1446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ ይከበራል
***
(ኢ ፕ ድ)
የሸዋል ወር ጨረቃ በመታየቷ 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል ነገ እሁድ መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓም ይከበራል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ 1446ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸውም፤ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር አስተምኅሮቱን በመተግበር ሊሆን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓም

❤2👍2👏1
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለዒድ አል ፈጥር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
እንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ
ከረመዳን ወር ጾም በኋላ የሚመጣው ዒድ አል ፈጥር፣ የአንድነትና የበጎነት በዓል ነው። በረመዷን ጊዜ ጾሙም፣ ሶላቱም ሆነ ኢፍጣሩ በአንድነት የሚደረግ ነው። ይሄም አብሮነትን ያጠናክራል።
በሌላ በኩል በጾሙና በበዓሉ ጊዜ ድኾችን ረስቶ፣ ዐቅመ ደካሞችን ትቶ ማፍጠር አይፈቀድም። በጎ ማድረግ ዋናው የረመዳንም ሆነ የዒድ ዕሴት ነው።
የዒድ አል ፈጥር ዕሴቶች ለሀገር ግንባታ አስፈላጊ ዕሴቶች ናቸው። ሀገር ያለ አብሮነትና ያለበጎነት ልትገነባ አትችልም፤ ኅብረ ብሔራዊነትን ጌጥና ውበት የሚያደርገው አብሮነት ነው። ብዝኃነትን ዕድልና ጸጋ የሚያደርገው አብሮነት ነው።
አብሮነት ዘላቂ የሚሆነው ደግሞ በበጎነት ዕሴት ላይ ከተገነባ ነው። በጎነት የራስን ለሌላው መተዉ ነው፤ የሌላውን ሕመም መካፈል ነው፤ ለሌላው በደል ዕውቅና መስጠት ነው። በእነዚህ ጠቃሚ ዕሴቶች ሀገርን እየገነባን በዓሉን እንደምናከብር ተስፋ አደርጋለሁ።
መልካም የዒድ አል ፈጥር በዓል ይሁንልን።
መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓ.ም

