አቶ አደም ፋራህ ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ አደም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ድልብ የሆኑ የማኅበራዊ እሴቶቻችንን በማጎልበት የማኅበራዊ ልማታችንን ማጠናከርና በሀገራችን ያሉ የቱሪዝም ፀጋዎችን በማልማት የብዝኃ ዘርፍ ኢኮኖሚ መገንባት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።
በዚህ የለውጥ ዓመታት ጉዞ ውስጥ በበርካታ የአገራችን አካባቢዎች የሚገኙ የሕዝባችንን መልካም እሴቶች የሚያጠናክሩ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለመገንባት የሚያስችሉ ባህሎቻችንና እሴቶቻችንን ለማጎልበት በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ ብለዋል።
ባለፉት ዓመታት በማይዳሰስ ቅርስነት በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበው የሸዋል ዒድ (ሹዋሊድ) ባህላዊ ክብረ በዓል አንዱ እንደሆነ ነው የገለጹት።
በመሆኑም ይህ በዓል በሐረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፉን ከማጎልበት አንፃር ጠቀሜታው የጎላ ነው። ሸዋሊድ ሐረር የምትታወቅበት የአብሮነትና የመቻቻል እሴትም ጎልቶ የሚታይበት የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች በጋራ የሚሳተፉበት ባህላዊ ክብረ በዓል ነው ብለዋል።
በቀጣይ እንደ ብልፅግና ፓርቲ ባህላዊ ቅርሶቻችንና ሌሎች ድልብ ማኅበራዊ ሀብቶቻችን ተጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉና ለሀገራችን ተገቢውን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲሰጡ ይበልጥ አበክረን መስራታችንን እንቀጥላለን ሲሉ አረጋግጠዋል።

👍4❤2
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
❤3👍1
"ኢትዮጵያ ወደ ሞንጎሊያና ቻይና የተቀቀለ ሥጋ መላክ መጀመሯ ትልቅ ስኬት ነው" – አምባሳደር ድሪባ ኩማ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ወደ ቻይና እና ሞንጎሊያ ጥራቱና ደኅንነቱ የተረጋገጠ የተቀቀለ ሥጋ መላክ መጀመሯን የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ አስታወቁ፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት ከሚሌ ኳራንታይን 400 ሺህ የቁም እንስሳት ወደ ውጭ ሀገር በመላክ ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ተናግረዋል።
አምባሳደር ድሪባ ለኢፕድ እንዳስታወቁት፤ ባለሥልጣኑ በጀት ዓመቱ የስድስት ወር ግምገማ ከያዛቸው እቅዶች 96 በመቶውን ማሳካት ችሏል። ከእነዚህ ሥራዎችም ኢትዮጵያ ጥራቱና ደኅንነቱ የተጠበቀ የተቀቀለ ሥጋ ወደ ቻይና መላክ መጀመሯ ይጠቀሳል። ወደ ቻይና ብቻ ሳይሆን ወደ ሞንጎሊያም መላክ ጀምራለች ብለዋል፡፡
ትልቁ ስኬት ነው ብለን የምንለው የሥጋ ምርታችን ወደ ቻይና እንዲገባ ማድረግ ተችሏል። ከዚሁ ከሥጋ ምርት ጋር በተያያዘ የቻይና ኤክስፐርቶች ያለውን ሁኔታ አይተው ማስተካከል የሚገባንን ምክረ ሃሳብ ሰጥተውናል ብለዋል፡፡
“ቻይና በምትፈልገው የሥጋ ንግድ ሥርዓት መሠረት በመቃኘታችን ቻይናውያን ተቀብለው ውል መፈራረም ችለናል፤ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ሥጋ ወደ ቻይና መግባት ጀምሯል”....https://press.et/?p=148915

