Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
“የሲሚንቶ ገበያውን ለማረጋጋት የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት ሊሠሩ ይገባል”
- የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ
*****
(ኢ.ፕ.ድ)

በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፤ “የተጋነነ እና ሕገ-ወጥነት የሚስተዋልበትን የሲሚንቶ ገበያ ለማረጋጋት፤ የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት ሊሠሩ ይገባል” ሲል አሳሰበ፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ይህንን የመስክ ምልከታ ጥቆማ የሰጠው፤ ሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ በአካል ተገኝቶ ናሽናል ሲሚንቶ እና ቱሬ ሲሚንቶ ፋብሪካዎችን በአካል ተዘዋውሮ በጎበኘበት ወቅት፤ ከፋብሪካዎቹ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተደረገ ውይይት ነው፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት በዚሁ የመስክ ምልከታቸው፤ የናሸናል ሲሚንቶ እና የቱሬ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበሮች፤ አንዱን ከረጢት ሲሚንቶ እስከ 4 መቶ 40 ብር ብቻ እንደሚሸጡ ተረድተዋል። ይሁን እንጂ ከፋብሪካዎቹ በዚሁ ተመን የሚወጡት እነዚሁ ምርቶች፤ እስከ 1 ሺህ 2 መቶ ብር እና ከዚያ በላይ የሚሸጡበት ሁኔታ፣ በባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ርብርብ መፍትሔ ሊበጅለት እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ፋብሪካው ጥሬ ዕቃ በሚያገኝበት ቦታ ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራ እየተደረገ ስለመሆኑም፤ የየፋብሪካው አመራሮች ለቋሚ ኮሚቴው አባላት በተጨማሪነት አስረድተዋል።

የናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ እግዝኤል ብዙአየሁ እንደጠቆሙት፤ ገበያን በማረጋጋት ረገድ መንግስት ክትትል እና ቁጥጥር ሊያደርግ ይገባል፡፡ የዘርፉን የምርት አቅርቦት እና ፍላጎቱን ለማመጣጠን አክሲዮን ማህበሩ በተለያዩ አካባቢዎች የጀመራቸው አዳዲስ ፕሮጄክቶች በመንግሥት እንዲደገፉም ጥያቄያቸውን አያይዘው አቅርበዋል።

በተመሳሳይ የቱሬ ሲሚንቶ ፋብሪካ ጥሬ እቃዎችን ጭኖ ወደ ፋብሪካው ለመውሰድ በአንድ መኪና እስከ 100 ብር በሕገ-ወጥ መንገድ ለግለሰቦች እየከፈለ ስለመሆኑ፤ የፋብሪካው ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ዚዳይዳን በክሪ ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ገልፀዋል።

የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በበኩሉ፤ የተጠቀሱትን ችግሮች ሁሉ ፋብሪካዎቹ ከአስተዳደሩ እና ከማኅበረሰቡ እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ሆነው ሊፈቷቸው እንደሚችሉ አስገንዝቧል፡፡

ከዚህ በዘለለ ግን ፋብሪካዎቹ ለአካባቢው ማኅበረሰብ እያበረከቱ ያለው ሁለገብ አስተዋጽዖ የሚደነቅ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው ቡድን መሪ የተከበሩ በጋሻው ተክሉ አውስተው፤ አቅርቦትን ለማሳደግ የሚያስችል የማስፋፊያ ሥራ ግን በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባው አመላክተዋል።

የድሬደዋ መስተዳድር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ ደግሞ፤ መስተዳድሩ ለኢንዱስትሪ እና ለፋብሪካዎች ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ስለመሆኑ ገልጸው፤ በአካባቢው ያለውን የማዕድን ሀብት ለማወቅ እና ለመጠቀም የማዕድን ሚኒስቴር ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ለቋሚ ኮሚቴው አባላት አስረድተዋል ሲል ምክር ቤቱ ዘግቧል።
"ሃገራዊ ምክክሩን ለማሳካት የተረጋጋ ሰላምና አስተማማኝ ደህንነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል"
- አቶ አባተ ኪሾ
****
(ኢ ፕ ድ)

