በአፋር ክልል የተከሰተውን የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ አስመልክቶ በማዕድን ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የተሰጠ መግለጫ‼️
የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የተለያዩ የስነ ምድር የምርምር ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ የምርምር ተቋም ሲሆን የስነ-ምድር አደጋዎችንም የማጥናት ተልኮ እንዳለው ይታወቃል፡፡ ይሀንን ምርምር ለመከወንም ሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ ካሉ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡
በአሁን ወቅት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኤርታሌ አካባቢ ልዩ ቦታው ሃይሊ ጉብ በተባለ ስፍራ ሀዳር 14/2018 ዓ.ም ጠዋት አራት ሰዓት አካባቢ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታ(Volcanic Eruption) እንደተከሰተ ይታወቃል። ይህ የእሳተ ገሞራ ፈንዳታ ከመከሰቱ በፊት ከሃምሌ 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ለእሳተ ገሞራ ፍንዳታ መከሰት አመላካች ምልክቶችን በቅርበት የመከታተል፣ መረጃዎችን የማሰባሰብና መረጃዎችን የመስጠት ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡
አሁን ላይ የእሳተ ገሞራ ፍንዳታው ያለበትን ሁኔታ የሚመለከትና የሚያጠና የጥናት ቡድን ተቋቁሞ ወደ ቦታው በመላክ ጥናት እያደረገ የሚገኝ ሲሆን አሁን በቦታው ላይ ያለው ሁኔታ በአንጻራዊነት የተረጋጋ ስለሆነ ማሀበረሰቡ ተረጋግቶ ስራውን እንዲያከናውን እያሳሰብን በሃገር ውስጥና ከሃገር ዉጭ ካሉ ተቋማትና ተመራማሪዎች ጋር በጋራ እየተሰራ ያለው የምርምር ስራ ሲጠናቀቅ ተጨማሪ መግለጫ የምንሰጥ ይሆናል፡፡

❤1
"የሐረሪ የኮሪደር ልማት ለሌሎች ክልሎች ማሳያ ነው"
-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
+++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ| በሐረሪ ክልል በኮራደር ልማት የተገኘው ውጤት ለሌሎች ክልሎች ማሳያ የሚሆን ነው ሲሉ የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ።
ሐረሪ ክልል የራሱን የፈጠራ አቅም በመጠቀም የተሰራው ስራ ማራኪ በመሆኑ ለሌሎችም አስተማሪ የሚሆን ነው ብለዋል።
አዲስ አበባ ይብዛም ይነስም ብዙ አመራር፣ አጋዥና ብዙ አይን ያለው መሆኑንም ጠቅሰው፣ ክልሉ ባለው ውስን ሃብት ህዝብን አስተባብሮ ታሪካዊ ውጤት አምጥቷል።
ባነሰ ሀብት እንዲህ ያለ ታሪካዊ ስራ መስራት መቻላቸው ሁሉም ክልሎች ይችሉ እንደነበር ማሳያ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
በየትኛውም መመዘኛ ሐረሪ ክልል ከሌሎች ክልሎች ያነሰ ስፋትና ሃብት እንጂ የበለጠ እንደሌለው አብራርተዋል።
በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣ ፕላስ # ኮሪደርልማት

❤1👍1
“ህዳሴ ግድብ ከ1960ዎቹ የነፃነት ድል ወዲህ ለቀጠናው ሁለተኛው ድል ነው”
- ላውረንስ ፍሪማን (ዶ/ር)
+++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከ1960ዎቹ ከቅኝ ግዛት ነፃ የመውጣት ድል ወዲህ ሁለተኛው ድል ነው ሲሉ የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ተንታኝ ላውረንስ ፍሪማን (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ላውረንስ ፍሪማን (ዶ/ር) ከጋዜጣ ፕላስ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ የህዳሴ ግድብ ለቀጠናው ከ1960ዎቹ የነፃነት ድል ወዲህ ሁለተኛው ድል ነው፡፡
የኢትዮጵያ ታላቁ የህዳሴ ግድብ በአፍሪካ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትብብር ለማሳደግ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው ያሉት ላውረንስ (ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በመገንባት አስደናቂ ስኬት ተቀዳጅታለች ብለዋል፡፡
ግድቡን ሁለት ጊዜ የመጎብኘት ዕድል ማግኘታቸውን ገልጸው፤ ግድቡ የጋራ ትብብርን ከማሳደግ ውጪ ሌሎች ሀገራት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት አለመኖሩን አስረድተዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን በጋራ በመሆን ግድቡ እንዳይገደብ የሚደርስባቸውን ጫና መቋቋም ችለዋልም ነው ያሉት፡፡
አክለውም ''የግብጽ መሪዎች ከትብብር ይልቅ የዜሮ ድምር ፖለቲካ ያራምዳሉ'' ያሉ ሲሆን፤ በዚህም ዓባይን በጋራ አልምቶ ከመጠቀም ይልቅ ኢትዮጵያን በጠላትነት ይፈርጃሉ ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የህዳሴ ግድብ በቀጠናው የሚያደርሰው ጉዳት ባይኖርም፤ ግብጾች ''ኢትዮጵያ ጠንካራ ከሆነች ሀገራችን ደካማ ትሆናለች'' የሚል የተሳሳተ ግምት እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡
ግብጽ ሁሌም በጂኦ-ፖለቲካ የበላይ የመሆን አመለካከት አላት፤ ይሄም በጋራ ለማደግ ከባድ እንቅፋት ከመሆን ያለፈ ጥቅም አልባ መሆኑን አንስተዋል።
በልጅዓለም ፍቅሬ
+++++++++++++++++
#Gazetteplus #ጋዜጣ_ፕላስ #ህዳሴ_ግድብ #ኢትዮጵያ#

