የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ክፍል ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ ተገለጸ
*******
(ኢ ፕ ድ)
በአሸባሪው ህወሓት ምክንያት ውድመት ደርሶበት የነበረው የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከረጂ ድርጅቶ በተገኘ ድጋፍ የቀዶ ጥገና አገልግሎት ክፍሉከነገ ጀምሮ ወደ ስራ እንደሚገባ ተገለጸ።
የሆስፒታሉ ስራ አሰኪያጅ ዶክተር ሀይማኖት አየለ ለፋና እንደተናገሩት፥ ሆስፒታሉ ከዚህ በፌት 8 የሚደርሱ የቀዶ ጥገና ማሽነሪዎች የነበሩት ቢሆንም ቡድኑ ባደረሰው ጥቃት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።
የቀዶ ጥገና ክፍሉ አስፈላጊነት ላቅ ያለ መሆኑን የገለጹት ስራ አስኪያጇ ሰዎች ለሰዎች ድርጅት 5 ሚሊየን እንዱሁም ዮ ኤስ ኤይድ ትራንስፎርም የተባሉ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ባደረጉት ድጋፍ አሁን ላይ 7 ማሸነሪዎች የገጠማ ሰራቸው ተጠናቆ ከነገ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ብለዋል።
አሁን ላይ ስራ የሚጀምረው የቀዶ ጥገና ክፍሉ ከዚህ በፌት አገልግሎት ይሰጥበት ከነበረው በተሻለ መልኩ የተደራጀ መሆኑንም ገልጸዋል።
ሆስፒታሉ በመልሶ ግንባታ ሂደቱ በተሻለ መንገድ እየተገነባ ነው ያሉት ስራ አስኪያጇ የተገልጋዮች ማረፊያ ግንባታም እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በመልሶ ግንባታ ሂደቱ ረጂ ድርጅቶች እና ማህበረሰቡ እያደረገ ያለውን ጥረት ያደነቁት ስራ አስኪያጇ የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ከአምራች ኢንዱስትሪው ከ390 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለፀ
*******
(ኢ ፕ ድ)
ለአምራች ኢንዱስትሪው ትኩረት በመስጠት አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በመሳብ፣ ነባሮቹን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተሻለ የሀገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እየተሠራ መሆኑን የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ።
በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከአምራች ኢንዱስትሪው ምርት ለውጪ ገበያ በማቅረብ 390 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል። የእቅዱንም 87 በመቶ መፈፀሙን ነው የተገለጸው።
በዘርፉ ያሉ ችግሮችን መቅረፍ እና ምቹ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ሀገሪቷ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ለማሳደግ የሚመለከታቸው አካላት በትጋት ሊሠሩ ይገባልም ብለዋል።
የኢትዮጵያን እናምርት በሚል መሪ ሐሳብ የሌሎች ውጤታማ ሀገራት ተሞክሮ ተቀምሮበት አምራች ኢንዱስትሪው ተወዳዳሪና ውጤታማ ለማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ሚኒስትሩ መናገራቸውን የአሚኮ ዘገባ ያመለክታል።
የፌዴራል እና የክልሎች የሥራ ኀላፊዎች በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ ነባር ኢንቨስትመንቶችን ጎብኝተዋል፡፡

ምክር ቤቱ አገራዊ ምክክሩ አካታችና ግልጽ እንዲሆን በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አሳሰበ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
አገራዊ ምክክሩ አካታችና ግልጽ ሆኖ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘንድ ቅቡልነት እንዲኖረው በትኩረት መሥራት እንደሚገባ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አሳሰበ።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሔል ባፌ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አገራዊ ምክክሩ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣውን ችግር በመፍታት የሁሉም ነገር መፍትሔ ይሆናል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል። በመሆኑም ሂደቱ ግልጽና አካታች ሆኖ በሁሉም ባለድርሻ አካላት ዘንድ ቅቡልነት እንዲያገኝ መሥራት ይገባል ።
አገራዊ ምክክሩ ገና ጅምር ዝግጅት ላይ ይገኛል ያሉት ዶክተር ራሔል፤ የተጠበቀውን ውጤት እንዲያመጣ ከአሁን ጀምሮ ለሁሉም ግልጽ ሆኖ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በንቃት የሚሳተፉበት እንዲሆን መሠራት እንዳለበት
https://www.press.et/?p=71094

