Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
በአቶ አህመድ ሽዴ የተመራው ልዑክ ከብሪታንያ የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
********************
(ኢ ፕ ድ)

በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የተመራው ልዑክ በብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ቪኪ ፎርድ ጋር የሁለትዮሽና የኢኮኖሚ ትብብር ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያየ።

በውይይቱም ለኢትዮጵያ እና እንግሊዝ ጠቃሚ በሆኑ የሁለትዮሽና የኢኮኖሚ ትብብር ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

የሰብዓዊ አቅርቦት እና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ሁሉ መደረግ ስላለበት ድጋፍ መወያየታቸውም ተገልጸዋል።

በተመሳሳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በኤርትራ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋርም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በባንኩ ፖርትፎሊዮ አፈጻጸም፣በአለም ባንክና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ተወያይተዋል። ሚኒስትሩ በቅርቡ ዓለም ባንክ በግጭት ለተጎዱ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ በደቡብ ሱዳንና በኤርትራ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን፣ በበኩላቸው መንግስት ቅድሚያ ለሰጣቸው የልማት ፕሮጀክቶችለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ የተመራው ልዑክ በዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ዋሺንግተን ዲሲ መግባቱ ይታወሳል።
በወላይታ ሶዶ ከተማ በሀሰተኛ የብር ኖቶች ሊገበያይ የሞከረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ ተያዘ
*********************
(ኢ ፕ ድ)

በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ በሚገኘው መርካቶ ገበያ 15 ሺህ ሐሰተኛ የብር ኖቶችን ይዞ ሊገበያይ የሞከረው ግለሰብ ዛሬ እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማዋ ፖሊስ ዋና አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ ዘውዴ እንዳሉት፤ ግለሰቡ ከአንድ ሱቅ ዘይትና ስኳር እንዲሁም ሌሎች የፍጆታ ምርቶች ከገዛ በኋላ ክፍያ ሊፈጽም ሲል ባለቤቱ ጥርጣሬ አድሮበት ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ስር በዋለበት ወቅት 75 ባለ 200 ሐሰተኛ የብር ኖቶች እጁ ላይ መገኘቱን ገልጸዋል።

ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አስታውቀዋል።

ህብረተሰቡ በተለይ የበዓል ወቅት መሆኑን ተከትሎ መሠል ማጭበርበርና ህገወጥ ተግባራት የሚፈጠር መሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ ሊያደረግ እንደሚገባ አሳስበዋል ሲል የኢዜአ ዘግቧል።

ሐሰተኛ የብር ኖቶችና መሰል ጥርጣሬ የሚፈጥሩ የወንጀል ድርጊቶች እንቅስቃሴ ሲመለከትም ለፀጥታ አካላት በአፋጣኝ እንዲጠቁምም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ትዊተር 👇
https://twitter.com/PressEthio
"በዓሉ የአስተሳሰብ ትንሳኤ የምናመጣበት ሊሆን ይገባል"
– መላከምህረት ቆሞስ አባ ጌዴዎን ብርሃነ በቅድስት ስላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የስነልቦና መምህር
*******
(ኢ ፕ ድ)

መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የዘንድሮውን የትንሳኤ በዓል ሲያከብር ከመብልና መጠጥ ባለፈ የአስተሳሰብ ትንሳኤ ለማምጣት ቁርጠኛ የሚሆንበት ሊሆን እንደሚገባ በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የስነልቦና መምህር መላከምህረት ቆሞስ አባ ጌዴዎን ብርሃነ አሳሰቡ፡፡

አባ ጌዴዎን ብርሃነ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት፤ ትንሳኤ ሰዎች እንዲኖሩ ክርስቶስ ራሱን በመስቀል ላይ መስዋዕት አድርጎ ያቀረበበት የመጨረሻው የሰላም ምዕራፍ ነው፡፡ በመሆኑም መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሚከበርበትን መሰረታዊ ዓላማን ከግምት ውስጥ በማስገባት የአስተሳሰብ ለውጥ ለማምጣት ሊተጉ ይገባል::

‹‹ትንሳኤ ማዕከሉ አዲስ ህይወት ነው:: ያ አዲስ ህይወት ደግሞ በመብል ላይ የተመሰረተ ሳይሆን በአስተሳሰብ ትንሳኤ ላይ የተመሰረተ ነው:: ትንሳኤ ዶሮ መብላት አይደለም፤ ዶሮና ሌሎቹ ግርግሮች ለስጋችን ደስታ ማድመቂያ እንጂ የነፍስ ደስታ ማዕከል አይደለም›› ብለዋል:: የእምነቱ ተከታዮች የደስታው ምንጭና ማዕከል ክርስቶስ ብቻ መሆኑን ሊዘነጉ እንደማይገባም አስገንዝበዋል::

‹‹ይህ በዓል የኢትዮጵያን ትንሳኤ የምናይበት ቀን እንዲሆን ሁላችንም በበኩላችን መረባረብ አለብን›› ያሉት አባ ጌዲዎን፤ ለሀገሪቱ እድገት እና ለሰላም ማነቆ የሆኑ ችግሮቻችንን በመተጋገዝ ማስወገድ እንደሚገባ ተናግረዋል::

‹‹ኢትዮጵያ ለሁላችንም በማንም የማትተካ ወርቃችን፣ ጌጣችን፤ ክብራችን፤ ማንነታችን ናት:: ስለዚህ እርስበርስ መለያየትና መጋጨታችንን በመተው በአንድ ልብ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71422

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የላልይበላ ገዳም ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው የሚያስችል እንቅስቃሴ ተጀመረ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የላልይበላ ገዳም ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ፡፡

የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስተባባሪ ዲያቆን አንተነህ እሸቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ እንደገለጹት፤ የላልይበላ ገዳም በነበረበት ለመመለስ በዘላቂነት መፍትሔ የሚሆነው በተቻለ ፍጥነት የሀገርን ሰላም እና የቱሪዝም ፍሰቱን ወደነበረበት መመለስ ነው።

ግሸን በዓመት እስከ አንድ ሚሊየን ዜጎች እንደሚጎበኙት የጠቆሙት አስተባባሪው፤ በላልይበላም የሀገር ውስጥ የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለማነቃቃት እንዲሁም ደብሩ መሰል ችግር ሲገጥመው መቋቋም የሚችልበት ቋሚ የገቢ ምንጮችን በሂደት ለመመስረት መታሰቡን አመላክተዋል።

አስራ አንድ አብያተ-ክርስቲያናትን አቅፎ የያዘው ላልይበላ በውስጡ ከአንድ ሺህ በላይ አገልጋይ ካህናት፣ ከ100 በላይ የቅርስ ጠባቂዎች እንዲሁም በላልይበላ ከተማ ልመና እንዲቀር ለማድረግ ያደራጃቸውና ከደብሩ በቀጥታ የሚደጎሙ አረጋውያን ተጧሪዎች፣ ሕጻናት ከነወላጆቻቸው በድምሩ ከ10 ሺህ በላይ በቀጥታ በገዳሙ የሚደጎሙ ዜጎች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

ገዳሙ ቀደም ሲል ለካህናትና ቅርስ ጠባቂዎች ደመወዝ፣ ለሚያስተዳድራቸው አረጋውያን እና ሕጻናት ድጋፍ የሚያስፈልገውን አራት ሚሊየን ብር ወርሃዊ ወጪውን ሸፍኖ በዙሪያው ላሉ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71435

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
"ጥላቻ፣ ኢ-ፍትሐዊነትና አመጸኝነት ለትውልድ የሚተላለፉ ክፉ ዘሮች በመሆናቸው መገታት ይገባቸዋል"
– ፓስተር ጻድቁ አብዶ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ቂም በቀል፣ ጥላቻ፣ ኢ-ፍትሃዊነት፣ አመጸኝነት እና አድመኝነት ለትውልድ የሚተላለፉ ክፉ ዘሮች በመሆናቸው መጸየፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ ገለጹ፡፡

ፓስተር ጻድቁ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገጹት፤ ቂም በቀል፣ጥላቻ፣ ኢፍትሃዊነት፣ አመጸኝነትና አድመኝነት፣ ለትውልድ የሚተላለፍ ክፉ ዘሮች ናቸው:: በመሆኑም ድርጊቶቹ አንድ ቦታ ላይ መገታት ይገባቸዋል::

ይህንን መርገም ለማስወገድ ትክክለኛው መንገድ የሰላም፣ የእርቅ፣ የይቅርታና የምህረት መንገድ ነው:: ከጥላቻ በመላቀቅ፣ ከቂም በቀል ፍላጎት በመጽዳት በአገር ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በውስጣችን ካለው ክፉ ሃሳብ መላቀቅ ይገባናል ብለዋል::

በአገር ሰላም እንዲሰፍን መጸለይ ይገባናል:: በተለያየ እምነት ያለን ኢትዮጵያውያን ሃይማኖተኛ ናቸው የሚባለውን ዛሬ በተግባር መግለጽ ይገባናል:: በክርስትና፣ በእስልምናና ሌሎች እምነቶች ሁሉም መጽሐፍት ጥላቻን አያስተምሩም፣ ቂም በቀልን ለእግዚአብሄር ተው እንደሚል እንደቃሉ መታዘዝ ያስፈልጋል::

መዘዙ ለልጅ ልጆችና ለትውልድ ስለሚተርፍ ከዚህ መንገድ መመለስ ያስፈልጋል:: የሌላው ህመም...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71424

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የተለያዩ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር እየተወያዩ ነው
******
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የተለያዩ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመሥገን ጥሩነህ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱም የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሚገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ መሠረት ያደረጉ ጥያቄዎች በተሳታፊዎቹ ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
በአማራ ክልል በቀጣዩ የምርት ዘመን 143 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዷል
*******
(ኢ ፕ ድ)
በቀጣዩ ዓመት የምርት ዘመን በጦርነቱ ሳቢያ የቀነሰውን ምርት ታሳቢ በማድረግ 143 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ::

በክልሉ ይሰበሰባል ተብሎ ከታቀደው 243 ሺ ኩንታል ምርጥ ዘር እስካሁን 112 ሺ ኩንታል ምርጥ ዘር መሰብሰቡ ተገለጸ::

በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማት ክትትልና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ አለባቸው አሊጋዝ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2014/2015 የምርት ዘመን አራት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሄክታር በዘር በመሸፈን 143 ሚሊዮን ምርት ለማምረት እየተሰራ ነው::

እንደ አቶ አለባቸው ገለጻ፤ በ2014 ዓ.ም በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ ምክንያት ቀንሶ የነበረውን ምርት ታሳቢ በማድረግ የተሻለ ምርት ለማምረት የግብርና ቢሮው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው:: ለዚህም የሙያተኞችን አቅም ማጎልበት ሲሆን በየደረጃው ያሉ የግብርና ባለሙያዎች የአሰራር ክለሳ በማድረግ እስከ ቀበሌ ድረስ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል::

በተጨማሪም በስልጠናው አርሶ አደሮች እንዲሳተፉ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል::

የምርት እድገትን ለማምጣት ከአርሶ አደሩ እስከ አመራሩና የግብርና ባለሙያው ከፍተኛ ቁርጠኝነትና የነቃ ስራ የሚጠይቅ መሆኑን የገለጹት የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተሩ፤ ለታቀደው ምርት ከሚያስፈልጉ ግብዓቶች መካከል..

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71452

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