👏5❤3
“የማዕድን ልማት በእቅድና በእውቀት መመራት አለበት”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የማዕድን ልማት በእቅድና በእውቀት መመራት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚንስትሩ በመደመር መንግሥት ዕይታ የዘርፎች እመርታ በሚል መሪ ሀሳብ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልጠና ላይ፤ የማዕድን ልማት በእቅድና በእውቀት መመራት አለበት ብለዋል።
ክልሎችና የማዕድን ሚኒስቴር ማዕድን ለሚያወጡ አካላት ፍቃድ ሲሰጡ በከፍተኛ ጥንቃቄ አቅም ያላቸውን አልሚዎች በመለየት በጥናት መሰረተ መስጠት አለባቸው ብለዋል።
ማዕድን ትልቅ ሀብትና ብልፅግናን ለማስፈንጠር የሚያገለግል መሳሪያ ስለሆነ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የኢንዱስትሪ ልማት ኢምፖርትን መተካትና በኤክስፖርት መቃኘት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
የኢንዱስትሪ ልማቱን የግል ሴክተሩ እንዲሰራ የሚያስችል አውድ መፍጠርና መደገፍ ይገባል፤ ይህ ካልሆነ ኢንዱስትሪ ማንሰራራት አይችልም ካላንሰራራ ደግሞ ብልፅግናን ማምጣት አይቻልም ብለዋል።
በክብረአብ በላቸው
#ጋዜጣፕላስ #ኢትዮጵያ #ማዕድን #ኢንዱስትሪ

❤2
የባሕር በር ጥያቄ የመንግሥት ፖለቲካዊ ፍላጎት ተደርጎ መወሰድ የለበትም
++++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የባሕር በር ጥያቄ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ እንጂ የመንግሥት ፖለቲካዊ ፍላጎት ተደርጎ መወሰድ የለበትም ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ሙሉዓለም ሀይለማርያም ተናገሩ።
በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ሙሉዓለም ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለፁት፤ የባሕር በር ጥያቄ የብሔራዊ ጥቅም እንጂ የመንግሥት ፍላጎት ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም።
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር መሰረታዊ ከምትላቸው የብሔራዊ ጥቅም አጀንዳዎች መካከል አንዱ የሆነውን የባሕር በር መልሶ የማግኘት ጉዳይ ከዘላቂ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ጋር ብቻ ተያይዞ መታየት ያለበት እንደሆነ ገልፀዋል።
እያደገ የመጣውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና የህዝብ ቁጥር ሊሸከም የሚችል መሰረተ ልማት ካልተገነባ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ አፍኖ ማቆየት የሚቻልበት ሁኔታ የለም፤ ከዚህ አኳያ ሀገሪቱ የምታስተዳድረው የባሕር በር ከምንጊዜውም በላይ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።
ከጂኦፖለቲካ አንፃር በቀጣናው የሀገሪቱን ተደማጭነት ለማሳደግ፤ የተሳለጠና ደህንነቱ የተረጋገጠ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖር፤ በከፍተኛ ፍጥነት ቁጥሩ እየጨመረ ላለው ህዝብ ዘላቂ ጥቅም ለማስከበር የባሕር በር ጨዋታ ቀያሪ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።
የባሕር በር ጥያቄ ማንሳት እንደ ነውር መታየቱ ቀርቶ የዜጎች አጀንዳ ወደ መሆን መጥቷል ያሉት አቶ ሙሉዓለም፤ ይህንን ተከትሎ ጥያቄው ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱን ተናግረዋል።
ይህ ፍትሐዊ የባሕር በር ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኝ የተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት መቀጠል እንዳለበት እና በተለይም የቀጣናው ሀገራት እርስበርስ ከለመተማመን አባዜ ወጥተው በሰጥቶ መቀበል መርህ እንዲሰሩ ጠንካራ ሥራ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በክብረአብ በላቸው
#ጋዜጣፕላስ #ኢትዮጵያ #የባሕርበር #ብሔራዊጥቅም

❤14👍1
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈ
++++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታ የኬንያ አቻውን 3 ለ 0 በማሸነፍ ከ22 ዓመታት በኃላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ተመልሷል።
በሴካፋ መጠሪያ የመጨረሻ ጨዋታ የኬንያ አቻውን የኢትዮጵያ ከ17 ዓመታ በታች ብሔራዊ ቡድን 3 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን፣ የማሸነፊያ ግቦችን ዳዊት ካሳው፣ ቢኒያም አብረሀ እና ብሩክ አስቆጥረዋል።
ቀይ ቀበሮዎቹ ውድድሩን በሶስተኝነት በማጠናቀቅ ለ17 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ከ22 ዓመታት በኋላ ነው ወደ አፍሪካ ዋንጫው የተመለሰው።
#ጋዜጣፕላስ #ኢትዮጵያ #ሴካፋ

❤7
በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የሰላም ስምምነት ተደረገ
++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ l በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የሰላም ስምምነት ተደርጓል።
የስምምነት ሰነዱን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኩል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ተወካይ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ተፈራርመዋል።
የሰላም ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ ያደራደሩት ሲሆን የሰላም ስምምነቱ በሁለቱም ወገን ሰላም ፈላጊነት የተገኘ መሆኑንም ተገልጿል።
በማርቆስ በላይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazette_plus_english #አማራ #ሰላም

🤣8👏5❤4👎3