Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያ የሥራ ቀናቸው የፈረሟቸው ትዕዛዞች‼️

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበዓለ ሲመታቸው ላይ የፈረሙባቸውን ውሳኔዎች በዝርዝር አሳውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ ፊርማቸውን ያኖሩባቸው ጉዳዮች፤

👉 በዩናይትድ ስቴትስ ለሁለት ጾታዎች ብቻ እውቅና ትሰጣለች፣ ለወንድ እና ሴት ብቻ

👉 ሕገ-ወጥ ስደትን ለማስቆም ብሔራዊ የድንበር ድንገተኛ አደጋ መከላከል

👉 የደቡብ ድንበርን ለማስጠበቅ ወታደራዊ ሃይል ማሰማራት

👉 በአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎችና ዓለም አቀፍ የሽብርተኞች ቡድኖች ላይ የሚካሄድ ዘመቻን ማጠናከር

👉 የድንበር ግድግዳ ግንባታን እንደ አዲስ መጀመር

👉 ተጥለው የነበሩ የነዳጅ ቁፋሮ ገደቦችን ማቋረጥ

👉 የሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤን የአሜሪካ ባሕረ ሰላጤ ማድረግ

👉 የፌዴራል ሠራተኞች ወደ ቢሮ እንዲመለሱ ማዘዝ

👉 የኃይል አቅርቦት ምርት እና ኤክስፖርትን ለማሳደግ ብሄራዊ የሃይል ድንገተኛ አደጋ ጊዜ አዋጅ

👉 በአረንጓዴ ስምምነት እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ላይ ተጥለው የነበሩ ገደቦችን ማንሳት

👉 የወጭ ገቢ አገልግሎትን የታክስ ስርዓት የተመለከተ አሰራር መፍጠር

👉 የፓናማ ባህረ ሰላጤን መልሶ መቆጣጠር

👉 የጠፈር ተጓዦች የዩናይትድ ስቴትስ ባንዲራን ማርስ ላይ እንዲተክሉ ማድረግ

👉 የመንግስት ሳንሱርን በማስቆም የመናገር ነፃነትን ወደነበረበት መመለስ

እነዚህ የአስተዳደር እርምጃዎች በኢሚግሬሽን ቁጥጥር፣ በባሕላዊና ማኅበራዊ ፖሊሲዎች እና የሀገር ውስጥ የኃይል ምርት እንዲጠናከር እና የዋጋ ግሽበትን ለማስወገድ በሚያችሉ ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው።

በክብረአብ በላቸው

#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #Ethiopia #ትራምፕ #አሜሪካ  #Trump #USA
👍131
የኢትዮጵያ መንግስት በቱርክ በተከሰ የእሳት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን ገለፀ
******
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ መንግስት በቱርክ ቦሉ ግዛት በተከሰተ የእሳት አደጋ በደረሰው ጉዳት የተሰማውን ሀዘን መግለፁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው የሀዘን መግለጫ አሰታውቋል።

በዚህ አስቸጋሪ ወቅትም ኢትዮጵያ ከቱርክ መንግሥትና ህዝብ ጎን እንደምትቆም በመግለጫው አመላክቷል፡፡

ጥር 13 ቀን 2017 ዓም
👍17🤣7
የራንሰምዌር ጥቃትን ለመከላከል ሊተገበሩ የሚገቡ የጥንቃቄ መንገዶች‼️

የራንሰምዌር ጥቃቶች አጥፊ ተልእኮ ያላቸዉን ሶፍትዌሮችን በመጠቀም መረጃ የመያዝና የማገት እንቅስቃሴ ሲሆን ባለፉት ጥቂት አመታት በመረጃ መዝባሪዎች ዘንድ ተመራጭ የሳይበር ጥቃት መፈጸሚያ መንገድ እየሆነ መጥቷል፡፡ 

ራንሰምዌር ጥቃት እኤአ በ2021 ካስከተላው 20 ቢሊየን ዶላር ኪሳራ ባሳለፍነው 2024 ወደ 42 ቢሊየን ዶላር ከፍ ብሏል። በ2031 በራንሰም የሚደርሰው የኢኮኖሚ ኪሳራ ወደ  265 ቢሊየን ዶላር ሊደርስ አንደሚችል የትንበያዎች መረጃዎች ያሳያሉ ፡፡

በሀገር ላይ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ኪሳራ የሚያደርሰውን ይህን ጥቃት እንዴት መከላከል ይቻላል⁉️

👉 የመጠባበቂያ መረጃ መያዝ (backup)

👉 በኢ-ሜይል ለሚላኩ የማይታወቁ መልዕክቶች፣ የማናውቃቸው የስልክ ጥሪዎች፣ የጽሑፍ መልዕክቶችና ጥያቄዎች ግላዊ መረጃን አሳልፎ አለመስጠት፤

