Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ሐረርን እንደ ተምሳሌት በመውሰድ አካባቢን ለመቀየር የሚያስችሉ ሰባት ልምዶችና አቅጣጫዎች ‼️

✍️ የአመራር ቁርጠኝነት

ሐረርን በዋናነት የቀየራት የአመራር ቁርጠኝነት ነው። ዓመታዊ ገቢያቸው ከሌሎች ያነሰ ነው። ለሥራው ያዋሉት በጀትም ዝቅተኛ ነው። ቀሪውን ያሟሉት አመራሩ ቁርጠኛ ሆኖ ቀን ከሌት በመሥራትና ዐቅሙን አሟጥጦ በመጠቀም ነው። ሌሎች ከዚህ መማር አለብን።

✍️ ታሪካዊ ሀብትን ዐውቆ ማልማት

ሐረር ና አካባቢዋ ከሺ ዓመታት የዘለለ ታሪካዊ ሀብት አላቸው። ይሄንን ሀብት በማወቅ እና በመለየት ለጉብኝት ምቹ አድርገውታል። መንገድ ተሠርቷል፤ ሙዝየም ተገንብቷል። የአካባቢውን ንጽሕና የመጠበቅ ሥራም እየተሠራ ነው። ይሄ ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ነው።

✍️ጥንታዊ አካባቢን አናብቦ ማዘመን

የሺ እና የመቶ ዓመታት ታሪክ ያላቸው የኢትዮጵያ ከተሞች እንዴት መቀየር እንዳለባቸው ሐረር ተምሳሌት ናት። ጀጎል ተለውጧል። የውስጥ ለውስጥ መንገዱ ተዘርግቷል። ግንቡን ለመጠገን የተሠራው ሥራ፣ የመብራት ሥራው፤ ጥንታዊው ከተማ የወዳደቁ ቤቶች መከማቻ እንዳይሆን እየተሠራ ያለው ሥራ፣ ጀጎልን ሁሌ አዲስ እንድትሆን አድርጓታል። ያረጁና ያፈጁ ከተሞች እንዴት እንደሚቀየሩ መማሪያ ነው።

✍️ አካባቢያዊ ልዩ ጸጋን ለቱሪዝም መጠቀም

ሐረር ሰዎችና የዱር እንስሳት ተግባብተው የሚኖሩባት ከተማ ናት። ለዚህ አንዱ ማሳያ የጅብ ትርዒት ነው። ከመቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ ሐረርን የጎበኙ ጸሐፍት ይሄንን ትርዒት አድንቀው ጽፈዋል። ይሄንን ትርዒት ወደ ዘመናዊ የቱሪስት መዳረሻነት ለመቀየር በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ መነሻነት የጅብ ትርዒት ማሳያ አምፊ ቴአትር በሐረር ተገንብቷል። በየአካባቢያችን ያሉትን ልዩ ጸጋዎች በዚህ መንገድ ነው ዐውቀን ማልማት ያለብን።

✍️ ለኮሪደር ሥራ አካባቢያዊ ዕውቀትን መጠቀማቸው

በአንዳንድ ከተሞች የኮሪደር ልማት በውድ ዋጋ የሚገኙትን የመንገድ መብራቶች ሐረሮች በአካባቢያቸው በማምረት በርካሽ አግኝተዋቸዋል። የመንገድ መብራትን ለመጠገን ያለውን ችግር በሚፈታ መልኩ ሐረሮች የመንገዶቻቸውን መብራቶች በርካሽና በተሻለ መንገድ ሠርተዋል። ሥራን ውድ የሚያደርገው ሀብትንና ዕውቀትን በሚገባ አለመጠቀም ነው።

✍️ በአካባቢ ጸጋ አካባቢን ማስዋብ

ሐረር ላይ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የተሠሩት በሐረር ድንጋይ ተጠርበው ነው። ይሄ ተግባር አዱሱ ግንባታ ከነባሩ ጋር እንዲጣጣም አድርጓል። ለአካባቢው ወጣቶችም የሥራ ዕድል ፈጥሯል፤ በጥቂት ወጪ ብዙ ሥራ ለመሥራትም አስችሏል፤ የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር አድርጓል። ዘወር ዘወር ብለን መሬቱን እንየው። ለልማት የሚውል ብዙ ሀብት አለው።

✍️ አስፍቶ ማሰብ

ሐረር በቆዳ ስፋት ከብዙ ክልሎች ያነሰች ናት። ታሪካዊ ከተማ በመሆኗም የነዋሪዎች መጨናነቅ እና የቦታ ጥበት አለ። ጠባብን ቦታን የሚያሰፋው ሰፊ አመለካከት ነው። ሩቅን የሚያቀርበው አርቆ ተመልካችነት ነው። የሐረር የኮሪደር ልማት ሰፊ የሆነው በዚህ ዕይታ ነው። በዚህ ዕይታ የተሠሩት የእግረኛ መንገዶች፣ ፓርኮች፣ አምፊ ቴአትሮች፣ አረንጓዴ ሥፍራዎች፣ ወዘተ አስደናቂ ናቸው። አስፍቶ ማሰብ ጥቁቱን ያበዛል፣ ሩቁን ያቀርባል።

መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓም
👍41
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍6👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት የእምነበረድ ፋብሪካ፣ የዘይት ማቀነባበሪያና ለምሥራቅ ዕዝ የተገነቡ አፓርትመንቶች ምረቃን ጨምሮ የመከላከያ ሆስፒታል ጉብኝት በፎቶ‼️
👍6👏2
የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ ነገ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርና የኮሚሽነሮች ይፋዊ የስራ ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።

በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት መሃመድ አሊ ዩሱፍ ከተሰናባቹ ሙሳ ፋኪ ማሀማት ስልጣን በመረከብ በይፋ ስራ ይጀምራሉ።

መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓም
👍13👏1
አዲስ ዘመን https://press.et/?p=147386
ዘኢትዮጵያ ሄራልድ https://press.et/herald/?p=111852
1