Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለጥቁር ህዝቦች ታሪክ፣ ቅርስ ማቆያና የትምህርት ማዕከል ምስረታ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናገሩ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከጥቁር ህዝቦች የህግ፣ የታሪክና የማህበራዊ ሳይንስ ምሁራን ጋር ባካሄዱት ውይይት የጥቁር ህዝቦች የታሪክ፣ የቅርስ ማቆያና የትምህርት ማእከል በአዲስ አበባ ላይ ለማቋቋም የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በፓን አፍሪካን እንቅስቃሴ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው በመሆኑና ጉዳዩን በቁርጠኝነት የሚከታተሉት ስለሆነም ለምስረታው ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ እንደሚያመቻቹ ተናግረዋል።
የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ስፔሻሊስትና ደራሲ ሮቢን ዎከር በበኩላቸው ከድህረ ቅኝ አገዛዝ በኋላ ያለው በጥቁር ህዝቦች ላይ ያተኮረ ትርክት እጅግ የተዛባና ነው። በዚህ ወቅት ግን ምሁራን በሚያደርጉት ያላሰለሰ ጥረት በራስ መተማመን ላይ የተመሰረተ ስነ ልቦና መላበስ ለጥቁር ህዝቦች ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህን የጥቁር ህዝቦች በራስ የመተማመን ስነልቡና ለማጎልበት ቅድመ ቅኝ አገዛዝ የጥቁር ህዝቦችን ታሪክና ቅርስ መመርመር የሚያስችል ማእከል አዲስ አበባ ላይ መመስረት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በዩናትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ቡድኑ ማእከሉን በአዲስ አበባ ለማቋቋም በኤምባሲው ተደጋጋሚ ውይይቶች መካሄዳቸውን አስታውሰው ለስኬታማነቱ የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ተናገረዋል፡፡
የቡድኑ አስተባባሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ ጸጋዬ ጫማ እንደገለፁት ቡድኑ የማእከሉን ምስረታ ለማቀላጠፍ ወደ አዲስ አበባ በርካታ አባላቱን በመያዝ ይጓዛል። ኤምባሲው ለዚህ አላማ ስኬት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል፡።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
***************
(ኢ ፕ ድ)
ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
የ10 ዓመት ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰልና በሀሰተኛ ሰነድ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የተገኙ 11 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ ገልጸዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በ3 ክፍለ ከተሞች ስም የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነድ እንዲሁም የሃኪም ማስረጃዎችን ከሚለምኑባቸው 2 ሚኒባስ መኪኖች ጋር በህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማና በጸጥታ አካላት ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ብለዋል፡፡
በተደረገው የክትትል ስራ ለህገ-ወጥ ስራው የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነዶችን፣ ታርጋ ቁጥር 58456 እና 79169 ኮድ 3 ኦሮሚያ ሚኒባስ ታክሲዎችን እንዲሁም 9 ሴትና 2 ወንዶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል ብለዋል፡፡
በከተማዋ የተለያዩ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማዘጋጀትና ያልታመመ ሰውን ታመመ በማለት የሚመለከተው የህክምና ተቋም ማረጋገጫ ሳይሠጥ በህገ-ወጥ መንገድ የሚካሄዱ ልመናዎች መብዛታቸውን የጠቆሙት ኃላፊው ህብረተሰቡ ከአጭበርባሪ ራሱንና ንብረቱን እንዲጠብቅ ጥሪ ማቅረባቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዘንድሮው ዓመት በድምቀት ይከበራል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል አከባበርን አስመልክቶ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት ፊቼ ጫምባላላ በዓል በኮሮና ምክንያት በጉዱማሌ አልተከበረም። ዘንድሮ በሲዳማ ብሔር ዘንድ አልፎም በአደባባይ በጉዱማሌ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቋል ብለዋል።
ቀኑን ማስታወቅና ወዘተ እንዲሁም የበዓሉ ቅድመ ዝግጅት ቅቤ በማጠራቀም፣ የተጣሉትን የማስታረቅ፣ የከብቶች የግጦሽ ሳር ማዘጋጀትና የመሳሰሉ ልዩ ልዩ ክንውኖችን በቤተሰብ ደረጃ ይደረጋሉ ብለዋል።
