Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የታለመለትን ግብ አሳክቶ ተጠናቋል። በዛሬው እለትም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ አስጀምረናል።

ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር፤ በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች ናቸው።

እነዚህ ትልሞች እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ የሚከናወን ሲሆን፣ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ ናቸው።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

#DigitalEthiopia2030
5
“ኢትዮጵያ የማደግ ፍላጎትና አቅም ያላት ሀገር ናት። ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ ዲጂታል መርሃ ግብር ፈጠራ፣ ፍጥነትና እመርታን በማምጣት የማደግ ፍላጎታችንን ከአቅመችን ጋር እንዲናበብ እያደረገ ነው።

የዲጂታል 2025 ስትራቴጂ በኢትዮጵያ የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን በማስፋት ዘርፈ ብዙ ቱርፋቶች ተመዝግበውበታል።

በመንግስት አሰራር፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በፋይናንስ ተደራሽነት ላይም ከፍተኛ ለውጥ መጥቷል። ዛሬ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 በይፋ አሰጀምረናል።

በቀጣይ አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች ዘላቂ የዲጂታል እመርታ እንዲመዘገብ ይሰራል።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ብሔራዊ የዲጂታል ትራስፎርሜሽን ምክርቤት ሊቀመንብር

#DigitalEthiopia2030
#PMOEthiopia
ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ሰው ተኮርና ለሁሉም ሴክተሮች ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት ይሆናል። በዲጂታል 2025 የተመዘገቡ የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት ስራውን በተጨባጭ ውጤት የምናሳይበት ጭምር ነው።

ስትራቴጂው በግልጽ የአስተዳደር ስርዓት፣ በሚለካ ውጤትና በተጠያቂነት ላይ ተመስርቶ በቀጣይ አምስት ዓመታት ተግባራዊ ይሆናሉ። ለዚህ ደግሞ ሁሉም የሚመለከተው አካል የጋራ ርብርብ ማድረግ ይጠበቅበታል።

ሚሪያም አሊ
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የዲጂታል አማካሪ

#DigitalEthiopia2030
#PMOEthiopia
“ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በዲጂታል 2025 ስትራቴጂ ላይ ቁልፍ ጉዳይ ሆኖ ተተግብሯል። አሁን ላይ 30 ሚሊዮን ዜጎች ፋይዳ መታወቂያ ተመዝግበዋል።

በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ላይም ፋይዳ ስትራቴጂካዊ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ የማድረግ ስራም ይሰራል።

በተለይ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ያሉ አገልግሎቶችን ከፋይዳ ጋር በማስተሳሰር በስትራቴጂው የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት ይሰራል። ለዚህ ደግሞ ሁሉም በትብብር ሊሰራ ይገባል።

ዮዳሄ አርአያስለሴ
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ

#DigitalEthiopia2030
#PMOEthiopia #fayda
5
በሲዳማ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት 60 ሺህ ዜጎች ‘የኢትዮ ኮደርስ’ ሥልጠና ይወስዳሉ
+++++++++++++++++++++++++++++

ጋዜጣ_ፕላስ | በሲዳማ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት 60 ሺህ ዜጎች የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና እንዲወስዱ እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።

የሲዳማ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ባራሳ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት፤ በ2017 በጀት ዓመት 27 ሺህ ዜጎች ሥልጠናውን አጠናቅቀዋል።

በተያዘው የ2018 በጀት ዓመት ደግሞ 60 ሺህ ዜጎች ሥልጠናውን ወስደው ዕውቅና እንዲያገኙ በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

አገልግሎቶች እየዘመኑ በመምጣታቸው ዲጂታል ክህሎት የግድ አስፈላጊ መሆኑንና ለዚህም የኢትዮ ኮደርስ ሥልጠና በሦስት ዓመት ተፈፃሚ እንዲሆን በመንግሥት አቅጣጫ መሰጠቱን አስረድተዋል።

ዕቅዱንና ሥልጠናውን በተመለከተ ለሁሉም ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ መከናወኑን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ክልሉ ከዚህ ሥልጠና በተጨማሪ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያና መሰል አገልግሎቶችን በዕቅድ ይዞ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው፤ የአይቲ ባለሙያዎችና የቴክኒክና ሙያ ኤክስፐርቶች ሥራዎችን እንዲያቀላጥፉ መመሪያ መሰጠቱን አመላክተዋል።

የመንግሥት ሠራተኞችና ከሰባተኛ ክፍል በላይ ያሉ ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ እንዲሳተፉ አቅጣጫ መያዙን የጠቀሱት አቶ ተፈራ፤ በተለይም ወጣቶችና ሴቶች የሥልጠናው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ኤጀንሲው አስፈላጊውን የቴክኒክ እገዛና ክትትል እያደረገ መሆኑን አብራርተዋል።

