Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
“የማዕድን ልማት በእቅድና በእውቀት መመራት አለበት”

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የማዕድን ልማት በእቅድና በእውቀት መመራት እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ በመደመር መንግሥት ዕይታ የዘርፎች እመርታ በሚል መሪ ሀሳብ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልጠና ላይ፤ የማዕድን ልማት በእቅድና በእውቀት መመራት አለበት ብለዋል።

ክልሎችና የማዕድን ሚኒስቴር ማዕድን ለሚያወጡ አካላት ፍቃድ ሲሰጡ በከፍተኛ ጥንቃቄ አቅም ያላቸውን አልሚዎች በመለየት በጥናት መሰረተ መስጠት አለባቸው ብለዋል።

ማዕድን ትልቅ ሀብትና ብልፅግናን ለማስፈንጠር የሚያገለግል መሳሪያ ስለሆነ በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል።

በሌላ በኩል የኢንዱስትሪ ልማት ኢምፖርትን መተካትና በኤክስፖርት መቃኘት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የኢንዱስትሪ ልማቱን የግል ሴክተሩ እንዲሰራ የሚያስችል አውድ መፍጠርና መደገፍ ይገባል፤ ይህ ካልሆነ ኢንዱስትሪ ማንሰራራት አይችልም ካላንሰራራ ደግሞ ብልፅግናን ማምጣት አይቻልም ብለዋል።

በክብረአብ በላቸው
#ጋዜጣፕላስ #ኢትዮጵያ #ማዕድን #ኢንዱስትሪ
2
የባሕር በር ጥያቄ የመንግሥት ፖለቲካዊ ፍላጎት ተደርጎ መወሰድ የለበትም
++++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የባሕር በር ጥያቄ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ እንጂ የመንግሥት ፖለቲካዊ ፍላጎት ተደርጎ መወሰድ የለበትም ሲሉ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ሙሉዓለም ሀይለማርያም ተናገሩ።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ ሙሉዓለም ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለፁት፤ የባሕር በር ጥያቄ የብሔራዊ ጥቅም እንጂ የመንግሥት ፍላጎት ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም።

ኢትዮጵያ እንደ ሀገር መሰረታዊ ከምትላቸው የብሔራዊ ጥቅም አጀንዳዎች መካከል አንዱ የሆነውን የባሕር በር መልሶ የማግኘት ጉዳይ ከዘላቂ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ጋር ብቻ ተያይዞ መታየት ያለበት እንደሆነ ገልፀዋል።

እያደገ የመጣውን የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና የህዝብ ቁጥር ሊሸከም የሚችል መሰረተ ልማት ካልተገነባ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ህዝብ አፍኖ ማቆየት የሚቻልበት ሁኔታ የለም፤ ከዚህ አኳያ ሀገሪቱ የምታስተዳድረው የባሕር በር ከምንጊዜውም በላይ የሚያስፈልግበት ወቅት ላይ እንገኛለን ብለዋል።

ከጂኦፖለቲካ አንፃር በቀጣናው የሀገሪቱን ተደማጭነት ለማሳደግ፤ የተሳለጠና ደህንነቱ የተረጋገጠ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖር፤ በከፍተኛ ፍጥነት ቁጥሩ እየጨመረ ላለው ህዝብ ዘላቂ ጥቅም ለማስከበር የባሕር በር ጨዋታ ቀያሪ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።

የባሕር በር ጥያቄ ማንሳት እንደ ነውር መታየቱ ቀርቶ የዜጎች አጀንዳ ወደ መሆን መጥቷል ያሉት አቶ ሙሉዓለም፤ ይህንን ተከትሎ ጥያቄው ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱን ተናግረዋል።

ይህ ፍትሐዊ የባሕር በር ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ እንዲያገኝ የተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት መቀጠል እንዳለበት እና በተለይም የቀጣናው ሀገራት እርስበርስ ከለመተማመን አባዜ ወጥተው በሰጥቶ መቀበል መርህ እንዲሰሩ ጠንካራ ሥራ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በክብረአብ በላቸው
#ጋዜጣፕላስ #ኢትዮጵያ #የባሕርበር #ብሔራዊጥቅም
14👍1
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈ
++++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በሴካፋ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ ጨዋታ የኬንያ አቻውን 3 ለ 0 በማሸነፍ ከ22 ዓመታት በኃላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ተመልሷል።

በሴካፋ መጠሪያ የመጨረሻ ጨዋታ የኬንያ አቻውን የኢትዮጵያ ከ17 ዓመታ በታች ብሔራዊ ቡድን 3 ለ 0 ያሸነፈ ሲሆን፣ የማሸነፊያ ግቦችን ዳዊት ካሳው፣ ቢኒያም አብረሀ እና ብሩክ አስቆጥረዋል።