በኢትዮጵያና በጎረቤት አገራት መካከል ያለው የነዳጅ ዋጋ ልዩነት ሕገወጥ ንግዱን እያባበሰው መሆኑ ተገለጸ
****************
(ኢ ፕ ድ)
በአሁኑ ወቅት ነዳጅ በኢትዮጵያ የሚሸጥበት እና በጎረቤት አገራት የሚሸጥበት ዋጋ ልዩነት የተጋነነ መሆኑ ሕገወጥ ንግዱን እንዳባባሰው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ገለፀ።
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታደሰ ኃይለማርያም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ መንግሥት የነዳጅ ዋጋን ከጎረቤት አገራት የነዳጅ መሸጫ ዋጋ ያለው የተጋነነ ልዩነት ባለማጥበቡ ምክንያት አገር ውስጥ በተሰገሰጉ ሕገወጥ ነጋዴዎች አማካኝነት ከአገር በሚወጡና ሕገወጥ ንግዱ ተባብሷል።
በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ከተሞች ነዳጅ በየሥርቻው ሊሸጥ የበቃው ነዳጅ በተገቢው የዋጋ ተመን እንዲሸጥ ባለመደረጉ ነው ሲሉ
https://www.press.et/?p=71097

የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት በክልሉ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ናቸው
*************************
(ኢ ፕ ድ)
የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት በክልሉ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንደሆነ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል መንግስት አስታወቀ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት; ከክልሉ ነዋሪዎች ጋር በቅርቡ በተደረገው ውይይት ከተነሱ የሕዝብ ጥቄዎች አንዱ የኑሮ ውድነት ነው። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ኅብረተሰቡን በማደራጀት ሸቀጦችንና ምርቶች የፍጆታ እቃዎች በክልሉ ዋና ዋና ከተሞች በኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል እንዲቀርቡ የማድረግ ሥራ መጀመሩን የጠቆሙት ርዕሰ መስተዳድሩ፤በሚቀጥለው የምርት ዘመን ምግብ ነክ ምርቶች ላይ እጥረት እንዳይገጥም ከወዲሁ የግብርና ሥራዎች በተለየ ትኩረት
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ
https://www.press.et/?p=71101

የሸቀጦች ዋጋ ላይ እየታየ ያለው የዋጋ ጭማሪ የሸማቾችን የመግዛት አቅም ፈትኗል
****************
(ኢ ፕ ድ)
በየጊዜው እየጨመረ በመጣው የመሠረታዊ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ የመግዛት አቅማቸውን እየተፈታተነ መሆኑን ሸማቾች ተናገሩ። መንግሥት ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት መሠረታዊ በሆኑ ሸቀጦች ላይ የአጭር ጊዜ የዋጋ ተመን እንዲያወጣ ተጠየቀ።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር ሸማቾችንና ነጋዴዎችን በጉዳዩ ላይ አነጋግሯል፤ አስተያየታቸውን የሰጡት የአዲስ አበባ ነዋሪ ወይዘሮ ደስታ ደበሌ እንደሚሉት በመሠረታዊ የሸቀጦች ዋጋ ላይ በየጊዜው ከፍተኛ ጭማሪ እየታየ ነው። ይህ መሆኑም ምርቶችን የመግዛት አቅማቸው ላይ ጫና ፈጥሯል።
ከአንድ ወር በፊት 105 ብር የነበረው የአገር ውስጥ ምስር በአሁኑ ጊዜ 130 ብር ገብቷል፤ 95 ብር የነበረው ከውጭ የገባው ምስር ደግሞ ከ100 ብር በላይ እየተሸጠ ስለመሆኑ መታዘባቸውን ተናግረዋል። ቡና በኪሎ እስከ 400 ብር፣ ዘይት አምስት ሊትር ደግሞ 900 ብር መሸመታቸውን ተናግረዋል።
ለመሠረታዊ የሸቀጦች ዋጋ ጭማሪ ከነጋዴዎች በኩል የሚሰጠው ምላሽ ከአከፋፋዮች ጭማሪ በማሳየቱና እቃ ስለማይገባ የሚል ቢሆንም በአገር ውስጥ
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጠቀሙ
https://www.press.et/?p=71104