በሔርሞን ፍቃዱ
++++++++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #ሲዳማ #ኢትዮ_ኮደርስ #ዲጂታል_ኢትዮጵያ #ቴክኖሎጂ #ሥልጠና
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በሲቪል ምዝገባና የዜግነት አገልግሎት ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣቱ ተገለጸ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በሲቪል ምዝገባና የዜግነት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱንና አገልግሎቱን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር ረገድ ስኬታማ ሥራ መከናወኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለውን አሠራር በማስተሳሰር የቤተሰብ ምዝገባ፣ ወሳኝ ኩነት፣ የነዋሪዎች አገልግሎትና የማረጋገጥ ሥራዎች በዲጂታል ሥርዓት ተግባራዊ እየተደረጉ ነው።

ለሥራው የሚያገለግሉ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ አቅም የለሙ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ይህም ተቋማት በመረጃ የተሳሰሩ እንዲሆኑ ለሚከናወነው የ2030 ስትራቴጂ ትልቅ ተሞክሮ እንደሚሆን አስረድተዋል።

ይህ የዲጂታል ትስስር አሠራር አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ከማድረጉም በላይ፣ መረጃዎችን በአግባቡ ለመያዝ እና ለዜጎች ቀልጣፋ የዜግነት አገልግሎት ለመስጠት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገልጿል።

በ2030 ተቋማት ሙሉ ለሙሉ በመረጃ እንዲሳሰሩ ለተቀመጠው ግብም ይህ አሁናዊ ስኬት እንደ መነሻ እንደሚያገለግል ተጠቁሟል።

በጋዜጣ ፕላስ ሪፖርተር
++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #DigitalEthiopia2030 #ዲጂታል_ኢትዮጵያ #ሲቪል_ምዝገባ #አርቲፊሻል_ኢንተለጀንስ #ኢትዮጵያ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ ሁለት መሠረታዊ አስቻይ ጉዳዮች አሉ። አንደኛው የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ነው። ሁለተኛው የኢንተርኔት ትስስር ነው።

የኤሌክትሪክ ተደራሽነት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ምግብ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። የምንጠቀምባቸው የቴክኖሎጂ ጋጄቶች ኤሌክትሪክ ይፈልጋሉ። በመሆኑን በሁሉም አማራጮች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ማስፋት አለብን።

ሁለተኛው የኢንተርኔት ትስስር ነው። በርካታ ከተሞች የኢንተርኔት ትስስር ተጠቃሚ ሆነዋል። ነገር ግን በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ይህን ትስስር በሁሉም አካባቢዎች ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ ማድረግ ይገባል። ይህ እንደሚቻል አምነን በመስራት ለዜጎቻችን እኩል እድል መፍጠር አለብን።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
2
የሌሊትና የማለዳ ቅዝቃዜ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ይቀጥላል
++++++++++

ጋዜጣ_ፕላስ | የሌሊትና የማለዳው ቅዝቃዜ እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ በተለይም በደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለጋዜጣ ፕላስ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፤ ከሳይቤሪያ የሚነፍሰው ከፍተኛ የአየር ግፊት ወደ ኢትዮጵያ የሚዘልቅ በመሆኑ ደረቅ፣ ጸሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ይስተዋላል።

በተለይም በሰሜን፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛውና በደቡብ ደጋማ አካባቢዎች የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከአምስት ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ሊመዘገብ እንደሚችል ተጠቁሟል።

ይህ ቅዝቃዜ እስከ ወሩ ማጠናቀቂያ ድረስ የሚዘልቅ በመሆኑ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።

በመስከረም ሰይፉ
#ጋዜጣ_ፕላስ #የአየር_ንብረት #ሚቲዎሮሎጂ #ቅዝቃዜ #ኢትዮጵያ
3
#ዘመን_መጽሔት ገበያ ላይ ናት‼️

መጽሔቷን የት ያገኛሉ?

✍🏻 በጋዜጣ አዟሪዎች እጅ፤

✍🏻 መፅሃፍት ቤት፤

✍🏻 በድርጅቱ ኪዮስኮች፤

✍🏻 በሱፐር ማርኬቶች፤

✍🏻 አራት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት፤

✍🏻 ይህም ካልተመችዎት ከድርጅታችን ጋር የደንበኝነት ውል በመዋዋል ቤትዎ ድረስ በፍጥነት እናደርሳለን።

👉ለበለጠ መረጃ ይደዉሉልን! ይጻፉልን!

ስልክ፡ 0911351197/ 0920707752

ኢሜይል፡ -etpresspromotion@gmail.com

ዘመን ኢኮኖሚን ያንብቡ፤ በዘመን ኢኮኖሚ ይጻፉ

#ዘመን_ኢኮኖሚ #መጽሔት #ኢኮኖሚ #ኢትዮጵያ #ኢፕድ