Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
መንግሥት ጎንደር በታሪኳ ልክ የዕድገት መሻቷን እንድታሳካ አበክሮ እየሠራ ነው- ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ
*****
(ኢ ፕ ድ)
መንግሥት ጎንደር በታሪኳ ልክ የዕድገት መሻቷን እንድታሳካ አበክሮ እየሠራ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ። በወቅታዊ የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይቱም የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ጎንደር በኢትዮጵያ ስልጣኔ፣ ስርዓተ መንግሥትና ሀገር ግንባታ ጉልህ ስፍራ አላት ብለዋል።

አብያተ-መንግስታቱን፣ ቀደምት ቅርሶችንና ቅድመ አያቶች ለሀገራቸው ያበረከቱትን አስተዋጽኦ በማሳያነት አንስተዋል።

የአሁኑ ትውልድም የቀደሙ አባቶችን አርቆ አሳቢነትና ጥበብ በመያዝ የተገኙ ድሎችን ማስቀጠልና ሰላምን ማፅናት ላይ በአርዓያነት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የጎንደር ህዝብ ለዘመናት ሲያነሳቸው የነበሩ የልማት ጥያቄዎች በተጨባጭ ምላሽ እንዲያገኙ እያደረጉ መሆኑንም ገልጸዋል።

መንግስት ጎንደር በታሪኳ ልክ የከፍታና የዕድገት መሻቷን እንድታሳካ በሁሉም መስክ አበክሮ እየሠራ መሆኑንም ተናግረዋል።

ሆኖም የጎንደር መለወጥና የህዝቡ በልማት ተጠቃሚ መሆን የማይፈልጉ አንዳንድ አካላት አካባቢው ሰላም እንዳያገኝ ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበር አውስተዋል።

ይህን መጥፎ አካሄድ ቀድሞ የተቃወመውና ያከሸፈው የጎንደር ህዝብ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፥ በመሆኑም ሰላምና ልማትን አጠናክሮ ለማስቀጠል በጋራ መስራት ይገባል ነው ያሉት።

ችግሮች ሲኖሩ በሰላማዊ ውይይት የመፍታት ባህልን በማጎልበት መፃኢ ዕድሎችን በጋራ መተለምና ማሳካት የትውልዱ ኃላፊነት መሆኑንም ፕሬዝዳንቱ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ጥር 10 ቀን 2017 ዓም
👍5
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ከተራ_ጥምቀት

በከተራ በዓል ትኩረት የሳበችው #ጀርመናዊቷ_ወጣት ለምእመኑ ውሃ ስታጠጣ‼️ 

#ጥምቀት_2017
👍4
#ከተራ_ጥምቀት

የከተራ በዓል አከባበር በአዲስ አበባ በፎቶ‼️
👍8
#ጎንደር_የጥምቀት_በዓል

በርካታ የውጪ አገራት ጎብኚዎች የተሳተፉበት የማለዳው የጎንደር የጥምቀት በዓል ድባብ
******
(ኢ ፕ ድ)

በጎንደር ባህረ ጥምቀት ለሚካሄደው ሥርዓተ ጥምቀት ለመሳተፍ በርካታ ቁጥር ያላቸው የበዓሉ ተሳታፊዎች ወደ ስፍራው እያቀኑ ነው።

በበዓሉ አከባበር ላይ ለመሳተፍ በርካታ የውጪ አገራት ዜጎች በጎንደር ባህረ ጥምቀት ተገኝተዋል።

በአሁኑ ሰዓት የቅዳሴ ሥርዓት የተጠናቀቀ ሲሆን በቀጣይ የዝማሬና የጥምቀት ሥርዓት የሚካሄድ ይሆናል።

ማርቆስ በላይ (ጎንደር)
👍3👏3
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ዐህመድ የተላከ መልዕክት ለዩጋንዳ እና ለኬንያ መሪዎች አደረሱ
*******
(ኢ ፕ ድ)

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ መልዕክት ለዩጋንደው ፕሬዚደንት ዩዌሪ ሙሰቬኒና ለኬንያው ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ አደረሱ።

አምባሳደር ሬድዋን ሁለቱ መሪዎች መልካም ጉርብትናና ቀጣናዊ ትብበር እንዲጠናከር ለተጫወቱት በጎ ሚና እንዲሁም ለኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ላሳዩት ቀናዒነት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያላቸዉን አድናቆት ገልጸውላቸዋል።

ፕሬዚደንቶቹም ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ድርጅትና በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር እንዲሁም በራሷ አቅም በሶማሊያና በሌሎችም ሀገራት ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የበረከተችውን አይተኬ ሚና በማውሳት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመጫወት ላይ ያሉትን ጉልህ ሚና ማድነቃቸውንና  በቀጣይም በሶማሊያ ሰላምና ሽብርተኝነትን በማዋጋት ረገድ የሚኖራትን ወሳኝ ሚና አጠናክራ እንደምትቀጥል ያላቸውን ደጋፍና እምነት ገልፀዋል።

ከዚሁ በተያያዘ ፕሬዚደንት ዊሊያም ሩቶ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማጎልበትነና በኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና እንዲሰፍን ጠቀላይ ሚኒስተር ዐብይ በማድረግ ላይ ያሉት ጥረት እንደሚደግፉ የገለ‍ፁላቸው መሆኑንና የሀገሪቱ የፀጥታና ደህንነት ተቋማትም ለኢትዮጵያ አቻዎቻቸው አስፈላጊውን  ትብብር እንዲለግሱ መመሪያ መስጠታቸውን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለኢፕድ በላከው መረጃ አመላክቷል።

ጥር 11 ቀን  2017 ዓ.ም
👍4🔥1