Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመሰገኑ
******
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፥ ምሻውን የአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ግንባታ ከጅማሮው አንስቶ በስኬት እስኪጠናቀቅ ድረስ አስተዋጽኦ ያበረከቱ አካላትን አመስግነዋል።

ስንተባበርና በአንድነት ስንሰራ ስራችን ጥራት ያለውና ውጤታማ ይሆናልም ብለዋል።

ተግዳሮቶችን በመሻገር የጎደለውን እየሞላን ሀገራችንን ከፍ የሚያደርጉ ትላልቅ ስራዎች ለመስራት አቅም እየፈጠርን ሁላችንም ለስኬት እንደምንበቃ ማዕከሉ ትልቅ ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

የካቲት 30 ቀን 2017 ዓም
👍2👏21
የባሕር በር ጥያቄ የሀገርና የሕዝብ አጀንዳ እንጂ የመንግሥት ብቻ አይደለም
******
(ኢ ፕ ድ)
የባሕር በር ጥያቄ የሀገርና የሕዝብ አጀንዳ እንጂ የመንግሥት ብቻ ስላልሆነ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በባሕር በር ጉዳይ ላይ ከመንግሥት ጎን መቆም እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ በርሄ ገለፁ፡፡

ሊቀመንበሩ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ፓርቲያቸው በኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ዙሪያ ከ1984ዓ.ም አንስቶ የተለያየ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። መሰል አቋም ካላቸው ፓርቲዎች ጋርም በጋራ በመሆን ፊርማ የማሰባሰብ ሥራ ሲሠራ እንደነበር አስታውሰዋል።

አንዳንድ ሀገራት ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር የተደረገውን የባሕር በር ስምምነት እንዳይሳካ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር ገልፀው፤ እንዲህ ያለው የታሪካዊ ጠላቶቻችን እንቅስቃሴ ለእኛ አዲስ አይደለም ብለዋል። https://press.et/?p=146933
👍20👎32
"ክህሎት ስለ ኢትዮጵያ " የተሰኘ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ ተከፈተ

****

(ኢፕድ)

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት "ክህሎት ስለኢትዮጵያ" በሚል የተዘጋጀው የፎቶግራፍ አውደ ርዕይ እና ፓናል ውይይት በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል ተከፈተ።

የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕዩ በአዲስ አበባ የተከፈተ ሲሆን በዚህም ጥንታዊ የክህሎት አጀማመር መሠረቶች፣ በሰመር ካምፕ እና በስታርት አፕ የተሰሩ ሥራዎች፣ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የተሰሩ ማሽኖች እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ የተገኙ ውጤቶች ለእይታ ቀርበዋል።

በመክፈቻው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልን ጨምሮ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ተሻለ በሬቻ፣ አቶ ዳንኤል ተሬሳ፣ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፀዳለ ተክሉ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

መድረኩ ''ክህሎት ስለኢትዮጵያ'' በሚል ርዕሰ ጉዳይ የሚካሄድ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት (ኢፕድ) በምዕራፍ አንድ ስለኢትዮጵያ መድረኩ በ14 የተለያዩ ከተሞች በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይትና ምክክር ማካሄዱ ይታወሳል።

ሁለተኛው ምዕራፍ ደግሞ በቡታጅራና በሐረር ተካሄዷል። ይህ በአዲስ አበባ የሚካሄደው መድረክ የሁለተኛው ምዕራፍ ሶስተኛ ዙር ነው። በድምሩ "ስለኢትዮጵያ" የተሰኘው መድረክ የዛሬውን ጨምሮ ለ17ተኛ ጊዜ ተካሄዷል።

የኢፕድ ስለኢትዮጵያ የፎቶግራፍ አውደ ርዕይና የፓናል ውይይት የሁለተኛ ምዕራፍ የፎቶግራፍ አውደ ርዕዩና የፓናል ውይይቱ በቀጣይም በተለያዩ ከተሞች እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

