Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ለአምራች ኢንዱስትሪው ምቹ የገበያ ዕድል ፈጥሯል
*******
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ለአምራች ኢንዱስትሪው ምቹ የገበያ ዕድል መፍጠሩን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ታረቀኝ ቡሉልታ ገለጹ።

ሚኒስትር ዴኤታው ከቻይና ሻንዶንግ ግዛት ምክትል ገዢ ሶንግ ጁኒል ጋር ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል፣ በግብርና ሜካናይዜሽን፣ በማኑፋክቸሪግ፣ በማዕድንና በቱሪዝም ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ነው ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለው ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ለኢንዱስትሪው ምቹ የገበያ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል።

የቻይና ሻንዶንግ ግዛት ምክትል ገዢ ሶንግ ጁኒል ለኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ፣ በንግድ፣ በኢኮኖሚ፣ በቱሪዝምና በትምህርት ያለንን እውቀት ለማካፈልና ኢንቨስት ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ ገልጸዋል።

በሸገር ከተማ ሰበታ የሚገኘውን ውዳ ኢንዱስትሪል ግሩፕን ገብኝተዋል። ኢንዱስትሪ ግሩፕ ወደ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ማደጉ ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ እድገት ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ አቶ ታረቀኝ በጉብኝቱ ገልጸዋል፡፡

ኢንዱስትሪ ፓርኩ ወደ ስራ ሲገባ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂና ዘርፈ ብዙ ምርቶችን የሚያመርት በመሆኑ የኢንዱስትሪውን እደገት ማሳያ ነው።

ውዳ  ኢንዱስትሪያል ግሩፕ በሸገር ከተማ ሰበታ የኢንዱስትሪ ፓርክ ለማቋቋም ሂደት ላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ኢንዱስትሪ ፓርኩ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ ለአስር ሺህ ሰዎች የስራ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማምረት ሂደት ላይ መሆኑን ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓም
👍3😁2
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክት ‼️

ዛሬ ጠዋት የአልጀሪያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍን በጽሕፈት ቤታችን ተቀብያለሁ። እንደልዩ መልዕክተኛ ከፕሬዝዳንት አብዱልመጅድ ቴቡኔ የተላከ መልዕክት አድርሰዋል። በኢትዮጵያና በአልጀሪያ መካከል ያለንን የፀና ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።

ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍14
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአልጀሪያ ከፕሬዝዳንት አብዱልመጅድ ቴቡኔ የተላከ መልዕክት ተቀበሉ‼️
👍1
#ቱሪዝም_ገበታለሀገር_ገበታለትውልድ‼️

ኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ አምስት የአፍሪካ የቱሪዝም መዳረሻዎች አንዷ እንደትሆን በቱሪዝም የመሠረተ ልማት ሥራዎች ላይ እየሰራ ይገኛል። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ለጂዲፒ ባለው አስተዋፅዖ፣ በሚፈጥረው የሥራ እድልና በሚያስገኘው የውጭ ምንዛሪ የተነሳ እጅግ አስፈላጊ የእድገት ምሰሶ ነው።

ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍74😁2
#አዲስ_ዘመን_ዛሬ‼️
የታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ
https://press.et/?p=143135
1
ቻይና አረንጓዴ ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት በንቃት እየተሳተፈች ነው
*****
(ኢ ፕ ድ)

ቻይና በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው የአረንጓዴ ልማት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት በንቃት እየተሳተፈችና ድጋፍ እያደረገች መሆኑን በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቸን ሃይ ገለጹ።

አምባሳደሩ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ ቻይና እኤአ በ2030 የካርቦን ልቀትን ለመቀነስና በ2060 ካርቦን ነፃ የሆነ ኢኮኖሚ ለመገንባት የተለያዩ ስትራቴጂዎችንና ፖሊሲዎችን ቀርጻ በመተግበር ላይ ትገኛለች። በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ ደረጃ ቀጣይነት ያለው አረንጓዴ ኢኮኖሚያዊ እድገት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥም በንቃት እየተሳተፈችና ድጋፍ እያደረገች ነው ብለዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተነደፈው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርም በፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ ይፋ ከተደረገው ሥርዓተ ምሕዳርን የጠበቀ እድገት ማ ስመዝገብ ጋር የሚጣጣም መሆኑንም ጠቁመዋል።

