Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በሲቪል ምዝገባና የዜግነት አገልግሎት ላይ ትልቅ ለውጥ ማምጣቱ ተገለጸ
+++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በሲቪል ምዝገባና የዜግነት አገልግሎት ተደራሽነት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱንና አገልግሎቱን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር ረገድ ስኬታማ ሥራ መከናወኑን የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ታዬ ግርማ እንደገለጹት፤ በአዲስ አበባ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያለውን አሠራር በማስተሳሰር የቤተሰብ ምዝገባ፣ ወሳኝ ኩነት፣ የነዋሪዎች አገልግሎትና የማረጋገጥ ሥራዎች በዲጂታል ሥርዓት ተግባራዊ እየተደረጉ ነው።

ለሥራው የሚያገለግሉ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ አቅም የለሙ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ ይህም ተቋማት በመረጃ የተሳሰሩ እንዲሆኑ ለሚከናወነው የ2030 ስትራቴጂ ትልቅ ተሞክሮ እንደሚሆን አስረድተዋል።

ይህ የዲጂታል ትስስር አሠራር አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ ከማድረጉም በላይ፣ መረጃዎችን በአግባቡ ለመያዝ እና ለዜጎች ቀልጣፋ የዜግነት አገልግሎት ለመስጠት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ተገልጿል።

በ2030 ተቋማት ሙሉ ለሙሉ በመረጃ እንዲሳሰሩ ለተቀመጠው ግብም ይህ አሁናዊ ስኬት እንደ መነሻ እንደሚያገለግል ተጠቁሟል።

በጋዜጣ ፕላስ ሪፖርተር
++++++++++++++++++
#ጋዜጣ_ፕላስ #DigitalEthiopia2030 #ዲጂታል_ኢትዮጵያ #ሲቪል_ምዝገባ #አርቲፊሻል_ኢንተለጀንስ #ኢትዮጵያ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የተቀመጡ ግቦች እንዲሳኩ ሁለት መሠረታዊ አስቻይ ጉዳዮች አሉ። አንደኛው የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ነው። ሁለተኛው የኢንተርኔት ትስስር ነው።

የኤሌክትሪክ ተደራሽነት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ምግብ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል። የምንጠቀምባቸው የቴክኖሎጂ ጋጄቶች ኤሌክትሪክ ይፈልጋሉ። በመሆኑን በሁሉም አማራጮች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ማስፋት አለብን።

ሁለተኛው የኢንተርኔት ትስስር ነው። በርካታ ከተሞች የኢንተርኔት ትስስር ተጠቃሚ ሆነዋል። ነገር ግን በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ይህን ትስስር በሁሉም አካባቢዎች ሙሉ ለሙሉ ተደራሽ ማድረግ ይገባል። ይህ እንደሚቻል አምነን በመስራት ለዜጎቻችን እኩል እድል መፍጠር አለብን።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
2
የሌሊትና የማለዳ ቅዝቃዜ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ይቀጥላል
++++++++++

ጋዜጣ_ፕላስ | የሌሊትና የማለዳው ቅዝቃዜ እስከ ታህሳስ ወር መጨረሻ ድረስ በተለይም በደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ለጋዜጣ ፕላስ በላከው መረጃ እንዳመለከተው፤ ከሳይቤሪያ የሚነፍሰው ከፍተኛ የአየር ግፊት ወደ ኢትዮጵያ የሚዘልቅ በመሆኑ ደረቅ፣ ጸሐያማና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ይስተዋላል።

በተለይም በሰሜን፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛውና በደቡብ ደጋማ አካባቢዎች የሌሊቱና የማለዳው ቅዝቃዜ ከአምስት ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ሊመዘገብ እንደሚችል ተጠቁሟል።

ይህ ቅዝቃዜ እስከ ወሩ ማጠናቀቂያ ድረስ የሚዘልቅ በመሆኑ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።

በመስከረም ሰይፉ
#ጋዜጣ_ፕላስ #የአየር_ንብረት #ሚቲዎሮሎጂ #ቅዝቃዜ #ኢትዮጵያ
3
#ዘመን_መጽሔት ገበያ ላይ ናት‼️

መጽሔቷን የት ያገኛሉ?

✍🏻 በጋዜጣ አዟሪዎች እጅ፤

✍🏻 መፅሃፍት ቤት፤

✍🏻 በድርጅቱ ኪዮስኮች፤

✍🏻 በሱፐር ማርኬቶች፤

✍🏻 አራት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት፤

✍🏻 ይህም ካልተመችዎት ከድርጅታችን ጋር የደንበኝነት ውል በመዋዋል ቤትዎ ድረስ በፍጥነት እናደርሳለን።

👉ለበለጠ መረጃ ይደዉሉልን! ይጻፉልን!

ስልክ፡ 0911351197/ 0920707752

ኢሜይል፡ -etpresspromotion@gmail.com

ዘመን ኢኮኖሚን ያንብቡ፤ በዘመን ኢኮኖሚ ይጻፉ

#ዘመን_ኢኮኖሚ #መጽሔት #ኢኮኖሚ #ኢትዮጵያ #ኢፕድ
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተጻፉት “መደመር” ፣ “የመደመር መንገድ”፣ “የመደመር ትውልድ” እና “የመደመር መንግሥት” መጻሕፍት ሰው ተኮር በሆነ የብዝሃ ኢኮኖሚ ጉዞ ኢትዮጵያን በአጠረ ጊዜ ውስጥ ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር አግዘዋል። በእነዚህ መጻሕፍት የተነሱ እሳቤዎች ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር በተግባር የተገለጡና ለትውልዱ ብሩህ ተስፋን ያጎናጸፉ ናቸው። መጻሕፍቱ አሁን ከሕትመት ባሻገር በ Medemer መተግበሪያ አማካኝነት በድምጽ ተተርጉመው ቀርበዋል።

