የሲቪል ማህብረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የእውቅና እና የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር እያካሄደ ነው
****
(ኢ.ፕ.ድ)
የሲቪል ማህብረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣኑ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት እውቅና የመስጠትና የሁለተኛ ዙር የድጋፍ ማስባሰቢያ መርሃግብር እያካሄደ ነው
በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አስተባባሪነት በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ430 ሚሊዮን ብር በላይ የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዴልቦ በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል በተከሰተው ጦርነት ለጐዱና በኦሮሚያና አንዳንድ አካባቢዎች በድርቅ ለተጐዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ በተደረገው ጥሪ እስካሁን 413 ሚሊዮን ብር የሚገመት የአይነትና 17 ሚሊዮን ጥሬ ገንዘብ ድጋፍ በተቋሙ አማካአማካኝነትት ተደርጓል።
ለጥፋት የሚነሱ እጆች እንዳሉ ሁሉ እልፍ የሆኑ ለበጐ የሚዘረጉ እጆች አሉ። ለዚህም በተደረገው ጥሪ መሰረት ድጋፍ ያደረጉ አካላት ማሳያ ናቸው ብለዋል።
የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ጸጋ በበኩላቸው፤ በጦርነቱና በድርቅ ለተጐዱ ወገኖች ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።
በጦርነቱ ወቅት በታጣቂዎች የተደፈሩ፣ ለከፋ ስነልቦና ጉዳት የተዳረጉ እና የተፈናቀሉ ወገኖች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው፤ ጋን በጠጠር ይደገፋል እንደሚባለው የተጐዱትን ወገኖች ወገኖቻችን ናቸውና
ተከታታይ ድጋፍ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
በዚህ መርሀግብር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የሚቀርብ ሲሆን ድጋፍ ላደረጉ አካላት የምስጋናና የእውቅና እንዲሁም የሁለተኛ ዙር የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሃግብር የማስጀመር ቃል የማስገባት መርሃግብር እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል።
በሞገስ ተስፋ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

በአሸባሪው ህወሓት ከወደሙ 42 ሆስፒታሎች 36 ያህሉ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ መመለሳቸውን ጤና ሚኒስቴር ገለፀ
******
(ኢ ፕ ድ)
በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ከወደሙ 42 ሆስፒታሎች 36 ያህሉ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ መመለሳቸውን ጤና ሚኒስቴር አሰታወቀ።
በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዔታ ዶክተር አየለ ተሾመ በሰጡት መግለጫ በአሸባሪው ቡድን ከወደሙ 42 ሆስፒታሎች 36 ያህሉ ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ መመለሳቸውን አሳውቀዋል።
የወደሙ ሆስፒታሎች 40 ያህሉ በአማራ ክልል 2ቱ ደግሞ በአፋር ክልል እንደሚገኙ ሚኒስትር ዴዔታ ተናግረዋል።
ከወደሙት ሆስፒታሎች 36 ያህሉ ጥገና ተደርጎላቸውና የህክምና መሣሪያዎቻቸው ተተክተው ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ገብተዋል።
ስድስት ያህል ሆስፒታሎች ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በመሆናቸው ወደ ነበሩበት ለመመለስ ያልተቻለ መሆኑን በመግለጫው ተመላቷል።
በተጨማሪም ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ በክልሎቹ የሚገኙ የጤና ተቋማት በጥፋት ቡድኑ ወድመዋል ተብሏል።
ከወደሙት ጤና ተቋማት 87 በመቶ ያህሉም ወደ ሥራ መመለሳቸው ተገልጸዋል።
በውብሸት ሰንደቁ

የፋሲካ በዓል የገበያ ዋጋ በአዲስ አበባ
******
(ኢ ፕ ድ)
የፋሲካ በዓል ገበያ የተለያዩ የአዲስ አበባ ቦታዎች አንዳንድ ምርቶች ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ይታያል::በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ ምርቶች ዋጋ ላይ ይህ ነው የሚባል ጭማሪ እንዳልታየ ሸማቾች ነግረውናል።
ወይዘሮ ሶስና ሙሉጌታ በሾላ ገበያ ለበዓሉ ማክበሪያ የሚሆኑ ምርቶችን ሲገዙ ካገኘናቸው ሸማቾች አንዱ ናቸው::
