Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
“ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችው በባዳዎችና ባንዳዎች ዕኩይ ተግባር ነው”

- የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል አባል
++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችው በባዳዎችና ባንዳዎች ዕኩይ ተግባር ነው ሲሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ባህር ኃይል አባል ፒቲ ኦፊሰር ፈረደ ፍትሃነገስት ገለጹት።

የኢትዮጵያ ባህር ኃይል አባል ፒቲ ኦፊሰር ፈረደ ፍትሃነገስት ለጋዜጣ ፕላስ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችው በባዳዎችና ባንዳዎች ዕኩይ ተግባር ነው።

ሉዓላዊ ሀገርን መዝጋት በራሱ በህግ አግባብ ተጠያቂ የሚያደርግ በመሆኑ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ከህግ አግባብ ውጪ የሚሆንበት አንዳች ምክንያት የለም ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሰብን ማጣት ያልነበረባት መሆኑን የጠቀሱት አባሉ፤ ያለፈውን መውቀስ ብቻ ሳይሆን ከነበረው ሁኔታ ትምህርት ተወስዶ ችግሮችን እያረሙ መሄድ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ለተፈጠረው ችግር ከቀድሞ ባህር ኃይሎች ምን ይጠበቃል የሚለውን ምላሽ ለመስጠት ማህበር ተቋቁሞ እንቅስቃሴ ተጀምሯል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አያይዘው እንደገለጹትም፤ ለ36 ዓመታት በጠንካራ መሰረት ላይ የተገነባ ባህር ኃይል ማፍረስ በሀገር ላይ የተሰነዘረ ከባድ ጥቃት ነው።

በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ባህር_በር #ኢትዮጵያ #ቀይ_ባህር
6👍2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በአምባሳደር ባጫ ደበሌ የመጽሐፍ ምረቃ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ‼️
4🤯1
“ስደተኛዋ” የጦር መርከብ
++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በጦር ሜዳ ጀብድ ሠርታ፣ የሀገሪቱን ክብር በሚመጥን መልኩ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው መርከብ፣ ኃይለ ሥላሴ እናት መርከብ የሚል ስያሜ ተሰጥቷት ነበር።

በመናገሻነት በቀይ ባህር ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበች አገልግላለች።

ይህች መርከብ ታሪኳ በንጉስ ኃይለ ሥላሴ ይጀምርና መንግስቱ ኃይለ ማርያም ወደ ዚምባቢዌ ሲኮበልሉ የእርሷም እጣ ፋንታ ስደት ሆኖ ተቋጭቷል።

የቀድሞ ባህር ኃይል ባልደረባና ፎቶግራፈር አቶ ዳኜ አበራ፤ መርከቧ የኢትዮጵያ ስምና ኃያልነት የተጻፈባት ብዕር መሆኗን ይናገራል።

መርከቧ እ.ኤ.አ በ1962 ዓ.ም በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በነበሩት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ለንጉስ አጼ ኃይለ ሥላሴ በስጦታ የተሰጠች ነበረች።

ለኢትዮጵያ እስከተሰጠችበት ጊዜ ድረስ በአሜሪካ ባህር ኃይል ለበርካታ ዓመታት በማገልገል በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተካፍላለች። ወደ ኢትዮጵያ ስትመጣ የነበራት Orca 49 ስያሜ ተቀይሮ HMS A01 ኃይለ ሥላሴ እናት መርከብ ተብላለች።

የጦር መርከቧ ከ100 ሜትር በላይ ቁመት ያላት ሲሆን፣ በውስጧ ቤተ መንግስት ተገንብቶላት ነበር። ከ250 በላይ መርከበኞችንና ሰልጣኞችን የመያዝ አቅም ነበራት።

በውስጧ የተሟላ መለስተኛ ክሊኒክና የመዝናኛ ስፍራ ያካተተች ነበረች፤ ጠላትን መከላከል የሚያስችሉ መሳሪያዎችንም ታጥቃ ነበር ይላል አቶ ዳኜ።

በደርግ ዘመነ መንግስት ስሟ ዳግም ተቀይሮ "A01 ጦር መርከብ ኢትዮጵያ" ተብላ እንድትጠራ ተደርጓል።

በ1970 ዓ.ም ሻዕቢያ ምፅዋን ለመያዝ በሞከረበት ወቅት የባህር ኃይል መርከበኞችና መርከቦች ከፍተኛ ተጋድሎ ሲያደርጉ የጦር መርከቧ አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደነበር ዳኜ ይገልጻል።

