Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በ2017 በጀት ዓመት እስከ አሁን ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር አምርቷል
****
(ኢ ፕ ድ)

የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ በ2017 በጀት ዓመት እስከ አሁን ከ500 ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር ማምረቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አስታወቀ።

ፋብሪካው የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ብሩክ ታዬ(ዶ/ር)፣ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ እና የተቋሙ አመራሮች የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ የተቋሙን አፈጻጸም መገምገምና የመሰረተ ልማት አቅሙን መፈተሽ እንደሆነ ተገልጿል።

ፋብሪካው በበጀት ዓመቱ ማብቂያ ለማምረት ያቀደውን የአንድ ሚሊዮን ኩንታል ስኳር እቅድ ለማሳካት በትክክለኛ መስመር ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል። ፋብሪካው ከዋና ምርቱ በተጓዳኝ የግብርና ምርቶችን በማምረት ለሰራተኞቹና ለአካባቢው ማህበረሰብ እንቁላል፣ አሳና አትክልቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አመራሮች ኩባንያው በግብርናው መስክ እያሳየ ያለው ለውጥ፣ የሜካናይዜሽን አጠቃቀምን በማሳደግ፣ የእርሻ ስራዎችን በማስፋፋት፣ በአቅም ግንባታ እና ስትራቴጂካዊ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመጠቀም እያስመዘገበ ያለው ውጤት መልካም እንደሆነ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ መረጃ ያመለክታል።

#ወንጂሸዋ

መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓም
👍8👏1
ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት የመንገድ ደህንነት ፈንድ የቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በተባበሩት መንግስታት የመንገድ ደህንነት ፈንድ (ዩኤንአርኤስኤፍ) የቦርድ አባል ሆነው ተሾመዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሀገራዊ የመንገድ ደህንነት ስትራቴጂ በመቅረፅና የመንገድ ደህንነት ትምህርት በስርዓተ ትምህርት ውስጥ እንዲካተት በማድረግ የወሰደችው እርምጃ የመንገድ ደህንነትን ለማስፈን ያላትን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን ለሚኒስትሩ በተፃፈው የሹመት ደብዳቤ ተገልጿል፡፡

በኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ስራዎች የተገነቡ ምቹ የብስክሌትና የእግረኛ መንገዶች እንዲሁም የተሻሻሉ የመንገድ ትስስር ስራዎች እንደ ሀገር የትራንስፖርት መሰረተ ልማት ቅንጅትን የሚያሳድጉ መሆናቸውም በደብዳቤው ተጠቁሟል፡፡

የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ኢትዮጵያ በመንገድ ደህንነት ላይ ያላትን ቁርጠኝነትና የምታደርገውን ጥረት በመገንዘብና እውቅና በመስጠት ዓለሙ ስሜን (ዶ/ር) በዩኤንአርኤስኤፍ ስር የባለአደራዎች ቦርድ የቦርድ አባል ሆነው መሾማቸውን አሳውቋል፡፡

የሚኒስትሩ በቦርድ አባልነት መሾም ኢትዮጵያ ልምዷን ለሌሎች ሀገራት እንድታጋራና ከመላው ዓለም በመንገድ ደህንነት ላይ የተሻሉ ተሞክሮዎችን እንድታገኝ መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ዩኤንአርኤስኤፍ በፈረንጆቹ 2018 ሚያዚያ ወር ላይ የተመሠረተ ሲሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ጠቀሜታ ላላቸው ፕሮጀክቶች ተጨማሪ ገንዘብ የማሰባሰብ እና የመደገፍ ስራን የሚሰራ ተቋም እንደሆነም የትራስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓም
👍3👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬደዋ የተደረገላቸው አቀባበል‼️
👏42👍1
ሐረርን እንደ ተምሳሌት በመውሰድ አካባቢን ለመቀየር የሚያስችሉ ሰባት ልምዶችና አቅጣጫዎች ‼️

✍️ የአመራር ቁርጠኝነት

ሐረርን በዋናነት የቀየራት የአመራር ቁርጠኝነት ነው። ዓመታዊ ገቢያቸው ከሌሎች ያነሰ ነው። ለሥራው ያዋሉት በጀትም ዝቅተኛ ነው። ቀሪውን ያሟሉት አመራሩ ቁርጠኛ ሆኖ ቀን ከሌት በመሥራትና ዐቅሙን አሟጥጦ በመጠቀም ነው። ሌሎች ከዚህ መማር አለብን።

