Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
አለም አቀፍ የሠራተኞች ስምምነት በኢትዮጵያ የህግ ስርዓት ውስጥ ተካተው እንዲተገበሩ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሄደ
************************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን የሠራተኞች ፍልሰትን አስመልክቶ በአለም የሥራ ድርጅት በኩል የወጡት አለም አቀፍ ስምምነቶች በኢትዮጵያ የህግ አካል ሆነው ተግባራዊ ለማድረግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሐግብር አካሄደ።
በመረሐግብሩ ላይ በስራ ቦታ ላይ የሚደርስ ጥቃትንና ትንኮሳን መከላከል ስምምነት ቁጥር 190፤ የቤት ሠራተኞች ላይ የሚደርስ የመብት ጥሰትና እንግልትን ስለማስቆም ስምምነት ቁጥር 189፣ ከሰራተኛዉ መብት ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ስምምነት ቁጥር 97 እና 143 ተዋውቀዋል።
እነዚህ ህጎቹ ተቀባይነት አግኝተው በመጽቃቸው በአገሪቱ ስራ ቦታ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በመቅረፍና የሰራተኛውን መብት በማስከበር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት በመድረኩ ተገልጿል።
ለመንግስትም ሰራተኛ ተቀባይ ከሆኑ ሀገራት ጋር ለመደራደር ትልቅ አቅም እንደሚሆነም ተገልጿል።
በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ የሠራተኞች ፍልሰትን በአገር ውስጥም የሚሰሩ ሰራተኞችም መብታቸዉ ሊጠበቅ ይገባል። መንግስት ኮንቬንሽኖቹን በማጽደቅ ከኢሠማኮ ጎን እንዲሆን ጠይቀዋል።
በአለም አቀፍ የሥራ ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ ዋና ዳይሬክተር አሌክሶ ሙሴንዶ በበኩላቸው፣ የኮንቬንሽኖቹ መጽደቅ የሰራተኛውን መብት በማስከበር ትልቅ አስተዋጾ እንደሚኖረዉ ተናግረዋል።
የአለም ስራ ድርጅት የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር አሌክሶ ሙሲንዶ፣ የኢሠማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ የኢትዮጵያ አሠሪዎች ፌዴሬሽኖች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ታደሰ ይመር እና የሚመለከታቸዉ አካላት በጋራ በይፋ አስጀምረውታል።
በመዓዛ ማሞ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
በሀረሪ ክልል የፖሊዮ ክትባት መሰጠት ተጀምሯል
**************
(ኢ ፕ ድ)
በክልሉ ሁለተኛው የፖሊዮ ክትባት በዛሬው እለት መሰጠት ተጀምሯል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ኢብሳ ሙሳ በአቦነ እንድሪያስ ካቶሊክ ትምህርት ቤት የክትባት ዘመቻውን አስጀምረዋል።
በክልሉ በሚሰጠው የክትባት ዘመቻ ከ56 ሺህ 300 በላይ የሚሆኑ ህፃናትን ለመከተብ መታቀዱን ገልፀዋል።
ክትባቱም በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ቤት ለቤትና በትምህርት ቤቶች እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።
በመሆኑም ህብረተሰቡ ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት በማስከተብ የፖሊዮ በሽታ ለጥፋት በሚከናወኑ ተግባራት ሚናውን እንዲወጣ ጥሪ ማቅረባቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የምርምርና የልህቀት ማዕከላትን ለማበልጸግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ቋሚ ኮሚቴው አሳስበ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርና ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የእንስሳት ጤና የምርምርና ስልጠና የልዕቀት ማዕከላትን ለማበልጸግ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አሳሰበ።
በእንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት ባደረገው የመስክ ምልከታ የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ ሃመዱ ጋግስ በኢንስቲትዩቱ የሪፎርም ስራዎች ላይ የታዩ መዘግየቶችን በማሻሻል የላቦራቶሪ ጥራት ቁጥጥር ስርአት በማጠናከር የእንስሳት እርባታን በማስፋፋት ከባለሃብቶች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል፡፡