ወይዘሮዋን ዶሮና እንቁላል ሲገዙ ነው ያገኘናቸው:: ዘንድሮ የዶሮ ዋጋ ካሰቡት በላይ ጭማሪ አሳይቷል ይላሉ:: ከቤታቸው ወደ ገበያ ሲወጡ አንድ ዶሮ ከ400 እስከ 500 ብር ለመግዛት አስበው ቢሆንም፤ ገበያ ሲደርሱ ዶሮ ባሰቡት ዋጋ ማግኘት እንዳልቻሉ ነግረውናል::
ሀገሪቷ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የምርቶች ዋጋ ሊጨምር እንደሚችል አስበው የነበረ ቢሆንም፤ በዶሮ ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ አይነት ያጋጥማል ብለው አልጠበቁም:: መካከለኛ ዶሮ ከ700 እስከ 800 ብር እየተሸጠ ነው:: በገበያው ውስጥ ዶሮ በብዛት ቢኖርም ዋጋው እንዲህ የተወደደበት ምክንያት እንዳልገባቸው ገልጸዋል::
በውድ ዋጋም ቢሆን መካከለኛ ዶሮ ገዝተዋል:: ዶሮ ያለ ሽንኩርት መስራት እንደማይታሰብ የጠቆሙት ወይዘሮ ሶስና፤ የሽንኩርት ዋጋ ላይም መጠነኛ ጭማሪ መታየቱን..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71330

ለበዓላቱ ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት እያከፋፈለ መሆኑን የፊቤላ ዘይት ፋብሪካ አስታወቀ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
በመጪዎቹ የፋሲካ እና የኢድ አል ፈጥር በዓላት የዘይት እጥረት እንዳያጋጥም ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት እያከፋፈለ መሆኑን የፊቤላ ዘይት ፋብሪካ ገለጸ፡፡
የፋብሪካው ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ለመጪዎቹ የፋሲካ እና የኢድ በዓላት ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት እያከፋፈለ ነው፡፡
ድርጅቱ ለቀጣዮቹ በዓላት የምርት አቅርቦት እጥረት በገበያው እንዳይፈጠር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ ዘይት ለህብረተሰቡ በፍጥነት እንዲቀርብ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
በተለይ በእነዚህ ሁለት በዓላት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በበዓል ወቅት እንዳይቸገሩና የዘይት አቅርቦት እጥረት ገበያው ላይ እንዳይፈጠር ድርጅቱ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
እንደ አቶ በላይነህ ገለጻ፤ በዚህም በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ በሰባት ክልሎች እና በአንድ ከተማ አስተዳደር ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት ለህብረተሰቡ እንዲከፋፈል እየተደረገ ነው፡፡ የፋብሪካው ሠራተኞች በቀንና በምሽት እየሠሩ ነው። በየቀኑ ከ15 በላይ የዘይት ምርት የጫኑ ተሸከርካሪዎች ምርቱን እያጓጓዙ ይገኛሉ፡፡
በቀጣይም መንግሥት ዘይት ከወጭ እንዲገባ ለድርጅቱ የፈቀደውን የውጭ ምንዛሬ በመጠቀም ምርቱ ሳይቆራረጥ ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡
በየጊዜው አዋጭ የድፍድፍ ዘይት ዋጋን በማገናዘብ የዘይት ምርት በአገር ውስጥ ማምረት የጀመረው ፊቢላ የዘይት ፋብሪካ፤ በአምስት ዙር 116 ሺ ሜትሪክ ቶን ድፍድፍ ፓልም ዘይት ግዥ ፈጽሟል፡፡ በዚህም 75 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በማምረት ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መንግሥት በመደበው ኮታ መሰረት እየተከፋፈለ ነው ብለዋል፡፡
እንደ አገር ባለፉት ዓመታት ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዘይት ምርት ከውጭ ይገባ እንደነበር ያወሱት አቶ በላይነህ፤ ፋብሪካው ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት የቢዝነስ ጥናት በማድረግ ወደ ሥራ መግባቱን አንስተዋል፡፡
የፊቤላ የዘይት ፋብሪካ ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሆነው ሲሆን በ31 አከፋፋዮች አማካኝነት በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የዘይት ምርት ለህብረተሰቡ እየተሰራጨ ይገኛል ብለዋል፡፡
በጀማል ታመነ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመጋቢት ወር ብቻ ከ108 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል
👉 ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ780 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፤
👉 ግድቡ ከተጀመረ እስካሁን 16.5 ቢሊዮን ብር በላይ ከህዝብ ተሰብስቧል፣
