው ሚና ጉልህ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ተወዳዳሪና ተመራጭ አዬር መንገድ አንድኖራት ማስቻሉንም ገልፀዋል::

ከአቪዬሽን ኢንዱስትሪውን ፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይታያል ያሉት ሚኒስትር ድኤታው፤ ከጀርባ ደግሞ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ያለው ድርሻ ትልቅ ነው።

ባለፉት 80 ዓመታት ውስጥም ስኬታማ አየር መንገድ አብዲኖር የባለስልጣኑ ድርሻ ጉልህ መሆኑን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የኤርፖርቶች ቁጥር 23 ሲሆን ከዚህ ውስጥ 4ቱ ዓለም አቀፍ ደረጃ የያዙ መሆናቸውም ተጠቅሷል።

በሞገስ ፀጋዬ
ህዳር 23 ቀን 2017 ዓም
👍101
አቶ ፍሬዘር በቀለ ከመንገደኛ ወድቆ ያገኙትን 50ሺህ የአሜሪካ ዶላር በታማኝነት ለመንገደኛው አስረከቡ
****
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴኪዩሪቲ ክፍል ባልደረባ የሆኑት አቶ ፍሬዘር በቀለ ህዳር 16 ቀን 2024 ዓ.ም ከመንገደኛ ወድቆ ያገኙትን 50ሺህ የአሜሪካ ዶላር በታማኝንት ለመንገደኛው ማስረከባቸውን አየር መንገዱ አስታወቀ።

የአየር መንገዱ እንደገለጸው፥ ባልደረባው በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ሲቀጠር በገባው ቃል መሰረት አየር መንገዱ የሚመራበትን መርህና ሥነ ምግባር አክብሯል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም-አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና ስነ-ምግባር የተላበሰ የደንበኞች አገልግሎት ለማሳደግ ምንግዜም ያላሰለሰ ጥረት እንደሚያደርግ አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
👍147
ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ያደጉት ኢንዱስትሪ ፓርኮች‼️

✍️ አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ

✍️ ባህርዳር ኢንዱስትሪ ፓርክ

✍️ ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ

✍️ ደብረ ብረሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ

✍️ሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ

✍️ ጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ

✍️ ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ

✍️ ኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ

✍️ መቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ

✍️ ሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ፓርኮቹ ያሉበትን ደረጃ በመገምገም አስፈላጊውን መስፈርት ያማሉ 10 ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን እንዲያድግ ወስኗል።

በኢትዮጵያ የሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ለማሳደግ አዋጅ ቁጥር 1322/2016 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቆ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።

ህዳር 24 ቀን 2017 ዓም
👍6