ሃገራዊ ምክክሩን ለማሳካት የተረጋጋ ሰላምና አስተማማኝ ደህንነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የቀድሞ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባተ ኪሾ አመለከቱ።

በሃገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ በተገቢው መወጣት አለበትም ብለዋል።

አቶ አባተ ኪሾ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፤ ሃገራዊ ምክክር ለማካሄድ የታሰበው በሃገሪቱ መቀረፍ ያለበት አሳሳቢ ችግር በመኖሩ ነው። በየጊዜው እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች መንስዔም አለመግባባቶች በመኖራቸው ነው። መንግሥትም በጉዳዩ ዙሪያ ተደጋጋሚ መግለጫ አውጥቷል፤ በአንዳንድ አካባቢዎችም እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ብለዋል።

ከሁሉም በላይ ግን አለመግባባቶቹን ለመፍታት አይነተኛ መፍትሄ የሆነውን ሃገራዊ ምክክር ለማካሄድ የተረጋጋ ሰላምና አስተማማኝ ደህንነት መፍጠር የሁሉም ኃላፊነት መሆን እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

መንግሥት የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ቀዳሚ ተግባሩ በመሆኑ ሰሞኑን የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በጉዳዩ ዙሪያ ያወጣው መግለጫ የዚሁ አካል....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71641

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ለትግራይ የሚላከው እርዳታ ለሕዝቡ ሳይሆን ለሕወሓት ታጣቂዎች እየዋለ መሆኑን ትዴፓ ገለጸ

👉 የትግራይ ሕዝብ ሰቆቃ የሚያበቃው ሕወሓታዊ አስተሳሰብ ሲጠፋ ብቻ ነው፣
*****
(ኢ ፕ ድ)
ለትግራይ ሕዝብ የሚላከው እርዳታ ለሕዝቡ ሳይሆን ሕወሓት ራሱ ላደራጃቸው መደቦችና ታጣቂዎች እየዋለ መሆኑን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ገለጸ።

የትግራይ ሕዝብ ሰቆቃ የሚያበቃው ሕወሓታዊ አስተሳሰብ ሲጠፋ ብቻ እንደሆነም ተመላክቷል።

የትግራይ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉብርሃን ኃይሌ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል የሚላክ ቢሆንም ለሕዝቡ የሚደርስ እርዳታ የለም። እርዳታው ወደ ትግራይ ክልል ቢገባም ለሕዝቡ እየደረሰ አለመሆኑን ይልቁንም ለሕወሓት ታጣቂዎች እየተሰጠ መሆኑን ፓርቲያቸው ከተለያዩ ምንጮች እንዳረጋገጠ ገልጸዋል።

በሕዝብ ስም መነገድ የሕወሓት የዛሬ ባህሪው ብቻ ሳይሆን ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ ያለው ታሪክ እንደሚያስረዳ የገለጹት አቶ ሙሉብርሃን፤ ወደ ትግራይ ክልል የሚገባው የምግብ፣ መድኃኒትና ሌሎች መሰል እርዳታዎች.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71644

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የፍትሕ አካላት የሐሰተኛና ጥላቻ ንግግር ወንጀልን የሚፈጽሙ ሰዎችን ለሕግ እንዲያቀርቡ ተጠየቀ
*******
(ኢ ፕ ድ)
የፍትሕ ሚኒስቴርን ጨምሮ ፖሊስ፣ የክልልና የፌዴራል የፍትሕ ተቋማት የሐሰተኛና ጥላቻ ንግግር ወንጀልን የሚፈጽሙ ሰዎችን ወደ ሕግ ማቅረብ እንዳለባቸው ተጠቆመ።

በፍትሕ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አወል ሱልጣን ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ቁጥጥር ተፈጻሚ መሆን በሚገባው ደረጃ እየተፈጸመ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።

ከዚህ በኋላ ሐሰተኛ የመረጃ ስርጭትን የሚያሰራጩ ሰዎች በአዋጁ ላይ የተቀመጡትን የወንጀል ቅድመ ሁኔታዎች እስኪያሟሉ ድረስ ፖሊስ ምርመራ መጀመር እንዳለበት፤ ማኅበረሰቡም መጠቆም እንደሚችል፤ ዓቃቤ ሕግም ወንጀል የመመርመርና የመምራት ኃላፊነት ስላለበት በዚህ ሂደት ውስጥም ፖሊስ የወንጀል ምርመራ እንዲጀምርና የተጣራ ምርመራ ካለ ክስ መስርቶ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶ ክርክር ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል። ይህ በተጨባጭ እንደሚከናወንም ነው ያስታወቁት።