👏2👍1
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለ1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
“ዒድ አል ፈጥር” የረመዳን ጾምን የማጠናቀቂያ በዓል ነው፡፡ ዒድ አል ፈጥር “የምስጋና፣ የበጎ አድራጎት እና የወንድማማችነት/እኅትማማችነት” በዓል ነው፡፡ ዒድ አል ፈጥር ከአንድ ወር የጾም ጊዜ በኋላ የሚመጣ በዓል ነው፡፡ ጾሙ የሰውን ድካም፣ ዐቅም ማነስ እና ልክ የሚያሳይ ነው፡፡ ፈጣሪ ካልደገፈው በቀር የሰው ልጅ ዐቅም ውሱን መሆኑን ያሳያል፡፡ ትዕቢት፣ ጥጋብ እና ክፋት በዚህ ደካማ ሰው ላይ መብቀላቸውን ለተመለከተ፣ የሰው ጠላቱ የገዛ ጠባዩ መሆኑን ይማራል፡፡ ሰው በዘመናት ውስጥ ሌሎችን ለመግዛት የታገለውን ያህል ራሱን ለመግዛት አልታገለም፡፡ ዛሬም በሀገራችን የምናየው ፈተና በዋናነት ራስን ካለመግዛት የሚመጣ ፈተና ነው፡፡ ራሱን የማይገዛ ሰው ዐቅሙን አያውቀውም፡፡ ወደ ውስጡ አያይም፡፡ ጠላቱን ከገዛ ጠባዩ ውስጥ ከመፈለግ ይልቅ፣ ጠላቱን ከጎረቤቱ ይፈልገዋል፡፡ በዚህ የተነሣ ከገዛ ወገኑ ጋር ሲቃረን ይኖራል፡፡ እንደ ረመዳን ዓይነት ወቅቶች ውስጥን ለመመልከት የሚጠቅሙ ናቸው፡፡
ውስጣቸውን የተመለከቱ ሰዎች ምስጋና ገንዘባቸው ነው፡፡ ሰው የራሱን ልክ ካላወቀ ሌላውን አያደንቅም፤ ሌላውን አያመሰግንም፡፡ የሌለውን ካልተረዳ ያለውን አያውቅም፤ አያደንቅም፡፡ የራሱ ጠላት የገዛ ጠባዩ መሆኑ ካልገባው፣ ሌላውን ወገኑን አያፈቅርም፡፡ ለዚህ ነው የጾሙ መጨረሻ፣ ዒድ አል ፈጥር የምስጋና በዓል የሆነው፡፡ ጾሙ ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ ማኅበረሰብ ድረስ ራስን ገዝቶ ለመሰባሰብ ይጠቅማል፡፡ መሰባሰቡም ከስሜት የወጣ፣ ስክነትና ራስን መግዛት ያለበት ነው፡፡ ሀገራዊ ምክክራችን ይሄን ዕሴት ቢላበስ እንጠቀማለን፡፡ መነጋገሩ ብቻ አይጠቅምም፡፡ ከስሜት ወርዶ፤ በስክነት ተሞርዶ፤ ነገን ተመልክቶ - መመካከር፡፡ ያ ከሆነ እንደ ዒድ ሁሉ፣ የምክክራችን ፍጻሜው ምስጋና ይሆናል፡፡
የዒድ ሌላው ዕሴት በጎ አድራጎት ነው፡፡ ዐቅም ለሌላቸው፤ ሁኔታው ላልተሟላላቸው ወገኖች መልካምን ነገር ማድረግ፡፡ ዝምድናን፣ ዘርን ወይም እምነትን ሳይመለከቱ ሰውን በሰውነቱ ብቻ መርዳት፡፡ የጾም ምንዳዕ ሙሉ የሚሆነው በጎ አድራጎት ከተጨመረበት ነው፡፡ በጎ አድራጎት ማለት ከራስ አጉድሎ ሌላውን መሙላት ነው፡፡ እንደ ሀገር ለመቀጠልና እንደ ሕዝብ ለመተሣሠር በጎ አድራጎት እጅግ አስፈላጊ ዕሴት ነው፡፡ ራስን በሌላው ጫማ ላይ አስገብቶ ማየት፡፡ የሌላው ጉድለት ለመሙላት ሲባል የራስን ማጣት፡፡ ለምን ወገኔ ያዝናል? ለምን ወገኔ ይከፋል? ብሎ መንገብገብ፡፡
ሁላችንም የየራሳችንን ወገን ጥቅምና መብት በማስከበር ብቻ ሀገር ልንገነባ አንችልም፡፡ ትሥሥራችን ወገን ዘለል ሆኖ፣ የሌላውን ወገን ጉዳትና ፈተና መጋራት ይገባናል እንጂ፡፡ የእኔ ቤት ሲሟላ አይደለም የእርሱ ቤት የሚሟላው፡፡ የእርሱ ቤት ሲሟላ ነው የእኔ ቤት የሚሟላው፡፡ የፖለቲካ ምኅዳራችን በዚህ ነባር ዕሴታችን ላይ ካልተመሠረተ ፍትሐዊነትን እና እኩልነትን ለማስፈን እንቸገራለን፡፡
እነዚህን ሁለቱን ዕሴቶች የሚያስተሣሥረው የዒድ ዕሴት “ወንድማማችነት/እኅትማማችነት” ነው፡፡ ወንድማማችነት/ እኅትማማችነት ማለት በጋራ ዕሴቶች፣ በመተባበር እና በጋራ ግብ ላይ የተመሠረተ ወዳጅነት ነው፡፡ ይሄ ወዳጅነት በሥነ ምግባር የተገራ፣ ፍቅርንና አንዱ ለሌላው መቆምን መሠረት ያደርጋል፡፡ የጋራ ኃላፊነትን ይወስዳል፡፡ በሀገራችን የፖለቲካ ሕይወት እጅግ አስፈላጊው/ግን እጅግ የተረሳው ዕሴት ነው፡፡ መብትንም ሆነ ግዴታን በወንድማማችነት/እኅትማማችነት መነጽር መመልከት ነገሩን ለሰውነት ቅርብ ያደርገዋል፡፡ ለእኔ ከሚለው አውጥቶ ለእኛ፤ ለእኛ ከሚለውም ጭምር አውጥቶ “ለእነርሱ እና ለእኛ”፤ ለእነርሱ እና ለእኛ ከሚለውም አውጦቶ “ለእኛ ይቅርብን፤ ለእነርሱ ይደረግ “ወደሚለው የላቀ ሰብእና ያደርሰዋል፡፡
በእምነቶች፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በማኅበረሰቦች እና በልሂቃን መካከል የተሻለውን አብሮነት የሚፈጠረው ወንድማማችነት/እኅትማማችነት ነው፡፡ የተሻለ መረዳዳት፣ የተሻለ መተዋወቅ እና የተሻለ መግባባት ይፈጥራል፡፡ ለሌላው ሲል መተዉን፤ ለሌላው ሲል መቀበልን እና ለሌላው ሲል ለበደሎች ዕውቅና መስጠትን የሚያስገኘው ዕሴት - ወንድማማችነት/እኅትማማችነት ነው፡፡ የዒድ በዓል አንዱ ዕሴት የሆነውም በዚህ የተነሣ ነው፡፡ የዒድን በዓል እነዚህን የበዓሉ ዕሴቶች እያሰብን፣ እያዳበርንና ለሀገር ግንባታ እየተጠቀም እንድናከበረው ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ ቤተሰቦች፣ ጎረቤታሞች፣ ማኅበረሰቦች እና የእምነት አባቶች ሲሰባሰቡ እነዚህ ሦስት የዒድ ዕሴቶች ጎልተው እንዲወጡና ማኅበረሰባችን እንዲገነባባቸው እንዲያደርጉ አደራ እላለሁ፡፡
ኢድ ሙባረክ!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መጋቢት 20፣ 2017 ዓ.ም

