Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍2
ባለፉት ስድስት ወራት ከቡና 908 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ ተገለፀ
****
(ኢ ፕ ድ)

ባለፉት ስድስት ወራት ከቡና ወጪ ንግድ 908 ሚሊዮን ዶላር ገቢ መገኘቱ የቡናና ሻይ ባለስልጣን አሰታወቀ።

የስድስት ወራትን አፈጻጸምአሰመልክተው መግለጫ የሰጡት የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ኡመር እንደገለጹት፤ የቡና፣ ሻይና ቅመማቅመም ምርትን በማሻሻል የውጭ ምንዛሪ ግኝት የማሳደግ ስራ ተሠርቷል።

አሠራርን በማሻሻል ከቡና የሚገኘው ገቢ እያደገ ነው ያሉት አቶ ሻፊ ኡመር፣በ2017 400 ሺህ ቶን ቡና ወደ ውጭ በመላክ 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ለማግኘት እቅድ ተይዞ እየተሠራ ነው ብለዋል።

ባለፈው ስድስት ወር ከ204 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለውጭ ገበያ በማቅረብ 908 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።

ከ2017 እቅድ አንፃርና ከባለፈው ተመሣሣይ አመት ጋር ሲነፃፀር ትልቅ ብልጫ እንዳለው ገልፀዋል።

በሞገስ ጸጋዬ

ጥር 12 ቀን 2017 ዓም
👍8
ጥምቀትና ቃና ዘገሊላ በዓላት በድምቀት ተከብረው መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል አስታወቀ
******
(ኢ ፕ ድ)

የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ከማይዳሰሱ ቅርሶች ውስጥ አንዱ የሆነው የጥምቀት በዓል አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ በሰላም መጠናቀቁን አስታውቋል።

በተመሳሳይ በዛሬው ዕለት የተከበረው የቃና ዘገሊላ በዓልም በሰላም መከበሩን ጨምሮ ገልጿል።

በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የበኩላቸውን ድርሻ ላበረከቱት ለመላው የሀገራችን ሕዝብ፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለምዕመናን፣ ለሰላም ሠራዊት አባላት እና ለበዓሉ አስተባባሪዎች እንዲሁም የተሰጣቸውን ኃላፊነት በብቃት ለተወጡት የፀጥታ ተቋማት አመራርና አባላት የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል በመግለጫው ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

ጥር 12 ቀን 2017 ዓም
👍7👌1
በሀረሪ ክልል ከ13ሺህ ሊትር በላይ በሕገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ
*******
(ኢ ፕ ድ)

በሀረሪ ክልል ከ13 ሺህ 480 ሊትር ነዳጅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን እንዳሉት በክልሉ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይትን ለማስቆም በአንድ ወራት በተሰራው ስራ በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 13ሺ 480 ሊትር ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ነዳጁ በቁጥጥር ስር የዋለው በኬላዎች ላይ በተደረገ ፍተሻና ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በሕገወጥ መንገድ በቤት ውስጥ ተከማችቶ የተገኘ መሆኑን ገልጸዋል።

በመኖሪያ ቤታቸው ደብቀው የተገኙ ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መንግስት ከፍተኛ በጀት መድቦ የሚያስገባው ነዳጅ ለታለመለት አላማ ሊውል ይገባል ያሉት ኮሚሽነሩ በህገወጥ ግብይት በሚሳተፉ አካላት ላይ በቀጣይም የተጠናከረ ክትትል በማድረግ አስተማሪ የሆነ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

በቀጣይም ሕገ ወጥ ነዳጅን ጨምሮ ሌሎች ሕገ ወጥ ተግባራትን ለመከላከል የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ማህበረሰብ ሕገወጥ የነዳጅ ግብይትን ሲመለከት በአካባቢው ለፖሊስ ጽ/ቤት ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

ጥር 12 ቀን 2017 ዓም
👍3
ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሐላ ፈጸሙ
********
(ኢ ፕ ድ)
ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡

በቃለ መሐላ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ የተለያዩ የዓለም ሀገራት የቀድሞና የአሁን መሪዎችን ጨምሮ ከ500 በላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ኅዳር ወር በተካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ማሸነፋቸው ይታወሳል።

