የፋሲካ በዓል የገበያ ዋጋ በአዲስ አበባ
******
(ኢ ፕ ድ)
የፋሲካ በዓል ገበያ የተለያዩ የአዲስ አበባ ቦታዎች አንዳንድ ምርቶች ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ይታያል::በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ ምርቶች ዋጋ ላይ ይህ ነው የሚባል ጭማሪ እንዳልታየ ሸማቾች ነግረውናል።
ወይዘሮ ሶስና ሙሉጌታ በሾላ ገበያ ለበዓሉ ማክበሪያ የሚሆኑ ምርቶችን ሲገዙ ካገኘናቸው ሸማቾች አንዱ ናቸው::
ወይዘሮዋን ዶሮና እንቁላል ሲገዙ ነው ያገኘናቸው:: ዘንድሮ የዶሮ ዋጋ ካሰቡት በላይ ጭማሪ አሳይቷል ይላሉ:: ከቤታቸው ወደ ገበያ ሲወጡ አንድ ዶሮ ከ400 እስከ 500 ብር ለመግዛት አስበው ቢሆንም፤ ገበያ ሲደርሱ ዶሮ ባሰቡት ዋጋ ማግኘት እንዳልቻሉ ነግረውናል::
ሀገሪቷ ካለችበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የምርቶች ዋጋ ሊጨምር እንደሚችል አስበው የነበረ ቢሆንም፤ በዶሮ ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ አይነት ያጋጥማል ብለው አልጠበቁም:: መካከለኛ ዶሮ ከ700 እስከ 800 ብር እየተሸጠ ነው:: በገበያው ውስጥ ዶሮ በብዛት ቢኖርም ዋጋው እንዲህ የተወደደበት ምክንያት እንዳልገባቸው ገልጸዋል::
በውድ ዋጋም ቢሆን መካከለኛ ዶሮ ገዝተዋል:: ዶሮ ያለ ሽንኩርት መስራት እንደማይታሰብ የጠቆሙት ወይዘሮ ሶስና፤ የሽንኩርት ዋጋ ላይም መጠነኛ ጭማሪ መታየቱን..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71330
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ለበዓላቱ ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት እያከፋፈለ መሆኑን የፊቤላ ዘይት ፋብሪካ አስታወቀ
***************
(ኢ.ፕ.ድ)
በመጪዎቹ የፋሲካ እና የኢድ አል ፈጥር በዓላት የዘይት እጥረት እንዳያጋጥም ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት እያከፋፈለ መሆኑን የፊቤላ ዘይት ፋብሪካ ገለጸ፡፡
የፋብሪካው ባለቤት አቶ በላይነህ ክንዴ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ለመጪዎቹ የፋሲካ እና የኢድ በዓላት ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት እያከፋፈለ ነው፡፡
ድርጅቱ ለቀጣዮቹ በዓላት የምርት አቅርቦት እጥረት በገበያው እንዳይፈጠር ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ ዘይት ለህብረተሰቡ በፍጥነት እንዲቀርብ እየሠራ ነው ብለዋል፡፡
በተለይ በእነዚህ ሁለት በዓላት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በበዓል ወቅት እንዳይቸገሩና የዘይት አቅርቦት እጥረት ገበያው ላይ እንዳይፈጠር ድርጅቱ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
እንደ አቶ በላይነህ ገለጻ፤ በዚህም በአሁኑ ወቅት ድርጅቱ በሰባት ክልሎች እና በአንድ ከተማ አስተዳደር ሰባት ሚሊዮን ሊትር ዘይት ለህብረተሰቡ እንዲከፋፈል እየተደረገ ነው፡፡ የፋብሪካው ሠራተኞች በቀንና በምሽት እየሠሩ ነው። በየቀኑ ከ15 በላይ የዘይት ምርት የጫኑ ተሸከርካሪዎች ምርቱን እያጓጓዙ ይገኛሉ፡፡
በቀጣይም መንግሥት ዘይት ከወጭ እንዲገባ ለድርጅቱ የፈቀደውን የውጭ ምንዛሬ በመጠቀም ምርቱ ሳይቆራረጥ ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡
በየጊዜው አዋጭ የድፍድፍ ዘይት ዋጋን በማገናዘብ የዘይት ምርት በአገር ውስጥ ማምረት የጀመረው ፊቢላ የዘይት ፋብሪካ፤ በአምስት ዙር 116 ሺ ሜትሪክ ቶን ድፍድፍ ፓልም ዘይት ግዥ ፈጽሟል፡፡ በዚህም 75 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በማምረት ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መንግሥት በመደበው ኮታ መሰረት እየተከፋፈለ ነው ብለዋል፡፡
እንደ አገር ባለፉት ዓመታት ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነውን የዘይት ምርት ከውጭ ይገባ እንደነበር ያወሱት አቶ በላይነህ፤ ፋብሪካው ይህንን ግምት ውስጥ በማስገባት የቢዝነስ ጥናት በማድረግ ወደ ሥራ መግባቱን አንስተዋል፡፡
የፊቤላ የዘይት ፋብሪካ ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሆነው ሲሆን በ31 አከፋፋዮች አማካኝነት በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች የዘይት ምርት ለህብረተሰቡ እየተሰራጨ ይገኛል ብለዋል፡፡