👍10👏1😁1
ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ለሹዋሊድ ባህላዊ በዓል የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት አሰተላለፉ
****
(ኢ ፕ ድ)
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ለሹዋሊድ ባህላዊ በዓል የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት አሰተላፉ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ድህረገፃቸው ላይ ባሰፈሩት የእንኳን አደረሳቹ መልዕክት የሹዋሊድ በዓል የሀረሪ ህዝብ ባህላዊ በዓልን በ2016 ዓ.ም ሀገራችን ኢትዮዽያ በዩኔስኮ የአለም ቅርስነት አስመዝግባዋለች ብለዋል።
ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የሹዋሊድ በአል የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጎልበት እና ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለማጠናከር በሚያስችል መልኩ እየተከበረ እንደሚገኝም ገልፀዋል።
ሹዋሊድ የቱሪዝም ዘርፉን በማነቃቃት በኩልም ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው እና በበዩኔስኮ የአለም ቅርስነት የተመዘገበ አንዱ የለውጡ ፍሬአችን ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።
መጋቢት 27 ቀን 2017 ዓም

❤2
በሲዳማ ክልል የቱሪስት መስህቦችን ከጎበኙ ቱሪስቶች ሁለት ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኘ
******
(ኢ ፕ ድ)
በ2017 በበጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የቱሪስት መስህቦችን ከጎበኙ ቱሪስቶች ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር በላይ ወደ ኢኮኖሚው ፈሰስ መደረጉን የሲዳማ ክልል ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።
የሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አበበ ማሪሞ ለኢፕድ እንደገለጹት፤ በ2017 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ሁለት ሚሊዮን 400 ሺህ ቱሪስቶች በክልሉ የተለያዩ የቱሪስት መደረሻዎች ጎብኝተዋል።
ከጎበኙት ቱሪስቶች ሁለት ሚሊዮን 300 ሺህ የሚሆኑት የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ሲሆኑ፤ አንድ መቶ ሺህ ያህሉ የውጭ ቱሪስቶች መሆናቸውን ጠቁመው፤ ከዚህም ሁለት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ወደ ኢኮኖሚው ፈሰስ ተደርጓል ብለዋል።
አቶ አበበ እንደተናገሩት፤ እንደ ሀገር ሆነ፤ እንደ ሲዳማ ክልልም በደረሰኝ ገንዘብ የምንቀበልበት የቱሪስት መዳረሻ ስለሌለ፤ በዘርፉ ከሚገኘው አጠቃላይ ገቢ 99 በመቶ የሚሆነው ለንግድ ተቋማት ገቢ የሆነ ነው።
የቱሪዝም ዘርፍ ገቢ በሁለት መንገድ ገቢ ይደረጋል። አንደኛው የንግድ ተቋማት ማለትም ሆቴሎች፣ አስጎብኚ ድርጅቶች፤ ትራንስፖርት እና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚገኙት ገቢ መሆኑን ገልጸዋል።https://press.et/?p=148985

👍18😁2
የኦሮሚያ ክልል አንድ ሺህ 402 የግብርና ትራክተሮችን ለአርሶ አደሮች አስረከበ
****
(ኢ ፕ ድ)
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አንድ ሺህ 402 የግብርና ትራክተሮችን ከነመለዋወጫው ለአርሶ አደሮች፣ ለህብረት ስራ ማህበራት እና ዩኒየኖች በዛሬው እለት በሻሸመኔ ከተማ አስረክቧል።
ርክክቡ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የሰራ ኃላፊዎች በተገኙበት መከናወኑን ከፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኬኛ የግብርና መሳሪያዎች ማምረቻና ጠቅላላ ንግድ ሀላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት በሀገር ውስጥ የተገጣጠሙ ናቸው።
የክልሉ መንግስት ምርትና ምርታማነትን ለማሳድግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡ ትራክተሮቹ የክልሉ መንግስት የግብርና ሜካናይዜሽንን ለማስፋፋት ለያዘው ውጥን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል።
መጋቢት 29 ቀን 2017 ዓም

❤5👍2👏1
ሥራ ፈላጊ ነዎት❓
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
መልካም ዕድል‼️
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች‼️
ትዊተር https://twitter.com/PressEthio
ድረ ገጽ https://www.press.et
👍3❤2