✍️ ታሪካዊ ሀብትን ዐውቆ ማልማት

ሐረር ና አካባቢዋ ከሺ ዓመታት የዘለለ ታሪካዊ ሀብት አላቸው። ይሄንን ሀብት በማወቅ እና በመለየት ለጉብኝት ምቹ አድርገውታል። መንገድ ተሠርቷል፤ ሙዝየም ተገንብቷል። የአካባቢውን ንጽሕና የመጠበቅ ሥራም እየተሠራ ነው። ይሄ ለሌሎችም ትምህርት የሚሆን ነው።

✍️ጥንታዊ አካባቢን አናብቦ ማዘመን

የሺ እና የመቶ ዓመታት ታሪክ ያላቸው የኢትዮጵያ ከተሞች እንዴት መቀየር እንዳለባቸው ሐረር ተምሳሌት ናት። ጀጎል ተለውጧል። የውስጥ ለውስጥ መንገዱ ተዘርግቷል። ግንቡን ለመጠገን የተሠራው ሥራ፣ የመብራት ሥራው፤ ጥንታዊው ከተማ የወዳደቁ ቤቶች መከማቻ እንዳይሆን እየተሠራ ያለው ሥራ፣ ጀጎልን ሁሌ አዲስ እንድትሆን አድርጓታል። ያረጁና ያፈጁ ከተሞች እንዴት እንደሚቀየሩ መማሪያ ነው።

✍️ አካባቢያዊ ልዩ ጸጋን ለቱሪዝም መጠቀም

ሐረር ሰዎችና የዱር እንስሳት ተግባብተው የሚኖሩባት ከተማ ናት። ለዚህ አንዱ ማሳያ የጅብ ትርዒት ነው። ከመቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ ሐረርን የጎበኙ ጸሐፍት ይሄንን ትርዒት አድንቀው ጽፈዋል። ይሄንን ትርዒት ወደ ዘመናዊ የቱሪስት መዳረሻነት ለመቀየር በመደመር ትውልድ መጽሐፍ ሽያጭ መነሻነት የጅብ ትርዒት ማሳያ አምፊ ቴአትር በሐረር ተገንብቷል። በየአካባቢያችን ያሉትን ልዩ ጸጋዎች በዚህ መንገድ ነው ዐውቀን ማልማት ያለብን።

✍️ ለኮሪደር ሥራ አካባቢያዊ ዕውቀትን መጠቀማቸው

በአንዳንድ ከተሞች የኮሪደር ልማት በውድ ዋጋ የሚገኙትን የመንገድ መብራቶች ሐረሮች በአካባቢያቸው በማምረት በርካሽ አግኝተዋቸዋል። የመንገድ መብራትን ለመጠገን ያለውን ችግር በሚፈታ መልኩ ሐረሮች የመንገዶቻቸውን መብራቶች በርካሽና በተሻለ መንገድ ሠርተዋል። ሥራን ውድ የሚያደርገው ሀብትንና ዕውቀትን በሚገባ አለመጠቀም ነው።

✍️ በአካባቢ ጸጋ አካባቢን ማስዋብ

ሐረር ላይ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች የተሠሩት በሐረር ድንጋይ ተጠርበው ነው። ይሄ ተግባር አዱሱ ግንባታ ከነባሩ ጋር እንዲጣጣም አድርጓል። ለአካባቢው ወጣቶችም የሥራ ዕድል ፈጥሯል፤ በጥቂት ወጪ ብዙ ሥራ ለመሥራትም አስችሏል፤ የዕውቀት ሽግግር እንዲኖር አድርጓል። ዘወር ዘወር ብለን መሬቱን እንየው። ለልማት የሚውል ብዙ ሀብት አለው።

✍️ አስፍቶ ማሰብ

ሐረር በቆዳ ስፋት ከብዙ ክልሎች ያነሰች ናት። ታሪካዊ ከተማ በመሆኗም የነዋሪዎች መጨናነቅ እና የቦታ ጥበት አለ። ጠባብን ቦታን የሚያሰፋው ሰፊ አመለካከት ነው። ሩቅን የሚያቀርበው አርቆ ተመልካችነት ነው። የሐረር የኮሪደር ልማት ሰፊ የሆነው በዚህ ዕይታ ነው። በዚህ ዕይታ የተሠሩት የእግረኛ መንገዶች፣ ፓርኮች፣ አምፊ ቴአትሮች፣ አረንጓዴ ሥፍራዎች፣ ወዘተ አስደናቂ ናቸው። አስፍቶ ማሰብ ጥቁቱን ያበዛል፣ ሩቁን ያቀርባል።

መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓም
👍41
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍6👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት የእምነበረድ ፋብሪካ፣ የዘይት ማቀነባበሪያና ለምሥራቅ ዕዝ የተገነቡ አፓርትመንቶች ምረቃን ጨምሮ የመከላከያ ሆስፒታል ጉብኝት በፎቶ‼️
👍6👏2