ይህን ማድረግ ባለመቻላችን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ሰዎች ከመስመር ሲወጡና እንዲህ አይነት መረጃዎችን ሲያሰራጩ ቆይተዋል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በሐሰተኛ መረጃና ጥላቻ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71665

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጀ
በቀጣዮቹ 10 ዓመታት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች እንዲገነቡ ይሠራል

👉 በአሁኑ ወቅት 2 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች እጥረት አለ
*****
(ኢ ፕ ድ)
መንግሥት በራሱ ከሚገነባቸው ቤቶች በተጨማሪ ሌሎች አጋር አካላትን በማሳተፍና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በቀጣዮቹ 10 ዓመታት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶች እንዲገነቡ እንደሚሠራ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።

ለኑሮ ምቹ ያልሆኑና ፈርሰው መሠራት ያለባቸውን አንድ ሚሊዮን ቤቶችን ሳይጨምር በአሁኑ ወቅት የሁለት ሚሊዮን ቤቶች እጥረት እንዳለም ተገልጿል።

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ታደሰ ከበበ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መንግሥት በራሱ ከሚገነባቸው በተጨማሪ ሌሎች አጋር አካላትን በማሳተፍና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በቀጣዮቹ 10 ዓመታት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶችን እንዲገነቡ ይሠራል።

አሁን ባለው ደረጃ በከተሞች ያለው የቤት አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ ያሉት የቢሮ ኃላፊው፤ ለዚህም ከተሞች በፈጣን ዕድገት ውስጥ መገኘታቸው እና የሕዝብ ቁጥር ዕድገቱን...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71660

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
«የሩስያና የዩክሬን ግጭት እንደ ሃገር ራስን በምርት ለመቻል ለሚደረገው ጥረት እድል አምጥቷል»አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የሩስያና የዩክሬን ግጭት ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ ቢጎዳትም እራስን ለመቻል አስገድዶም ቢሆን እድል አምጥቷል ሲሉ የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገለጹ።

አቶ ዘመዴነህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የሩሲያ እና የዩክሬን ግጭት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተፅዕኖ ቢያሳርፍም አስገድዶም ቢሆን ራስን በምርት ለመቻል እድሉን አምጥቷል። እራስን መቻል ላይ ባሉን አማራጮች ሁሉ አጥብቀን እንድንሠራ ያደርጋል ብለዋል።

የአገራቱ ግጭት ከጀመረ በኋላ ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ላይ የሸቀጦች ዋጋ ጨምሯል ያሉት አቶ ዘመዴነህ፤ ስንዴንና መሰል ግብዓቶችን ከነሱ ያስገቡ የነበሩ ሃገራትና ኢትዮጵያ ራስን ለመቻል የሚያደርጉትን በሃገር ውስጥ የማምረት ትጋት ሽፋን እንዲሳድጉ ያደርጋል። ግጭቱም በክፉ ቀን የተገኘ መልካም አጋጣሚን ይዞ መጥቷል ብለዋል።

ግጭቱ የኢትዮጵያን የምግብ፣ ኢነርጂና ሌሎችም ቁሳቁሶች የዋጋ ግሽበት ከፍ አድርጎታል። ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ቀድሞውኑ ሲገቡም ጭምር ዋጋቸው ስለሚጨምርና የነዳጅ ዋጋም...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71654

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
"ፍቼ ጨምበላላ የቱሪስት መስህብ ከመሆኑ ባሻገር የፍቅርና የይቅርታ በዓል ነው" -መምህርና ደራሲ አለሙ ኪርባ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የፍቼ ጨምበላላ በዓል የቱሪስት መስህብ ከመሆኑ ባለፈ የፍቅርና የይቅርታ በዓል ነው ሲሉ መምህርና ደራሲው አለሙ ኪርባ ገለጹ።