ተቋሙ የምርምር ማዕከሉን ለማጠናከር መመሪያዎችና ደንቦችን ጊዜ ወስዶ በማየት ኢንስቲትዩቱን የተሻለ ደረጃ ላይ ለማድረስ የተጀመሩ ስራዎችን ከምርምር ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል።
ኢንስቲትዩቱ የሚታዩ ክፍተቶችን በማረም የምርምርና ስልጠና ተቋማትን የአፍሪካ የልህዕቀት ማዕከል ለማድረግ በእቅድ መስራት እንዳለባቸው የቋሚ ኮሚቴው አባላት ማሳሰባቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለኢንስቲትዩቱ የስራ እንቅስቃሴ ተግዳሮት የሆነው የግዢ ስርአት አሰራርን ለመቅረፍ በአምራችና በተጠቃሚ መካከል ያለውን የግዢ ሰንሰለት በመቀነስ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በመውሰድ የግዢ ስርአቱን በማዘመን የምርምር ስራዎችን ማሳለጥ እንደሚቻል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጌትነት አቤ (ዶ/ር)ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለጥቁር ህዝቦች ታሪክ፣ ቅርስ ማቆያና የትምህርት ማዕከል ምስረታ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናገሩ
********************
(ኢ ፕ ድ)
በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከጥቁር ህዝቦች የህግ፣ የታሪክና የማህበራዊ ሳይንስ ምሁራን ጋር ባካሄዱት ውይይት የጥቁር ህዝቦች የታሪክ፣ የቅርስ ማቆያና የትምህርት ማእከል በአዲስ አበባ ላይ ለማቋቋም የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በፓን አፍሪካን እንቅስቃሴ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው በመሆኑና ጉዳዩን በቁርጠኝነት የሚከታተሉት ስለሆነም ለምስረታው ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታ እንደሚያመቻቹ ተናግረዋል።
የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ስፔሻሊስትና ደራሲ ሮቢን ዎከር በበኩላቸው ከድህረ ቅኝ አገዛዝ በኋላ ያለው በጥቁር ህዝቦች ላይ ያተኮረ ትርክት እጅግ የተዛባና ነው። በዚህ ወቅት ግን ምሁራን በሚያደርጉት ያላሰለሰ ጥረት በራስ መተማመን ላይ የተመሰረተ ስነ ልቦና መላበስ ለጥቁር ህዝቦች ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህን የጥቁር ህዝቦች በራስ የመተማመን ስነልቡና ለማጎልበት ቅድመ ቅኝ አገዛዝ የጥቁር ህዝቦችን ታሪክና ቅርስ መመርመር የሚያስችል ማእከል አዲስ አበባ ላይ መመስረት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በዩናትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ቡድኑ ማእከሉን በአዲስ አበባ ለማቋቋም በኤምባሲው ተደጋጋሚ ውይይቶች መካሄዳቸውን አስታውሰው ለስኬታማነቱ የበኩላቸውን ጥረት እንደሚያደርጉ ተናገረዋል፡፡
የቡድኑ አስተባባሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊው አቶ ጸጋዬ ጫማ እንደገለፁት ቡድኑ የማእከሉን ምስረታ ለማቀላጠፍ ወደ አዲስ አበባ በርካታ አባላቱን በመያዝ ይጓዛል። ኤምባሲው ለዚህ አላማ ስኬት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባዋል ብለዋል፡።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
***************
(ኢ ፕ ድ)
ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰል ሲለምኑ የነበሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
የ10 ዓመት ህጻን ልጅን የኩላሊት ህመምተኛ በማስመሰልና በሀሰተኛ ሰነድ ገንዘብ ሲያሰባስቡ የተገኙ 11 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ጌታሁን አበራ ገልጸዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በ3 ክፍለ ከተሞች ስም የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነድ እንዲሁም የሃኪም ማስረጃዎችን ከሚለምኑባቸው 2 ሚኒባስ መኪኖች ጋር በህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማና በጸጥታ አካላት ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ብለዋል፡፡