የፊቼ ጫምባላላ በዓል የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኒስኮ የተመዘገበ የማይዳሰስ ቅርስ ነው ያሉት ኃላፊው በዓሉን ለመታደም ከተለያዩ ሀገራት ለሚመጡ ቱሪስቶችና ለባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ፊቼ ጫምባላላ በውስጡ የያዛቸው እሴቶች በመኖሩ ይሄንንም የሚገልጽ የፓናል ውይይት በፊቼ ቀን ይካሄዳል ብለዋል።
የክልሉ መንግሥት በኩል ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ እንደሆነ በመግለፅ ህዝቡ በዓሉን ያለ አንዳች ችግር እንዲያከብር የተለያዩ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሥራውን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ኃላፊው መግለፃቸውን ከሲዳማ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
መረጃ ያመለክታል።
ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሴቶች የሚሳተፉበት የውይይት መድረክ እንደሚያካሂድ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አሰታወቀ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፓርቲው ባከናወነው አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎችና ምግቤን ከጓሮዬ በሚል ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሴቶች የሚሳተፉበት ንቅናቄ ከሚያዚያ 8/8/2014 አስከ 25/8/2014 ዓ.ም እንደሚያከነውን አስታወቀ።
ውይይቱ የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ፤ በቀጣይ ለሚደረገው የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ እንደ ግበዓት እንደሚያገለግል የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ሀላፊ ወ/ሮ መብራት ባጫ ተናግረዋል።
በዕለቱ ምግቤን ከጓሮዬ ንቅናቄ በ21 ዞኖች፣19 ከተሞችና በ312 ወረዳዎች እንደሚካሄድ ሀላፊዋ ገልፀዋል።
ለመርሀ ግብሮቹ መሳካት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ ቀና ትብብር እንዲያደርግ ወ/ሮ መብራት ጥሪ አቅርበዋል።
የመርሀ ግብሮቹ ማስጀመሪያ ስነስረዓት ሚያዚያ ስምንት ሚያዚያ 8/8/2014 ዓ ም በገላን ከተማ እንደሚካሄድ የኦቢኤን ዘገባ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
"በአማራ ክልል የስንዴ ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ከፍተኛ ጥረት አደንቃለሁ። በመላዉ ክልል ከ41 ሺህ ሄክታር በላይ ሲያለሙ በሰሜን ሸዋ ዞን ብቻ ከ2 ሺህ 800 ሄክታር በላይ ምርታማነት አበረታች ነው። በክላስተር የግብርና አካሄዳችን በአንድነት ለምግብ ዋስትና እና ለሀገር ልማት ምን እንደምናሳካ ማሳያ ነው።"

-ጠቅላይ ሚኒስትር ዶከተር ዐቢይ አሕመድ
ኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የአስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች
****************
(ኢ ፕ ድ)

ኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የአስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና መመረጣን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት አሰታወቀ።

ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልክተኛ ጽ/ቤት ምርጫውን ተከትሎ ባስተላለፈው መልዕክት በዓለም የግዙፉ ሰብአዊ እርዳታ ሰጪ ድርጅት የቦርድ አባል ሆና ተመርጣለች።

በመላው ዓለም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሀገራት የተሻለ ሥራ እንዲከውን ኃላፊነቷን ትወጣለች ብሏል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
መኢአድ በሚያካሂደው ዓመታዊ ጉባኤ ታሪካዊ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
መኢአድ ከዛሬ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በሚያካሂደው ዓመታዊ ጉባኤው ታሪካዊ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡
የመኢአድ አገራዊ የፖለቲካ ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በቃሉ ደሳለኝ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፣ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ለአገራዊ የፖለቲካ ድርጅቶች ጉባኤቸውን እንዲያደርጉ ማሳሰቡን ተከትሎ ድርጅቱ ዛሬና ነገ ጉባኤውን ያካሂዳል።
ፓርቲው በጉባኤው አሁን ኢትዮጵያ ያለችበትን የጸጥታ ሁኔታ በጥልቀት ይገመግማል።እንደ አገርና የፖለቲካ ድርጅትም በአገራዊው የጸጥታ ሁኔታ እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ የጠቅላላ ጉባኤው ግምገማን ተንተርሶ ድርጅቱ የራሱን አቋም ይይዛል ብለዋል።
