Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"ጥላቻ፣ ኢ-ፍትሐዊነትና አመጸኝነት ለትውልድ የሚተላለፉ ክፉ ዘሮች በመሆናቸው መገታት ይገባቸዋል"
– ፓስተር ጻድቁ አብዶ
*****
(ኢ ፕ ድ)
ቂም በቀል፣ ጥላቻ፣ ኢ-ፍትሃዊነት፣ አመጸኝነት እና አድመኝነት ለትውልድ የሚተላለፉ ክፉ ዘሮች በመሆናቸው መጸየፍ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ ገለጹ፡፡

ፓስተር ጻድቁ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገጹት፤ ቂም በቀል፣ጥላቻ፣ ኢፍትሃዊነት፣ አመጸኝነትና አድመኝነት፣ ለትውልድ የሚተላለፍ ክፉ ዘሮች ናቸው:: በመሆኑም ድርጊቶቹ አንድ ቦታ ላይ መገታት ይገባቸዋል::

ይህንን መርገም ለማስወገድ ትክክለኛው መንገድ የሰላም፣ የእርቅ፣ የይቅርታና የምህረት መንገድ ነው:: ከጥላቻ በመላቀቅ፣ ከቂም በቀል ፍላጎት በመጽዳት በአገር ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በውስጣችን ካለው ክፉ ሃሳብ መላቀቅ ይገባናል ብለዋል::

በአገር ሰላም እንዲሰፍን መጸለይ ይገባናል:: በተለያየ እምነት ያለን ኢትዮጵያውያን ሃይማኖተኛ ናቸው የሚባለውን ዛሬ በተግባር መግለጽ ይገባናል:: በክርስትና፣ በእስልምናና ሌሎች እምነቶች ሁሉም መጽሐፍት ጥላቻን አያስተምሩም፣ ቂም በቀልን ለእግዚአብሄር ተው እንደሚል እንደቃሉ መታዘዝ ያስፈልጋል::

መዘዙ ለልጅ ልጆችና ለትውልድ ስለሚተርፍ ከዚህ መንገድ መመለስ ያስፈልጋል:: የሌላው ህመም...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71424

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የተለያዩ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር እየተወያዩ ነው
******
(ኢ ፕ ድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ከዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የተለያዩ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ ላይ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመሥገን ጥሩነህ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በውይይቱም የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሚገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ መሠረት ያደረጉ ጥያቄዎች በተሳታፊዎቹ ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
በአማራ ክልል በቀጣዩ የምርት ዘመን 143 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዷል
*******
(ኢ ፕ ድ)
በቀጣዩ ዓመት የምርት ዘመን በጦርነቱ ሳቢያ የቀነሰውን ምርት ታሳቢ በማድረግ 143 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማምረት ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ::

በክልሉ ይሰበሰባል ተብሎ ከታቀደው 243 ሺ ኩንታል ምርጥ ዘር እስካሁን 112 ሺ ኩንታል ምርጥ ዘር መሰብሰቡ ተገለጸ::

በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማት ክትትልና ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ አለባቸው አሊጋዝ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2014/2015 የምርት ዘመን አራት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሄክታር በዘር በመሸፈን 143 ሚሊዮን ምርት ለማምረት እየተሰራ ነው::

እንደ አቶ አለባቸው ገለጻ፤ በ2014 ዓ.ም በአሸባሪው ሕወሓት ወረራ ምክንያት ቀንሶ የነበረውን ምርት ታሳቢ በማድረግ የተሻለ ምርት ለማምረት የግብርና ቢሮው ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው:: ለዚህም የሙያተኞችን አቅም ማጎልበት ሲሆን በየደረጃው ያሉ የግብርና ባለሙያዎች የአሰራር ክለሳ በማድረግ እስከ ቀበሌ ድረስ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል::

በተጨማሪም በስልጠናው አርሶ አደሮች እንዲሳተፉ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል::

የምርት እድገትን ለማምጣት ከአርሶ አደሩ እስከ አመራሩና የግብርና ባለሙያው ከፍተኛ ቁርጠኝነትና የነቃ ስራ የሚጠይቅ መሆኑን የገለጹት የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተሩ፤ ለታቀደው ምርት ከሚያስፈልጉ ግብዓቶች መካከል..

