ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቭዥን በብርቱካን ተመስገን ዙሪያ ላስተላለፈው ዶክመንተሪ ይቅርታ ጠየቀ
******
(ኢ ፕ ድ)
ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቭዥን በብርቱካን ተመስገን ዙሪያ ላስተላለፈው ዶክመንተሪ ይቅርታ ጠይቋል።
የኢቢኤስ ቴሌቭዥን ዋና ስራ አስፈጻሚ አማን ፍስሀጽዮን በሰጡት መግለጫ በድርጅቱ ውስጥ የተቀናጀ ሀይል ከጋዜጠኝነት መርህ ውጭ ጥፋት መፈጸሙን ገልጸዋል።
ይህንንም አዘጋጆቹ ያለምንም የመረጃ ማጣራት ያከናወኑት መሆኑን አመላክተዋል።
ድርጅቱ ባደረገው ማጣራት ከባለጉዳይዋ የተወሰዱ ማስረጃዎች በአዘጋጆቹ በቂ ማጣራት ያልተደረገባቸው መሆኑን ተገንዝበናል ብለዋል።
ዶክመንተሪው የድርጅቱ ጋዜጠኞች መጠየቅ የነበረባቸው ጉዳዮችን በአግባቡ ሳያከናውኑ የፈጸሙት መሆኑን አስረድተዋል።
ዝግጅቱም ከማህበራዊ ገጽ የወረደው በራሷ በብርቱካን ጥያቄ መሰረት መሆኑን ገልፀው ግለሰቧ የሰጠቻቸው መረጃዎችን ለማጣራት ባደረጉት ጥረትም መረጃ ዎቹ ሀሰት ሆነው መገኘታቸውን ተናግረዋል።
ኢቢኤስ ቴሌቭዥን በዶክመንተሪው ምክንያት ለፈጠረው ችግር መላ ኢትዮጵያውያንን ይቅርታ ይጠይቃል። ጣቢያው የተፈጠረውን ስህተት እንደሚያምንና በጉዳዩ በተሳተፉ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድም ገልፀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓም

👍24👎7🙉5💩3
የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ ሆነ
****
(ኢ ፕ ድ)
ከሰኔ 2017 ዓም ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ መቀመጡ ተገልጿል።
የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚከናወን ተገልጿል።
የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝና ከከፍተኛ ትምህርት መረጃ አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር ጥራት ያለው መረጃ ለማግኘትና የሚሰጡ ሀገር ሀቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እንደሚረዳ የተቋሙ መረጃ ያመለክታል።
#Ethiopia #ፋይዳ #መታወቂያ #ዲጂታልኢትዮጵያ
መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓም

👍3😢2❤1👏1
የኢትዮጵያ ሥልጣኔ፣ ታሪክ፣ እምነትና ብልፅግና ከቀይ ባሕር ጋር የተያያዘ ነው
****
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሥልጣኔ፣ ታሪክ፣ እምነትና ብልፅግና ከቀይ ባሕር ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ አደም ካሚል (ረ/ፕ) ገለጹ፡፡
የታሪክ ተመራማሪ አደም ካሚል (ረ/ፕ) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ፣ ታሪክ፣ እምነትና ብልፅግና ከቀይ ባሕር ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ቀይ ባሕር ከጥንት ጀምሮ የአበሻ ባሕር በመባል የሚታወቅ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የባሕር በር እንደነበራት ከጥንትም ጀምሮ የተረጋገጠና ዓለም የሚመሰክረው ጉዳይ መሆኑን የጠቆሙት አደም ካሚል(ረ/ፕ)፤ ያለን አማራጭ ይህን ታሪካዊ ንብረታችንን በሰላማዊ መንገድ ማግኘት ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ተዋሳኝነቷን በሰላማዊ መንገድ መልሳ ማግኘት እንዳለባትና ፤ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከባሕሩ ተጋሪ ሀገራት ጋር ተጠቃሚ መሆን የምንችልበትን ዕድል መፍጠር እንደሚገባት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ኢትዮጵያ የባሕር በሯን ያጣችው በወቅቱ በነበረው በራሷ መንግሥታዊ አስተዳደርና ተመሳሳይ ፍላጎት ባላቸው ሌሎች ሃይሎች እንደነበር አስታውሰው፤ በዚያ የተሳሳተ ውሳኔ ላይ የሕዝቦች ይሁንታና የቅኝ ገዢዎች ጫና አለመኖሩን አደም ካሚል (ረ/ፕ) አስታውሰዋል።

