Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲን ለይፋዊ ጉብኝት በመቀበሌ ደስታ ተሰምቶኛል። የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል እያደገ የመጣውን ትስስር የሚያመለክት ሲሆን ውይይቶቻችን በጋራ የቅድሚያ ጉዳዮቻችን ላይ ትብብሮቻችንን የበለጠ የምናጠናክርበት እንደሚሆን እምነቴ ነው።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍61
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለህንድ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ዛሬ በቤተ መንግሥት ያደረጉላቸው አቀባበል።

Prime Minister Abiy Ahmed's official welcoming reception at the National Palace in honor of Prime Minister Narendra Modi.

#PMOEthiopia
13
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በዛሬው እለት በፓርላማ ተገኝተው የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በየኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ላይ ንግግር አድርገዋል። #PMOEthiopia
👍61
“ሕንድ ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን እንዲሆን ልምዷን ታካፍላለች”

- ናሬንድራ ሞዲ
+++++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስኬት ተሞክሮ በማካፈል "ዲጂታል ኢትዮጵያ" እውን እንዲሆን ለማገዝ ዝግጁ መሆኗን የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ገለጹ።

የሕንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በኢፌዴሪ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በንግግራቸው፤ በአሁኑ ወቅት በሕንድ እያንዳንዱ ዜጋ የአገልግሎት ክፍያን ለመፈጸም ሙሉ በሙሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂን እየተጠቀመ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በሕንድ በዓመት ሦስት ጊዜ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች የዲጂታል ፋይናንስ አጠቃቀም ድጋፍ እንደሚያገኙ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ አሠራር አገሪቱን በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቃሚ ማድረጉን አመላክተዋል።

ይህንን የቴክኖሎጂ ተሞክሮ ለኢትዮጵያ ለማካፈል አገራቸው ዝግጁ መሆኗንም ናሬንድራ ሞዲ አረጋግጠዋል።

በልጅዓለም ፍቅሬ

#ጋዜጣ_ፕላስ #ናሬንድራ_ሞዲ #ዲጂታል_ኢትዮጵያ #ዲጂታል_ፋይናንስ #ቴክኖሎጂ #ሕንድ
6
የህንድን አዲስ ታሪክ የከተቡት ታላቅ ሰው
+++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | እ.ኤ.አ በ1943 በቫድናጋር በምትገኝ አንዲት ጠባብ ቤት ውስጥ የተወለዱት ናሬንድራ ሞዲ፣ የዛሬው የፖለቲካ ቁመናቸው ትላንት ካለፉበት የሕይወት ውጣ ውረድ የተቀዳ ነው።

በቤተሰብ የሻይ መሸጫ ውስጥ እየረዱ፣ የሻይ ማፍያው እንፋሎትና የኑሮ ፈተና እያጠነከራቸው ያደጉት ሞዲ፣ ለድሆችና ለተገፉት ያላቸው ርኅራኄ መነሻው ይኸው ትሑት የቤተሰብ አስተዳደጋቸው ነው።

ገና በአፍላነታቸው ከመጻሕፍት ጋር የነበራቸው ጥብቅ ቁርኝትና በሂማላያ ተራሮችና ገዳማት ውስጥ ያሳለፉት መንፈሳዊ ሕይወት "ለሌላው መኖር" የሚለውን ትልቅ እውነት እንዲረዱ አድርጓቸዋል።

ሞዲ በፖለቲካው ዓለም ውስጥ ያሳዩት ብቃትና ጥንካሬ በሥራ የተገነባ ነው እየተባለም ይነገርላቸዋል።

በፖለቲካል ሳይንስ የመጀመርያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከዴልሂና ከጉጂራት ዩኒቨርሲቲዎች ካገኙ በኋላ፣ በ1980ዎቹ የሕንድ ሕዝቦች ፓርቲን (BJP) ተቀላቅለዋል።


ከ2001 እስከ 2014 ድረስ በጉጃራት ግዛት ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ያሳለፏቸው 13 ዓመታት፣ በግዛቲቱ ላይ ያመጡት ታላቅ ለውጥ ለሀገር መሪነታቸው እንደ ትልቅ ድልድይ ሆኖ አገልግሏል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ዲሲፕሊን የሚደነቅ ነው። ንጋት 11 ሰዓት ላይ ሥራቸውን በመጀመር እስከ እኩለ ሌሊት የሚዘልቁት ሞዲ፣ የሥራ መርሃቸው ብበዙዎች ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኙ አድርጓቸዋል።

ለእሳቸው መንግሥት በሰዎች ሕይወት ውስጥ እንቅፋት ሳይሆን የሥኬት ድልድይ መሆን አለበት።

ይህ በቢሮክራሲ ያልታጠረና ሕዝብን በቀጥታ የሚያገለግል አመራራቸው፣ ሕንድን ወደ ቀድሞ ክብሯ የመመለስ ራዕይ የሰነቀ ነው።

በዳግማዊት ግርማ
#ኢትዮጵያ #ህንድ #ጋዜጣ_ፕላስ #ወዳጅነት #ዲፕሎማሲ #ናሬንድራ_ሞዲ #ሕንድ
2