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71452

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለሃገራቸው በተለያዩ ሀገራዊ ጥሪዎች ያገለገሉ እናትን ጎበኙ
*****
(ኢ ፕ ድ)

ወ/ሮ ብርቄ አበበ ይባላሉ በለሚኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ነዋሪ ናቸው፡፡ እኚህ ጀግና እናት በወጣትነታቸው ከዚህ ቀደም ለሃገራቸው በተለያዩ አገራዊ ጥሪዎች የተፋለሙና አገር ያገለገሉ እናት ናቸው፡፡

ወ/ሮ ብርቄ ጉልበታቸው ቢደክምም ግን ደግሞ የወለዷቸው ልጆች በርሳቸው ምትክ ሃገር ማገልገላቸውን ቀጥለዋል፡፡

የአራት ልጆች እናት ሲሆኑ አንዱ ልጃቸው ህመምተኛ ሆኖ ከእርሳቸው ጋር ሲኖር የተቀሩት ሶስቱ ልጆቻቸው የእናታቸውን ፈለግ በመከተል እድሜያቸው ሲደርስ መከላከያን ተቀላቅለው ሃገር በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

ከሶስቱ አንዱ ልጃቸው ደግሞ በሰሜን እዝ በጀግንነት አገር በማገልገል እያለ በአሸባሪው ቡድን ጥቃት ደርሶበት ተጎድቶ ተመልሶ እናቱ ጋር ይገኛል፡፡

እኚህን ጀግና እናት በትንሳኤ በዓል ለማስታወስ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ቤታቸው አንዲታደስ በማድረግ የአመት በዓል ስጦታ የታደሰ ቤት ማበርከታቸውን ከከንቲባ ጽ/ቤት ዘግቧል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
አዲስ የወጣው መመሪያ እርስ በእርሱ የሚጣረስ መረጃ እንዳይፈጠር እንደሚረዳ አገልግሎቱ ገለጸ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዲስ ያወጣው መመሪያ እርስ በእርሱ የሚጣረስ መረጃ እንዳይፈጠር እንደሚረዳ ገለጸ::

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በተለይ የፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መረጃዎች በተገቢው መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆኑ አገልግሎቱ መመሪያ አውጥቷል::

በመመሪያው መሰረት በፌዴራል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የሚገኙ የኮሙኒኬሽን ክፍሎች አስፈላጊውን መረጃ ለሕዝቡ በቅንጅት እንዲያደርሱና ድጋፍም እንዲደረግላቸው ይረዳል::

እንደ አቶ ከበደ ማብራሪያ፤ በወጣው መመሪያ መሰረት የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የሚኒስቴር መስሪያ ቤት የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችን የመምራት፣ የማቀናጀት፣ የመደገፍና የመመደብ ስልጣን አለው:: የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎችን ለማብቃትም እገዛ ያደርጋል ብለዋል::

ተገቢውን መረጃ በተናበበ መልኩ በቀላሉ በህብረተሰብ ዘንድ እንዲያደርሱም መስሪያ ቤቱ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ጠቅሰዋል::

መረጃ በተናበበ መልኩ በቋሚነት ለሕዝቡ የሚደርስበት ሁኔታ ላይ ከሚዲያ አመራሮች ጋር...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71439

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
በጋምቤላ ክልል ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት ተደርጓል
***
(ኢ ፕ ድ)
ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የተፋሰስ ልማት ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ እንደሚገኝ የጋምቤላ ክልል አስታወቀ::

ዘንድሮ በክልሉ በ64 ተፋሰሶች ላይ አካባቢን የማልማት ሥራ ተሠርቷል::

