የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት
*******
(ኢ ፕ ድ)
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት ሕዝበ ሙስሊሙ የዒድ አል ፈጥር በዓልን ሲያከብር አብሮነትንና መደጋገፍን በሚያጠናክር መልኩ ሊሆን ይገባልም ነው ያሉት።
የዒድ አል ፈጥር በዓል የመረዳዳት፣ የመተሳሰብና የአብሮነት በዓል መሆኑን ጠቁመው በቀጣዩም ጊዜ ይህንኑ መረዳዳትና አብሮነት በማጠናከር ሰላማችንን ዘላቂ የምናደርግበት ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በዓሉን ስናከብርም የመተሳሰብና የሰላም እሴቶቻንን ከሚያጎድፉ ተግባራት በመታቀብ የክልሉን ከፍታ እውን ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የበኩላችንን ሚና በመወጣት መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።
መረዳዳትና መደጋገፍ ጎልቶ በሚታይበት በዚህ በዓል ያለው ለሌው በማካፈል በአብሮነት የሚያሳልፈውና ማህበራዊ ግንኙነትን የበለጠ የሚያጠናከርበት በመሆኑ፤ በዓሉን በመተዛዘንና አቅም የሌላቸውን በመረዳት ማሳለፍ አለብንም ብለዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ የዒድ አል ፈጥር በዓልን ሲያከብር ፍቅርን እና አንድነትን አጎልብቶ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የበኩሉን ሚና ለመወጣት እንዲዘጋጅ ጥሪ አቅርበዋል።
ህዝቡ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ ለዘመናት የገነባነውን የሰላም፣ የመቻቻል፣ የአብሮነት፣ የመከባበርና የመደጋገፍ እሴት በማጠናከር ሀገራዊ የለውጥ ጉዞውን እንዲያሳካ ጠይቀዋል።
ህዝበ ሙስሊሙ በጾም ወራት ያሳየውን መተሳሰብ በበዓሉ ወቅትም ሆነ በሌሎቹ ጊዜያት መድገም እንዳለበት አሳስበዋል።
መጋቢት 20 ቀን 2017 ዓም

❤8👍7👏3
#ዒድአልፈጥር
በሐረር ከተማ 1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል እየተከበረ ነው
1 ሺህ 446ኛው የዒድ አል-ፊጥር በዓል በሐረሪ ከተማ በታላቅ ድምቀት ተከብሯል።
በዓሉ በኢድ ሶላትና በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች እየተከበረ የሚገኘው። ምዕመናኑ በኢማም አህመድ እስታዲየም የኢድ ሰላታቸውን አድርሰው ፈጣሪያቸውን በማመስገን ወደ የመጡበት እየተመለሱ ይገኛሉ።

1446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በድምቀት ተከብሮ ተጠናቀቀ
በአዲስ አበባ 1446ኛው የዒድ አል-ፈጥር በዓል በድምቀት ተከብሮ ተጠናቅቋል።
በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል።
መጋቢት 21 ቀን 2017 ዓም

👍1
"በዓላቶቻችን ትናንትን ያኖሩን፤ ዛሬን ያስተሳሰሩንና ነገ ላይ የሚያደርሱን ዕሴቶች ናቸው"
– ኑረዲን ቃሲም (ዶ/ር)
*******
(ኢ ፕ ድ)
ዒድ አልፈጥርንና መሰል በዓላቶቻችን ትናንትን ያኖሩን፤ ዛሬን ያስተሳሰሩንና ነገ ላይ የሚያደርሱን ዕሴቶች መሆናቸውን ዓለም አቀፍ የቁርዓን ዳኛ ኑረዲን ቃሲም (ዶ/ር) አስታወቁ።
ኑረዲን (ዶ/ር) ለኢፕድ እንደተናሩት፤ ዒድ አልፈጥር በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ዘንድ ትልቅ የበረከትና የተቸገሩ ሳይቀሩ ተደስተው እንዲውሉ የሚደረግበት ልዩ ጊዜ ነው። በዚህም ሙስሊሙ ይህንን የእምነቱን አስተምሮ ተግባራዊ ሲያደርግ በዓሉን በተለያየ አግባብ እንዲመለከተውና ነገውን እንዲሠራ ያስችለዋል።
በመረዳዳት ውስጥ፤ በአብሮነት ውስጥ ያለውን ታላቅነት እንዲረዳው ያግዘዋል ብለዋል።
በዓላቶቻችን እምነታችንን በተግባር እንድንኖረው የሚያስችሉን ናቸውም የሚሉት ኑረዲን (ዶ/ር)፤ በዒድ ጊዜ የሚደረገው ሰዎችን የማገዝ ተግባር አንዱ እንደሆነ ጠቅሰዋል።
በዓሉ አንድም ሰው ወደ ልመና እንዳይወጣ በማገዝ አብሮነታችንን ማሳየት እንደሚገባ አመልክተው፤ ኢትዮጵያውያን ለበዓላት ልዩ ትርጉም የሚሰጡበት ዋነኛ ምክንያት በበዓላቶቻችን ውስጥ ትናንትን ማሰብ፤ ዛሬን መተሳሰርና ነገን አሻግሮ ማየት ስላለ መሆኑን ገልጸዋል።
በዓላቶቻችን ትናንትን በፍቅርና በደስታ አቆይተው ዛሬን አሳይተውናል። ዛሬን አስተሳስረው ደግሞ ነጋችን መልካም እንደሚሆን ይነግሩናል። ሁሌ ቅንና ለሰዎች የምንጨነቅም እንድንሆን መልካም ሥነምግባርን ያላብሱናል።

👏5👍3