ከኢድ እስከ ኢድ መርሐ ግብር ላይ በአማራና አፋር በጦርነቱ የተጎዱ መስጅዶችን የማስጎብኘት ዕቅድ ተይዟል
*************
(ኢ ፕ ድ)
ከኢድ እስከ ኢድ በተሰኘው መርሐ ግብር በአማራና አፋር ክልሎች በጦርነቱ የተጎዱ መስጅዶችንና አካባቢዎችን የማስጎብኘት ዕቅድ መያዙን የከኢድ እስከ ኢድ አገራዊ ጥሪ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ።
በጦርነቱ ምክንያት ውድመት የደረሰባቸውን መስጂዶች የማስጎብኘትና ከዲያስፖራው ማኅበረሰብ ጋር የመልሶ ማቋቋም ዕቅድ እንዳለም አስተባባሪ ኮሚቴው ገልጿል።
የአስተባባሪ ኮሚቴው አባል ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ በኢድ እስከ ኢድ የተሰኘውን አገራዊ ጥሪ ተከትለው ወደ አገር ቤት የሚመጡ ዳያስፖራዎች በአማራና አፋር አካባቢዎች በጦርነቱ የተጎዱ የተመረጡ ስፍራዎችንና መስጂዶችን እንዲጎበኙ ይደረጋል።
የጉብኝት መርሐ ግብሮቹ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች መካከል በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር፤ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች እንዲሁም በአፋር ክልል የተለያዩ ዞኖች
https://www.press.et/?p=71111

አፓርታማዎችን በሳምንት የሚያጠናቅቅ የፈጠራ ውጤት ይዞ በፋይናንስ የሚፈተነው ወጣት
****************
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ በኮንስትራክሽን ዘርፍ 60 በመቶ ያህሉን ዋና ዋና የግንባታ ዕቃዎቿን ከውጭ አገራት ነው የምታስገባው። ለዚህም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪ ታደርጋለች። ይህን የውጭ ምንዛሪ ለማደን በአገር ልጆች የሚሠሩ የፈጠራ ውጤቶችን ከመጠቀም ይልቅ ከውጭ የሚመጡ ግብዓቶችን መጠቀም የተለመደ ተግባር ሁኗል።
በዚህ ምክንያትም የአገር ውስጥ የፈጠራ ባለቤቶችን ደግፎ ለቁም ነገርና ለውጤት ማብቃት አልተለመደም። ወንድማገኝ ገለታ ከእነዚያ የፈጠራ ባለቤቶች መካከል አንዱ ነው። የዜጎችን ሕይወት ይቀይራሉ፤ የኑሯቸውንም ሁኔታ ያሻሽላሉ ያላቸውን የተለያዩ ፈጠራዎችን
https://www.press.et/?p=71112

‘'ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ
****
(ኢ ፕ ድ)
ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ።
ዋይት ሃውስ ፊት ለፊት በተካሄደው ሰልፍ “ማዕቀብ ይገድላል”፣”ጸረ-ኢትዮጵያ፣ኤርትራና አሜሪካ የሆኑትን ረቂቅ ሕጎች እንቃወማለን”፣”‘ኤችአር 6600’ እና ኤስ 3199’ ይሰረዙ” እና ”ፍላጎትን በኃይል ለመጫን የሚደረግ ማንኛውም ድርጊት እንቃወማለን አንቀበልም” የሚሉ መልዕክቶች መተላለፋቸው ተገልጿል።
ረቂቅ ሕጎቹ ኢትዮጵያን እንዲሁም የኢትዮጵያና አሜሪካን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚጎዱ በመሆናቸው በፍጥነት መሰረዝ አለባቸው የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ላይ መሰማቱን ተገልጿል።
ሕጎቹ በኢትዮጵያ ሰላምን ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ጥረት እውቅና ያልሰጠና የሰላም ሂደቱን አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር ነው ብለዋል ሰልፈኞቹ።
‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን በመቃወም በዋይት ሃውስ ፊት ለፊት የሚካሄደው ሰልፍ በቋሚነት በየሳምንቱ እንደሚከናወን የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበር የዋሺንግተን ግብረ ኃይል አስታውቋል።
በተያዘዘ ዜና ‘ኤችአር 6600’ እና ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ ከነገ በስቲያ በኒው ጀርዚ ግዛት ይካሄዳል።