በጀማል ታመነ

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመጋቢት ወር ብቻ ከ108 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል
👉 ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ780 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፤
👉 ግድቡ ከተጀመረ እስካሁን 16.5 ቢሊዮን ብር በላይ ከህዝብ ተሰብስቧል፣
********************************
(ኢ ፕ ድ)
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተያዘው የበጀት አመት መጋቢት ወር ብቻ 108 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ደግሞ ለግድቡ ግንባታ ከ780 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።
ከተሰበሰበው ብር ውስጥ 399 ሚሊዮን የሚሆነው ከሀገር ውስጥ ቦንድ ግዢና ልገሳ የተገኘ ሲሆን፤ 243 ሚሊዮን የሚሆነው ገንዘብ ደግሞ ከዲያስፖራ ቦንድ ግዢና ልገሳ መሆኑ ታውቋል።
የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ በሀገር ውስጥ ቦንድ ግዢና ልገሳ 14 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር፤ ከዲያስፖራ ቦንድ ግዢ፤ እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ልገሳ ደግሞ አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል ።
በተመሳሳይ በ8100 A አጭር የፅሁፍ መልዕክት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 128 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘው መረጃ ያሳያል።
በወይንሸት ካሳ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
👉 ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ780 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል፤
👉 ግድቡ ከተጀመረ እስካሁን 16.5 ቢሊዮን ብር በላይ ከህዝብ ተሰብስቧል፣
********************************
(ኢ ፕ ድ)
ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተያዘው የበጀት አመት መጋቢት ወር ብቻ 108 ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር ተሰብስቧል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ደግሞ ለግድቡ ግንባታ ከ780 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።
ከተሰበሰበው ብር ውስጥ 399 ሚሊዮን የሚሆነው ከሀገር ውስጥ ቦንድ ግዢና ልገሳ የተገኘ ሲሆን፤ 243 ሚሊዮን የሚሆነው ገንዘብ ደግሞ ከዲያስፖራ ቦንድ ግዢና ልገሳ መሆኑ ታውቋል።
የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ አንስቶ በሀገር ውስጥ ቦንድ ግዢና ልገሳ 14 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር፤ ከዲያስፖራ ቦንድ ግዢ፤ እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ልገሳ ደግሞ አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል ።
በተመሳሳይ በ8100 A አጭር የፅሁፍ መልዕክት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 128 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡንም የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ያገኘው መረጃ ያሳያል።
በወይንሸት ካሳ
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስሩ ከራሺያ ማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ዋና ሹም ኤቭጅኒ ፔትሮቭ ጋር በበየነ መረብ ውይይት አደረጉ
******************
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮ-ራሺያን የምጣኔ ሃብት፣ የሳይንቲፊክ፣ የቴክኒካልና የንግድ ትብብር ኢንተር-ገቨርንመንታል ኮሚሽንን በጋራ ሊቀመንበርነት የሚመሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) እና የማዕድን ሃብት ኤጀንሲ ዋና ሹም ኤቭጅኒ ፔትሮቭ በበየነ መረብ ውይይት አደረጉ።