ዛሬ በሚያካሂደው ዓመታዊ ጉባኤም በፖለቲካ ድርጅቱ በኩል ለአገር የሚበጁና አሁን ያለውን አገራዊ ሁኔታ አንድ እርምጃ ሊያራምዱ የሚችሉ ታሪካዊ ውሳኔዎች....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70967
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ኤጀንሲው ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ወጣቶች እየደገፈ እንደሚገኝ ገለጸ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ወጣቶች በመደገፍ አቅማቸውን የሚያሳድጉበትንና ራሳቸውም ሆነ አገራቸው የሚጠቅሙበትን ምቹ ዕድል ለመፍጠር እየሠራ መሆኑን የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አስታወቀ።
የሥራ እድል ፈጠራ ላይ የሚሠሩ ድርጅቶችና ተቋማት ለወጣቶቹ ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባም አመልክቷል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ኤጀንሲያቸው በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ፍላጎትና ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ልጆች በማሰልጠን እንዲሁም ከስራው ጋር ትውውቅ እንዲያደርጉ እድል በመስጠት ላይ ይገኛል። ወጣቶች በመደገፍ አቅማቸውን የሚያሳድጉበትንና ራሳቸውንና አገራቸውን የሚጠቅሙበት ሁኔታ እንዲፈጥሩ እየሠራ ነው።
የፈጠራ ባለሙያዎችን የመደገፍ ሥራ ለመንግሥት ብቻ የሚተው አይደለም ያሉት ዶክተር ሹመቴ ፤የሚመለከታቸው አካላትና ባለሀብቶች ልዩ ተሰጥዖና ችሎታ ያላቸውን ሰዎች በመደገፍ በጋራ ተጠቃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ ሊፈጥሩ ይገባል ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ላይ ተስፋ የሚጣልባቸው ፈጠራዎችን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70964
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በትግራይ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶች በተረጂዎች ዝርዝር መሠረት እንደሚከፋፈሉ ተገለጸ
**********************
(ኢ ፕ ድ)
ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች በትግራይ ክልል የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሶችን በተረጂዎች ዝርዝር መሠረት እንደሚያከፋፍሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ ወደ ትግራይ ክልል ድጋፍ እያቀረቡ ያሉ ድርጅቶች መብትና ግዴታ ያላቸው ናቸው ። መብትና ግዴታቸው መሠረት አድርገውም ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በየብስ አጓጉዞ ትግራይ ክልል የማድረስና በተጠቃሚዎች ዝርዝር መሠረት ምግብ የማከፋፈል ሥራ ይሠራሉ።
በትግራይ ክልል ምግብ በማቅረብ ረገድ የዓለም የምግብ ፕሮግራም፣ ኬቬ ኢንተርናሽናል፣ ሲአር ኤስ፣ ወርልድ ቪዥንና የዓለም የምግብ ፕሮግራም ሥራቸውን እየሠሩ እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ ዩኒሴፍ፣ የዓለም የጤና ድርጅትና መሰል ድጋፍ አድራጊ ተቋሞች ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70958
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ሕዝቡን የሚያጋጩ ልሂቃን ከጥፋት ጎዳናቸው ሊመለሱ እንደሚገባ ተጠቆመ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ ጎራ ፈጥረው ሕዝቡን የሚያጋጩ ልሂቃን ከጥፋት ጎዳናቸው ሊመለሱ እንደሚገባ የቀድሞ ሠራዊት አባልና ደራሲ አቶ ማሞ አፈታ አስታወቁ።
አቶ ማሞ አፈታ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚስተዋሉ አብዛኞቹ ግጭቶች መነሻ የተማረው የኅብረተሰብ ክፍል በሚያዛምተው ሐሰተኛ ወሬና ቅስቀሳ መሆኑን ገልጸዋል።
ምሑራኑ በኅብረተሰቡ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት በመጠቀም ለራሳቸው የሚጠቅማቸውን የግጭት አጀንዳ እየፈጠሩ ለዘመናት ተከባብሮና ተቻችሎ የኖረውን ማኅበረሰብ እያቃረኑ ነው የኖሩት። በመሆኑም ትክክለኛ እና ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ልሂቃኑ ከዚህ ተግባራቸው መታቀብ ይገባቸዋል።
በተለይም በአሁኑ ወቅት እየተበራከተ ለመጣው ግጭት መነሳትም ሆነ መባባስ ዋነኛ ተጠያቂ.....
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=70955
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️