ሁለቱ ሀገራት ቃላቸውን ወደ ተግባር በመቀየር ላይ የሚገኙና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት ምሳሌ የሚሆን ሥራ እየሠሩ ነው ያሉት አምባሳደር ቸን፤ የቻይና ባለሀብቶች የአረንጓዴ ዐሻራ....https://press.et/?p=143140
👍3
ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ማጠናከር ትሻለች
******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ማጠናከር እንደምትሻ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) አስታወቁ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ በጀመረው የኢትዮጵያና የአውሮፓ ኅብረት የስትራቴጂክ አጋርነት መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የሚመራ የኢትዮጵያ ልዑክ እና በአዲስ አበባ የሚገኙ የአውሮፓ ኅብረት አባል አገራት አምባሳደሮች እና ተወካዮች እየተሳተፉ ናቸው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በዚሁ ጊዜ የአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ ቁልፍ የሠላምና የልማት አጋር መሆኑን ገልጸዋል።

አጋርነቱን ተጠቅማ ኢትዮጵያ ከኅብረቱ ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እንደምትሻ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ከአውሮፖ ኅብረት አምባሳደሮችና ተወካዮች ጋር የሚደረገው ውይይትም በሠላምና ጸጥታ፣ በኢኮኖሚ ልማትና በባለብዙ ወገን ትብብር ላይ ያተኮረ መሆኑን አመልክተዋል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ኅብረት አምባሳደር ሶፊ ፍሮም ኢመስበርገር በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሠላምና መረጋጋት ወሳኝ ሚና እንዳላት አስረድተዋል።

የአውሮፓ ኅብረት በቀጣናው ሠላምና ደህንነት እንዲሰፍን የበኩልን ድርሻ እንዳለውም መናገራቸውን ውይይቱን የተከታተሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያና የአውሮፓ ኅብረት ያላቸውን ትስስር ለማጠናከር እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2016 የስትራቴጂክ አጋርነት ትብብር መፈራረማቸው ይታወቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓም
👍5😁1
ኢትዮጵያ ከ400 በላይ የባቡር ምህንድስና ባለሙያዎች ቢኖሯትም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት የለም
******
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ ከ400 በላይ የባቡር ምህንድስና ባለሙያዎች ቢኖሯትም፣ በባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ የተሰማራ ተቋም አለመኖሩን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጌቱ ግዛው (ኢ/ር) ለኢፕድ እንደገለጹት፣በኢትዮጵያ ውስጥ የባቡር መንገድ የሚገነባ አንድም ድርጅት የለም፡፡

በዚህም ኮርፖሬሽኑ በራስ አቅም ወደ ዘርፉ ኮንስትራክሽንና ማማከር ሥራ ለመግባት እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ወደ ኢንደስትሪው ለመግባት ከፋይናንስ እጥረት ውጪ የባለሙያዎች ችግር እለመኖሩን በመግለጽ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ400 በላይ በባቡር ምህንድስና የሰለጠኑ ባለሙያዎች መኖራውን ተናግረዋል።

ኮርፖሬሽኑ ባለሙያዎቹን በመጠቀም በባቡር መንገድ ግንባታ ዘርፍ ለመስራት ማቀዱን ጠቁመው የባለሙያዎች አቅም በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በምስራቅ አፍሪካም ጭምር መስራት የሚስችል ነው በማለት ገልጸዋል፡፡

የፋይናንስ ችግሩን በመቅረፍ እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ከተለያዩ የውጪ ተባባሪ አካላት ጋር በጋራ እየተሰራ እንደሚገኝ አመላክተዋል፡፡

በማርቆስ በላይ

ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍7
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው‼️

👉 በኢትዮጵያ የውጭ ባንኮች እንዲሳተፉ የሚፈቅደውን የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል፣

👉 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል ፣

ብሔራዊ ባንክ የውጭ ባንኮችን ለመቆጣጠርና ለማስተዳደር የሚያስችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋት እንደሚገባ የምክር ቤት አባላት አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ፤ የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጅ በፋይናንስ ዘርፉ ዓለም አቀፍ ተወዳደሪ ለመሆንና ኢንቨስትመንትን ለማሳብ ያግዛል።

የውጭ ባንኮች ወደ ሀገር ውስጥ ይገባሉ ማለት በጋርና በሽርክና ጭምር ከሀገር ውስጥ ባንኮች ጋር በትብብር ይሰራሉ። የባንክ ሥራ ረቂቅ አዋጁ ለሀገር ውስጥ ባንኮችም የዕውቀት ሽግግርን ይፈጥራል።

የሀገር ውስጥ ባንኮችም አቅማቸውን በማጎልበት ተወዳደሪ ለመሆን ሰብሰብ ብለው የፋይናንስ አቅማቸውን ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል።

የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ቀርቦ መፅደቁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመለክታል።

ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓም

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/@ethiopianpressagency...
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍122👎1