ቀይ ቀበሮዎቹ ውድድሩን በሶስተኝነት በማጠናቀቅ ለ17 ዓመት በታች አፍሪካ ዋንጫ ውድድር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ ከ22 ዓመታት በኋላ ነው ወደ አፍሪካ ዋንጫው የተመለሰው።

#ጋዜጣፕላስ #ኢትዮጵያ #ሴካፋ
7
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ
👍6
በአማራ ክልል መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የሰላም ስምምነት ተደረገ
++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ l በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እና በአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት መካከል የሰላም ስምምነት ተደርጓል።

የስምምነት ሰነዱን ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኩል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ እና ከአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት ተወካይ ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ ተፈራርመዋል።

የሰላም ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ ያደራደሩት ሲሆን የሰላም ስምምነቱ በሁለቱም ወገን ሰላም ፈላጊነት የተገኘ መሆኑንም ተገልጿል።

በማርቆስ በላይ
#ጋዜጣ_ፕላስ #gazette_plus_english #አማራ #ሰላም
🤣8👏54👎3
"ኢትዮጵያ ከአይ ኤም ኤፍ /IMF/ ጋር ያላትን ጠንካራ አጋርነት አጠናክራ ትቀጥላለች"

- አህመድ ሺዴ
++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ ከአይ ኤም ኤፍ /IMF/ ጋር ያላትን ጠንካራ አጋርነት አጠናክራ ታስቀጥላለች ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ ገለጹ።

የአይ ኤም ኤፍ ምክትል ሊቀመንበር ናይጄል ክላርክ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ይገኛል።

የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና የአይ ኤም ኤፍ ምክትል ሊቀመንበር ናይጄል ክላርክ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ እንደገለጹት፤ መንግስት የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ ማሻሻያ በማጠናከር ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማረጋገጥ የሚሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ ያስቀጥላል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በፋይናንስ በግብርና፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም እና በሌሎች ዘርፎች ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።

የማሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በዓለም ደረጃ ጥሩ ግምት የሚሰጠው ውጤት እያስገኘ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፣ ኢትዮጵያ ከአይ ኤም ኤፍ ጋር ያላትን ጠንካራ አጋርነትም አጠናክራ ለማስቀጠል ያላትን ፍላጎት አፅንኦት ሰጥተዋል።

የአይ ኤም ኤፍ ምክትል ዳይሬክተር ናይጄል ክላርክ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ያላትን እድገት አድንቀዋል።

በማሻሻያው የዋጋ ግሽበት መቀነሱን፣ የውጭ ምንዛሪ ክምችት መጨመሩን ፣ የመንግስት ፋይናንስ መጠናከሩን እና የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት መጠናከሩን አስታውቀዋል።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም በርካታ ውጤቶችን እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል።

አይ ኤም ኤፍ ለሀገሪቱ እና ለህዝቦቿ ኢኮኖሚውን የበለጠ ለማጠናከር በተራዘመ ብድር ኢትዮጵያን ለመደገፍ ቁርጠኛ ሆኖ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የአይኤምኤፍ ምክትል ሊቀመንበር ናይጄል ክላርክ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ጋር በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ባሉ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ በአይኤምኤፍ ድጋፍ እና የቀጣይ ትብብር ላይ ውይይት አድርገዋል።

በተጨማሪም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን፣ ኮይሻን እና ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

በሄለን ወንድምነው

#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ #አይኤምኤፍ
4👍2
"መምህራን በደመወዝ ይበልጠናል የሚሉት ‘ሴክተር’ የለም"
- ሽመልስ አበበ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት
++++++++++++++++++

#ጋዜጣ ፕላስ | በአሁኑ ጊዜ መምህራን በደመወዝ ይበልጠናል የሚሉት ‘ሴክተር’ የለም ሲሉ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አበበ ገለጹ።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አበበ ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ባለፉት ጊዜያት የመምህራን ደመወዝ ከሌላው ሴክተር በብዙ መንገድ የተጎዳ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከሲቪል ሰርቪስ እና ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በሚገባ በአጋርነት በመሰራቱ መምህራን አሁን ላይ በደመወዝ ይበልጠናል የሚሉት ሴክተር የላቸውም ሲሉ አስታውቀዋል።

መምህራን የተሻለ ደመወዝ ላይ ቢሆኑም፤ በሀገሪቱ ያለው የዋጋ ንረት ላይ መንግሥት ትኩረት ማድረግ ይገባዋል ብለዋል።

በሄለን ወንድምነው
++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #መምህራን #ኢትዮጵያ #መምህር
11👍5👎2