መምህሩ የዘመን መለወጫ በዓሉን ትውፊትና ዕሴቱን በጠበቀ መንገድ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባም አሳስበዋል።

መምህርና ደራሲ አለሙ ኪርባ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ፍቼ ጨምበላላ ብዙዎች ሊታደሙበት የሚመኙት የፍቅር፣ የሰላም፣ የመረዳዳትና የይቅርታ በዓል ነው።

በዓሉ የአንድነትና የመተሳሰብ በመሆኑ ፍቼ ጨምበላላን የሚያከብር ሁሉ የበዓሉን ዕሴት በጠበቀ መልኩ ችግረኞችን በመርዳትና በመደጋገፍ ሊሆን እንደሚገባውም መምህር አለሙ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፍቼ ጨምበላላ ስለ ሃገር ሰላም፣ ስለ አዝመራው ደህንነት እንዲሁም ስለእንስሳቱ ጤንነት እንዲሁም ስለ መላው ሃገር ወደ ፈጣሪ የሚለመንበት ክብረ በዓል ነው ብለዋል።

በዓሉ ኢትዮጵያውያን ሰላማቸውን፣ ፍቅር አንድነትና ወዳጅነታቸውን የሚያጠናክሩበት ነው ያሉት መምህሩ፤ በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በመዋደድና ሰላምን በመፈለግ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71651

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የውስጥና የድንበር ዘለል የጸጥታ ችግሮችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ክልሉ አሳሰበ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በክልሉ የሚከሰቱ የውስጥና የድንበር ዘለል የጸጥታ ችግሮችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሠሩ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል አሳሰበ።

የጋምቤላ ክልል መንግሥት የፀጥታ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ትናንትና በጋምቤላ ከተማ አካሂዷል።

በወቅቱ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ፤ በክልሉ የውስጥና የድንበር ዘለል የጸጥታ ችግሮችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባል ብለዋል።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚዋሰነው የጋምቤላ ክልል ውስጥ በመግባት በነዋሪዎች ላይ ከሚፈጸሙት ጥቃት በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቀንድ ከብቶች በተደጋጋሚ ዘርፈው ሲወስዱ እንደነበር አስታውሰዋል።

የጥፋት ኃይሎች በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ሊያደርሱ የሚችሉትን ጥፋት ለመከላከል መንግሥት በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር /ጋነግ/ ብሎ የሚጠራው የአሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ ተላላኪ እኩይ ሴራውን ለማምከን የተለያዩ የጸጥታና ደህንነት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።

በተያያዘ የሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ጨምሮ በክልሉ ጠረፋማ አካባቢዎች....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71648

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከጃፓን የልማት ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ልዑክ ጋር ተወያዩ
****
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከጃፓን ልማት የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዶክተር ፍጹም በፕሮፌሰር ኬኒቺ ኦህኖ ከተመራው የኤጀንሲው ልዑክ ጋር የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ አተገባበር ያለበት ደረጃ፣ ውጤትና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ መክረዋል።

የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አተገባበርና የታለመላቸውን ውጤት ያመጣ ስለመሆኑ ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ የሦስት ዓመት ዕቅድ ተግባራዊነት ውጤታማነት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዶክተር ፍጹም ይህ እቅድ የተሳካ እንዲሆን በዋነኝነት በአገር በቀል እውቀትና ክህሎትን ለማጎልበት እንደሚሠራ የጠቆሙ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን ከውጭ አገራት የሚገኙ ድጋፎችን አስፈላጊነት አንስተው አብራርተዋል፡፡

እንደ ጃፓን ዐይነት የዓላማችን አገራት ያለፉበትን ሂደት ማየት እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ የገለጹት ዶክተር ፍጹም፣ ኢትዮጵያ በቀጣይ ይፋ ከምታደርገው የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ጋር በተገናኘም ምርትን በማሳደግ፣ በሰው ሃብት፣ በተቋም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በተሳካ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ትግበራ ዙርያ ከጃፓን ጋር በትብብር ሊሠራባቸው እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡

በፕሮፌሰር ኬኒቺ ኦህኖ በበኩላቸው ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ከኢንዱስትሪ ፖሊሲ ትግበራ ጋር በተገናኘ በትብብር ለመስራት ያላትን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