👍8❤3👏1
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
****
(ኢ ፕ ድ)
መላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛ የኢድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ኢድ ሙባረክ!!
የኢድ አል-ፈጥር በዓል የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነትና በረመዳን የጾም ወር የነበረ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና የአንድነት የሚጠናከርበት በአል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።
በድጋሚ ኢድ ሙባረክ፤ ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!!

❤3👏2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለ1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ባስተላለፉት መልዕክት ካነሷቸው ሀሳቦች‼️
✍️ ዒድ አል ፈጥር “የምስጋና፣ የበጎ አድራጎትና የወንድማማችነትና እኅትማማችነት” በዓል ነው፣
✍️ የሰውን ድካም ፈጣሪ ካልደገፈው በቀር የሰው ልጅ ዐቅም ውሱን መሆኑን ያሳያል፣
✍️ ትዕቢት፣ ጥጋብና ክፋት በዚህ ደካማ ሰው ላይ መብቀላቸውን ያየ ሰው ጠላቱ የገዛ ጠባዩ መሆኑን ይማራል፣
✍️ ሰው በዘመናት ውስጥ ሌሎችን ለመግዛት የታገለውን ያህል ራሱን ለመግዛት አልታገለም፣
✍️ ዛሬም በሀገራችን የምናየው ፈተና በዋናነት ራስን ካለመግዛት የሚመጣ ፈተና ነው፣
✍️ ራሱን የማይገዛ ሰው ዐቅሙን አያውቀውም፣ ጠላቱን ከገዛ ጠባዩ ከመፈለግ ይልቅ፣ ጠላቱን ከጎረቤቱ ይፈልገዋል፣
✍️ ሰው የራሱን ልክ ካላወቀ ሌላውን አያደንቅም፤ ሌላውን አያመሰግንም፤ የሌለውን ካልተረዳ ያለውን አያውቅም፣
✍️ ዐቅም ለሌላቸው፤ ሁኔታው ላልተሟላላቸው ዝምድናን፣ ዘርን ወይም እምነትን ሳይመለከቱ ሰውን በሰውነቱ ብቻ መርዳት፤ የጾም ምንዳዕ ሙሉ የሚሆነው በጎ አድራጎት ከተጨመረበት ነው፣
✍️ እንደ ሀገር ለመቀጠልና እንደ ሕዝብ ለመተሣሠር በጎ አድራጎት እጅግ አስፈላጊ ዕሴት ነው፣
✍️ ሁላችንም የየራሳችንን ወገን ጥቅምና መብት በማስከበር ብቻ ሀገር ልንገነባ አንችልም፡፡
✍️ የፖለቲካ ምኅዳራችን በዚህ ነባር ዕሴታችን ላይ ካልተመሠረተ ፍትሐዊነትንና እኩልነትን ለማስፈን እንቸገራለን፣
✍️ ሁለቱን ዕሴቶች የሚያስተሣሥረው የዒድ ዕሴት “ወንድማማችነትና እኅትማማችነት” ነው፡፡
✍️ ለእኔ ከሚለው አውጥቶ ለእኛ፤ ለእኛ ከሚለው አውጥቶ “ለእነርሱና ለእኛ”፤ ለእነርሱና ለእኛ ከሚለውም አውጦቶ “ለእኛ ይቅርብን፤ ለእነርሱ ይደረግ “ወደሚለው የላቀ ሰብእና ያደርሳል፣
✍️ በእምነቶች፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በማኅበረሰቦችና በልሂቃን መካከል የተሻለውን አብሮነት የሚፈጠረው ወንድማማችነትና እኅትማማችነት ነው፣
✍️ ለሌላው ሲል መተዉን፤ ለሌላው ሲል መቀበልንና ለሌላው ሲል ለበደሎች ዕውቅና መስጠትን የሚያስገኘው ዕሴት ወንድማማችነትና እኅትማማችነት ነው፤
✍️ እነዚህን የበዓሉ ዕሴቶች እያሰብን፣ እያዳበርንና ለሀገር ግንባታ እየተጠቀም እንድናከበረው ጥሪ አቀርባለሁ፣