********************************
(ኢ ፕ ድ)
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተያዘው የበጀት አመት መጋቢት ወር ብቻ 108 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ደግሞ ለግድቡ ግንባታ ከ780 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።
ከተሰበሰበው ብር ውስጥ 399 ሚሊዮን የሚሆነው ከሀገር ውስጥ ቦንድ ግዢና ልገሳ የተገኘ ሲሆን፤ 243 ሚሊዮን የሚሆነው ገንዘብ ደግሞ ከዲያስፖራ ቦንድ ግዢና ልገሳ መሆኑ ታውቋል።
የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ በሀገር ውስጥ ቦንድ ግዢና ልገሳ 14 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር፤ ከዲያስፖራ ቦንድ ግዢ፤ እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ልገሳ ደግሞ አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል ።
በተመሳሳይ በ8100 A አጭር የፅሁፍ መልዕክት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 128 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘው መረጃ ያሳያል።
በወይንሸት ካሳ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
👉 ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ780 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፤
👉 ግድቡ ከተጀመረ እስካሁን 16.5 ቢሊዮን ብር በላይ ከህዝብ ተሰብስቧል፣
********************************
(ኢ ፕ ድ)
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተያዘው የበጀት አመት መጋቢት ወር ብቻ 108 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ደግሞ ለግድቡ ግንባታ ከ780 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።
ከተሰበሰበው ብር ውስጥ 399 ሚሊዮን የሚሆነው ከሀገር ውስጥ ቦንድ ግዢና ልገሳ የተገኘ ሲሆን፤ 243 ሚሊዮን የሚሆነው ገንዘብ ደግሞ ከዲያስፖራ ቦንድ ግዢና ልገሳ መሆኑ ታውቋል።
የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ በሀገር ውስጥ ቦንድ ግዢና ልገሳ 14 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር፤ ከዲያስፖራ ቦንድ ግዢ፤ እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ልገሳ ደግሞ አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል ።
በተመሳሳይ በ8100 A አጭር የፅሁፍ መልዕክት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 128 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘው መረጃ ያሳያል።
በወይንሸት ካሳ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስሩ ከራሺያ ማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ዋና ሹም ኤቭጅኒ ፔትሮቭ ጋር በበየነ መረብ ውይይት አደረጉ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮ-ራሺያን የምጣኔ ሃብት፣ የሳይንቲፊክ፣ የቴክኒካልና የንግድ ትብብር ኢንተር-ገቨርንመንታል ኮሚሽንን በጋራ ሊቀመንበርነት የሚመሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና የማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ዋና ሹም ኤቭጅኒ ፔትሮቭ በበየነ መረብ ውይይት አደረጉ።
ኢትዮጵያና ራሺያ በዲፌንስ፣ በትምህርት፣ በኢነርጂ፣ በጤና፣ በንግድና ኢንቨስትመንት በትብብር ይሰራሉ።
ሰባተኛው ኢትዮ-ራሺያ ኢንተር-ገቨርንመንታል ኮሚሽን ውይይት ፒተርስበርግ ከተማ እ.አ.አ.በጥቅምት 2019 መካሄዱ ይታወቃል። ውይይቱም በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያሉትን የሁለትዮሽ የንግድ፣ የምጣኔ ሃብት፣ የሳይንቲፊክና የቴክኒካል ትብብሮችን ስለማጠናከር ነበር።
ኢትዮጵያና ራሺያ በትብብር ከሚሰሩባቸው ዘርፎች ውስጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የራሺያ መንግስት አቶሚክ ኢነርጂ ትብብር እ.አ.አ. በጥቅምት 2019 የተፈረመ ሲሆን በኒውክለር ኢነርጂ ስልጠና ለመስጠት በሚያዚያ 15/ 2021 እ.አ.አ. የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።