👍7👏2
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
❤1👍1
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️
ዛሬ በለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2ኛ ዙር ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 380 ሰልጣኞችን አስመርቀን ወደ ስራ አሰማርተናል።
ከአስከፊ ህይወት ወጥታችሁ ስልጠናችሁን በብቃት በማጠናቀቅ ለምርቃት የበቃችሁ እንዲሁም ወደ ስራ ለመሰማራት የተዘጋጃችሁ ልጆቻችን እና እህቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!
ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለማህበራዊ፣ ለኢኮኖሚያዊና ለስነ ልቦና ስብራት የተጋለጡ ሴቶችን ካሉበት የህይወት ውጣ ውረድ እንዲወጡ በማድረግ፣ የስነ ልቦና ድጋፍና የሙያ ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ በማሰማራት ላይ የሚገኝ ማዕከል ሲሆን በ2ኛው ዙርም በ17 የሞያ አይነቶች የብቃት ምዘና ያለፉ 380 ሰልጣኞችን አስመርቀን የስራ እድልም ተፈጥሮላቸዋል።
ለማዕከሉ ድጋፍ በማድረግና የስራ እድል በመፍጠር ላይ የምትገኙ ባለሀብቶች እንዲሁም ሰልጣኞቹ በማዕከሉ በነበራቸው ቆይታ እናትም አባትም ሆናችሁ ከስልጠና በላይ የሆነ እንክብካቤና ፍቅር በመስጠት ከልብ ያሰለጠናችሁ፣ የተንከባከባችሁና ወደ ስራ ያሰማራችሁ አመራሮች እና መምህራንን በሰልጣኞቹ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

👍8👏1
"በኢቢኤስ የተላለፈው ሀሰተኛ ዘጋቢ ፊልም ኢትዮጵያን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው"
- ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
*****
(ኢ ፕ ድ)
በኢቢኤስ ቴሌቭዥን የተላለፈው የብርቱካ ተመስገን ሀሰተኛ መረጃ ኢትዮጵያ የግጭትና የትርምስ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ተናገሩ።
የጋራ እሴትን የሚሸረሽር ነጠላ ትርክት በማህበራዊ ሚዲያ እየተስፋፉ በመሆኑ ሕዝቡ ሊጠነቀቅ ይገባልም ብለዋል።

❤9👍6👏2😭1
ምዕራፍ አንድ ጊንጭ - ሽኩቴ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ 72 በመቶ ተከናወነ
******
(ኢ ፕ ድ)
በጊንጪ-ካቺሴ-ጩሉጤ የመንገድ ፕሮጀክት ምዕራፍ አንድ ጊንጭ - ሽኩቴ 59 ኪሜ የአስፋልት ኮንክሪት ግንባታ 72 በመቶ ደርሷል፡፡ በፕሮጀክቱ 48 ኪሜ የአስፋልት ንጣፍ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡
ለፕሮጀክቱ የሚውለው 898 ሚሊዮን 273 ሺህ ብር በጀት በኢትዮጵያ መንግስት ይሸፈናል።
ግንባታውን ሀገር በቀሉ የሥራ ተቋራጭ ገምሹ በየነ ጠቅላላ የሥራ ተቋራጭና ፎርትረስ ኢንጂነሪንግ ኮንሰልታንትስና አሶሼትስ ሀ.የተ.የግ.ማህበር ማማከር ስራ እያከናወነው ይገኛል፡፡
የጊንጪ - ካቺሴ - ጩሉጤ መንገድ ወረዳዎችን፣ ከተሞችንና ቀበሌዎችን በቅርበት ከማገናኘት ባለፈ በአካባቢው የሚመረቱ የተለያዩ የግብርና ውጤቶችን ለገበያ ለማውጣት የሚያግዝ ይሆናል ፡፡

👍3👏2