የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በዘርፉ የጓሮ አትክልት ዘመቻን አስጀመረ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በዘርፉ ባሉ የተለያዩ አካላት የሚከናወነውን የጓሮ አትክልት ዘመቻ በሐዋሳ አስጀምሯል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዘጠኝ ወር የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ገምግሟል።
በዛሬው እለት በተጀመረው የጓሮ አትክልት ማልማት ዘመቻ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሠራተኞችና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ተሳትፈዋል።
የክልል ቢሮዎችም በተመሳሳይ መልክ እስከቀበሌ የጓሮ አትክልት ዘመቻ ማካሄድ እንዳለበቸው በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማህበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ድኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ ገልጸዋል።
ዘመቻው የገቢ ምንጭ፣ የምግብ ፍጆታን ለመሸፈንና ገበያ ላይ ያለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት አማራጭ መሆኑንም ወይዘሮ አየለች አስታውቀዋል።
በቀጣይ ሦስት ወራት አንድም ስንዝር መሬት ጾሙን ሊያድር እንደማይገባ የጠቀሱት ሚኒስትር ድኤታዋ፤ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋውያን የጓሮ አትክልት እንዲያለሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በቀጣዩ ሦስት ወራት ሚኒስቴሩ ለዘመቻው ትኩረት በመስጠት ክትትል እንደሚያደርግም ተገልጿል።
በቤዛ እሸቱ (ሀዋሳ )

ታሽጎ የነበረን የንግድ ቤት ለመክፈት 100 ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለ የንግድ ጽ/ቤት ሃላፊ መያዙን ቢሮው አስታወቀ
******
(ኢ ፕ ድ)
የቦሌ ክፍለ ከተማ ንግድ ጽ/ቤት ሃላፊ በህገ ወጥ ንግድ ምክንያት የታሽገን የንግድ ቤት እከፍትልሃለሁ በሚል 100 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበል እጅ ከፍንጅ መያዙን የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።
ሃላፊው አቶ አለማየሁ ዋንዴቦ የግል ጥቅሙን በማስቀደም ታሽጎ የነበረን የንግድ ቤት በህገ ወጥ መንገድ ለመክፈት ተስማምቶ 100 ሺህ ብር ሲቀበል በህብረተሰቡ ጥቆማ መሠረት ሊያዝ ችሏል።
የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር ነዋሪዎች መብታቸውን በጎቦ እንዳይገዙ ከህግ አስከባሪ አካላት ጎን በመቆም በህግ የተረጋገጠላቸውን መብቶች እንዲጠብቁና እንዲያስጠብቁ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ህገ ወጥ ተግባራትን የሚፈጽሙ አካላትን በማጋለጥ ሌብነትን መከላከል እንደሚገባም አሳስበዋል።
ማንኛውም አይነት የሙስና የሌብነት ተግባራትን ለመከላከል የከተማዋ ነዋሪ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ የተለመደ ትብብሩን እንዲያጠናክር ቢሮው ጥሪ ማቅረቡን የአዲስ አበባ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቀዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

"የእስካሁኑ ጥፋት ይብቃ፤ ከአሁን በኋላ ችግሮቻችንን በምክክር እንፍታ" - ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
እስካሁን የጠፋው ጥፋት ይብቃ ከአሁን በኋላ ችግሮቻችንን በምክክርና በውይይት እንፍታ ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ገለፁ። ተቀዳሚ ሙፍቲው አገርን ለማስቀጠል የአገራዊ ምክክሩ ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነም ተናግረዋል።
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ እስካሁን የጠፋው ጥፋት ይበቃል በማለት ፊትን ወደ ሰላም ማዞር ይገባል።
አገርን ለማስቀጠል የአገራዊ ምክክሩ ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ የጠቆሙት ፕሬዚዳንቱ፤ ምክክሩ እኩልነት በሰፈነበት፤ በእውነትና በአንድነት መንገድ የሚከወን ከሆነ ለአገራችን አወንታዊ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
መመካከርና መወያየት የቆየ የኢትዮጵያውያን ትወፊት እንደሆነ ያወሱት ሃጂ ዑመር፤ በመመካከርና በመወያየት ችግራችንን ልንፈታ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።
ተቀዳሚ ሙፍቲው አገራዊ ምክክሩ ወደታች ወርዶ ተፈፃሚ እንዲሆን እንዲሁም አገር ወደ ሰላማዊ ሁኔታዋ እንድትመለስ ከመንግሥትና ከኅብረተሰቡ ብዙ ይጠበቃል ብለዋል።
ሕዝቡ ጥፋተኛን ለይቶ በማውጣትና የጥፋት መንገዶችን በመዝጋት....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70676
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

"አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስዎች ያወጡት ሪፖርት ከመረጃ አሰባሰቡ እስከ ውጤቱ ለአንድ ወገን ያደላ ነው" -አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
*********************
(ኢ ፕ ድ)
ከሰሞኑ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች በጋራ በመሆን ኢትዮጵያን በሚመለከት ያወጡት ሪፖርት ከመረጃ አሰባሰቡ እስከ ውጤቱ ለአንድ ወገን ያደላ መሆኑን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፁ።
አምባሳደር ዲና በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፣ ተቋማቱ መሬት ላይ የሚታዩና በርካታ መረጃዎችና ሁኔታዎችን በተገቢው ሁኔታ ሳይከታተሉ እንዲሁም ተገቢውን የማጣራት ሂደት ሳይከተሉ ለአንድ ወገን በማድላት ሌላኛውን ደግሞ በመኮነን ሪፖርት አውጥተዋል።
አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች በጋራ በመሆን ያወጡት ሪፖርት ወገንተኛነታቸውንና ጭፍን አቋማቸውን ያራመዱበት ሪፖርት ትክክል አለመሆኑን የተናገሩት አምባሳደር ዲና፣ የአማራ ክልል መንግሥት ይህን በሚመለከት ያወጣው መግለጫ ተገቢነት ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ በክልሉም ሆነ በፌዴራሉ መንግሥት ጉዳዩን በገለልተኛ አካል ለማጣራት ቀደም ተብሎ የታቀደና አቋም የተወሰደበት፤ በዚህም ወደ ተግባር ተገብቶ የጥናት ውጤቶች ይፋ እየተደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና በኢትዮጵያ በኩል የሚመለከታቸው አካላት በጋራ በመሆን ባደረጉት ምርመራ በወጣው.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70674
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

በእስራኤል በአምስት ከተሞች ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የድጋፍ ማሰባሰብ ዝግጅት ተካሄደ
******************
(ኢ ፕ ድ)
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበትን 11ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በእስራኤል በአምስት የተለያዩ ከተሞች የድጋፍ ማሰባሰቢያና ግንዛቤ መፍጠሪያ መርሃ ግብሮች በኤምባሲው አስተባባሪነት ተካሄደዋል።
በቴል- አቪቭ፣ እየሩሳሌም፣ሃይፋና አካባቢው፣ በናታኒያና በቂሪያት ጋት ከተሞች ነው የተካሄደው።
አምባሳደር ረታ ዓለሙ ባስተላለፉት መልዕክት በእስራኤል የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ እስካሁን ድረስ ከአንድ ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ በቦንድ ግዥና በስጦታ ድጋፍ አድርገዋል።
ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ወደፊትም ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
በአጠቃላይ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በቦንድ ግዥና በስጦታ ከ11 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ከመደረጉ ባሻገር፤ ግንዛቤ መፍጠር ተችሏል።
በየከተሞች በነበሩት ዝግጅቶች አስተባባሪ አካላት መርሐ ግብሩ እንዲሳካ አስተዎፆኦ አበርክተዋል።
በቢኒ ፊልም ፕሮዳክሽን የተዘጋጀው በአባይ ጉዳይ ላይ የሚያጠነጥን ፊልምና ሌሎች የኪነጥበብ ሥራዎች ለታዳሚዎች መቅረቡን ኤምባሲው አሰታውቋል።

«ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደት የማይተካ ሚና እየተጫወተች ነው» - አምባሳደር ጄምስ ፒቲአ ሞርጋን
******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የሰላምና መረጋጋት ሂደት መሳካት የማይተካ ሚና እየተጫወተች ነው ሲሉ በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጄምስ ፒቲአ ሞርጋን አስታወቁ።
የአገራቱ ግንኙነት መጠናከር ጠቀሜታው ለምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ጭምር መሆኑን አምባሳደሩ ገልጸዋል።
ጄምስ ፒቲአ ሞርጋን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ለደቡብ ሱዳን የሰላምና መረጋጋት ሂደት መሳካት እያበረከተችው ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው።
የደቡብ ሱዳን መረጋጋት የኢትዮጵያም መረጋጋት ነው ከሚል እሳቤ የመነጨው ድጋፍ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና እንዲረጋጋ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል ያሉት አምባሳደሩ፤ ይህ የኢትዮጵያ አቋም ለደቡብ ሱዳናውያን ትልቅ ትርጉም አለው ብለዋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳናውያን ችግር በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ የሚያደርጉት ጥረት የሚደነቅ ነው፤ ይህ ወንድማዊ አካሄዳቸውም ኢትዮጵያ ምንጊዜም ከደቡብ ሱዳን ጎን እንድትቆም የሚያደርጋት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያና ደቡብ ሱዳን እ.አ.አ. በ2018 በአዲስ አበባ የተፈራረሙት ስምምነት
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70719