Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
40K photos
302 videos
7 files
5.75K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን በፍራንኮ ቫሉታ የማስገባት ትግበራው ያላግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል ጥንቃቄ ያስፈልጋል" የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ክቡር ገና
*******************
(ኢ ፕ ድ)
መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን ያለምንም የውጭ ምንዛሬ ፈቃድ (ፍራንኮ ቫሉታ) ያላግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል መጠንቀቅ እንደሚገባና ትግበራው ለረጅም ጊዜ መፍትሄ እንደማይሆን የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ክቡር ገና ገለጹ።
የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ክቡር ገና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ፍራንኮ ቫሉታ መፈቀዱን ተከትሎ ያላግባብ ጥቅም ላይ እንዳይውል መጠንቀቅ ይገባል፣ ትግበራው ለረጅም ጊዜ መፍትሄ እንደማይሆንና ለኢኮኖሚ እድገት ሰላም መስፈን ይኖርበታል።
ፍራንኮ ቫሉታ ለመጀመሪያ ጊዜ ሲፈቀድ ለተወሰነ ጊዜ ሊያስቸግር ይችላል።ዓላማውን ለማሳካት ሳይሆን የራሳቸውን ጥቅም የበለጠ ለማዳበር ሊጠቀሙ የሚፈልጉ ግለሰቦችና አካላት ያላግባብ እንዳይጠቀሙበት ሂደቱ በጥብቅ ሥነ ምግባር እንዲመራ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
ፍራንኮ ቫሉታ በተለያየ ጊዜ ይፈቀዳል አንዳንዴ ደግሞ ይከለከላል ያሉት አቶ ክቡር፤ በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከሚያገኙት የውጭ ምንዛሬ በመጠቀም ዕቃ በማስገባት እንዲሸጡ የሚያደርግ አሠራር መሆኑንም ጠቁመዋል።
አሠራሩ ተግባራዊ በተደረገበት አጋጣሚ የቀነሰበት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70904
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
"ኢትዮጵያ ውስጥ ዓለምአቀፍ ሁነቶች መካሄዳቸው የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማሳየት ዕድል ይፈጥራል "
- ቱሪዝም ሚኒስቴር
******************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ዓለምአቀፍ ሁነቶች መካሄዳቸው የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማሳየት የተሻለ ዕድል እንደሚፈጥር የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
የኢፌዴሪ ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ትልልቅ ዓለምአቀፍ ሁነቶችን ኢትዮጵያ ውስጥ ማካሄዳቸው የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለማሳየት ዕድል ይፈጥራል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ኮንፈረስ በዓለምአቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ አመልክተው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ በጀርመን የሚካሄዱ ዓለምአቀፍ ሁነቶች በኢትዮጵያ እንዲካሄዱ ከጀርመን መንግሥት ጋር ሥራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
እንደ ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ፤ መሰል ዓለም አቀፍ ሁነቶች በኢትዮጵያ መካሄዳቸው ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጠቀሜታዎችን ያስገኛል።ኢትዮጵያ በዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘንድ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70895
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ አካባቢን የኤሌክትሪክ ችግር በአጭር ጊዜ መፍታት አልተቻለም
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ አካባቢ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትን በአጭር ጊዜ እንዲያገኙ ለማድረግ መቸገሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ፡፡
በሽብር ቡድኑ ምክንያት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ኃይል ከተቋረጠ ከአንድ ዓመት በላይ ሆኖታል፡፡ የተቋረጡትን መሥመሮች ለመጠገንና አካባቢዎቹ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ ተቋሙ መቸገሩን ገልጸዋል።
