Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትሃድ አየር መንገድ ስትራቴጂክ የቢዝነስ ስምምነት ተፈራረሙ

👉 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሀምሌ 8 ቀን 2017 ጀምሮ ከአዲስ አበባ አቡዳቢ በረራ ይጀምራል፣

👉 ኢታሃድ አየር መንገድ ከመስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከአቡዳቢ አዲስ አበባ ቀጥታ በራራ ይጀምራል፣

*
**
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኢትሃድ አየር መንገድ የአየር ትራንስፖርት ትስስርን ለማጠናከርና በትብብር ለመስራት የሚስችላቸውን ስትራቴጂክ የቢዝነስ ስምምነት ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፤ በኢትሀድ ኤርዌይስ በኩል የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንቶላዶ ኔቬስ ፈርመዋል።

ስምምነቱ ለደንበኞች የተቀላጠፈ የበረራ አማራጭ ለማቅረብ በሁለቱ አየር መንገዶች መካከል “የኮድ ሼር” አገልግሎት፣ በአዲስ አበባና አቡዳቢ መካከል የበረራ አገልግሎት መጀመርን ያካተተ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሀምሌ 8 ቀን 2017 ጀምሮ ከአዲስ አበባ አቡዳቢ በረራ ይጀምራል። ኢታሃድ አየር መንገድ ከመስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከአቡዳቢ አዲስ አበባ ቀጥታ የበራራ አገልግሎት ይጀምራል ተብሏል።

በስምምነት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሌ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢቲሃድ ኤርዌይስ ቦርድ ሰብሳቢ ሞሀመድ አሊን፣ የሁለቱ አየር መንገዶች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች መሳተፋቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍82👏1
የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የተዳራደሪ ቡድን ስብሰባ በጄኔቫ መካሄድ ጀመረ
****
(ኢ ፕ ድ)

5ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር የስራ ቡድን አባላት ስብሰባ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ መካሄድ ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ ቡድን መሪ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ኢትዮጵያ ለዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ዝግጁ መሆኗን በመድረኩ አስረድቻለሁ ብለዋል፡፡

አባል ሀገራት የሁለትዮሽ የንግድ ድርድራቸውን ከወዲሁ እንዲያጠናቅቁ በመድረኩ ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጸው በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ከ19 ሀገራት በላይ የድጋፍ መልእክት በማስተላለፍ ኢትዮጵያን ማበረታታቸውን ገልፀዋል፡፡

መድረኩ በጥያቄና መልስ መርሐ-ግብር እስከምሽት እንደሚቀጥልም አመላክተዋል፡፡

መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓም
👍6👏1
ሀገር በቀል እውቀቶችን ከፋሽን ኢንዱስትሪው ጋር አስተሳስሮ የዜጎችን ተጠቃሚነትን ማላቅ ያሰፈልጋል
****
(ኢ ፕ ድ)

የማፊ ፋሽን ዲዛይን መሥራች ወ/ሮ ማህሌት አፈወርቅ ጋር በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ ላይ በቅንጅት መሥራት በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እያደገ የመጣው የፋሽን ኢንዱስትሪ ያለውን እምቅ አቅም አሟጦ ለመጠቀም የግሉ ዘርፍ ሚና የማይተካ መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገር በቀል እውቀቶችን ከፋሽን ኢንዱስትሪው ጋር አሰናስሎ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማላቅ ሥነ-ምኅመዳሩን ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል ብለዋል።

የማፊ ፋሽን ዲዛይን መሥራች ወ/ሮ ማህሌት አፈወርቅ በመስኩ በትብብር በመሥራት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማላቅ ላሳዩት ቁርጠንነትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓም
👍112👏2
"በየአካባቢው የምንዋጋቸው ሰዎች የድንቁርና ጌቶች ናቸው፣ አትማሩ፣ አትታከሙ፣ አታልሙ፣ የሚሉ ናቸው።

በሀገሪቱ በየትኛውም ጎጥ ያለ የጎበዝ አለቃ ይደራደራል፣ ነገር ግን መደራደሩ ጥቅም እንደሌለው የሚዘምተውም ራሱ ነው"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍7👏1
ሁለተኛው የኢትዮጵያ ህዳሴ የአፍር ማዳበሪያ ፋብሪካን ማቋቋም ነው
*******
(ኢ ፕ ድ)

ሁለተኛው የኢትዮጵያ ህዳሴ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካን ማቋቋም ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ ማዳበሪያን ማምረት አለመቻሏ በርካታ አርሶ አደርን የሚነካ ጉዳይ በመሆኑ በዘላቅነት ለመፍታት ጥናት ሲደረግ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

በተደረገው ጥናት ከ2 ነጥብ 5 እስከ 3 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል፤ የማዳበሪያ ፋብሪካውን አቋቁሞ ለመስራት በትንሹ ሶስት ዓመትና ከዚያ በላይ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቁመዋል፡፡

