ለዋግኽምራ ብሔረሰብ ተፈናቃዮች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ ማዕድ ያጋሩ አካላትን አቡነ በርናባስ አመሰገኑ
*****
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር እና የካናዳ አሕጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ በርናባስ ለዋግኽምራ ተፈናቃዮች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ በትንሣኤ በዓል ማዕድ ያጋሩ አካላትን አመስግነዋል።
በማዕድ ማጋራቱ በርካታ አካላት 3 ሚሊየን ብር የሚገመት ድጋፍ በማድረግ መሳተፋቸውን የገለፁት አቡነ በርናባስ ኮሜዲያን እሹቱ መለሰ እና ጋዜጠኛ መታሰብያ ቀጸላ ጉልህ አስተዋጽኦ አድርገዋል ብለዋል።
አቡነ በርናባስ ተፈናቃዮች በዘላቂነት እንዲቋቋሙ በትኩረት እንዲሠራ ጠይቀዋል።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ ከፍያለው ደባሽ ሰው ሁሉ ወደ ዋግ ፊቱን እንደመለሰ ተገንዝበናል፣ ሰው በሰው ተደጋግፎ ችግርን ማለፍ እንደ ሚቻል ከዚህ ጊዜ በላይ የምንረዳበት ጊዜ አይኖርም ብለው ተፈናቃዮች በዘላቂነት እንዲቋቋሙ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
በብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከአበርገሌ ወረዳ፣ ጻግብጅ ወረዳ፣ ዛታ ወረዳ፣ ወፍላ (ኮረም) ወረዳ፣ ዝቋላ 6 ቀበሌና ሰቆጣ ወረዳ 1 ቀበሌ ተፈናቅለው በአራት (4) መጠለያ ጣብያዎች እንደሚገኙ አቶ ከፍያለው ተናግረዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ሆነ
********************
(ኢ ፕ ድ)
ትምህርት ሚኒስቴር የ2013ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ አድርጓል።
የ2013 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ መንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) የመግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ምደባ ተደርጓል።
ከዚህ በፊት በተገለጸዉ የመቁረጫ ነጥብ እና ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋርና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች ምደባ የሚያስገኝላቸው ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ የተመደቡበትን ዩኒቨርስቲ ለማየት በድህረገፅ፡-https://result.ethernet.edu.et ፣
በSMS፡- 9444 እንዲሁም
በቴሌግራም፡- @moestudentbot መጠቀም ይችላሉ።
ተማሪዎች ከምደባ ጋር ተያይዞ ላላችው ማንኛውም ጥያቄ በድህረገፅ https://complaint.ethernet.edu.et በማመልከት ጥያቄዎቻቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 24/2014 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

መገናኛ ብዙኃን የምክክር ሂደቱን ሊያደናቅፍ ከሚችል ዘገባ መቆጠብ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አሳሰበ
*****
(ኢ ፕ ድ)
መገናኛ ብዙኃን የአገራዊ ምክክር ሂደቱን ሊያደናቅፍ ከሚችል ዘገባ መቆጠብ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አሳሰበ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መገናኛ ብዙኃን የአካታች አገራዊ የምክክር ሂደቱን ከሚያደናቅፍ መንገድ ተቆጥበው መሥራት ይኖርባቸዋል።
በምክክር ሂደቱ ወቅት በሚካሄዱ ውይይቶች ላይ የሚነሱ ሃሳቦችን ለማንቋሸሽና ለመግፋት ከሚደረጉ ጥረቶች፤ በጽንፈኝነት የሚወጡ ሃሳቦችን ሌሎች ላይ ከማራገፍ እንዲሁም የአንድን አካል ሃሳብ ባልተገባ መንገድ ከመጠቀም የመቆጠብ ግዴታ አለባቸው ብለዋል።
የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በሚፈጥራቸው ሁነቶች ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎችንና ሃሳቦች በማይጨፈልቅ መንገድ ዘገባ በመስራት ለምክክሩ ውጤታማነቱ መትጋት ይኖርባቸዋል ሲሉ
https://www.press.et/?p=71572
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
*****
(ኢ ፕ ድ)
መገናኛ ብዙኃን የአገራዊ ምክክር ሂደቱን ሊያደናቅፍ ከሚችል ዘገባ መቆጠብ እንዳለባቸው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አሳሰበ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መገናኛ ብዙኃን የአካታች አገራዊ የምክክር ሂደቱን ከሚያደናቅፍ መንገድ ተቆጥበው መሥራት ይኖርባቸዋል።