የላሊበላ እና የዋግ ኽምራ ዞን በርካታ አካባቢዎችም ለወራት የኤሌክትሪክ ኃይል እያገኙ አይደለም ብለዋል፡፡
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ እንደገለፁት የላሊበላ፣ ሰቆጣ፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ እና ሰቲት ሑመራ አካባቢዎች ኃይል ያገኙ የነበሩት በሽብር ቡድኑ በተያዙ አካባቢዎች ከሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ከተዘረጉ መሥመሮች ነበር ብለዋል።
ለላሊበላና አካባቢው ሌሎች አማራጮችን እየታዩ በመሆናቸው በአጭር ጊዜ ሊፈቱ እንደሚችሉ የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈፃሚው ለወልቃይት ጠገዴ አካባቢ መፍትሔ ለመስጠት ከጎንደር ወይም ከመተማ ኃይል መዘርጋት ግድ ስለሚል ረጅም ጊዜ እንደሚጠይቅ ጠቅሰዋል፡፡
በወልቃይት ጠገዴን ያለው ችግር ከሌሎች አካባቢዎች በተለየ ከዓመት በላይ የቆየው በአካባቢው አማራጭ መስመር ባለመኖሩና የአዲስ መስመር ዝርጋታው ትልቅ ኢንቨስትመንት የሚጠይቅና ረዘም ያለ ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
በአጭር ጊዜ መፍትሔ ለመስጠት የክልሉ መንግስት፣ የፌደራል መንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ሊሳተፉበት ይገባል ያሉት አቶ አሸብር የአጭር ጊዜ መፍትሔ ሊሆን የሚችለው ኦፍ ግሪድ የሆኑ አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ እንደሆነ አሳስበዋል፡፡
ላሊበላን በጄኔሬተር መብራት ለመስጠት የተደረገው ሙከራ በነዳጅ አቅርቦት ምክንያት መስተጓጎሉ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ነዋሪዎችን ያማረረው የበዓል ወቅት የዋጋ ንረት
**************
(ኢ ፕ ድ)
በበዓል ወቅት በመሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች ላይ የሚስተዋለው የተጋነነ የዋጋ ንረት እንዳስመረራቸው አስተያየታቸውን ለኢፕድ የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።ለገበያ የዋጋ ንረት የደላላዎች አሻጥር ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ተጠቅሷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪው አቶ ሚኪያስ ሳምሶን እንደሚሉት፤ በአሁኑ ወቅት በበዓል ሰሞን የሚስተዋለው የሸቀጦች ዋጋ መናር የሁሉም ኅብረተሰብ ጥያቄ እየሆነ ነው።በአዲስ አበባ የትንሳኤ በዓል መቃረብን ተከትሎ ከወዲሁ ዋጋ ንሯል።የአንዳንድ ሸቀጦች ዋጋ በፊት ከነበረው በእጥፍ ጨምሯል።ይህ በምን ምክንያት እንደሆነ አይታወቅም።ለበዓል ፍጆታ የሚውሉ ነገሮች ከወዲሁ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ማሳየታቸው በዓሉ ሲቀርብ ከዚህ በላይ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡
የአሁን ዋጋ መናር በዓሉን በአግባቡ ለማክበር አደጋች እንደሆነ የጠቀሱት አቶ ሚኪያስ፤ በዚህ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ገበያውን ለማረጋጋት፣ ምን እየሠሩ እንዳሉ ማወቅ አልቻልንም ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ ምንም እንኳን መንግሥት ገበያውን ለማረጋጋት እርምጃ እወስዳለሁ ቢልም ገበያ ላይ አንዴ የጨመረ ነገር በዚያው እየቀጠለና ኅብረተሰቡንም እያማረረ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
አብዛኛው ሰው ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ተመሳሳይ ኖሮ ላይ በመሆኑ በተለይ ነጋዴዎችና አቅራቢዎች የተጠቃሚውን ኅብረተሰብ የኑሮ ሁኔታ ያገናዘብ የዋጋ ተመን ሊያስቀምጡ...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70880
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ግብር ከፋዮች ሐሰተኛ መረጃ ከማቅረብ እንዲቆጠቡ ተጠየቀ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ግብር ከፋዮች ሐሰተኛ መረጃ ከማቅረብ እንዲቆጥቡ ግብር ሰብሳቢዎችም ሕጋዊ አሠራርን እንዲከተሉ የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን አሳሰበ፡፡
ኮሚሽኑ ትናንት የዘጠኝ ወር የሥራ አፈጻጸሙን በገመገመበት ወቅት እንደተነሳው፤ የቀረቡ ቅሬታዎች ሲመረመሩ በግብር ከፋዮች ዘንድ ያልተሟሉና ግልጽነት የጎደላቸው ሰነዶች የማቅረብ ችግር ታይቷል።በግብር ሰብሳቢዎች ዘንድም የተቀመጠው ሕጋዊ አሠራር ያለመከተል ችግር መኖሩን ኮሚሽኑ ማረጋገጡን ጠቅሷል፡፡
የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት አቶ ሙሉጌታ አያሌው በዚህ ወቅት እንደጠቀሱት፤ በዘንድሮ በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከንግዱ ማኅበረሰብ ለኮሚሽኑ የቀረቡት 866 ቅሬታዎች መካከል 529ኙ ውሳኔ ያገኙ ሲሆን ሁለቱ ደግሞ አስፈላጊው መረጃ ባለመቅረቡ ወደ ቀጣይ ሩብ ዓመት ተላልፈዋል።ቀሪዎቹ ደግሞ ለቃል ክርክርና ለመልስ ያልደረሱ በመሆናቸው ቀጣይ የሚታዩ ይሆናሉ ብለዋል፡፡