ኢትዮጵያና ራሺያ በዲፌንስ፣ በትምህርት፣ በኢነርጂ፣ በጤና፣ በንግድና ኢንቨስትመንት በትብብር ይሰራሉ።
ሰባተኛው ኢትዮ-ራሺያ ኢንተር-ገቨርንመንታል ኮሚሽን ውይይት ፒተርስበርግ ከተማ እ.አ.አ.በጥቅምት 2019 መካሄዱ ይታወቃል። ውይይቱም በሁለቱ ሃገሮች መካከል ያሉትን የሁለትዮሽ የንግድ፣ የምጣኔ ሃብት፣ የሳይንቲፊክና የቴክኒካል ትብብሮችን ስለማጠናከር ነበር።
ኢትዮጵያና ራሺያ በትብብር ከሚሰሩባቸው ዘርፎች ውስጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የራሺያ መንግስት አቶሚክ ኢነርጂ ትብብር እ.አ.አ. በጥቅምት 2019 የተፈረመ ሲሆን በኒውክለር ኢነርጂ ስልጠና ለመስጠት በሚያዚያ 15/ 2021 እ.አ.አ. የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

“በሚዲያዎች ላይ የሚታየውን ጠቃሚ ያልሆነ ውድድር ማስቀረት ይኖርብናል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ
******
(ኢ ፕ ድ)
ኢትዮጵያ ውስጥ በየሰፈሩ ያሉ ሚዲያዎች ላይ የሚታየውን ጠቃሚ ያልሆነ ውድድር ማስቀረት ይኖርብናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ‹‹አዲስ ፖለቲካዊ እይታ-አዲስ ሀገራዊ እመርታ›› በሚል መሪ ሐሳብ ለብልጽግና ፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሰጡት ሥልጠና እንደገለጹት፤ በየሰፈሩ ያለ ሚዲያዎች ውስጥ ጥሩ ያልሆነ ውድድር አለ። ይህ ጠቃሚ ያልሆነ ውድድር ለማንም የማይበጅ በመሆኑ መስተካከል ይኖርበታል።
ለአብነት ኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትወርክ /ኦቢኤን/ ብንመለከት አርሲ ውስጥ ስንዴ እንዴት ተመርቶ ምን ለውጥ አመጣ? የሚለውን ማሳየት ሲገባው፤ ጣቢያው ግን በየጊዜው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በዚህ ተገኙ ነገ በዚያ ብሎ ዜና ይሰራል ብለዋል።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽንም በተመሳሳይ ብንመለከተው ስለጎርጎራና ስለአካባቢው ሥራዎች መናገር ሲገባው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ብሎ ያወራል ያሉት ዶክተር ዐቢይ፤ አዲስ ቲቪም ሆነ ሌላው የፌዴራል ያልሆኑ በሌሎች የክልሎች መገናኛ ብዙሃን ላይ ችግሩ ተመሳሳይ መሆኑን ገልጸዋል።
አዲስ ቲቪ ስለአዲስ አበባ መረጃዎች ቢያቀርብ፤ ኦሮሚያም፣ ደቡብም ሆነ አማራ ያሉ መገናኛ ብዙሃኑ በተመሳሳይ ስለክልላቸው ጉዳዮች ቢዘግቡ ውጤት ያመጡ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።
ምክንያቱም ሰው ስለክልሉ መረጃ ሲፈልግ አማራጭ ካቀረብንለት...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71356

ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች‼️
👉 ከ3 ሺህ በላይ የጤና ተቋማት ጉዳት ደርሶባቸዋል፣
👉 በሕወሓት ከወደሙ 42 ሆስፒታሎች 36 ያህሉ ወደሥራ ተመልሰዋል፣
👉 ከ708 ሚሊዮን በላይ ብር ለክልል ጤና ተቋማት ድጋፍ መቅረቡ ተገልጿል፣
*****
(ኢ ፕ ድ)
ግጭት በነበረባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች በአጠቃላይ ከ3 ሺህ በላይ የጤና ተቋማት ጉዳት እንደደረሰባቸው ባደረገው የጉዳት ዳሰሳ ጥናት ማረጋገጡን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
ጤና ሚኒስቴር በሰጠው መግለጫ ግጭቶች በነበሩባቸው አካባቢዎች ሰብዓዊ ጥፋት ከመድረሱ በተጨማሪ ሕዝብ የሚገለገልባቸው የጤና ተቋማት፤ የሕክምና ግብዓት ማከማቻዎች እና ሌሎች ማኅበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት መውደማቸው ተጠቁሟል።
የህክምና መሣሪያዎች እና ሌሎች ግብዓቶችንም አገልግሎት እንዳይሰጡ ከጥቅም ውጪ መደረጋቸውንና ዝርፊያ እንደተፈጸመባቸው መግለጫውን የሰጡት ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር አየለ ተሾመ ተናግረዋል።
ሆስፒታሎች፣ ጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች እንዲሁም የህክምና ግብዓት ማከማቻ ተቋማት ላይ በግጭቱ ምክንያት መጠነ ሰፊ ውድመት መድረሱ በተለይ ድጋፍ የሚሹ ዜጎችን የመሰረታዊና ድንገተኛ ሕክምና...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71358