ሰልፉ የ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕግ አርቃቂ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ(ኒው ጀርዚ) ቢሮ ፊት ለፊት እንደሚካሄድ ኢዜአ ከኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ተስፋ ለኢትዮጵያ ድርጅት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአሜሪካ የኮንግረስ አባል ቶም ማሊኖውስኪ (ኒውጀርሲ) ዋና አርቃቂነት፣ በያንግ ኪም (ካሊፎርኒያ)፣ ግሪጎሪ ሚክስ (ኒው ዮርክ)፣ ዴቪድ ሲሲሊን (ሮድ አይላንድስ)፣ ብራድ ሼርማን(ካሊፎርኒያ) እና ማይክል ማካውል (ቴክሳስ) ደጋፊነት የተዘጋጀው ‘ኢትዮጵያ ስታብላይዜሽን ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ አክት’ ወይም ኤችአር 6600 ረቂቅ ሕግ የኮንግረሱ የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ተወያይቶበት ለኮንግረሱ መምራቱ የሚታወስ ነው።
የ‘ኤችአር 6600’ ተጓዳኝ ወይም አጋዥ (ኮምፓኒየን ቢል) የሆነው የኢትዮጵያ ፒስ ኤንድ ዴሞክራሲ ፕሮሞሽን አክት ኦፍ 2022’ ወይም ‘ኤስ.3199’ በአሜሪካ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ (ኒው ጀርዚ) ዋና አርቃቂነት፣ በሴናተር ጀምስ ሪስች (ኢዳሆ)፣ በሴናተር ክሪስ ኩንስ (ዴልዌር) እና በሴናተር ቶም ቲሊስ (ኖርዝ ካሮላይና) ደጋፊነት የተዘጋጀ ሲሆን፤ሴኔቱ እ.አ.አ በ2022 ሊመለከታቸው በጊዜ ሰሌዳው ከያዛቸው ረቂቅ ሕጎች አንዱ ሆኖ እንዲካተት መወሰኑ ይታወሳል።
በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ረቂቅ ሕጎቹ በሕግ አውጪው አካል ድምጽ ተሰጥቶባቸው እንዳይጸድቁ ለማድረግ ሴናተሮችና የኮንግረስ አባላትን በማናገር፣ደብዳቤ በመጻፍ፣ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ፣ፊርማ በማሰባሰብና በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘመቻ በማድረግ ጥረት እያደረጉ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
https://twitter.com/PressEthio

ከታንዛኒያ ብሔራዊ ወታደራዊ ኮሌጅ የመጡ መኮንኖች በኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ
****************
(ኢ ፕ ድ)
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገርት የተውጣጡና በታንዛኒያ ወታደራዊ ኮሌጅ ውስጥ በትምህርት ላይ የሚገኙት ወታደራዊ መኮንኖች በመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ በዋር ኮሌጅ፣ በሰላም ማስከበር ማዕከል እና በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ነው ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ።
የየተቋማቱ አመራሮችም ለትምህርታዊ ጥናት ቡድኑ ገለፃ አድርገዋል።
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡትና በታንዛኒያው ወታደራዊ ኮሌጅ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩት ወታደራዊ መኮንኖች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ውጪ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጄነራል ሜ/ጀ ተሾመ ገመቹ ናቸው።
ጀነራል መኮንኑ ኢትዮጵያ ለሰላምና ደህንነት በቀጠናው ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አውስተው ኢትዮጵያ በስትራተጂክ ደረጃ እያከናወነችው ያለው ተግባር ለጥናት ቡድኑ ትልቅ ግብዓት ይሆናል ብለዋል።
አፍሪካ የራሷን ሰላም በራሷ መጠበቅ አለባት ለዚህም ሲባል በየቀጠናው ያለውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ አፍሪካውያን ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ በአንድነት መቆም ይገባናል ያሉት ደግሞ የጥናት ቡድኑን የሚመሩት ብ/ጀኔራል ቼርለስቲኖ ኤሊያስ ናቸው።
የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ኃላፊ ብ/ጀኔራል ይታያል ገላው የጥናት ቡድኑ ኢትዮጵያን መርጦ መምጣቱ አሁን ላይ በተቋማችን ደረጃ ለትምህርት የተሰጠው ትኩረት አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
ቡድኑ በመከላከያ በደህንነት በስልጠና እና በቴክኖሎጂ ሽግግር የቀጠናው ሀገራት ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ ለማጠናከር እየሰራ ነው።
ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ቀደም ሲል በወታደራዊ ጉዳዮች አብረው ለመስራት መስማማታቸው ይታወሳል ሲል የሀገር የሀገር መካለከያ ሚኒስቴር በማህበራዊ ገጹ ዘግቧል።

ዛሬ ከሳዑዲ አረቢያ በተደረገው ሁለተኛ በረራ 354 ዜጎች ተመለሱ
*************
(ኢ ፕ ድ)
ዛሬ ከጂዳ በተደረገው ሁለተኛ በረራ 354 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ናቸው።
ተመላሾች አዲስ አበባ ሲገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
መንግሥት በሳዑዲ አረቢያ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራና 16 መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን በአባልነት ያቀፈ ብሔራዊ ኮሚቴ በማዋቀር 102 ሺህ ዜጎችን ወደ ሃገር ለመመለስ በማቀድ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል ።
*************
(ኢ ፕ ድ)
ዛሬ ከጂዳ በተደረገው ሁለተኛ በረራ 354 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ተመላሾች ሁሉም ወንዶች ናቸው።
ተመላሾች አዲስ አበባ ሲገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰራተኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
መንግሥት በሳዑዲ አረቢያ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራና 16 መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን በአባልነት ያቀፈ ብሔራዊ ኮሚቴ በማዋቀር 102 ሺህ ዜጎችን ወደ ሃገር ለመመለስ በማቀድ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል ።
ከታንዛኒያ ብሔራዊ ወታደራዊ ኮሌጅ የመጡ መኮንኖች በኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ
************
(ኢ ፕ ድ)
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገርት የተውጣጡና በታንዛኒያ ወታደራዊ ኮሌጅ ውስጥ በትምህርት ላይ የሚገኙት ወታደራዊ መኮንኖች በመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል፣ በዋር ኮሌጅ፣ በሰላም ማስከበር ማዕከል እና በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ነው ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ።
የየተቋማቱ አመራሮችም ለትምህርታዊ ጥናት ቡድኑ ገለፃ አድርገዋል።
ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ለተውጣጡትና በታንዛኒያው ወታደራዊ ኮሌጅ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለነበሩት ወታደራዊ መኮንኖች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የመከላከያ ውጪ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጄነራል ሜ/ጀ ተሾመ ገመቹ ናቸው።
ጀነራል መኮንኑ ኢትዮጵያ ለሰላምና ደህንነት በቀጠናው ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አውስተው ኢትዮጵያ በስትራተጂክ ደረጃ እያከናወነችው ያለው ተግባር ለጥናት ቡድኑ ትልቅ ግብዓት ይሆናል ብለዋል።
አፍሪካ የራሷን ሰላም በራሷ መጠበቅ አለባት ለዚህም ሲባል በየቀጠናው ያለውን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ አፍሪካውያን ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ በአንድነት መቆም ይገባናል ያሉት ደግሞ የጥናት ቡድኑን የሚመሩት ብ/ጀኔራል ቼርለስቲኖ ኤሊያስ ናቸው።
የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ኃላፊ ብ/ጀኔራል ይታያል ገላው የጥናት ቡድኑ ኢትዮጵያን መርጦ መምጣቱ አሁን ላይ በተቋማችን ደረጃ ለትምህርት የተሰጠው ትኩረት አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።
ቡድኑ በመከላከያ በደህንነት በስልጠና እና በቴክኖሎጂ ሽግግር የቀጠናው ሀገራት ያላቸውን ልምድና ተሞክሮ ለማጠናከር እየሰራ ነው።
ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ ቀደም ሲል በወታደራዊ ጉዳዮች አብረው ለመስራት መስማማታቸው ይታወሳል ሲል የሀገር የሀገር መካለከያ ሚኒስቴር በማህበራዊ ገጹ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ትዊተር 👇

አምባሳደር ሀሰን ታጁ በኩዌት ከጊዜያዊ የማቆያ ማዕከላት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተነጋገሩ
👉 ከ100 በላይ ሰነድ አልባ ዜጎች ወደ ሀገራቸዉ እንዲመለሱ ተደረገ፣
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በኩዌት የኢትዮጵያ ባለሙሉስልጣን አምባሳደር ሀሰን ታጁ በጊዜያዊ ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱም ከጊዚያዊው ማቆያዉ ሀላፊ ኮሎኔል ሀሚድ ሙሀመድ አልዐዝሚ፣ ከዲፖርትሽን ክፍል ሀላፊ ኮሎኔል ወሊድ ዐሊ ጁምዐ እና ከሌሎች የስራ ሀላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
አምባሳደር ሀሰን ታጁ በማቆያ የሚገኙ ዜጎች አያያዝ መልካም መሆኑን ጠቅሰው፣ ባለፉት 6 ወራት ለዜጎቻችን ስለተደረገላቸዉ እንክብካቤ፣ እንደዚሁም የማቆያዎቹ ሀላፊዎች ከኤምባሲዉ ጋር ሁልየም ስለሚያሳዩት ቀና ትብብር የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።
ባለፉት 3 ሳምንታት በኩዌት የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተደረገ ጥረት በየማቆያ ጣቢያዎች የነበሩ ከ100 በላይ ሰነድ አልባ ዜጎች ሰነዳቸዉ ተሟልቶ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር የምርምር ውጤቶች የገንዘብ ድጋፍ ውድድር እየተካሄደ ነው
*******************
(ኢ ፕ ድ)
የዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር የምርምር ውጤቶች ወደ ገበያ የሚገቡበት የገንዘብ ድጋፍ ውድድር እየተካሄደ ነው::
የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም እና የእንግሊዝ ተራድኦ ድርጅት ድጋፍ የሚያደርጉለት ኢኖቬሽን ለልማት ፕሮግራም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ተግባራዊ እየተደረገ ነው።
በዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ማዕቀፍ ውስጥ የኢንደስትሪውን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የምርምር ውጤቶችን ወደ ገበያ ለማስገባት የሚያስችላቸውን የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ያስችል ዘንድ የመጨረሻውን ውድድር እየተካሄደ ነው
በውድድሩ ከሀያ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡት አርባ ዘጠኝ ውጤታማ፣ የተጠናቀቁና ወደ ገበያ ሊገቡ የሚችሉ የምርምር ውጤቶች ቀርበዋል፡፡
በመጀመሪያው ዙር ውድድር ያለፉ አስራ አንድ ፕሮጀክቶች የመጨረሽውን ውድድር እያካሄዱ ነው፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሀገራዊ የምርምር ስራዎች ወደ ገበያ ገብተው የኢንዱስትሪውን ችግር በመፍታት ምርታማነትን የሚጨምሩ እንዲሆኑ ለማስቻል ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ ነው ተብሏል። የምርምር ውጤቶችን ወደ ገበያ ማስገቢያ የድጋፍ ስርዓት አንዱ ነው።
በቀጣይም እንዲህ አይነት ድጋፎች በሌሎች ከፍተኛ የትምህርትና የምርምር ተቋማት ተጠናከሮ እንደሚቀጥል ሚኒስቴር መስሪያቤቱ አስታውቋል።