ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሰገን ጥሩነህ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት‼️
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ!
ጥምቀት፣ ከሰማየ ሰማያት ወረደ፣ በባሕር መካከልም ቆመ ብለን የምናከብረው በዓል ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የሕዝቡን ችግር ለመፍታት ማድረግ ያለብንን አራት ነገሮች አስተምሮናል።
እነዚህም ወደ ሕዝቡ መውረድ፣ ራስን አሳልፎ መስጠት፣ ሕዝቡ የሚፈልገውን ብቻ ሳይሆን ለሕዝቡ የሚያስፈልገውን ማድረግ እና ዓላማን ብቻ መመልከት ናቸዉ።
አንደኛ የሕዝብን ችግር ለመፍታት ወደ ሕዝብ መውረድ ያስፈልጋል። የሕዝብን ፈተና በሪፖርት መስማት ሳይሆን ወርዶ ማየትና መቅመስ ያስፈልጋል። በየአካባቢው፣ በየፕሮጀክቱ፣ በየማኅበረሰቡ እየሄድን ለማየት የምንሞክረውም ለዚህ ነው።
ሁለተኛዉ የሕዝብን ችግር ለመፍታት ራስን አሳልፎ መስጠት ነዉ። በጎችን ለማዳን መፍትሔዉ በጎችን መሠዋት አይደለም። በጎችን ለመታደግ ራስን መሠዋት እንጂ። የሕዝብን ችግር ለመፍታት ጊዜን፣ ጉልበትን፣ ዕውቀትን፣ መሠዋት ያስፈልጋል። የዕረፍት ሰዓትን፣ የድካም ውጤትን መሠዋት። በመደመር መጽሐፍ ሽያጭ የሚሠሩ ፕሮጀክቶችም የዚህ ምሳሌዎች ናቸው።
ሶስተኛዉ በምንፈልገውና በሚያስፈልገን መካከል ብዙ ጊዜ ልዩነት አለ። የመንግሥት ዋና ተግባር በጥናት ተመሥርቶ፣ ዐቅሙን አደራጅቶ ለሕዝብ የሚያስፈልገውን መሥራት ነው።
እሥራኤል ክርስቶስ እንዲነግሥ ይፈልጉ ነበር። እርሱ ግን በከብቶች በረት ተወለደ። እንዲዋጋ ይፈልጉ ነበር። እርሱ ግን ሰላማዊ ሆኖ መጣ። የሚፈልጉትን ሳይሆን የሚያስፈልጋቸውን አደረገ።
ከልደት እስከ ጥምቀት፣ ከጥምቀት እስከ ስቅለት ብዙ ፈተናዎች አሉ። በኃይል፣ በማባበል፣ በማታለል፣ እንደ ወዳጅ በመቅረብ፣ በከንቱ ውዳሴ፣ ብዙ ፈተናዎች ቀርበዋል። ክርስቶስ ግን የሰውን ልጅ ማዳን ነበር ዓላማው። ከጽንሰት እስከ ዕርገት የፈጸማቸው ሥራዎች ሁሉ ዓላማቸው ድኅነት ነው።
አራተኛዉ ከግራ ከቀኝ፣ ከፊት ከኋላ ብዙ መጎተቻዎች አሉ። ብዙ ማሳሳቻዎች አሉ። ብዙ ማሰናከያዎች አሉ። ብዙ ማስፈራሪያዎች አሉ። ግን ከዓላማችን ዝንፍ አንልም። ዓላማችን ሕዝቡን ከድህነት ማውጣት ነው። ኢትዮጵያን ወደ ልዕልና ማድረስ ነው። ኢትዮጵያን ማበልጸግ ነው።
የዘንድሮውን የጥምቀት በዓል የምናከብረው እነዚህን ትምህርቶች እየወሰድን ነው።
መልካም በዓል ይሁንልን።
ጥር 10 ቀን 2017 ዓም
ፎቶ ከፋይል