ጥር 12 ቀን 2017 ዓም
👍11
በጅማ፣ በቡኖ በደሌና በኢሉባቡር ዞኖች 7 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሻይ ቅጠል እየተመረተ ነው
*****
(ኢ ፕ ድ)

በኦሮሚያ ክልል በጅማ፣ በቡኖ በደሌ፣በኢሉባቡር ዞኖች 7 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የሻይ ቅጠል ምርት እየተመረተ መሆኑን የቡናና ሻይ ባለስልጣን የስድስት ወር አፈጻጸሙን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሻፊ ዑመር እንደገለጹት፤ የሻይ ምርትን በኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት የሚያመርቱት ኢትዮ አግሪሴፍት፣ ኢስት አፍሪካና ቨርዳንታ ድርጅቶች ብቻ እንደነበሩ ጠቁመዋል።

የቡናና ሻይ ባልስልጣን ከኦሮሚያ ክልል ጋር በመሆን ሰፊ የሻይ ማሳዎች እንዲለሙ መደረጉን የገለፁት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጅማ፣ ቡኖ በደሌና ኢሉባቡር ዞኞች ላይ 7 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ሻይ እየተመረተ ይገኛል።

ከምርት በኋላ ባለው ሂደት ማቀነባበሪያ በመትከል ወደ ውጭ የመላክ ስራ ይሰራል፡፡ ለዚህ የሚሆን ዝግጅት ተጠናቆ ለባለሀብቶች ቦታ ተሰጥቶ ወደ ስራ እንደሚገቡ ገልጸዋል፡፡

የሀገር ውስጥ የሻይ ፍላጎት መጨመሩን የገለጹት አቶ ሻፊ፤ ቨርዳንታና ኢስት አፍሪካ ምርታቸውን ለሀገር ውስጥ ገበያ እያቀረቡ ይገኛሉ። አሁን ላይ የሻይ ምርትን እየላከ ያለው ኢትዮ አግሴፍት ብቻ መሆኑም ተገልጿል።

#የሻይ ምርት #ቡና #ቡኖ በደሌ ጅማ #ኢሉባቡር

በሞገስ ጸጋዬ

ጥር 13 ቀን 2017 ዓም
👍12
በአዲስ አበባ በሁለት ወር 1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ነዋሪዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበዋል

👉 15 ሺህ 574 የጋብቻ ምዝገባና 3 ሺህ 769 ፍቺ ምዝገባ ተከናውኗል
****
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ባለፉት ስድስት ወራት የተከናወኑ ስራዎችን አሰመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸው ካነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች፤

👉 ወደ ዲጂታል ምዝገባ ያልተቀላቀሉ 340 ሺህ ነዋሪዎችን ከማኑዋል ወደ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መመዝገብ ተችሏል፣

👉 ለ268 ሺህ 470 የነዋሪዎች መታወቂያ የተሰጠ ሲሆን 99.84 በመቶ የሚሆነው ዲጂታል መታወቂያ ነው፣

👉 41 ሺህ 183 የልደት ምዝገባን በወቅቱ፤ 195 ሺህ 402 በዘገየና የጊዜ ገደቡ ባለፈት ምዝገባ ተከናውኗል፣

👉 በከተማው ከተከሰተው ሞት ከ11 ሺህ 300 በላይ የሚሆነውን ምዝገባ በማደረግ ተችሏል

👉 በህገወጥ ተግባራት ላይ የተሳተፉ 71 የተቋሙ ሰራተኞች ላይ የዲሲፕሊን እርምጃ ተወስዷል

👉 ሐሰተኛ ሰነድ ይዘው በመቅረብ 28 ባለጉዳዮች ለህግ እንዲቀርቡ ተደርጓል፣

አገልግሎት ላይ የተሰራጩ የካርድ፣ የሰርተፍኬትና የዲጂታል መታወቂያ አሰራርን ባለመከተል፣ አሰራርን በመጣስ፣ ጉድለት በመፍጠር፣ ስራን በአግባቡ ባለመምራት በስድስት ክፍለ ከተሞች ጉድለት ተገኝቷል።

በዚህም 33 ሰራተኞች ተጠያቂነት ያረፈባቸው ሲሆን 19 በወንጀል ፣ 24 በአስተዳደራዊ እንዲሁም አንድ አመራር ስራን በአግባቡ ባለማምራት በሃላፊነት እንዲጠየቁ መወሰኑን አቶ ዮናስ አብራርተዋል፡፡

