Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ኢትዮጵያና የአፍሪካ ልማት ባንክ አዲስ ለሚገነባው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ
********
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ልማት ባንክ ቢሾፍቱ አቅራቢያ አቡሴራ አካባቢ አዲስ ለሚገነባው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የፍላጎት መግለጫ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት አኪንዌሚ አዴሲና ለኢትዮጵያ ልዑክ አቀባበል አድርገዋል።

ልዑኩ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰውን ያካተተ ነው።

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት በቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ የሚገነባ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድን አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ያሳድጋል ተብሎም ይጠበቃል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓም
👍8👏21
ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በባሕር ኃይል በትብብር መሥራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መከሩ
*******
(ኢ ፕ ድ)
የሩሲያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ አድሚራል ቪላዲሚር ቮሮቢቭ የተመራ ልዑክ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የሚገነባቸውን የባሕር ኃይል ተቋማት ጠቅላይ መምሪያውና ቢሾፍቱ የሚገኘውን ማሰልጠኛ ማዕከል ጎብኝቷል፡፡

በጉብኝቱ በጋራ ባሕር ኃይልን በሚያጠናክሩና በቀጣይ ትብብሮች ለማመቻቸት ስምምነት ተፈርሟል፡፡ በቀጣይ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጋር በሚኖሩ ትብብሮች ዙሪያ ምክክር አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሞዶር ጀማል ቱፊሳ፤ ትብብሩ በስልጠናና ዐቅም ግንባታ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በቀጣይም አብሮ በመሥራት ተቋማችን የጀመረውን የባሕር ኃይል ግንባታ ለማጠናከርና በዓለም አቀፍ ውኃ ላይ የሀገራችንን ጥቅም ለማስከበር ዝግጁነታችንን የበለጠ ለማጠናከር መክረናል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓም
👍17👏63😁3
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍11👏1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በየአመቱ የሚያከናውኑትን የኢፍጣር መርሐግብር በዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች በብሔራዊ ቤተመንግሥት አከናውነዋል።

#PMOEthiopia
👍10👏21