የክልሉ ግብርና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ኃላፊ አቶ አጃክ ኡቻላ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ በተፋሰስ ልማት ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጓል:: አየር ንብረት ለውጥና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን በመጨመር በክልሉ የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ተፋሰስ ልማት ጉልህ ሚና አለው ብለዋል::

ይህንን ለማሳካት በርእሰ መስተዳድሩ የሚመራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እስከታችኛው የኅብረተሰብ ክፍል ድረስ ንቅናቄ ውስጥ መገባቱን ገልጸዋል:: እስከአሁን ድረስ በተሰራው ስራ በ64 ተፋሰስ አካባቢዎች ልማት ማካሄድ ተችሏል::

እንደ ቢሮ ኃላፊው ገለጻ፤ በተፋሰስ ልማቱ የተሰሩ እርከኖችና እስትራክቸሮች እንዳይበላሹ በአረንጓዴ ልማት ሥራዎች በመታገዝ ባለፈው ዓመት ስድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ችግኞች ተተክለዋል:: ዘንድሮ ደግሞ አምስት ሺህ 325 ተፋሰስ አካባቢዎች ላይ የሚተከሉ ዘጠኝ ነጥብ አምስት ሚሊዮን..

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71443

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የላልይበላ ገዳም ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው የሚያስችል እንቅስቃሴ ተጀመረ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የላልይበላ ገዳም ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲኖረው ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩ ተገለጸ፡፡

የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስተባባሪ ዲያቆን አንተነህ እሸቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ እንደገለጹት፤ የላልይበላ ገዳም በነበረበት ለመመለስ በዘላቂነት መፍትሔ የሚሆነው በተቻለ ፍጥነት የሀገርን ሰላም እና የቱሪዝም ፍሰቱን ወደነበረበት መመለስ ነው።

ግሸን በዓመት እስከ አንድ ሚሊየን ዜጎች እንደሚጎበኙት የጠቆሙት አስተባባሪው፤ በላልይበላም የሀገር ውስጥ የቱሪዝም እንቅስቃሴውን ለማነቃቃት እንዲሁም ደብሩ መሰል ችግር ሲገጥመው መቋቋም የሚችልበት ቋሚ የገቢ ምንጮችን በሂደት ለመመስረት መታሰቡን አመላክተዋል።

አስራ አንድ አብያተ-ክርስቲያናትን አቅፎ የያዘው ላልይበላ በውስጡ ከአንድ ሺህ በላይ አገልጋይ ካህናት፣ ከ100 በላይ የቅርስ ጠባቂዎች እንዲሁም በላልይበላ ከተማ ልመና እንዲቀር ለማድረግ ያደራጃቸውና ከደብሩ በቀጥታ የሚደጎሙ አረጋውያን ተጧሪዎች፣ ሕጻናት ከነወላጆቻቸው በድምሩ ከ10 ሺህ በላይ በቀጥታ በገዳሙ የሚደጎሙ ዜጎች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡

ገዳሙ ቀደም ሲል ለካህናትና ቅርስ ጠባቂዎች ደመወዝ፣ ለሚያስተዳድራቸው አረጋውያን እና ሕጻናት ድጋፍ የሚያስፈልገውን አራት ሚሊየን ብር ወርሃዊ ወጪውን ሸፍኖ በዙሪያው ላሉ....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71435

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
"ዛሬ ከጀግኖች የማዕከላዊ ዕዝ ብሔራዊ ኃይላች አባላት ጋር ጊዜ በማሳለፌ ክብር ይሰማኛል። ብዙዎች ሀገራችንን ለማገልገልና ታላቋን #ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ ሲሉ መሥዋዕትነት ከፍለዋል። መሥዋዕትነት፣ ትጋት፣ ዕውቀት፣ ርኅራኄና አንድነት ሀገራችንን ልትደርስበት ወደሚገባት ከፍታ ያሻግሯታል።"

- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