Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"የጣና ዳር ንግሥቷ፣ ባለዘንባባዋ ሙሽራ፣ የቱሪዝም አስኳሏ ባህር ዳር ስራ ላይ ነች"
- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሰገን ጥሩነህ
***

ፍፁም የሰላም አየር፣ የዓይንና የመንፈስ ማረፊያ ውብ ሥፍራ የታደለችው ባህር ዳር ከመዝናኛ እስከ ግዙፍ የንግድ ስፍራዎቿ በእንቅስቃሴ ተሞልተዋል፤ ሀገሬው ከጧት እስከ ማታ ሥራ ላይ ነው፡፡

የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራዎች ከልጅ እስከ አዋቂ በልዩ ልዩ ስፖርቶች ደምቀዋል፤ ከዚሁ ጎን ለጎን ግዙፉ የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ከተማዋን የስፖርት ቱሪዝም ማዕከል የሚያደርጋት ይሆናል።

ሀገሬው በሥራ የደከመ አካሉንና አዕምሮውን ለማደስ ስፖርት ሲሠራ፣ በመዝናኛ ማዕከላት ሲዝናና፣ በዘንባባዋ ጥላ ስር አረፍ ሲል፣ በጣና ዳርቻ ሰብሰብ ብሎ ሲጫወት፣ በምሽት በእግር ሲንቀሳቀስ ማየት ልብን ሀሴት ያወርሳል።

ወቅቱ የዐቢይና የረመዳን አፅዋማት የሚፆሙበት ነው። የከተማዋ ምዕመን ሰርክ ወደ መስጂድና ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሲተምም ማየት መንፈሳዊ ኩራትን ይፈጥራል።

ውቧ ከተማ ልማቷን እያፋጠነች፣ ፍፁም የሰላም ድባብ፣ እረፍት አልባ የልማት ሥራ፣ ሞቅ ያለ የመዝናኛና የንግድ እንቅስቃሴ የሚታይባት ሆናለች።

ባየነው የሠላም ንፋስ የልማትና የሥራ ጥድፊያ እንዲሁም የቱሪዝም መነቃቃት ተደሰተናል። የተጀመሩ ስራዎችን ዓይናችንን ሳንነቅል በተገቢው ጥራት እንዲጠናቀቁ ክትትላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡

መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓም
👍7👏1
የባሕር በር ጥያቄ የመጪውን ትውልድ ሕልውና የሚወስን ነው
****
(ኢ ፕ ድ)
የባሕር በር ጉዳይ የመጪውን ትውልድ የመኖር እና ያለመኖር ሁኔታ የሚወስን ስለሆነ ከወዲሁ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባል ሲሉ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ሃሳቡ ተስፋ ገለጹ፡፡

መምህር ሃሳቡ ተስፋ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በሚያስተዳድራት በራሷ መንግሥት ድጋፍ አድራጊነት የነበራትን የባሕር በር እንድታጣ መደረጓ ሁሌም የሚያስቆጭ ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡ የባሕር በር ከሉዓላዊ ግዛትነቱም በላይ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ጥቅሙ የሕልውና ጉዳይ ያደርገዋል፡፡

አንድ ሀገር የባሕር በር አለው ማለት ሌሎች የባሕር በር ካላቸው የዓለም ሀገራት ጋር ይዋሰናል ማለት ነው ያሉት መምህሩ፤ ይህ ደግሞ ያለማንም ጣልቃ ገብነት የንግድ ልውውጥ እና ማኅበራዊ ትስስር ለመፍጠር ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

እንደ መምህር ሃሳቡ ገለጻ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፤ በዚያው ልክ ፍላጎቱና የንግድ እንቅስቃሴውም አድጓል፤ ዓለም አቀፍ ግንኙነቱና ኢኮኖሚያዊ ትስስሩም ጨምሯል፡፡

እያደገ ከሚሄደው የሕዝብ ቁጥርና ፍላጎት አንጻር፤ የባሕር በር በተለይም የመጪውን ዘመን ትውልድ የመኖርና ያለመኖር ሁኔታ የሚወስን በመሆኑ ከወዲሁ መፍትሔ ሊበጅለት ይገባዋል።
👍13👏2😢2
የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትሃድ አየር መንገድ ስትራቴጂክ የቢዝነስ ስምምነት ተፈራረሙ

👉 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሀምሌ 8 ቀን 2017 ጀምሮ ከአዲስ አበባ አቡዳቢ በረራ ይጀምራል፣

