ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👏2👍1
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
ብልጽግና ፓርቲ የተከተለው አካሄድ የጸረ ሰላም ቡድኖችን ዓላማና ሕልውና ማክሸፍ አስችሏል - አቶ ይርጋ ሲሳይ **** (ኢ ፕ ድ) ብልጽግና ፓርቲ የተከተለው በመርሕ ላይ የተመሰረተ አካሄድ የጸረ ሰላም ቡድኖችን ዓላማና ሕልውና ለማክሸፍ አስችሏል ሲሉ በፓርቲው የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ ገለጹ፡፡ በአማራ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩና አካባቢውን ለማተራመስ ሲጥሩ በነበሩ ፀረ…
ብልጽግና ፓርቲ የተከተለው አካሄድ የጸረ ሰላም ቡድኖችን ዓላማና ሕልውና ማክሸፍ አስችሏል - አቶ ይርጋ ሲሳይ
****
(ኢ ፕ ድ)
ብልጽግና ፓርቲ የተከተለው በመርሕ ላይ የተመሰረተ አካሄድ የጸረ ሰላም ቡድኖችን ዓላማና ሕልውና ለማክሸፍ አስችሏል ሲሉ በፓርቲው የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይ ገለጹ፡፡
በአማራ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩና አካባቢውን ለማተራመስ ሲጥሩ በነበሩ ፀረ-ሰላም ቡድኖች በርካታ ፈተናዎችን ሲያስተናግድ መቆየቱን ጠቁመዋል።
በሕዝቡ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ክልሉ አስደናቂ ለውጦችን እውን ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
የለውጡ አመራር የሚከተላቸው ሀገራዊ አንድነትን ማዕከል ያደረጉ፣ ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በውይይት የመፍታት እና ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚያዊ ልማትን እውን የማድረግ መርሆዎች ውጤት አስመዝግበዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሁሉም ማዕዘናት ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ያለው ቁርጠኛ አቋም ፍሬዎች መታየት መጀመራቸው የፓርቲውን እሳቤዎችና ሀገራዊ ራዕይ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ማስቻሉን አንስተዋል፡፡
የፓርቲው ጥረት በአማራ ክልል ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡን ጠቁመው÷ የክልሉን ሰላምና የሕዝቡን ደህንነት ለአደጋ አጋልጠው የቆዩትን ፀረ-ሰላም ቡድኖች እውነተኛ ማንነትና ዓላማ ሕዝብ እንዲገነዘብ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ፀረ-ሰላም ቡድኖቹ በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክመው ወደማይቀረው የክስመት ደረጃ ላይ ደርሰዋል መድረሳቸውን ያመላከቱት አቶ ይርጋ ሲሳይ ፓርቲው ከምሥረታው ጀምሮ ዘላቂ ሰላምን እውን ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው አጀንዳዉ አድርጎ መቆየቱን አስታውሰዋል፡፡
የማህበረሰብ ውይይትን በስፋት በማካሄድ፣ ከታሪክ የተወረሱ ሀገራዊ የትርክት ቅራኔዎችን ለመፍታት በመስራትና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማምጣት የሚያስችሉ ሰፋፊ ሥራዎች መከናወናቸውንም አንስተዋል፡፡
ሁሉን አቀፍ፣ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሲሰራ መቆየቱን አብራርተዋል።
በመከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራልና የክልል መንግስታትና የፀጥታ ሃይሎች የተቀናጀ ጥረትም የፀረ-ሰላም ቡድኖች ተጽእኖ በእጅጉ መቀነሱን አንስተዋል፡፡
ብልጽግና ፓርቲ ችግሩን ለመፍታት መሰረታዊ የማህበረሰብ ተሳትፎን በማበረታታቱና በሕዝብ ባለቤትነት በሚመራ ስልት ላይ ትኩረት በማድረጉ የፅንፈኛ ቡድኖችን አጀንዳዎችና ዓላማ በማክሸፍ ዜጎች በጋራ ሆነው በሰላም ዙሪያ እንዲሰባሰቡ በማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው የፓርቲው መረጃ ያመላክታል፡፡
መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓም

👍9
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት ልዩ የማኅበረሰብ ጤና ተቋም የሆነውን የአፍሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል መቀመጫ በመሆኗ ክብር ይሰማታል።
በማዕከሉ ያሉት ላቦራቶሪዎችና የምርምር አቅሞች በበሽታ መቆጣጠር ብሎም በወረርሽኞችና ተላላፊ በሽታዎች ምላሽ በመስጠት ሥራ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታሉ። ይኽ እድል ለሀገራችን የጤናው ዘርፍ ተመራማሪዎችና ባለሞያዎች በአኅጉራዊ የምርምር ጥረቶች በመሳተፍ በዘመናዊ ላብራቶሪዎች እንዲጠቀሙም መንገድ ይከፍታል።
አባል ሀገራት ከአጋሮች ጋር በመተባበር ይኽን ተቋም ማጠናከር ይገባናል። በመሆኑም የአፍሪካ መሪዎች አኅጉራዊ የማኅበረሰብ ጤና ተቋማችን በመላው አኅጉራችን የጤና አገልግሎት በማሳደግ ላይ ተቀዳሚ በማድረግ ሥራ ላይ በሙሉ ኃላፊነት እንድንተባበር ጥሪ አቀርባለሁ።
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

❤5👍3👏1🤔1
ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ባንክ አዲስ ለሚገነባው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ
********
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ቢሾፍቱ አቅራቢያ አቡሴራ አካባቢ አዲስ ለሚገነባው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የፍላጎት መግለጫ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።
የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዌሚ አዴሲና ለኢትዮጵያ ልዑክ አቀባበል አድርገዋል።
ልዑኩ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ያካተተ ነው።
ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድን አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ያሳድጋል ተብሎም ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

👍8👏2❤1
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባሕር ኃይል በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ
*******
(ኢ ፕ ድ)
የሩሲያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ አድሚራል ቪላዲሚር ቮሮቢቭ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የሚገነባቸውን የባሕር ኃይል ተቋማት ጠቅላይ መምሪያውና ቢሾፍቱ የሚገኘውን ማሰልጠኛ ማዕከል ጎብኝቷል፡፡
በጉብኝቱ በጋራ ባሕር ኃይልን በሚያጠናክሩና በቀጣይ ትብብሮች ለማመቻቸት ስምምነት ተፈርሟል፡፡ በቀጣይ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጋር በሚኖሩ ትብብሮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳ፤ ትብብሩ በስልጠናና ዐቅም ግንባታ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በቀጣይም አብሮ በመሥራት ተቋማችን የጀመረውን የባሕር ኃይል ግንባታ ለማጠናከርና በዓለም አቀፍ ውኃ ላይ የሀገራችንን ጥቅም ለማስከበር ዝግጁነታችንን የበለጠ ለማጠናከር መክረናል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

👍17👏6❤3😁3
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍11👏1