👍4
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለጥምቀት በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት‼️
👉 ጥምቀት ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ኅብረ ብሔራዊ በዓላችን ነው፣
👉 ኢትዮጵያ ከቤተልሔም እስከ ቀራንዮ የወደቀችበት ብዙ ነው፤ በእያንዳንዱ ውድቀት ተከትለን ማንሣት አለብን፣
👉 የትርክት፣ የሀገረ መንግሥት፣ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ፣ የመግባባት ውድቀቶቿን ወደ ትንሣኤዋ መቀየር አለብን፣
👉 ኢትዮጵያችን በዘመናት መከራዎች ደክማለች፣
👉 ስለሀገራችን እኛ ቤዛ እንሁን፤ ቤተልሔም መወለድ ካለብን እንወለድ፤
👉 በባሕር መካከል መቆም ካለብን እንቁም፤ መሰደብ ካለብን እንሰደብ፣ መሰቀል ካለብንም እንሰቀል፣
👉 ነገር ግን ይህ ሁሉ የኢትዮጵያን ትንሣኤ የሚያመጣ ይሁን፤ ዛሬ እያደረግነው ያለነውም ይሄንኑ ነው፣
👉 ጥምቀት የኢትዮጵያ የመስክ ላይ ትዕይንት ማቅረቢያ፤ የኢትዮጵያ ባህል የአደባባይ ሙዝየም ነው፣
👉 ብዙ ቱሪስቶች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ይሄንን ወቅት የሚመርጡት አንዱ ምክንያት የአደባባይ ሙዝየም ነው፣
👉 ከገጠር እስከ ከተማ ፤ ከዳር እስከ መሐል፤ ከውጭ እስከ ሀገር የጥምቀት በዓል የእኛነታችን መገለጫ ነው፣
👉 እነዚህን የመሰሉ ዕሴቶቻችንን ስላስረከቡን ቀደምቶቻችንን እናመሰግናቸዋለን፣
👉 የጥምቀትን አስተምህሮ ለሀገር ግንባታ በመጠቀም፤ ባህላዊ እሴቱን በማጎልበት ኅብረ ብሔራዊነቱን በማጠናከር በዓሉን እንድናከብር አደራ እላለሁ፣

👍6🥰2
መንግሥት ጎንደር በታሪኳ ልክ የዕድገት መሻቷን እንድታሳካ አበክሮ እየሠራ ነው- ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
*****
(ኢ ፕ ድ)
መንግሥት ጎንደር በታሪኳ ልክ የዕድገት መሻቷን እንድታሳካ አበክሮ እየሠራ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ። በወቅታዊ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱም የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ጎንደር በኢትዮጵያ ስልጣኔ፣ ስርዓተ መንግሥትና ሀገር ግንባታ ጉልህ ስፍራ አላት ብለዋል።
አብያተ-መንግስታቱን፣ ቀደምት ቅርሶችንና ቅድመ አያቶች ለሀገራቸው ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በማሳያነት አንስተዋል።
የአሁኑ ትውልድም የቀደሙ አባቶችን አርቆ አሳቢነትና ጥበብ በመያዝ የተገኙ ድሎችን ማስቀጠልና ሰላምን ማፅናት ላይ በአርዓያነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጎንደር ህዝብ ለዘመናት ሲያነሳቸው የነበሩ የልማት ጥያቄዎች በተጨባጭ ምላሽ እንዲያገኙ እያደረጉ መሆኑንም ገልጸዋል።
መንግስት ጎንደር በታሪኳ ልክ የከፍታና የዕድገት መሻቷን እንድታሳካ በሁሉም መስክ አበክሮ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሆኖም የጎንደር መለወጥና የህዝቡ በልማት ተጠቃሚ መሆን የማይፈልጉ አንዳንድ አካላት አካባቢው ሰላም እንዳያገኝ ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበር አውስተዋል።
ይህን መጥፎ አካሄድ ቀድሞ የተቃወመውና ያከሸፈው የጎንደር ህዝብ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፥ በመሆኑም ሰላምና ልማትን አጠናክሮ ለማስቀጠል በጋራ መስራት ይገባል ነው ያሉት።
ችግሮች ሲኖሩ በሰላማዊ ውይይት የመፍታት ባህልን በማጎልበት መፃኢ ዕድሎችን በጋራ መተለምና ማሳካት የትውልዱ ኃላፊነት መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

👍5
#ጎንደር_የጥምቀት_በዓል
በርካታ የውጪ አገራት ጎብኚዎች የተሳተፉበት የማለዳው የጎንደር የጥምቀት በዓል ድባብ
******
(ኢ ፕ ድ)
በጎንደር ባህረ ጥምቀት ለሚካሄደው ሥርዓተ ጥምቀት ለመሳተፍ በርካታ ቁጥር ያላቸው የበዓሉ ተሳታፊዎች ወደ ስፍራው እያቀኑ ነው።
በበዓሉ አከባበር ላይ ለመሳተፍ በርካታ የውጪ አገራት ዜጎች በጎንደር ባህረ ጥምቀት ተገኝተዋል።
በአሁኑ ሰዓት የቅዳሴ ሥርዓት የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ የዝማሬና የጥምቀት ሥርዓት የሚካሄድ ይሆናል።
ማርቆስ በላይ (ጎንደር)

👍3👏3