አንዳንድ ነጋዴዎች በስፋት የሚያቀርቡት ቅሬታ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከንግድ ሥራቸው ጋር የማይጣጣምና የተጋነነ ተመን መሆኑን በመረጃ አስደግፈው...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70887
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የአምነስቲና ሂዩማን ራይትስ ዎች ያወጡት መግለጫ በሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የሚገባ ነው
******************
(ኢ ፕ ድ)
የአምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂዩማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵያ ላይ ያወጡት መግለጫ በሉዓላዊነት ላይ ጣልቃ የሚገባና ለአንድ ወገን ያዘነበለ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በትናንትናው ዕለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በሳምንቱ የተካሄዱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊያና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲን አስመልክቶ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር መገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንደገለጹት፤ የአምነስቲና ሂዩማን ራይትስ ዎች ኢትዮጵያን በሚመለከት ያወጡት መግለጫ፤ ወደ አንድ ወገን የሚያዘነብልና የፖለቲካ ይዘት ያለው ነው።ሪፖርቱ ከሰብአዊ ጥሰት ውጭ ስለ ድንበር ጉዳይ ማንሳቱ አግባብ አይደለም፤ የአንድ አገር ሉአላዊ ጉዳይ ውስጥ ይገባል ብለዋል።
ሪፖርቱ የተወሰነ ወገንን የማንቋሸሽ ሁኔታ ይስተዋልበታል ያሉት አምባሳደር ዲና፣ መረጃውን ያሰባሰቡት ከአንድ ወገን ብቻ ነው።ሪፖርቱ በርካታ ጉድለቶች ቢኖሩበትም...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70882
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በከተማዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 377 አደጋዎች ተከስተዋል
👉 ሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን የሚገመት ንብረት ከአደጋ ማዳን ተችሏል
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 377 ተፈጥሮዓዊና ሰው ሠራሽ አደጋዎች መከሰታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሰለሞን ፍሰሐ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመኪና፣ በእሳት፣ በሕንፃዎች መደርመስ፣ በጎርፍና በመሰል ምክንያቶች 377 አደጋዎች በአዲስ አበባ ከተማ ተከስተዋል።
በዘጠኝ ወራት በአዲስ አበባ ከተማ በደረሱ አደጋዎች ከ700 ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ ንብረቶች መውደማቸውን አመልክተው፤ የተከሰቱ አደጋዎችን በተቀናጀ መልኩ መከላከል በመቻሉ በአደጋው ሊወድም የነበረውን ሁለት ነጥብ አምስት ቢሊዮን የሚገመት ንብረት ማዳን የተቻለ መሆኑን አብራርተዋል።
የአደጋው መጠንም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር የአደጋ ብዛት መቀነሱን አውስተው፤ በሟች የሰው ቁጥር በሁለት ሰዎች ብቻ ብልጫ መኖሩን ገልጸዋል፡፡
እንደ ሰለሞን ገለጻ፤ ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ መግቢያ አካባቢ በተደጋጋሚ ከተከሰቱ የጎርፍ አደጋዎች መነሻ በማድረግ በአደረገው ጥናት....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70909
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የኢዜአን የ80 ዓመት ጉዞ የሚያስቃኝ አውደ ርዕይ በሀዋሳ ተከፈተ
****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት(ኢዜአ) የተመሰረተበት 80ኛ ዓመት በማስመልከት የተዘጋጀ የፎቶና ቪዲዮ ዓውደ ርዕይ በደቡብና ሲዳማ ክልሎች ደረጃ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተከፈተ።
ዓውደ ርዕዩን መርቀው የከፈቱት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ልዩ አማካሪ አቶ ተሰማ ዲማ፣ የሲዳማ ክልል ፕሬስ ሴክሬተርያት ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፍሊጶስ ናሆም ፣ የደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ሰናይት ሰለሞን እና የደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብሩክ ሀብቴ ከኢዜአ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ ጋር በመሆን ነው።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ተገኝተዋል።