በሳሙኤል ወንደሰን
👍5
"የየካቲት ወር ሀገርን ሳይሆን አስተሳሰብን ድል የነሳንበት ነው"
- ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል
*******
(ኢ ፕ ድ)

የየካቲት ወር ሀገርን ሳይሆን አስተሳሰብን ድል የነሳንበት ነው ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

ሁለተኛው ምዕራፍ ሦስተኛ ዙር ስለኢትዮጵያ መድረክ "ክህሎት ስለኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ይገኛል።

የየካቲት ወር አባቶቻችን በብዙ መስዋዕትነት ከፍለው የሀገርን ሉዓላዊነት ያስጠበቁበት ነው ያሉት ሚኒስትሯ።

ስለኢትዮጵያ መድረክም የኢትዮጵያ ክብር የሚያሳድጉና የሚያጎለብቱ ተጨባጭ እንዲሁም አሻጋሪ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩበት ነው ብለዋል።

በተለይ ሀገሪቱ ክህሎትን በእጅጉ የሚያስፈልጓት ጊዜ በመሆኑ የመድረኩ ሚና ከፍተኛ ስለመሆኑንም ነው ወይዘሮ ሙፈሪሃት የገለጹት።

ሁለተኛውን ዙር ሶስተኛ መድረክ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።

በልጅዓለም ፍቅሬ

መጋቢት 1 ቀን 2017ዓ.ም
👍71
“ትርክት ከሚገነባባቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ ክህሎት ነው”
- ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር)
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

******

(ኢፕድ)

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ ዶ/ር በክህሎት የበቃ የሰው ሃይል ለአንድ ሀገር ምን አስተዋጽኦ ይኖረዋል በሚል ርዕሰ ጉዳይ ጹሁፍ አቅርበዋል፡፡

ትርክት ከሚገነባባቸው ቁልፍ ጉዳዮች አንዱ ክህሎት መሆኑን ገልጸው፤ ጥራት ያለው ክህሎት ለዜጎች ተደራሽ ለማድረግ አቅረቦት መር ከሆነው ወደገበያ መር ለመቀየር በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የትራንስፎርሜሽን ጉዟችንን ለማሳካት የክህሎት ሚና ትልቅ ነው ያሉት ዶክተር ተሻለ፤ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ኢኮኖሚያዊ ስብራትን መጠገን የሚያስችል ክህሎት መር ሥራዎች ተሰርተዋል ነው ያሉት።

ከኢንዱስትሪው እና ከግል ሴክተሩም ጋር በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና በባህሪው ተግባር ተኮር መሆኑን አንስተው፤ ተግብር ተኮር ስልጠናን እውን ለማድረግ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል ህጋዊ ማዕቀፍ መዘጋጀቱን አብራርተዋል፡፡

እንደ ዶክተር ተሻለ ገለጻ፣ ብቁ የሰው ሃይል ማለት በእውቀት፣ በክህሎት እና በአስተሳሰቡ ዝግጁ የሆነ ነው። የመንግስትና የገል ተቋማት አጋርነታቸውን በማጠናከር እና ክህሎት ልማት ላይ በትኩረት በመስራት በሀገሪቱ ብቁ የሰው ሀይል ማፍራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል፡፡

የስልጠናን ጥራት ለማምጣት ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለውን ትስስር አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በአጫጭር ስልጠና ከሶስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች በመደበኛው ደግሞ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች የሚያልፉ ቢሆንም፤ የክህሎት ልማቱን ከዚህ በላይ ለማሳደግ በትብብር መስራትን ይጠይቃል፡፡

በዘርፉ ያለን ሰዎችም የክህሎት ጥራትን ለማምጣት ያደረግነው ጥረት እና የማስተዋወቅ ስራው በቂ እንዳልሆነ ገልጸው፤ ለክህሎት ልማት ትኩረት መስጠት እና ለሙያና ሙያተኞች የምንሰጠውን ክብርም ማሳደግ ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

በሄለን ወንድምነው

መጋቢት 1/2017ዓ.ም
👍21
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍51👏1