በማህሌት ብዙነህ

ጥር 13 ቀን 2017 ዓም
👍4
ዩሪያና ዳፕ ማዳበሪያ የጫኑ 6 መርከቦች ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸው ተገለፀ
***
(ኢ ፕ ድ)

እስከአሁን ጅቡቲ ወደብ ከደረሰው 313 ሺህ 260 ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ 256 ሺህ 398.2 ሜትሪክ ቶን ወደ ኢትዮጵያ ተጓጉዟል። ቀሪው ማዳበሪያ በመጓጓዝ ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም 56 ሺህ 000 ሜትሪክ ቶን ዳፕ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች ሰባተኛ መርከብ ትናንት ዶራሌ ሁለገብ ወደብ ደርሳ ጭነት እያራገፈች እንደምትገኝ ተጠቁሟል።

በሚቀጥሉት ቀናትም ተጨማሪ 4 የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ መርከቦች ጅቡቲ ይደርሳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

ጥር 13 ቀን 2017 ዓም
👍10
ፕሬዚዳንት ታዬ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን የጋምቢያ አምባሳደር አሰናበቱ
***
(ኢ ፕ ድ)

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሥራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የጋምቢያ አምባሳደር ጃይናባ ጃግኔን አሰናበቱ፡፡

በኢትዮጵያ እና ጋምቢያ መካከል ያለው ግንኙነት በማጠናከር ረገድ አምባሳደሩ ላበረከቱት ሚና ፕሬዚዳንቱ አመሥግነዋል፡፡

ጥር 13 ቀን 2017 ዓም
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመትና የሆስፒታሉ 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከነገ ጀምሮ መከበር ይጀምራል
*******
(ኢ ፕ ድ)

#የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ፣ አንጋፋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመትና የአጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታሉ #100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ከነገ ጀምሮ እሰከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓም ድረስ ይከበራል።

ዩኒቨርሲቲያው በዕውቀት፤ በምርምር፣ በጤና ዘርፍና በማኅበረሰብ አገልግሎት ያበረከተው አስተዋፅኦ የሚዘከርበት በዓል ነው ብለዋል።

የ100ኛ አመት የታሪክ መጽሐፍ ምረቃ እንደሚካሄድ በመግለጽ የቀድሞ ተመራቂዎች ቀን፣ የመሠረተልማቶ ፕሮጀክቶች ምርቃት፣ የፕሬዚዳንቶች ቀን፣ የጎንደር ቀን፣ የአርሶ አደሮች ቀንን ጨምሮ በርካታ መርሐግብሮች ተዘጋጅተዋል።

ዩኒቨርሲቲው በ11 ኮሌጆች በተለያዪ የትምህርት መርሐግብሮች ከ40 ሺህ በላይ ተማሪዎች እያስተማረ እንደሚገኝ ጠቅሰው 12 የምርምር ማዕከላት እንዳሉት ተናግረዋል።

በዓሉ ስፖርታዊ ውድድር፣ የማህበረሰብ አገልግሎት፣ የቃል ኪዳን ቤተሰብ ቀን፣ የህክምና ተማሪዎች ምርቃትን ጨምሮ አውደርዕይና የተማሪዎች ሳምንት ይካሄዳል።

ዩኒቨርሲቲው እስከ 2016 ዓም ድረስ ከ100 ሺህ በላይ ተማሪዎችን በተለያዩ የትምህርት መሰኮች አስመርቋል።

በማርቆስ በላይ (ጎንደር)

ጥር 13 ቀን 2017 ዓም
👍14
ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያ የሥራ ቀናቸው የፈረሟቸው ትዕዛዞች‼️

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበዓለ ሲመታቸው ላይ የፈረሙባቸውን ውሳኔዎች በዝርዝር አሳውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ፊርማቸውን ያኖሩባቸው ጉዳዮች፤

👉 በዩናይትድ ስቴትስ ለሁለት ጾታዎች ብቻ እውቅና ትሰጣለች፣ ለወንድ እና ሴት ብቻ

👉 ሕገ-ወጥ ስደትን ለማስቆም ብሔራዊ የድንበር ድንገተኛ አደጋ መከላከል

👉 የደቡብ ድንበርን ለማስጠበቅ ወታደራዊ ሃይል ማሰማራት

👉 በአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎችና ዓለም አቀፍ የሽብርተኞች ቡድኖች ላይ የሚካሄድ ዘመቻን ማጠናከር