ይህንን ከተቻለ ከግሉ ዘርፍ ጋር፣ በግለሰብ ኢንቨስትመንት ካልተቻለም መንግስት በራሱ የሚገነባ ይሆናል ብለዋል።

የአፍር ማዳበሪያ የኢትዮጵያን ፍላጎት በሚመልስ መልኩ መመረት እንዳለበት ጠቅሰወ፣ ፋብሪካው የማቋቋም ሂደቱ ምናልባትም በሚቀጥለው ዓመት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እንደሚጀመሩ አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ 24 ሚሊየን ኩንታል ገደማ የአፍር ማዳበሪያ የሚያስፈልጋት ሲሆን፤ በቀን 150 ሺህ ኩንታል የአፍር ማዳበሪያ ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ ታጓጉዛለች፤ ይህንን ወደ እያንዳንዱ አርሶ አደር በወታደር ታጅቦ ይሰራጫል።

በአማራ ክልል ለሚገኙ አርሶአደሮች 7ሺህ የጭነት ትራንስፖርት የአፍር ማዳበሪያ በመከላከያ ሰራዊት ታጅቦ መዳረሱን አስታውሰው፤ መንግስት በብዙ ሂደት አልፎ ማዳበሪያውን ወደሀገር ውስጥ ካመጣ በኋላ ለአርሶ አደሩ ማዳረሱም ሌላ ወጭ እየሆነበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በቃልኪዳን አሳዬ

መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓም
👍94👏1🙏1
"የፕሪቶሪያውን ስምምነት በሚያከብር መልኩ የትግራይ ህዝብ ምርጫ መምረጥ ይኖርበታል"

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
****
(ኢ ፕ ድ)

የፕሪቶሪያውን ስምምነት በሚያከብር መልኩ ለውጦች ተደርገው የትግራይ ህዝብ ምርጫ መምረጥ ይኖርበታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ ምንም አይነት ግጭት እንዳይኖር ችግሮች በንግግር እንዲፈቱ የበኩሉን ጥረት አድርጓል፡፡

አሁን ላይ የተሰጠው የሁለት ዓመት ጊዜ እየተጠናቀቀ ስለሆነ የህግ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አሉ ብለዋል፡፡

በመሆኑን የነበረው አፈጻጸም ተገምግሞ የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚያከብር መልኩ መጠነኛ ለውጥ ተደርጎ የክልሉ ህዝብ ምርጫ የሚያካሂድበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል፡፡

ይህን ለማድረግም ከጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ውይይት ተደረጓል ብለዋል፡፡

የፕሪቶሪያው ስምምነት ታሪካዊና በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይ ህዝብ በውጊያው ጊዜ ምንም አገልግሎት አላገኘም፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ምንም አይነት ውጊያ አለመኖሩ ትልቅ ነገር ነው።

የተፈናቀሉ ዜጎችን በተለመከተ መንግስት በቂ ትብብር ከተደረገለት የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዳግማዊት አበበ

መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓም
👍102👏1
“እንደ ህዳሴ ግድብ ሁሉ የኢትዮጵያ ቀጣዩ ታላቅ ስራ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ነው"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍27👏75
አዲስ ዘመን መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓም
https://press.et/?p=147950
👏3👍2
በሰሜን ተራሮች የሚገኙ የዋልያዎች ቁጥር ወደ 300 መውረዱን የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ

👉 ብዝሃ ሕይወትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ለመንከባከብ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ያሰፈልጋል
*******
(ኢ ፕ ድ)

በሰሜን ተራሮች የብርቅዬ ዋልያዎች ቁጥር ከዚህ በፊት ከነበረው ተመናምኖ ወደ 300 ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ።
👍4😱21👏1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
🥰1
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
በሰሜን ተራሮች የሚገኙ የዋልያዎች ቁጥር ወደ 300 መውረዱን የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ 👉 ብዝሃ ሕይወትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ለመንከባከብ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ያሰፈልጋል ******* (ኢ ፕ ድ) በሰሜን ተራሮች የብርቅዬ ዋልያዎች ቁጥር ከዚህ በፊት ከነበረው ተመናምኖ ወደ 300 ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ።
በሰሜን ተራሮች የሚገኙ የዋልያዎች ቁጥር ወደ 300 መውረዱን የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ

👉 ብዝሃ ሕይወትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ለመንከባከብ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ያሰፈልጋል
*******
(ኢ ፕ ድ)

በሰሜን ተራሮች የብርቅዬ ዋልያዎች ቁጥር ከዚህ በፊት ከነበረው ተመናምኖ ወደ 300 ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ።

የዱር እንስሳት ልማት እና ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኩማራ ዋቅጅራ ለኢፕድ እንደገለፁት፤ በሰሜን ተራሮች የብርቅዬ ዋልያዎች ቁጥር ከዚህ በፊት አደጋ ላይ መውደቁን ተከትሎ በተሠራ የእንክብካቤ ሥራ የዋልያዎቹ ቁጥር አንድ ሺህ መድረስ ችሎ ነበር ብለዋል።