በተደረገው የክትትል ስራ ለህገ-ወጥ ስራው የተዘጋጁ ሃሰተኛ ሰነዶችን፣ ታርጋ ቁጥር 58456 እና 79169 ኮድ 3 ኦሮሚያ ሚኒባስ ታክሲዎችን እንዲሁም 9 ሴትና 2 ወንዶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል ብለዋል፡፡
በከተማዋ የተለያዩ ሃሰተኛ መረጃዎችን በማዘጋጀትና ያልታመመ ሰውን ታመመ በማለት የሚመለከተው የህክምና ተቋም ማረጋገጫ ሳይሠጥ በህገ-ወጥ መንገድ የሚካሄዱ ልመናዎች መብዛታቸውን የጠቆሙት ኃላፊው ህብረተሰቡ ከአጭበርባሪ ራሱንና ንብረቱን እንዲጠብቅ ጥሪ ማቅረባቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዘንድሮው ዓመት በድምቀት ይከበራል
*****************
(ኢ ፕ ድ)
የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል አከባበርን አስመልክቶ የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት ፊቼ ጫምባላላ በዓል በኮሮና ምክንያት በጉዱማሌ አልተከበረም። ዘንድሮ በሲዳማ ብሔር ዘንድ አልፎም በአደባባይ በጉዱማሌ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቅቋል ብለዋል።
ቀኑን ማስታወቅና ወዘተ እንዲሁም የበዓሉ ቅድመ ዝግጅት ቅቤ በማጠራቀም፣ የተጣሉትን የማስታረቅ፣ የከብቶች የግጦሽ ሳር ማዘጋጀትና የመሳሰሉ ልዩ ልዩ ክንውኖችን በቤተሰብ ደረጃ ይደረጋሉ ብለዋል።
የፊቼ ጫምባላላ በዓል የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኒስኮ የተመዘገበ የማይዳሰስ ቅርስ ነው ያሉት ኃላፊው በዓሉን ለመታደም ከተለያዩ ሀገራት ለሚመጡ ቱሪስቶችና ለባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት ይሰጣል። ፊቼ ጫምባላላ በውስጡ የያዛቸው እሴቶች በመኖሩ ይሄንንም የሚገልጽ የፓናል ውይይት በፊቼ ቀን ይካሄዳል ብለዋል።
የክልሉ መንግሥት በኩል ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ እንደሆነ በመግለፅ ህዝቡ በዓሉን ያለ አንዳች ችግር እንዲያከብር የተለያዩ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሥራውን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ኃላፊው መግለፃቸውን ከሲዳማ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
መረጃ ያመለክታል።
ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሴቶች የሚሳተፉበት የውይይት መድረክ እንደሚያካሂድ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አሰታወቀ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፓርቲው ባከናወነው አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ያስተላለፋቸውን ውሳኔዎችና ምግቤን ከጓሮዬ በሚል ከሁለት ሚሊዮን በላይ ሴቶች የሚሳተፉበት ንቅናቄ ከሚያዚያ 8/8/2014 አስከ 25/8/2014 ዓ.ም እንደሚያከነውን አስታወቀ።
ውይይቱ የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ተሳትፎ፤ በቀጣይ ለሚደረገው የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ አንደኛ መደበኛ ጉባኤ እንደ ግበዓት እንደሚያገለግል የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ሀላፊ ወ/ሮ መብራት ባጫ ተናግረዋል።
በዕለቱ ምግቤን ከጓሮዬ ንቅናቄ በ21 ዞኖች፣19 ከተሞችና በ312 ወረዳዎች እንደሚካሄድ ሀላፊዋ ገልፀዋል።
ለመርሀ ግብሮቹ መሳካት ባለድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ ቀና ትብብር እንዲያደርግ ወ/ሮ መብራት ጥሪ አቅርበዋል።
የመርሀ ግብሮቹ ማስጀመሪያ ስነስረዓት ሚያዚያ ስምንት ሚያዚያ 8/8/2014 ዓ ም በገላን ከተማ እንደሚካሄድ የኦቢኤን ዘገባ ያመለክታል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼️
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️