👉 የድንበር ግድግዳ ግንባታን እንደ አዲስ መጀመር

👉 ተጥለው የነበሩ የነዳጅ ቁፋሮ ገደቦችን ማቋረጥ

👉 የሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤን የአሜሪካ ባሕረ ሰላጤ ማድረግ

👉 የፌዴራል ሠራተኞች ወደ ቢሮ እንዲመለሱ ማዘዝ

👉 የኃይል አቅርቦት ምርት እና ኤክስፖርትን ለማሳደግ ብሄራዊ የሃይል ድንገተኛ አደጋ ጊዜ አዋጅ

👉 በአረንጓዴ ስምምነት እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦችን ማንሳት

👉 የወጭ ገቢ አገልግሎትን የታክስ ስርዓት የተመለከተ አሰራር መፍጠር

👉 የፓናማ ባህረ ሰላጤን መልሶ መቆጣጠር

👉 የጠፈር ተጓዦች የዩናይትድ ስቴትስ ባንዲራን ማርስ ላይ እንዲተክሉ ማድረግ

👉 የመንግስት ሳንሱርን በማስቆም የመናገር ነፃነትን ወደነበረበት መመለስ

እነዚህ የአስተዳደር እርምጃዎች በኢሚግሬሽን ቁጥጥር፣ በባሕላዊና ማኅበራዊ ፖሊሲዎች እና የሀገር ውስጥ የኃይል ምርት እንዲጠናከር እና የዋጋ ግሽበትን ለማስወገድ በሚያችሉ ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው።

በክብረአብ በላቸው

#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #Ethiopia #ትራምፕ #አሜሪካ  #Trump #USA
👍131
የኢትዮጵያ መንግስት በቱርክ በተከሰ የእሳት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለፀ
******
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ መንግስት በቱርክ ቦሉ ግዛት በተከሰተ የእሳት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን መግለፁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው የሀዘን መግለጫ አሰታውቋል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ኢትዮጵያ ከቱርክ መንግሥትና ህዝብ ጎን እንደምትቆም በመግለጫው አመላክቷል፡፡

ጥር 13 ቀን 2017 ዓም
👍17🤣7
የራንሰምዌር ጥቃትን ለመከላከል ሊተገበሩ የሚገቡ የጥንቃቄ መንገዶች‼️

የራንሰምዌር ጥቃቶች አጥፊ ተልእኮ ያላቸዉን ሶፍትዌሮችን በመጠቀም መረጃ የመያዝና የማገት እንቅስቃሴ ሲሆን ባለፉት ጥቂት አመታት በመረጃ መዝባሪዎች ዘንድ ተመራጭ የሳይበር ጥቃት መፈጸሚያ መንገድ እየሆነ መጥቷል፡፡ 

ራንሰምዌር ጥቃት እኤአ በ2021 ካስከተላው 20 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ ባሳለፍነው 2024 ወደ 42 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። በ2031 በራንሰም የሚደርሰው የኢኮኖሚ ኪሳራ ወደ  265 ቢሊየን ዶላር ሊደርስ አንደሚችል የትንበያዎች መረጃዎች ያሳያሉ ፡፡

በሀገር ላይ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ኪሳራ የሚያደርሰውን ይህን ጥቃት እንዴት መከላከል ይቻላል⁉️

👉 የመጠባበቂያ መረጃ መያዝ (backup)

👉 በኢ-ሜይል ለሚላኩ የማይታወቁ መልዕክቶች፣ የማናውቃቸው የስልክ ጥሪዎች፣ የጽሑፍ መልዕክቶችና ጥያቄዎች ግላዊ መረጃን አሳልፎ አለመስጠት፤

👉 ተቀባይነት ያለው ጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌር መጠቀም፤

👉 የይዘት ማጣሪያና መለያን ለመልዕክት መቀበያ ሰርቨሮች መጠቀም፤

👉 ሁሉም ሥርዓቶችና ሶፍትዌሮች ወቅታዊ የክፍተት መሙያ ዝመና የተደረገላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤

👉 የህዝብ ዋይፋይ ከመጠቀም መቆጠብ እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አሳስቧል።

ጥር 13 ቀን 2017 ዓም
👍1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et