👍11❤3👏2
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ለዒድ አልፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐመድ አሊ ዩሱፍ ለ1446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸው የረመዷን በአፍሪካና በተቀረው ዓለም ሰላምን፣ ፍትህንና አጋርነትን ይዞ እንደሚመጣ አምናለሁ። ለሁሉም ሙስሊሞች የደስታና የበረከት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል።

👍8❤2👏1
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
*******
(ኢ ፕ ድ)
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አል ፈጥር በዓልን ሲያከብር አብሮነትንና መደጋገፍን በሚያጠናክር መልኩ ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት።
የዒድ አል ፈጥር በዓል የመረዳዳት፣ የመተሳሰብና የአብሮነት በዓል መሆኑን ጠቁመው በቀጣዩም ጊዜ ይህንኑ መረዳዳትና አብሮነት በማጠናከር ሰላማችንን ዘላቂ የምናደርግበት ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በዓሉን ስናከብርም የመተሳሰብና የሰላም እሴቶቻንን ከሚያጎድፉ ተግባራት በመታቀብ የክልሉን ከፍታ እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን ሚና በመወጣት መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
መረዳዳትና መደጋገፍ ጎልቶ በሚታይበት በዚህ በዓል ያለው ለሌው በማካፈል በአብሮነት የሚያሳልፈውና ማህበራዊ ግንኙነትን የበለጠ የሚያጠናከርበት በመሆኑ፤ በዓሉን በመተዛዘንና አቅም የሌላቸውን በመረዳት ማሳለፍ አለብንም ብለዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ የዒድ አል ፈጥር በዓልን ሲያከብር ፍቅርን እና አንድነትን አጎልብቶ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የበኩሉን ሚና ለመወጣት እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል።
ህዝቡ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ ለዘመናት የገነባነውን የሰላም፣ የመቻቻል፣ የአብሮነት፣ የመከባበርና የመደጋገፍ እሴት በማጠናከር ሀገራዊ የለውጥ ጉዞውን እንዲያሳካ ጠይቀዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ በጾም ወራት ያሳየውን መተሳሰብ በበዓሉ ወቅትም ሆነ በሌሎቹ ጊዜያት መድገም እንዳለበት አሳስበዋል።

❤8👍7👏3
#ዒድአልፈጥር
በሐረር ከተማ 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል እየተከበረ ነው
1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል በሐረሪ ከተማ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
በዓሉ በኢድ ሶላትና በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ የሚገኘው። ምዕመናኑ በኢማም አህመድ እስታዲየም የኢድ ሰላታቸውን አድርሰው ፈጣሪያቸውን በማመስገን ወደ የመጡበት እየተመለሱ ይገኛሉ።