👉 ተቀባይነት ያለው ጸረ-ቫይረስ ሶፍትዌር መጠቀም፤

👉 የይዘት ማጣሪያና መለያን ለመልዕክት መቀበያ ሰርቨሮች መጠቀም፤

👉 ሁሉም ሥርዓቶችና ሶፍትዌሮች ወቅታዊ የክፍተት መሙያ ዝመና የተደረገላቸው መሆኑን ማረጋገጥ፤

👉 የህዝብ ዋይፋይ ከመጠቀም መቆጠብ እንደሚገባ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አሳስቧል።

ጥር 13 ቀን 2017 ዓም
👍1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
"የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እውቀትና ፈጠራ በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷል" - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

👉 በቀጣይ ሁለት ዓመታት 10 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን ራስ ገዝ ይሆናሉ፣
*
(ኢ
ፕ ድ)
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በትምህርት በምርምርና በጤና አጠባበቅ እውቀትና ፈጠራ እንዲስፋፋ የበኩሉን ድርሻ ሲወጣ ቆይቷል ሲሉ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ።

የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሳደግ በምታደርገው ጥረት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቅሰው ተቋሙ የቀረጻቸው የህክምናና የህብረተሰብ ጤና መርሃግብሮች ለኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ሥርዓት መሻሻል አስተዋጽኦ አድርጓል።

ዩኒቨርሲቲው በህክምና እና በጤና ሳይንስ ዘርፍ እውቀትን የተካኑ ባለሙያዎችን በማፍራት የላቀ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛል ያሉት ፕሮፈሰር ብርሃኑ

ዩኒቨርሲቲዎች አገር ተረካቢዎችንንና የነገ መሪዎችን በመቅረጽ ረገድ በትኩረት ሊሰሩበት እንደሚገባ አመላክተዋል።

በአሁኑ ጊዜ የትምህርት ጥራት ችግሮችን ለመቅረፍ ፓሊሲዎችና ስታራቴጂዎች ተቀርጸው እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፣ ዩኒቨርሲቲዎች ችግር ፈቺ የምርምር ሥራዎችን እንዲሰሩ እየተሰራ ነው ሲሉም ጠቁመዋል።

ዩኒቨርስቲዎችን ወደ የራስገዝነት ሂደት ማስገባት የቀጣይ የሪፎርም መዳረሻ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲው በትምህርት በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ማዕከል ለመሆን መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስራት አፀደወይን(ዶ/ር)፣ በፓለቲካ አለመረጋጋት ፈተናዎች ቢገጥሙት በርካታ ፈተናዎችን ተቋቁሞ አገርና ህዝብን ማገልገሉን ገልጸዋል። የጤና ኮሌጁ የአገሪቱን የጤና ችግር ሊቀርፉ የሚችሉ ሞያተኞችን አፍርቷል።

የ70 አመት እድሜ ባለጸጋው ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2006 ዓም የ60ኛ አመት የምስረታ በዓልን ማክበሩን አስታውሰው፣ የምስረታ በዓሉ እስከ ሰኔ 30 ድረስ ማህበረሰቡን በማሳተፍ እንደሚከበር ገልጸዋል።

ማርቆስ በላይ (ጎንደር)

ጥር 14 ቀን 2017 ዓም
👍7
ከወርቅ ወጪ ንግድ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ
****
(ኢ ፕ ድ)
ባለፉት ሥድስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

#ኢትዮጵያ ባላት መልከዓ ምድር ምቹ የአየር ንብረት ብዝሃ-ምርቶችን አምርታ ለዓለም የማቅረብ ዕምቅ አቅም አላት፡፡

ከማዕድን ባለፉት ስድስት ወራት #ከወርቅ ብቻ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ አግኝተናል። አቅማችንን አጎልብተን ወደ ገቢራዊ ውጤት መቀየርና ማስተዋወቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

የቡና፣ የጥራጥሬ፣ የቅባት እህሎች፣ ሰብሎች፣ ቅመማቅመም፣ አትክልትና ፍርፍሬ፣ ማዕድንና ሌሎች ምርቶቻችንን በጥራት አምርተን በውጪ ንግድ የዓለም ገበያ ያለን ድርሻ እያሻሻልን ከሄድን ከዘርፉ የምናገኘው ገቢ በብዙ እጥፍ እንደሚጨምር ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያና የጃፓን የንግድና ኢንቨስትመንት ሲምፖዚየም ተሳታፊዎች በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ አውደርዕይ ማዕከልን ጎብኝተዋል፡፡