በምክክር ሂደቱ ወቅት በሚካሄዱ ውይይቶች ላይ የሚነሱ ሃሳቦችን ለማንቋሸሽና ለመግፋት ከሚደረጉ ጥረቶች፤ በጽንፈኝነት የሚወጡ ሃሳቦችን ሌሎች ላይ ከማራገፍ እንዲሁም የአንድን አካል ሃሳብ ባልተገባ መንገድ ከመጠቀም የመቆጠብ ግዴታ አለባቸው ብለዋል።
የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በሚፈጥራቸው ሁነቶች ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎችንና ሃሳቦች በማይጨፈልቅ መንገድ ዘገባ በመስራት ለምክክሩ ውጤታማነቱ መትጋት ይኖርባቸዋል ሲሉ
https://www.press.et/?p=71572
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
‹‹ክስተቶችን ከማራገብ ይልቅ ኢትዮጵያ ከገባችበት ችግር እንድትላቀቅ መሥራት ከልሂቁ ይጠበቃል›› ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ- የታሪክ ተመራማሪ
********
(ኢ ፕ ድ)
አገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ክስተቶችን በማራገብ ወደ ጠርዝ ከመግፋት ይልቅ ኢትዮጵያ የገባችበትን ችግር ምክንያታዊ ሃሳብ በማቅረብና አገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን መስራት ከልሂቁ ይጠበቃል ሲሉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ ተናገሩ።
ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ እንደ ኢትዮጵያ ያለ በአብዛኛው ከ80 በመቶ የማይተናነስ ሕዝብ በግብርና ስራ የተሰማራ አርሶአደር ሕዝብ በመሆኑ በርካታ አገራዊ ጉዳዮች የሚቀነቀኑት በልሂቁ ክፍል ነው።
ይህ ክፍል የአገሪቱን እጣፋንታ በመወሰን ረገድ ትልቅ ሚና መሆኑን አመልክተው፤ ልሂቁ ሊገነዘብ የሚገባው ጉዳይ ያለችን አንድ አገር በመሆኑ በጊዜ ተባብሮ አሁን ከተጠናወታት በሽታ ማዳን ያስፈልጋል። ካልሆነ ለልሂቃኑም የማይመች ሁኔታ ሊፈጠር የሚችል መሆኑን
https://www.press.et/?p=71576
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
********
(ኢ ፕ ድ)
አገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ክስተቶችን በማራገብ ወደ ጠርዝ ከመግፋት ይልቅ ኢትዮጵያ የገባችበትን ችግር ምክንያታዊ ሃሳብ በማቅረብና አገራዊ ምክክሩ ስኬታማ እንዲሆን መስራት ከልሂቁ ይጠበቃል ሲሉ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ ተናገሩ።
ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ እንደ ኢትዮጵያ ያለ በአብዛኛው ከ80 በመቶ የማይተናነስ ሕዝብ በግብርና ስራ የተሰማራ አርሶአደር ሕዝብ በመሆኑ በርካታ አገራዊ ጉዳዮች የሚቀነቀኑት በልሂቁ ክፍል ነው።
ይህ ክፍል የአገሪቱን እጣፋንታ በመወሰን ረገድ ትልቅ ሚና መሆኑን አመልክተው፤ ልሂቁ ሊገነዘብ የሚገባው ጉዳይ ያለችን አንድ አገር በመሆኑ በጊዜ ተባብሮ አሁን ከተጠናወታት በሽታ ማዳን ያስፈልጋል። ካልሆነ ለልሂቃኑም የማይመች ሁኔታ ሊፈጠር የሚችል መሆኑን
https://www.press.et/?p=71576
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ከኢድ እስከ ኢድ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ ለማስተዋወቅ ተገቢ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል
*******
ከኢድ እስከ ኢድ መርሀ ግብር ላይ የኢትዮጵያን መልካም ገጽታ በውል ለማስተዋወቅ ተገቢ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉ የታሪክ ምሁሩ ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል አመለከቱ።
ረዳት ፕሮፌሰር አደም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፣በመርሀ ግብሩ ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ የዓለም አገራት የሚመጡ ኢትዮጵያውያን፣ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በቆይታቸው ስለ ኢትዮጵያ ነበራዊ ሁኔታ በቂ እውቀት እንዲኖራቸው ሁኔታዎችን ከወዲሁ ማመቻቸት ያስፈልጋል። በተለየ መልኩ ደግሞ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉባዔ ብዙ ነገር ይጠበቅበታል።
ኢትዮጵያ እንደ ክርስትና እምነት ሁሉ ለእስልምና እምነትም የማትረሳ ባለውለታ በመሆኗ ከተለያዩ የዓረብ አገራት ለሚመጡ እንግዶች የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴዎች ማድረግ እንደሚያስፈልግ አመልክተው፤ በተለይ በዓረብኛ ቋንቋ ሃማኖታዊ ክንዋኔዎችን፣የቱሪስት መስህቦችን፣የኢንቨስትመንት አማራጮችንና በንግድ ዘርፎች እንቅስቃሴ ግንዛቤ የሚሰጡ መጽሔቶች ወይም መጽሐፎች አዘጋጅቶ ለመስጠት ከወዲሁ መታሰብ እንዳለበት አስገንዝበዋል። ለዚህ ደግሞ የእስልምና ጉባዔው ከውጭ ጉዳይ ጋር በመሆን የድርሻውን