መተግበሪያው ይፋ በሆነበት መድረክም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በመደመር እሳቤ የተከናወኑ ተግባራት ያስመዘገቡት ተጨባጭ ውጤት በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ቋሚ ዘጋቢዎች እንደበት ተዳሰዋል። #PMOEthiopia
2
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትን የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶን ተቀብለዋል። #PMOEthiopia
👏3
ዛሬ የኬንያ ፕሬዝደንት ዊልያም ሳሞይ ሩቶን ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት ተቀብያለሁ።

ጉብኝቱ በሁለቱ ሀገሮቻችን መካከል ያለውን ጥልቅ፣ ታሪካዊና ወንድማዊ ግንኙነት የሚያንፀባርቅ ነው።

በውይይታችን የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን በሚጠናከርበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ የተለዋወጥን ሲሆን ይኽም በሰላምና መረጋጋት፣ ንግግር ብሎም በአፍሪካ መር መፍትሔዎች ላይ ያለንን የወል ጽኑ አቋም የሚያሳይ ነበር።

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
👍103
90ኛው የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምሥረታ በዓል ዓለም አቀፍ ይዘት ባላቸው ዝግጅቶች ይከናወናል
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | 90ኛው ዓመት የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምሥረታ በዓል "የኢትዮጵያ አየር ኃይል የነፃነትና የአንድነት ምልክት" በሚል መሪ ቃል ከጥር 15 እስከ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም በተለያዩ ታላላቅ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር ተገለጸ።

አየር ኃይሉ የምሥረታ በዓሉን አስመልክቶ በቢሾፍቱ ከተማ ዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ሩጫ በማካሄድ ዝግጅቱን የጀመረ ሲሆን፤ ዋናው የበዓሉ ኩነት በሚከበርባቸው ቀናትም ዓለም አቀፍ ይዘት ያላቸው ልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከናወናሉ።

በዚሁ መሠረት "የአንበሶች ሰማይ ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የኢትዮጵያ፣ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ፣ የሩሲያ፣ የሞሮኮ እና የቼክ ሪፐብሊክ አየር ኃይሎች በጋራ የሚሳተፉበት "የጥቁር አንበሳ የአየር ትርኢት 2026" በድምቀት ይካሄዳል።

በተጨማሪም "የወደፊቱን የአቪዬሽን አቅም በጋራ እንገንባ" በሚል መሪ ቃል የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ታላላቅ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ኤክስፖ 2026 እንደሚሰናዳ ታውቋል።

በሌላ በኩል ከ38 በላይ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ኃይል አዛዦችና ባለሙያዎች የሚሳተፉበት 3ኛው "ፊውቸር አፍሪካ አየር ኃይሎች ፎረም" በተመሳሳይ ወቅት የሚካሄድ ሲሆን፤ ይህም ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የተቋሙን የታሪክ ጉዞና የበዓሉን ዝርዝር መረጃዎች ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ 'etaf90years.com' የተሰኘ ድረ-ገጽ የበለጸገ ሲሆን፤ ፍላጎት ያላቸው ዜጎች በድረገጹ አማካኝነት የመግቢያ ትኬት መግዛትና ኩነቶቹን መከታተል እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

በክብረአብ በላቸው
#ጋዜጣ_ፕላስ #የኢትዮጵያ_አየር_ኃይል #አቪዬሽን #ጥቁር_አንበሳ
#ኢትዮጵያ
በትግራይ ክልል ለተፈናቃዮች ከ257 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ሰብዓዊ እርዳታ ተሰራጨ
++++++++++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ | በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን አስገደ ወረዳ "ህፃፅ" ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ257 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ሰብዓዊ እርዳታ መሰራጨቱን የኢፌድሪ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በትግራይ ክልል የተፈናቃዮችን የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፤ በአሁኑ ወቅት ሰብዓዊ እርዳታ እየደረሳቸው አይደለም ተብሎ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች የቀረበው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ገልጿል።

ከመስከረም እስከ ታኅሣሥ 2018 ዓ.ም ባሉት ወራት ውስጥ ለተፈናቃዮቹ ያልተቋረጠ የምግብ እርዳታ ሲደረግ መቆየቱንም ኮሚሽኑ አብራርቷል።

በዚህም መሠረት ባለፉት አራት ወራት ውስጥ 11 ሺህ 406 ኩንታል ስንዴ፣ ማሽላ፣ ጥራጥሬ እንዲሁም የምግብ ዘይት ለተፈናቃዮቹ መሰራጨቱን ኮሚሽኑ በመግለጫው ጠቁሟል።

የእርዳታ አሰጣጡም በመስከረም፣ ጥቅምት፣ ኅዳር እና ታኅሣሥ ወራት በቋሚነት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ተደራሽ መደረጉን መግለጫው አመልክቷል።

ኮሚሽኑ ለተፈናቃዮች የሚላከው እርዳታ ለታለመለት ዓላማ መዋሉን የማረጋገጥ ኃላፊነት የክልሉና የአካባቢው ጊዜያዊ አስተዳደር መሆኑን አሳስቦ፤ ተጨማሪ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያስፈልግ ከሆነ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

በልጅዓለም ፍቅሬ
#ጋዜጣ_ፕላስ #ትግራይ #ሰብዓዊ_እርዳታ #አደጋ_ሥጋት
#ኢትዮጵያ #ህፃፅ
4