በሰሜኑ ክፍል ካለው የፀጥታ ችግር ሳቢያ የቁጥጥር መላላት፣ የእሳት አደጋና የሕገወጥ አደኖች መበራከት አንድ ሺህ መድረስ ችሎ የነበረው የሰሜን ተራሮች የዋልያዎች ቁጥር ተመናምኖ ወደ 300 መውረዱን ገልጸዋል።

እአአ በ1973 ሀገራት ቁጥራቸው እየተመናመኑ የሚገኙ እንስሳትና ዕፅዋትን ከጥፋት ለመታደግ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት "ሳይተስ" የሚባል ስምምነት አድርገዋል፤ ስምምነቱ ዓለም አቀፍ ንግድን የሚቆጣጠር አሠራር ነው። ኢትዮጵያም ከ1989 ጀምሮ የስምምነቱ አካል ሆናለች።

ከስምምነቱ አስቀድሞ በርካታ የእንስሳትና እፅዋት ዝርያዎች ለዓለም አቀፍ ንግድ ይውሉ ነበር። አብዛኞቹም ለመጥፋት የተቃረቡበት ወቅት ነበር የሚሉት አቶ ኩመራ፤ አሁን ላይ 38 ሺህ የሚደርሱ ዕፅዋትና የዱር እንስሳት ዓለም አቀፍ የንግድ ቁጥጥር እንደሚደረግባቸው አመላክተዋል።

የብዝኃ ሕይወትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ለመንከባከብ እስከ 300 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግና ይህን የፋይናንስ ክፍተት መሙላት እንደሚገባ ገልጸዋል። https://press.et/?p=147765
👍2👏1😁1
ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውኃ ትራንስፖርት የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች እየገቡ ነው
******
(ኢ ፕ ድ)

በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውሃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ የተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች ከጅቡቲ ወደብ ተጭነው ወደ ሀገር ቤት በማምራት ላይ ናቸው።

ጣና ነሽ ፪ የተሰኘችው ዘመናዊ የህዝብ ትራንስፖርት ጀልባ 38ሜ እርዝመት እንዳላት እና በአንድ ግዜ 188 ሰዎችን የመጫን አቅም እንዳላት መዘገቡ ይታወሳል።

ሌላኛዋ መለስተኛ ፈጣን ቃኝ ጀልባ ዘመናዊ የሰው ማጓጓዣና የመዝናኛ ጀልባ እንደሆነች የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መረጃ ያመለክታል።

መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓም
👍7👏2
የአፍሪካ ህብረት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ ገለጸ
***
(ኢ ፕ ድ)

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ለማምጣት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፍ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ የሱፍ ገለጹ።

ሊቀመንበሩ የአንጎላ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የህብረቱ ሊቀመንበር ጆአኦ ሎሬንሶ ኮንካልቬስ በሉዋንዳ የሰላም ሂደት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ያለውን ግጭት ለመፍታት እያደረጉት ላለው ጥረት እውቅና ሰጥተዋል።

ፕሬዝዳንት ሎሬንሶ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ፣ ውይይቶች እንዲደረጉና የጋራ መተማመን እንዲፈጠር ቀጣይነት ባለው መልኩ እያደረጉት ያለውን ውይይትና ቁርጠኝነት አድንቀዋል።

በአፍሪካ ህብረት የሰላም እና የእርቅ ጥረቶች ግንባር ቀደም ሚና በመወጣት ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ እንዲመጣ ተምሳሌታዊ የአመራር ቁርጠኝነት አሳይቷል ሲሉ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል።

ዩሱፍ የሉዋንዳ የሰላም ሂደቱ ለውይይት ምቹ ሁኔታ የፈጠረ እና ለቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተሳትፎ በር የከፈተ መልካም አጋጣሚ እንደሆነም ተናግረዋል።

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን የሚያስችል መድረክ ፈጥሯል።

የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ቲሺሴኬዲ እና የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ግጭቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ያሳዩትን ቁርጠኝነትም አድንቀዋል።

አፍሪካ የሚያገጥሟት ችግሮች በአፍሪካ መር የመፍትሄ አማራጮች መፈታት አለባቸው ያሉት ሊቀ መንበሩ በዚህ ረገድም የአፍሪካ ህብረት በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምስራቃዊ ክፍል ዘላቂ ሰላም እና መረጋጋት የሚያመጡ ጥረቶችን እንደሚደግፍ ገልጸዋል።

የአፍሪካ ህብረት ሰላም እና ፀጥታን ጨምሮ አፍሪካ እያጋጠሟት ያሉ ፈተናዎች በአፍሪካውያን መሪነት እና ባለቤትነት እንዲፈቱ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንደሚወጣ መግለጻቸውን የኢዜአ ዘገባ ያመለክታል።

መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓም
👍12🥰1