ከኢድ እስከ ኢድ መርሐ ግብር ላይ በአማራና አፋር በጦርነቱ የተጎዱ መስጅዶችን የማስጎብኘት ዕቅድ ተይዟል
*************
(ኢ ፕ ድ)
ከኢድ እስከ ኢድ በተሰኘው መርሐ ግብር በአማራና አፋር ክልሎች በጦርነቱ የተጎዱ መስጅዶችንና አካባቢዎችን የማስጎብኘት ዕቅድ መያዙን የከኢድ እስከ ኢድ አገራዊ ጥሪ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ።
በጦርነቱ ምክንያት ውድመት የደረሰባቸውን መስጂዶች የማስጎብኘትና ከዲያስፖራው ማኅበረሰብ ጋር የመልሶ ማቋቋም ዕቅድ እንዳለም አስተባባሪ ኮሚቴው ገልጿል።
የአስተባባሪ ኮሚቴው አባል ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በኢድ እስከ ኢድ የተሰኘውን አገራዊ ጥሪ ተከትለው ወደ አገር ቤት የሚመጡ ዳያስፖራዎች በአማራና አፋር አካባቢዎች በጦርነቱ የተጎዱ የተመረጡ ስፍራዎችንና መስጂዶችን እንዲጎበኙ ይደረጋል።
የጉብኝት መርሐ ግብሮቹ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች መካከል በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር፤ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እንዲሁም በአፋር ክልል የተለያዩ ዞኖች
https://www.press.et/?p=71111

አፓርታማዎችን በሳምንት የሚያጠናቅቅ የፈጠራ ውጤት ይዞ በፋይናንስ የሚፈተነው ወጣት
****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ 60 በመቶ ያህሉን ዋና ዋና የግንባታ ዕቃዎቿን ከውጭ አገራት ነው የምታስገባው። ለዚህም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪ ታደርጋለች። ይህን የውጭ ምንዛሪ ለማደን በአገር ልጆች የሚሠሩ የፈጠራ ውጤቶችን ከመጠቀም ይልቅ ከውጭ የሚመጡ ግብዓቶችን መጠቀም የተለመደ ተግባር ሁኗል።
በዚህ ምክንያትም የአገር ውስጥ የፈጠራ ባለቤቶችን ደግፎ ለቁም ነገርና ለውጤት ማብቃት አልተለመደም። ወንድማገኝ ገለታ ከእነዚያ የፈጠራ ባለቤቶች መካከል አንዱ ነው። የዜጎችን ሕይወት ይቀይራሉ፤ የኑሯቸውንም ሁኔታ ያሻሽላሉ ያላቸውን የተለያዩ ፈጠራዎችን
https://www.press.et/?p=71112