በ1982 ዓ.ም ሻዕቢያ አጥፍቶ ጠፊ ጀልባዎችን ቢያሰማራም መርከቧ የጠላትን ጀልባ ዶግ አመድ ማድረግ ችላ ነበር።

በ1983 ዓ.ም ሻዕቢያ አሰብና አካባቢዋን በመቆጣጠሩ መርከቧ ወደ የመን ተሰድዳ ለረጅም ጊዜ ባህር ላይ ቆማ ጉዳት ደርሶባታል።

በመጨረሻም መርከቧ ጨረታ ወጥቶ በአሮጌ ላንድሮቨር ዋጋ የተሸጠች ሲሆን፤ ገዢው አካል ምንም ነገር ሳያስተርፍ ቆራርጦ እንደወሰዳት አብራርቷል።

መርከቧ በዓለም ውድ ከሆኑ ብረት የተሰራች መሆኗን የሚናገረው የቀድሞ ባህር ኃይል አባሉ፤ መርከቧ እንደሄደች የቀረችውም ሆነ በጨረታ የተሸጠችው መርከበኞቹ ቢጮሁም ሰሚ በማጣታቸው ነው ባይ ነው።

ዛሬ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ትንሣኤ መጀመሩ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለቀድሞ ባህር ኃይሎችም ትልቅ ስሜት ፈጥሯል በማለትም ደስታውን ይገልጻል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ስደተኛዋ_መርከብ #ኢትዮጵያ_ባህር_ኃይል #ታሪክ #ቀይ_ባህር
11👍4
የኢትዮጵያና ሕንድ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጥልቅና ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ እየጎለበተ መምጣቱ ተገለጸ
+++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የኢትዮጵያና ሕንድ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጥልቅና ስትራቴጂካዊ በሆነ መንገድ እየጎለበተ መምጣቱን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለጋዜጣ ፕላስ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ የሁለቱ አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ሰፊና ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን አብራርተዋል።

በግብርና፣ በማዕድን፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በሌሎች ቁልፍ ዘርፎች የተሻለ ትብብር ለመፍጠር ጉልህ ዕድሎች መኖራቸውን አጽንዖት ሰጥተዋል።

“በዓለም ደቡባዊ ቀጣና ውስጥ የሚገኙ በማደግ ላይ ያሉ አገራት እንደመሆናቸው፣ ኢትዮጵያና ሕንድ የጋራ የልማት ቅድሚያዎችን እና ዲፕሎማሲያዊ ዓላማዎችን ይጋራሉ” ሲሉ አምባሳደሩ ተናግረዋል።

ብሪክስን የመሰሉ ሁለቱንም አገራት ያካተቱ ዓለም አቀፍ መድረኮች የጋራ ጥቅሞቻቸውን ለማስፋት ወሳኝ መድረክ እንደሚሰጡ አመልክተዋል።

በዓለም አቀፍ መድረክም፣ ሁለቱ አገራት የጸጥታው ምክር ቤትን ጨምሮ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋማት በማደግ ላይ ያሉ አገራትን ፍትሐዊ ውክልና ማስጠበቅን በመሳሰሉ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ የተጣጣሙ አቋሞችን ይዘዋል ብለዋል።

“በማደግ ላይ ያሉ አገራት የሚያጋጥሟቸውን ዓለምአቀፍ ተግዳሮቶች ለመፍታት የደቡብ-ደቡብ ትብብር እጅግ አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል” ሲሉ አምባሳደሩ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ሕንድ ለኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ዋና ምንጭ መሆኗን ጠቁመው፤ የሕንድ አስተማሪዎች በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በብዛት መገኘታቸው በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ዘላቂ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ያሳያል ብለዋል።

መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተመሰረተው በ1948 እና 1952 ዓ.ም መካከል ቢሆንም፤ የሁለቱ አገራት ንግድና ትብብር ከዚያ በፊትም ሆነ በኋላ ተጠናክሮ መቀጠሉን አምባሳደሩ አስታውሰዋል።

ልጅዓለም ፍቅሬ

#ጋዜጣ_ፕላስ #ኢትዮጵያ_ሕንድ_ግንኙነት #ብሪክስ #ዲፕሎማሲ #የደቡብ_ደቡብ_ትብብር
2
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ለይፋዊ ጉብኝት በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል። የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል እያደገ የመጣውን ትስስር የሚያመለክት ሲሆን ውይይቶቻችን በጋራ የቅድሚያ ጉዳዮቻችን ላይ ትብብሮቻችንን የበለጠ የምናጠናክርበት እንደሚሆን እምነቴ ነው።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍61
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለህንድ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ዛሬ በቤተ መንግሥት ያደረጉላቸው አቀባበል።

Prime Minister Abiy Ahmed's official welcoming reception at the National Palace in honor of Prime Minister Narendra Modi.

#PMOEthiopia
13
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዛሬው እለት በፓርላማ ተገኝተው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል። #PMOEthiopia
👍61