ጥር 14 ቀን 2017 ዓም
👍3
በአገልግሎትና አስተዳደር የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የተጀመሩ ሥራዎች አበረታች መሆናቸው ተገለጸ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር የሚታዩ ችግሮችን በመሰረታዊነት ለመፍታት የተጀመሩ የሪፎርም ትግበራና የዝግጅት ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም አመራር ዐቢይ ኮሚቴ ሦስተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂደናል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው እንዳስታወቁት፣ በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽንና በመጀመሪያ ዙር የተመረጡ ተቋማት ያከናወኗቸውን የሪፎርም ሥራዎች ተገምግመዋል።

የሪፎርም አስተዳደራዊ ሥራዎች፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሥርዓትን መዘርጋት፣ #ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት አገልግሎቶችንና ውሳኔዎችን ማቀላጠፍ ላይ ጥሩ ጅምሮች አሉ ብለዋል።

በሪፎርሙ የታቀፉ ተቋማት ያላቸውን ልምዶች የሚቀያየሩበት እና በጋራ የሚሰሩበትን አውድ መፍጠር ተችሏል፡፡

ተቋማት ያከናወኗቸውን ተግባራት በዝርዝር በመቃኘት ጥንካሬዎችንን ውስንነቶችን የለየን ሲሆን በቀጣይ ትኩረት ሊደረግባቸው የሚገባቸው ጉዳዮች ላይም አቅጣጫ አስቀምጠናልም ብለዋል።

ጥር 14 ቀን 2017 ዓም
👍4
ዛሬ በባሕርዳር ከተማ በጣና ሀይቅ ላይ የታንኳ ቀዘፋ ውድድር ይካሄዳል
***
(ኢ ፕ ድ)

ዛሬ በባሕርዳር ከተማ ከቀኑ 7 ሠዓት ጀምሮ በጣና ሀይቅ ላይ የታንኳ ቀዘፋ ውድድር፣ የጀልባ ትርዒትና ሽርሽር ይካሄዳል።

በጥር ወር በአማራ ክልል የቱሪስት መስኅብ የሆኑ ዝግጅቶች በተለያዩ አካባቢዎች ይደረጋሉ፤ የዛሬው የታንኳ ቀዘፋ ውድድር፣ የጀልባ ትርዒትና ሽርሽርም አንዱ መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

#ባህርዳር #ቱሪዝም #ቱሪስት

ጥር 15 ቀን 2017 ዓም
👍94
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን አጸደቀ
****
(ኢ ፕ ድ)

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባው የተለያዩ ሹመቶችን አጽድቋል።

1. ወ/ሮ ስመኝ ውቤ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም ዋና ዕምባ ጠባቂ

2. ዶ/ር የኔነህ ስመኝ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም ምክትል ዋና ዕምባ ጠባቂ

3. አቶ አባይነህ አዴቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም የዘርፍ ዕምባ ጠባቂ ሆነው ተሹመዋል።

ምክር ቤቱ #ኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴ አቋቁሞ ሲሰራ መቆየቱን አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በወቅቱ ተናግረዋል።

በዳግማዊት አበበ

ጥር 15 ቀን 2017 ዓም
👍21
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ካነሷቸው ዋና ዋና ሀሳቦች‼️

👉 ለአምራች ኢንዱስትሪዎች 369 ሚሊየን 110 ሺህ ዶላር የውጭ ምንዛሬ ቀርቧል፣

👉 ከሁለት ቢሊየን በላይ የአሜሪካን ዶላር የገቢ ምርት መተካት ተችሏል፣

👉 አማካኝ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም አጠቃቀም 61 ነጥብ 2 በመቶ ደርሷል፣

👉 በወጪ ንግድ 95 ሺህ 167 ቶን ምርት ወደ ውጭ ተልኳል፣

👉 ከዘርፉ 149 ሚሊዮን 334 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ማግኘት ተችሏል፣

👉 ለቆዳና ቆዳ ውጤቶች አምራች ኢንዱስትሪዎች 10 ሚሊዮን 400 ሺህ ቶን ማቅረብ ተችሏል፣

👉በጨርቃጨርቅ፣ በምግብና መጠጥ፣ በኬሚካልና ኮንስትራክሽን ዘርፍ 9 ሚሊየን 527 ሺህ ቶን ግብዓት ቀርቧል፣

👉 ለአምራች ኢንዱስትሪዎች 61ሺህ የሰለጠነ የሰው ሃይል ማቅረብ ተችሏል

👉 ለከፍተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች 24 ቢሊየን 870 ሚሊየን ብር ብር ቀርቧል፣

👉ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የሥራ ማስኬጃ 5,365,455,942 ብር ፣