‘'ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ
****
(ኢ ፕ ድ)
ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ።
ዋይት ሃውስ ፊት ለፊት በተካሄደው ሰልፍ “ማዕቀብ ይገድላል”፣”ጸረ-ኢትዮጵያ፣ኤርትራና አሜሪካ የሆኑትን ረቂቅ ሕጎች እንቃወማለን”፣”‘ኤችአር 6600’ እና ኤስ 3199’ ይሰረዙ” እና ”ፍላጎትን በኃይል ለመጫን የሚደረግ ማንኛውም ድርጊት እንቃወማለን አንቀበልም” የሚሉ መልዕክቶች መተላለፋቸው ተገልጿል።
ረቂቅ ሕጎቹ ኢትዮጵያን እንዲሁም የኢትዮጵያና አሜሪካን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚጎዱ በመሆናቸው በፍጥነት መሰረዝ አለባቸው የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ላይ መሰማቱን ተገልጿል።
ሕጎቹ በኢትዮጵያ ሰላምን ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ጥረት እውቅና ያልሰጠና የሰላም ሂደቱን አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር ነው ብለዋል ሰልፈኞቹ።
‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን በመቃወም በዋይት ሃውስ ፊት ለፊት የሚካሄደው ሰልፍ በቋሚነት በየሳምንቱ እንደሚከናወን የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበር የዋሺንግተን ግብረ ኃይል አስታውቋል።
በተያዘዘ ዜና ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ ከነገ በስቲያ በኒው ጀርዚ ግዛት ይካሄዳል።
ሰልፉ የ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕግ አርቃቂ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ(ኒው ጀርዚ) ቢሮ ፊት ለፊት እንደሚካሄድ ኢዜአ ከኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ተስፋ ለኢትዮጵያ ድርጅት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአሜሪካ የኮንግረስ አባል ቶም ማሊኖውስኪ (ኒውጀርሲ) ዋና አርቃቂነት፣ በያንግ ኪም (ካሊፎርኒያ)፣ ግሪጎሪ ሚክስ (ኒው ዮርክ)፣ ዴቪድ ሲሲሊን (ሮድ አይላንድስ)፣ ብራድ ሼርማን(ካሊፎርኒያ) እና ማይክል ማካውል (ቴክሳስ) ደጋፊነት የተዘጋጀው ‘ኢትዮጵያ ስታብላይዜሽን ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ አክት’ ወይም ኤችአር 6600 ረቂቅ ሕግ የኮንግረሱ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ተወያይቶበት ለኮንግረሱ መምራቱ የሚታወስ ነው።
የ‘ኤችአር 6600’ ተጓዳኝ ወይም አጋዥ (ኮምፓኒየን ቢል) የሆነው የኢትዮጵያ ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ ፕሮሞሽን አክት ኦፍ 2022’ ወይም ‘ኤስ.3199’ በአሜሪካ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ (ኒው ጀርዚ) ዋና አርቃቂነት፣ በሴናተር ጀምስ ሪስች (ኢዳሆ)፣ በሴናተር ክሪስ ኩንስ (ዴልዌር) እና በሴናተር ቶም ቲሊስ (ኖርዝ ካሮላይና) ደጋፊነት የተዘጋጀ ሲሆን፤ሴኔቱ እ.አ.አ በ2022 ሊመለከታቸው በጊዜ ሰሌዳው ከያዛቸው ረቂቅ ሕጎች አንዱ ሆኖ እንዲካተት መወሰኑ ይታወሳል።
በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ረቂቅ ሕጎቹ በሕግ አውጪው አካል ድምጽ ተሰጥቶባቸው እንዳይጸድቁ ለማድረግ ሴናተሮችና የኮንግረስ አባላትን በማናገር፣ደብዳቤ በመጻፍ፣ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ፣ፊርማ በማሰባሰብና በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘመቻ በማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
https://twitter.com/PressEthio

ከታንዛኒያ ብሔራዊ ወታደራዊ ኮሌጅ የመጡ መኮንኖች በኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገርት የተውጣጡና በታንዛኒያ ወታደራዊ ኮሌጅ ውስጥ በትምህርት ላይ የሚገኙት ወታደራዊ መኮንኖች በመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ በዋር ኮሌጅ፣ በሰላም ማስከበር ማዕከል እና በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ነው ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ።
የየተቋማቱ አመራሮችም ለትምህርታዊ ጥናት ቡድኑ ገለፃ አድርገዋል።
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡትና በታንዛኒያው ወታደራዊ ኮሌጅ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩት ወታደራዊ መኮንኖች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ውጪ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጄነራል ሜ/ጀ ተሾመ ገመቹ ናቸው።
ጀነራል መኮንኑ ኢትዮጵያ ለሰላምና ደህንነት በቀጠናው ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አውስተው ኢትዮጵያ በስትራተጂክ ደረጃ እያከናወነችው ያለው ተግባር ለጥናት ቡድኑ ትልቅ ግብዓት ይሆናል ብለዋል።
አፍሪካ የራሷን ሰላም በራሷ መጠበቅ አለባት ለዚህም ሲባል በየቀጠናው ያለውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ አፍሪካውያን ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ በአንድነት መቆም ይገባናል ያሉት ደግሞ የጥናት ቡድኑን የሚመሩት ብ/ጀኔራል ቼርለስቲኖ ኤሊያስ ናቸው።
የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ኃላፊ ብ/ጀኔራል ይታያል ገላው የጥናት ቡድኑ ኢትዮጵያን መርጦ መምጣቱ አሁን ላይ በተቋማችን ደረጃ ለትምህርት የተሰጠው ትኩረት አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
ቡድኑ በመከላከያ በደህንነት በስልጠና እና በቴክኖሎጂ ሽግግር የቀጠናው ሀገራት ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ ለማጠናከር እየሰራ ነው።
ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ቀደም ሲል በወታደራዊ ጉዳዮች አብረው ለመስራት መስማማታቸው ይታወሳል ሲል የሀገር የሀገር መካለከያ ሚኒስቴር በማህበራዊ ገጹ ዘግቧል።