👉 ኢታሃድ አየር መንገድ ከመስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከአቡዳቢ አዲስ አበባ ቀጥታ በራራ ይጀምራል፣

*
**
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኢትሃድ አየር መንገድ የአየር ትራንስፖርት ትስስርን ለማጠናከርና በትብብር ለመስራት የሚስችላቸውን ስትራቴጂክ የቢዝነስ ስምምነት ዛሬ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፤ በኢትሀድ ኤርዌይስ በኩል የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንቶላዶ ኔቬስ ፈርመዋል።

ስምምነቱ ለደንበኞች የተቀላጠፈ የበረራ አማራጭ ለማቅረብ በሁለቱ አየር መንገዶች መካከል “የኮድ ሼር” አገልግሎት፣ በአዲስ አበባና አቡዳቢ መካከል የበረራ አገልግሎት መጀመርን ያካተተ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሀምሌ 8 ቀን 2017 ጀምሮ ከአዲስ አበባ አቡዳቢ በረራ ይጀምራል። ኢታሃድ አየር መንገድ ከመስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ከአቡዳቢ አዲስ አበባ ቀጥታ የበራራ አገልግሎት ይጀምራል ተብሏል።

በስምምነት ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የቦርድ ሰብሳቢ ሌ/ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ የኢቲሃድ ኤርዌይስ ቦርድ ሰብሳቢ ሞሀመድ አሊን፣ የሁለቱ አየር መንገዶች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች መሳተፋቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።

#የኢትዮጵያአየርመንገድ
👍82👏1
የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት የተዳራደሪ ቡድን ስብሰባ በጄኔቫ መካሄድ ጀመረ
****
(ኢ ፕ ድ)

5ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር የስራ ቡድን አባላት ስብሰባ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ መካሄድ ጀምሯል።

የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ ቡድን መሪ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ኢትዮጵያ ለዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ዝግጁ መሆኗን በመድረኩ አስረድቻለሁ ብለዋል፡፡

አባል ሀገራት የሁለትዮሽ የንግድ ድርድራቸውን ከወዲሁ እንዲያጠናቅቁ በመድረኩ ጥሪ ማቅረባቸውን ገልጸው በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ከ19 ሀገራት በላይ የድጋፍ መልእክት በማስተላለፍ ኢትዮጵያን ማበረታታቸውን ገልፀዋል፡፡

መድረኩ በጥያቄና መልስ መርሐ-ግብር እስከምሽት እንደሚቀጥልም አመላክተዋል፡፡

መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓም
👍6👏1
ሀገር በቀል እውቀቶችን ከፋሽን ኢንዱስትሪው ጋር አስተሳስሮ የዜጎችን ተጠቃሚነትን ማላቅ ያሰፈልጋል
****
(ኢ ፕ ድ)

የማፊ ፋሽን ዲዛይን መሥራች ወ/ሮ ማህሌት አፈወርቅ ጋር በክህሎት ልማትና ሥራ ዕድል ፈጠራ መስኩ ላይ በቅንጅት መሥራት በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።

ሚኒስትሯ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እያደገ የመጣው የፋሽን ኢንዱስትሪ ያለውን እምቅ አቅም አሟጦ ለመጠቀም የግሉ ዘርፍ ሚና የማይተካ መሆኑን ገልጸዋል።

ሀገር በቀል እውቀቶችን ከፋሽን ኢንዱስትሪው ጋር አሰናስሎ የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማላቅ ሥነ-ምኅመዳሩን ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ ይሆናል ብለዋል።

የማፊ ፋሽን ዲዛይን መሥራች ወ/ሮ ማህሌት አፈወርቅ በመስኩ በትብብር በመሥራት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማላቅ ላሳዩት ቁርጠንነትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓም
👍112👏2
"በየአካባቢው የምንዋጋቸው ሰዎች የድንቁርና ጌቶች ናቸው፣ አትማሩ፣ አትታከሙ፣ አታልሙ፣ የሚሉ ናቸው።

በሀገሪቱ በየትኛውም ጎጥ ያለ የጎበዝ አለቃ ይደራደራል፣ ነገር ግን መደራደሩ ጥቅም እንደሌለው የሚዘምተውም ራሱ ነው"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍7👏1
ሁለተኛው የኢትዮጵያ ህዳሴ የአፍር ማዳበሪያ ፋብሪካን ማቋቋም ነው
*******
(ኢ ፕ ድ)