👉 ለአነስተኛናመካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ለሊዝ ፋይናንስ 2,490,604,769 ብር ማቅረብ ተችሏል፣

👉 350 ሺህ 600 ኪሎዋት ሀይል ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ማቅረብ ተችሏል፣

👉 ለቆዳና ለሌሎች ኢንዱስትሪዎች 269 ሺህ ኩንታል ጨው ማቅረብ ቀርቧል፣

👉 በኢንዱስትሪዎች መካከል 110,058 ቶን የግብዓት ትስስር ተፈጥሯል፣

👉 የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተሻለ የዉጭ ምንዛሬ ክምችትና አቅርቦት እንዲኖር ከፍተኛ እገዛ አድርጓል፣

#ኢትዮጵያ_ታምርት #አምራች_ዘርፍ #ኢንዱስትሪ
👍121🖕1
ኢትዮጵያ ከናሚቢያ እና ሲሸልስ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለፀ
*****
(ኢ ፕ ድ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከናሚቢያና ሲሼልስ አምባሳደሮች ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮቾ ላይ መክረዋል።

በኢትዮጵያ የናሚቢያ አምባሳደር ምባፔዋ ሙቫንጓ ጋር ባደረጉት ውይይት በንግድ፣ ኢንቨስትመንትና #አቪዬሽን የትብብር መስኮች ማጠናከር እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጵያ ከሲሼልስ አምባሳደር ኮንራድ ቪንሴንት ሜድሪች ጋር በነበራቸው ውይይት #ኢትዮጵያ ከሲሸልስ ሁለትዮሽ ግንኙነት አህጉር አቀፍ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመስራት እንደምትሻ መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

ጥር 15 ቀን 2017 ዓም
👍1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በካሳንቺስ አያት የመኖሪያ መንደር የ13 ሺህ 752 መኖሪያ ቤቶች ግንባታን አስጀመሩ
***
(ኢ ፕ ድ)

በካሳንቺስ በ18 ወራት ተገንብተው የሚጠናቀቁ 13 ሺህ 752 የመኖሪያ ቤቶች በመንግስትና በግል አጋርነት ሊገነቡ ነው።

መኖሪያ ቤቶቹ ከአያት አክሲዮን ማህበር ጋር በትብብር የሚገነባ "የካሳንቺስ አያት መኖሪያ መንደር" መሆኑ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግስትና በግል አጋርነት የሚስራ መኖሪያ ቤቶች የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሄዷል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት፤ መኖሪያ ቤት አንገብጋቢ ጉዳይ ነው። ይህንን ለመመለስ የህግ ማሻሻያ ተደርጓል።

በዚህም ቤቶችን ለመገንባት በአራት አማራጮች በመንግስት፣ በመንግስትና በግል፣ በማህበርና በሪል ስቴት በርካታ ቤቶች እንዲገነቡ ማድረግ ነው ብለዋል።

በእነዚህ አማራጮች እስከ አሁን 270 ሺህ ቤቾች መገንባታቸውን የጠቆሙት ከንቲባ አዳነች፤ የቤት አቅርቦት በማስፋት አብዛኛውን ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

የአያት አክሲዮን ማህበር የቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዐቢይ ማሞ፤ "የካሳንቺስ አያት መኖሪያ መንደር" 13 ሺህ 752 የመኖሪያ ቤቶች በውስጡ እንዳሉት ገልፀዋል።

መኖረያ ቤቶች፣ ንግድ ማዕከላት፣ የህዝብ መሰብሰቢያ ፕላዛዎች፣ የልጆች መጫወቻና የስፖርት ማዘውተርያዎችን፣ መዋለ ህጻናቶች፣ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የጤና ተቋማት፣ የህዝብ መጸዳጃ ቤቶችን፣ የመኪና ቻርጂንግ እስቴሽኖች፣ የመኪና እና የብስክሌት ፓርኪንግን አካቶ በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት የሚገነባ ይሆናል ብለዋል።

በሳሙኤል ወንደሰን
👍9🖕1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍4
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 777F እቃ ጫኝ አውሮፕላን ተረከበ
******
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና አለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የአየር እቃ ጭነት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

አየር መንገዱ በዛሬው ዕለት #ቦይንግ 777F እቃ ጫኝ አውሮፕላንም ተረክቧል። ይህም እያደገ የመጣውን የካርጎ አገልግሎት ለማስተናገድ የራሱ አስተዋፅዖ ይኖረዋል ብሏል።

ይህ አዲስ የካርጎ #አውሮፕላን አየር መንገዱ ማህበራዊ ሀላፊነቱን በመወጣት ረገድ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን የሚያግዙና የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ተቋማት የሚለገሱ ቁሳቁሶችን ወደ ሀገር ማምጣቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍14