Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ ሆነ
****
(ኢ ፕ ድ)
ከሰኔ 2017 ዓም ጀምሮ የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና ለመውሰድ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ቅደመ ሁኔታ መቀመጡ ተገልጿል።

የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በሁሉም የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚከናወን ተገልጿል።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የተማሪዎችን እና የሰራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝና ከከፍተኛ ትምህርት መረጃ አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር ጥራት ያለው መረጃ ለማግኘትና የሚሰጡ ሀገር ሀቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለመጠበቅ እንደሚረዳ የተቋሙ መረጃ ያመለክታል።

#Ethiopia #ፋይዳ #መታወቂያ #ዲጂታልኢትዮጵያ

መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓም
👍3😢21👏1
የኢትዮጵያ ሥልጣኔ፣ ታሪክ፣ እምነትና ብልፅግና ከቀይ ባሕር ጋር የተያያዘ ነው
****
(ኢ ፕ ድ)

የኢትዮጵያ ሥልጣኔ፣ ታሪክ፣ እምነትና ብልፅግና ከቀይ ባሕር ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ አደም ካሚል (ረ/ፕ) ገለጹ፡፡

የታሪክ ተመራማሪ አደም ካሚል (ረ/ፕ) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ፣ ታሪክ፣ እምነትና ብልፅግና ከቀይ ባሕር ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ ቀይ ባሕር ከጥንት ጀምሮ የአበሻ ባሕር በመባል የሚታወቅ ነው፡፡

ኢትዮጵያ የባሕር በር እንደነበራት ከጥንትም ጀምሮ የተረጋገጠና ዓለም የሚመሰክረው ጉዳይ መሆኑን የጠቆሙት አደም ካሚል(ረ/ፕ)፤ ያለን አማራጭ ይህን ታሪካዊ ንብረታችንን በሰላማዊ መንገድ ማግኘት ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የቀይ ባሕር ተዋሳኝነቷን በሰላማዊ መንገድ መልሳ ማግኘት እንዳለባትና ፤ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከባሕሩ ተጋሪ ሀገራት ጋር ተጠቃሚ መሆን የምንችልበትን ዕድል መፍጠር እንደሚገባት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የባሕር በሯን ያጣችው በወቅቱ በነበረው በራሷ መንግሥታዊ አስተዳደርና ተመሳሳይ ፍላጎት ባላቸው ሌሎች ሃይሎች እንደነበር አስታውሰው፤ በዚያ የተሳሳተ ውሳኔ ላይ የሕዝቦች ይሁንታና የቅኝ ገዢዎች ጫና አለመኖሩን አደም ካሚል (ረ/ፕ) አስታውሰዋል።
👍7👏2
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
1👍1
የከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት‼️

ዛሬ በለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2ኛ ዙር ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ 380 ሰልጣኞችን አስመርቀን ወደ ስራ አሰማርተናል።

ከአስከፊ ህይወት ወጥታችሁ ስልጠናችሁን በብቃት በማጠናቀቅ ለምርቃት የበቃችሁ እንዲሁም ወደ ስራ ለመሰማራት የተዘጋጃችሁ ልጆቻችን እና እህቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!

ለነገዋ የሴቶች የተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ለማህበራዊ፣ ለኢኮኖሚያዊና ለስነ ልቦና ስብራት የተጋለጡ ሴቶችን ካሉበት የህይወት ውጣ ውረድ እንዲወጡ በማድረግ፣ የስነ ልቦና ድጋፍና የሙያ ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ በማሰማራት ላይ የሚገኝ ማዕከል ሲሆን በ2ኛው ዙርም በ17 የሞያ አይነቶች የብቃት ምዘና ያለፉ 380 ሰልጣኞችን አስመርቀን የስራ እድልም ተፈጥሮላቸዋል።

ለማዕከሉ ድጋፍ በማድረግና የስራ እድል በመፍጠር ላይ የምትገኙ ባለሀብቶች እንዲሁም ሰልጣኞቹ በማዕከሉ በነበራቸው ቆይታ እናትም አባትም ሆናችሁ ከስልጠና በላይ የሆነ እንክብካቤና ፍቅር በመስጠት ከልብ ያሰለጠናችሁ፣ የተንከባከባችሁና ወደ ስራ ያሰማራችሁ አመራሮች እና መምህራንን በሰልጣኞቹ እና በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓም
👍8👏1
"በኢቢኤስ የተላለፈው ሀሰተኛ ዘጋቢ ፊልም ኢትዮጵያን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው"
-  ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር
*****
(ኢ ፕ ድ)

በኢቢኤስ ቴሌቭዥን የተላለፈው የብርቱካ ተመስገን ሀሰተኛ መረጃ ኢትዮጵያ የግጭትና የትርምስ ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ተናገሩ።

የጋራ እሴትን የሚሸረሽር ነጠላ ትርክት በማህበራዊ ሚዲያ እየተስፋፉ በመሆኑ ሕዝቡ ሊጠነቀቅ ይገባልም ብለዋል።
9👍6👏2😭1
ምዕራፍ አንድ ጊንጭ - ሽኩቴ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ  ግንባታ 72 በመቶ ተከናወነ
******
(ኢ ፕ ድ)

በጊንጪ-ካቺሴ-ጩሉጤ የመንገድ ፕሮጀክት ምዕራፍ አንድ ጊንጭ - ሽኩቴ 59 ኪሜ የአስፋልት ኮንክሪት ግንባታ 72 በመቶ  ደርሷል፡፡ በፕሮጀክቱ 48 ኪሜ የአስፋልት ንጣፍ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ለፕሮጀክቱ  የሚውለው  898 ሚሊዮን  273 ሺህ  ብር በጀት በኢትዮጵያ  መንግስት ይሸፈናል።

ግንባታውን ሀገር  በቀሉ የሥራ ተቋራጭ  ገምሹ  በየነ  ጠቅላላ  የሥራ  ተቋራጭና ፎርትረስ ኢንጂነሪንግ ኮንሰልታንትስና አሶሼትስ ሀ.የተ.የግ.ማህበር ማማከር ስራ እያከናወነው  ይገኛል፡፡

የጊንጪ - ካቺሴ - ጩሉጤ  መንገድ  ወረዳዎችን፣ ከተሞችንና ቀበሌዎችን በቅርበት ከማገናኘት ባለፈ በአካባቢው  የሚመረቱ  የተለያዩ  የግብርና  ውጤቶችን ለገበያ ለማውጣት የሚያግዝ ይሆናል ፡፡

መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓም
👍3👏2
ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ አሳሳች መረጃዎች መጠንቀቅ እንዳለበት ተገለፀ
*******
(ኢ ፕ ድ)

በኢቢኤስ ቴሌቭዥን ወጣት ብርቱካን ተመስገንን አስመልከቶ የተላለፈው ሀሰተኛ መረጃ በተመለከተ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዛዲግ አብርሃ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት ማብራሪያ ሕብረተሰቡ በሚዲያዎች የሚሰራጩ መረጃዎች ትክክለኛነት ማረጋገጥ ይኖርበታል።

ሀገር የሚያፈርሱና ህዝብና ህዝብን የሚያጋጩ መረጃው እየፈበረኩ የሚያሰራጩበት ጊዜ በመሆኑ ሕብረተሰብ የሚጠቀማቸውን መረጃዎች ማጣራት ይኖርበታል ብለዋል።

ሚዲያ የራሱ ጥቅምና ጉዳት አለው ያሉት አቶ ዛዲግ፣ ከሰሞኑ በኢቢኤስ ቴሌቭዥን የተላለፈው ሀሰተኛ መረጃ መነሻው ማህበራዊ ሚዲያ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በኢትዮጵያ ጉዳይ በርካታ ፍላጎት ያላቸው አካል እየመሩት በመሆን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ ጠቅሰዋል።

ሴቶችን አጀንዳ በማድረግ የፖለቲካ ፍላጎትን ለማሳካት የተሰራጨ መረጃ ነው ያሉት አቶ ዛዲግ አብርሃ፣ መንግስት ለሴቶች ብዙ ዕድል በሰጠበት በዚህ ጊዜ ለፖለቲካ ፉክክር መዋል ያልነበረበት ድርጊት መሆኑን ተናግረዋል።

ሐሰተኛ መረጃን በመከላከል ረገድ ጋዜጠኞችና ምሁራን ትልቅ ሚና እንዳለባቸው ጠቅሰዋል።

በሞገስ ፀጋዬ

መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓም
👍6👏21😁1