ሁለተኛው የኢትዮጵያ ህዳሴ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካን ማቋቋም ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ ማዳበሪያን ማምረት አለመቻሏ በርካታ አርሶ አደርን የሚነካ ጉዳይ በመሆኑ በዘላቅነት ለመፍታት ጥናት ሲደረግ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡

በተደረገው ጥናት ከ2 ነጥብ 5 እስከ 3 ቢሊየን ዶላር ያስፈልጋል፤ የማዳበሪያ ፋብሪካውን አቋቁሞ ለመስራት በትንሹ ሶስት ዓመትና ከዚያ በላይ እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቁመዋል፡፡

ይህንን ከተቻለ ከግሉ ዘርፍ ጋር፣ በግለሰብ ኢንቨስትመንት ካልተቻለም መንግስት በራሱ የሚገነባ ይሆናል ብለዋል።

የአፍር ማዳበሪያ የኢትዮጵያን ፍላጎት በሚመልስ መልኩ መመረት እንዳለበት ጠቅሰወ፣ ፋብሪካው የማቋቋም ሂደቱ ምናልባትም በሚቀጥለው ዓመት ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እንደሚጀመሩ አመላክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ 24 ሚሊየን ኩንታል ገደማ የአፍር ማዳበሪያ የሚያስፈልጋት ሲሆን፤ በቀን 150 ሺህ ኩንታል የአፍር ማዳበሪያ ከወደብ ወደ ሀገር ውስጥ ታጓጉዛለች፤ ይህንን ወደ እያንዳንዱ አርሶ አደር በወታደር ታጅቦ ይሰራጫል።

በአማራ ክልል ለሚገኙ አርሶአደሮች 7ሺህ የጭነት ትራንስፖርት የአፍር ማዳበሪያ በመከላከያ ሰራዊት ታጅቦ መዳረሱን አስታውሰው፤ መንግስት በብዙ ሂደት አልፎ ማዳበሪያውን ወደሀገር ውስጥ ካመጣ በኋላ ለአርሶ አደሩ ማዳረሱም ሌላ ወጭ እየሆነበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በቃልኪዳን አሳዬ

መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓም
👍94👏1🙏1
"የፕሪቶሪያውን ስምምነት በሚያከብር መልኩ የትግራይ ህዝብ ምርጫ መምረጥ ይኖርበታል"

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
****
(ኢ ፕ ድ)

የፕሪቶሪያውን ስምምነት በሚያከብር መልኩ ለውጦች ተደርገው የትግራይ ህዝብ ምርጫ መምረጥ ይኖርበታል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ ምንም አይነት ግጭት እንዳይኖር ችግሮች በንግግር እንዲፈቱ የበኩሉን ጥረት አድርጓል፡፡

አሁን ላይ የተሰጠው የሁለት ዓመት ጊዜ እየተጠናቀቀ ስለሆነ የህግ ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች አሉ ብለዋል፡፡

በመሆኑን የነበረው አፈጻጸም ተገምግሞ የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚያከብር መልኩ መጠነኛ ለውጥ ተደርጎ የክልሉ ህዝብ ምርጫ የሚያካሂድበት ሁኔታ መፈጠር ይኖርበታል፡፡

ይህን ለማድረግም ከጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች ጋር ውይይት ተደረጓል ብለዋል፡፡

የፕሪቶሪያው ስምምነት ታሪካዊና በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግራይ ህዝብ በውጊያው ጊዜ ምንም አገልግሎት አላገኘም፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ምንም አይነት ውጊያ አለመኖሩ ትልቅ ነገር ነው።

የተፈናቀሉ ዜጎችን በተለመከተ መንግስት በቂ ትብብር ከተደረገለት የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዳግማዊት አበበ

መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓም
👍102👏1
“እንደ ህዳሴ ግድብ ሁሉ የኢትዮጵያ ቀጣዩ ታላቅ ስራ የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ነው"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
👍27👏75
አዲስ ዘመን መጋቢት 12 ቀን 2017 ዓም
https://press.et/?p=147950
👏3👍2
በሰሜን ተራሮች የሚገኙ የዋልያዎች ቁጥር ወደ 300 መውረዱን የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ

👉 ብዝሃ ሕይወትና የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎችን ለመንከባከብ እስከ 300 ሚሊዮን ብር ያሰፈልጋል
*******
(ኢ ፕ ድ)

በሰሜን ተራሮች የብርቅዬ ዋልያዎች ቁጥር ከዚህ በፊት ከነበረው ተመናምኖ ወደ 300 ዝቅ ማለቱን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አሰታወቀ።
👍4😱21👏1
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
🥰1