ለሶስት ቀናት የሚቆየው ዓውደ ርዕዩ ኢዜአ ባለፉት 80 ዓመታት ሲገለገልባቸው የነበሩ መሳሪያዎችና ፎቶ ግራፎች ለዕይታ ከቀረቡት መካከል ይገኙበታል።
ኢዜአ ባለፈባቸው ዓመታት አስተማማኝ የዜና ምንጭ በመሆን መረጃ ለመገናኛ ብዙሃን በማቀበል የነበረውና በቀጣይ በሚኖረው ሚና ላይ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በማረሚያ ቤቶች የሰብዓዊ መብት አያያዙ ቢስተካከልም የፍትህ አሰጣጡ መሻሻል እንዳለበት ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች ይታዩ የነበሩ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግሮች ቢስተካከሉም የፍትህ አሰጣጥ ሥርዓቱ ግን መሻሻል እንዳለበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ትናንት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡ ቋሚ ኮሚቴው የታራሚዎችን ሰብዓዊ አያያዝ በተመለከተና የማረሚያ ቤት አስተዳደር አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታዎችን ቃኝቷል።
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ታራሚዎች ለቋሚ ኮሚቴው በሰጡት አስተያየት ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮች እንደሌሉ ጠቁመው፤ ከፍርድ አሰጣጥ መዘግየትና ፍትህ መዛባት ችግሮች መኖራቸውን ግን ተናግረዋል።
በተለይም ፍርድ ቤቶች የሚወስኑትን ውሳኔዎች ተፈፃሚ ያለማድረግ፣ የይቅርታ አሰጣጥ ሥርዓት ተገቢው የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶለት በግልፀኝነት አለመመራቱ....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70901
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ባለስልጣኑ 150 ሺህ የቀበሌ ቤቶችን ኦዲት እንደሚያደርግ አስታወቀ
**************
(ኢ ፕ ድ)
በከተማዋ የሚገኙ 150 ሺህ የቀበሌ ቤቶችን ኦዲት ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን አስታወቀ።
የባለስልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ የሱፍ ኢብራሂም ትናንት የተቋሙን የዘጠኝ ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳስታወቁት፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ባለስልጣኑ በከተማዋ የሚገኙ 150 ሺህ የቀበሌ ቤቶች ላይ የኦዲት ሥራ ያከናውናል።
የኦዲቱ ሥራው የቀበሌ ንግድ ቤቶችንና መኖሪያ ቤቶችን የሚያካትት ሲሆን፤ የማጣራት ሥራው የሚከናወነው በየክፍለ ከተሞች ካሉ አመራሮች ጋር ነው ብለዋል።
የቀበሌ ቤቶች ጉዳይ ሰፊ የፍትህ ጥያቄና ቅሬታ የሚቀርብበት ነው ያሉት አቶ የሱፍ፤ ሥራው ሲጠናቀቅ ግልጽነት ያለው አሠራር ለመዘርጋት ይረዳል። በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩም ምን ያህል ቤት በምን ዓይነት ሁኔታ..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70913
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የኢትዮጵያ ሐኪሞች ማህበር 58ኛው ዓመታዊ የህክምና ጉባኤውን እያካሄደ ነው
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሐኪሞች ማህበር 58ኛው ዓመታዊ የህክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ ዓወደ ርዕይ እየተካሄደ ነው።
በመርሃ ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝደንት ተግባር ይግዛው (ዶክተር) ያለፈው ዓመት በጦርነትና በኮቪድ 19 ምክንያት ለጤና ሴክተሩ ፈታኝ ነበር ብለዋል።
በጦርነት ምክንያት የወደሙ በርካታ የጤና ተቋማትን መልሶ ለመገንባትና በሌሎች አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው ለሰጡት ሙያዊ አገልግሎት የጤና ባለሙያዎችን አመሥግነዋል።
የ21ኛው ክፍለ ዘመን ያልተጠበቁና አደገኛ የሆኑ የጤና ቀውሶች ሊፈጠሩ የሚችሉበት ወቅት በመሆኑ የጤና ባለሙያዎች በሙያዊ እውቀትና በሥነልቦና ራሳቸውን ሊያዘጋጁ ይገባል ብለዋል።
ማህበሩ የጤና ባለሙያዎችን ብቃት ለማሳደግና ህይወት ለመቀየር ሲሠራ ቆይቷል። ይህን ተግባሩን አጠናካሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
በውብሸት ሰንደቁ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️