Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
303 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ አዲስ አበባ ገቡ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የአንጎላው ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ አዲስ አበባ ገብተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ጆአዎ ሎሬንዞ ነገ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበርና የኮሚሽነሮች ይፋዊ የስራ ርክክብ ስነ-ስርዓት ላይ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።

በ38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት መሃመድ አሊ ዩሱፍ ከተሰናባቹ ሙሳ ፋኪ ማሀማት ስልጣን በመረከብ በይፋ ስራ ይጀምራሉ።

መጋቢት 3 ቀን 2017 ዓም
👍13👏1
አዲስ ዘመን https://press.et/?p=147386
ዘኢትዮጵያ ሄራልድ https://press.et/herald/?p=111852
1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍71
"የአንጎላ ፕሬዝዳንት ማኑኤል ጎንካልቬስ ሎሬንቾን ወደ ኢትዮጵያ እንኳን ደህና መጡ እላለሁ። ውይይታችን የሁለትዮሽ ጉዳዮችን ለመዳሰስ እንዲሁም ክቡር ፕሬዝደንቱ በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነታቸው ቁልፍ አኅጉራዊና ባለ ብዙወገን ጉዳዮችን ለመመልከት ችለናል"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓም
👍1
ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በወታደራዊ ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተፈራረሙ
******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የሩዋንዳ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሙባረክ ሙጋጋ ተፈራርመዋል።

የመከላከያ ውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ ኢትዮጵያና ሩዋንዳ በልዩ ልዩ ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለረጅም ዓመታት ሲሰሩ መቆየታቸውን አንስተዋል።

አሁን ላይ የነበረውን ሁለንተናዊ ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸውም ተገልጿል።

በወታደራዊ አቅም ግንባታ ስልጠና፣ በተሞክሮ ልውውጥ፣ ሽብርተኝነትን በመከላከል እና በሌሎች ተያያዥ ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ከስምምነት ላይ መደረሱን ተናግረዋል።

በሩዋንዳ መከላከያ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄነራል ብርጋዲየር ጄኔራል ፓትሪክ ካሪታዋ በበኩላቸው ኢትዮጵያና ሩዋንዳ ረጅም ጊዜያትን ያስቆጠረ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው አስታውሰዋል።

ኢትዮጵያ በችግራችን ጊዜ ፈጥና የደረሰችልን ሀገር ነች ያሉት ብርጋዲየር ጄኔራሉ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ ጉዳዮች ያለንን ግንኙነት አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓም
👍4👏1