https://www.press.et/?p=71579

ኦሮሚያ በበጋ መስኖ 27 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል
*****
(ኢ ፕ ድ)
👉 በመኸር ምርት ዘመን ከ48 ሚሊዮን በላይ ኩንታል ስንዴ ለማምረትም ታቅዷል
በኦሮሚያ ክልል በሁለት ዙር የበጋ መስኖ ብቻ 27 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን ኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ ።
በመኸር ምርት ዘመን 48 ሚሊዮን 259 ሺህ 89 ኩንታል የስንዴ ምርት ለማምረት መታቀዱም አመልክቷል።
በክልሉ ግብርና ቢሮ የበጋ ስንዴ ምርት ኢንሼቲቪ አስተባባሪ አቶ ጠሃ ሙሜ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ከክልሉ በበጋ መስኖና በመኸር ምርት ዘመን ከፍተኛ የስንዴ ምርት በማምረት እንደ አገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። በበጋ መስኖ ብቻ 27 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ምርት ለማምረት እየተሰራ ነው።
በበጋ መስኖ 350ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ ለመሸፈን ታቅዶ 355 ሺህ 106 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን አመልክተው፤በአሁኑ ጊዜም በበልግ ዝናብ የሚታገዝ ሁለተኛ ምዕራፍ የመስኖ እርሻ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑንና እስካሁንም
https://www.press.et/?p=71582

ለአገራዊ ምክክሩ ሚዲያው የሚመራበት መመሪያ ሊዘጋጅ እንደሚገባ ተጠቆመ
******
(ኢ ፕ ድ)
በኢትዮጵያ ሊደረግ በታሰበው አገራዊ ምክክር የሚዲያው ሚና ጉልህ በመሆኑ ሚዲያው የሚመራበት ዝርዝር መመሪያ ሰነድ ሊዘጋጅለት እንደሚገባ ተገለጸ።
ሚዲያው አገራዊ ጥቅምና ሙያዊ ስነ ምግባርን ማዕከል በማድረግ ለሀገራዊ ውይይቱ የበኩሉን በጎ አስተዋፅኦ ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቁሟል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሳምሶን መኮንን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ አገራዊ ምክክር በማድረግ የተሳካላቸው በርካታ ሀገራት እንዳሉ ሁሉ ምክክሩ ሳይሳካላቸው የቀሩ አገራት አሉ። ለአገራዊ ምክክሩ ስኬታማ ሆነ ስኬታማ ላለመሆኑ ሚዲያው እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚጠቀስ
https://www.press.et/?p=71585

በመጪው አርብ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በአዲስ አበባ ይካሄዳል
*****
(ኢ.ፕ.ድ)
በመጪው አርብ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የ"ከኢድ እስከ ኢድ" አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
የኮሚቴው ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ መርሀግብሩን ለመታደም እንግዶች ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ ሀገራቸው በመግባት ላይ የሚገኙ ሲሆን በመጪው አርብ ታላቅ የጎዳና ላይ ኢፍጣር በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡
ከኢድ እስከ ኢድ ጥሪን ለማስተባበር እስካሁን ከሁለት ሺህ አምስት መቶ በላይ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተሳትፈዋል ያሉት ኡስታዝ አቡበከር በመጪው ረቡዕ የኢድ ኤክስፖ መርሀግብር እንደሚከፈትም ተናግረዋል፡፡
መርሀግብሩ የኢትዮጵያን በጎ ጎን ለዓለም ማስተዋወቂያ እድል እንደሚፈጥርም ኡስታዝ አቡበከር ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤ ቀደም ሲል ኢድን በአገር ቤት እናክብር በማለት “ታላቁ የኢድ ሰላት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ለኢትዮጵያ ወዳጆች ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
በዳግማዊት ግርማ

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውሰጥ ከ248 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለጸ
******
(ኢ ፕ ድ)
በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውሰጥ 248 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ
መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትሩ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ መሰረት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 267 ቢሊዮን 558 ሚሊዮን 565 ሺህ 762 ብር ከ 32 ለመሰብሰብ ታቅዶ፤ 248 ቢሊዮን 618 ሚሊዮን 35 ሺህ 417 ብር ከ 89 መሰብሰብ ተችሏል።
ይህ አፈጻጸም ከእቅዱ አንጻር የ93 በመቶ ድርሻ እንዳለው ነው ሚኒስትሩ የገለጹት።
የተሰበሰበው ገቢ ከ2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ሲታይ የብር 36 ቢሊዮን 310 ሚሊዮን 719 ሺህ 438 ብር ከ79 ወይም የ17 ነጥብ 10 ከመቶ እድገት አለውም ብለዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
******
(ኢ ፕ ድ)
በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውሰጥ 248 ነጥብ ስድስት ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ
መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትሩ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ አቶ ላቀ አያሌው በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መረጃ መሰረት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 267 ቢሊዮን 558 ሚሊዮን 565 ሺህ 762 ብር ከ 32 ለመሰብሰብ ታቅዶ፤ 248 ቢሊዮን 618 ሚሊዮን 35 ሺህ 417 ብር ከ 89 መሰብሰብ ተችሏል።
ይህ አፈጻጸም ከእቅዱ አንጻር የ93 በመቶ ድርሻ እንዳለው ነው ሚኒስትሩ የገለጹት።
የተሰበሰበው ገቢ ከ2013 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ሲታይ የብር 36 ቢሊዮን 310 ሚሊዮን 719 ሺህ 438 ብር ከ79 ወይም የ17 ነጥብ 10 ከመቶ እድገት አለውም ብለዋል።
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
በኦሮሚያ ክልል ድርቁ ባስከተለው ጉዳት አንድ ነጥብ ሦስት ሚሊዮን እንስሳት መሞታቸው ተገለጸ
******
(ኢ ፕ ድ)
በኦሮሚያ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከ26 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመቱ አንድ ነጥብ ሶስት ሚሊዮን እንስሳት መሞታቸውን የክልሉ የአደጋና ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
በኮሚሽኑ የቅድመ ማስጠንቀቂያና አደጋ ስጋት ቅነሳ ዳይሬክተር አቶ ቤኛ ዱሬሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በስምንት ዞኖች በተከሰተው ደርቅ 14 ሚሊዮን የሚሆኑ እንስሳት ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከ26 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመቱ አንድ ነጥብ ሶስት ሚሊዮን እንስሳት ሞተዋል።
በክልሉ የበልግና የመኸር ወቅት በተከታታይነት መጥፋቱ ስምንቱም ዞኖች ከፍተኛ ድርቅ እንዲከሰት አድርጓል ያሉት አቶ ቤኛ፤ በአጠቃላይ የምግብ እጥረትና የውሃ ችግር የገጠማቸውና ጉዳት ደርሶባቸዋል ተብለው በጥናት የተለዩት 14 ሚሊዮን ከብቶች
https://www.press.et/?p=71592

ፍራንኮ ቫሉታ ለህገ ወጥ የውጭ ምንዛሬ ዝውውር እንዳይዳርግ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል
****
(ኢ ፕ ድ)
ፍራንኮ ቫሉታ ለሕገ ወጥ የውጭ ምንዛሬ ዝውውር እንዳይዳርግ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ሲሉ የፖሊሲ ጉዳዮች ባለሙያው አቶ አማንይሁን ረዳ አስታወቁ።
የፖሊሲ ጉዳዮች ባለሙያው አቶ አማንይሁን ረዳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ ያለ ውጭ ምንዛሬ ፈቃድ መሠረታዊ የምግብ ሸቀጦች ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ የሚፈቅደው “ፍራንኮ ቫሉታ” አሁን ኢትዮጵያ የምትገኝበት ሁኔታ የተለየ ችግር የተከሰተበት ወቅት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እንደ አገር የገጠመውን የምርት እጥረት ለመቅረፍ ጊዜያዊ መፍትሄ የሚሰጥ ነው። ሆኖም ለህገ ወጥነት በር የሚከፍት በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።
ፍራንኮ ቫሉታ የአጭር ጊዜ መፍትሄ ነው ያሉት ባለሙያው፤ ለአጭር ጊዜ መፍትሄ የምርት እጥረት ችግርን ለመቅረፍ በተለይ ምግብ ነክ እቃዎች ከውጭ በበቂ መጠን እንዲገቡና ሕዝቡን ለምሬትና ለብሶት እያደረገ ያለውን የዋጋ ንረት አቅርቦትን በማሻሻል ረገድ ሚና እንዳለው
https://www.press.et/?p=71586