Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.9K subscribers
39.9K photos
298 videos
7 files
5.74K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"ሃገራዊ ምክክሩን ለማሳካት የተረጋጋ ሰላምና አስተማማኝ ደህንነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል"
- አቶ አባተ ኪሾ
****
(ኢ ፕ ድ)

ሃገራዊ ምክክሩን ለማሳካት የተረጋጋ ሰላምና አስተማማኝ ደህንነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የቀድሞ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አባተ ኪሾ አመለከቱ።

በሃገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ በተገቢው መወጣት አለበትም ብለዋል።

አቶ አባተ ኪሾ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፤ ሃገራዊ ምክክር ለማካሄድ የታሰበው በሃገሪቱ መቀረፍ ያለበት አሳሳቢ ችግር በመኖሩ ነው። በየጊዜው እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮች መንስዔም አለመግባባቶች በመኖራቸው ነው። መንግሥትም በጉዳዩ ዙሪያ ተደጋጋሚ መግለጫ አውጥቷል፤ በአንዳንድ አካባቢዎችም እርምጃ እየወሰደ ይገኛል ብለዋል።

ከሁሉም በላይ ግን አለመግባባቶቹን ለመፍታት አይነተኛ መፍትሄ የሆነውን ሃገራዊ ምክክር ለማካሄድ የተረጋጋ ሰላምና አስተማማኝ ደህንነት መፍጠር የሁሉም ኃላፊነት መሆን እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

መንግሥት የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ቀዳሚ ተግባሩ በመሆኑ ሰሞኑን የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በጉዳዩ ዙሪያ ያወጣው መግለጫ የዚሁ አካል....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71641

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ለትግራይ የሚላከው እርዳታ ለሕዝቡ ሳይሆን ለሕወሓት ታጣቂዎች እየዋለ መሆኑን ትዴፓ ገለጸ

👉 የትግራይ ሕዝብ ሰቆቃ የሚያበቃው ሕወሓታዊ አስተሳሰብ ሲጠፋ ብቻ ነው፣
*****
(ኢ ፕ ድ)
ለትግራይ ሕዝብ የሚላከው እርዳታ ለሕዝቡ ሳይሆን ሕወሓት ራሱ ላደራጃቸው መደቦችና ታጣቂዎች እየዋለ መሆኑን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ገለጸ።

የትግራይ ሕዝብ ሰቆቃ የሚያበቃው ሕወሓታዊ አስተሳሰብ ሲጠፋ ብቻ እንደሆነም ተመላክቷል።

የትግራይ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሙሉብርሃን ኃይሌ በተለይም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል የሚላክ ቢሆንም ለሕዝቡ የሚደርስ እርዳታ የለም። እርዳታው ወደ ትግራይ ክልል ቢገባም ለሕዝቡ እየደረሰ አለመሆኑን ይልቁንም ለሕወሓት ታጣቂዎች እየተሰጠ መሆኑን ፓርቲያቸው ከተለያዩ ምንጮች እንዳረጋገጠ ገልጸዋል።

በሕዝብ ስም መነገድ የሕወሓት የዛሬ ባህሪው ብቻ ሳይሆን ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ ያለው ታሪክ እንደሚያስረዳ የገለጹት አቶ ሙሉብርሃን፤ ወደ ትግራይ ክልል የሚገባው የምግብ፣ መድኃኒትና ሌሎች መሰል እርዳታዎች.....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71644

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የፍትሕ አካላት የሐሰተኛና ጥላቻ ንግግር ወንጀልን የሚፈጽሙ ሰዎችን ለሕግ እንዲያቀርቡ ተጠየቀ
*******
(ኢ ፕ ድ)
የፍትሕ ሚኒስቴርን ጨምሮ ፖሊስ፣ የክልልና የፌዴራል የፍትሕ ተቋማት የሐሰተኛና ጥላቻ ንግግር ወንጀልን የሚፈጽሙ ሰዎችን ወደ ሕግ ማቅረብ እንዳለባቸው ተጠቆመ።

በፍትሕ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አወል ሱልጣን ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት ቁጥጥር ተፈጻሚ መሆን በሚገባው ደረጃ እየተፈጸመ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል።

ከዚህ በኋላ ሐሰተኛ የመረጃ ስርጭትን የሚያሰራጩ ሰዎች በአዋጁ ላይ የተቀመጡትን የወንጀል ቅድመ ሁኔታዎች እስኪያሟሉ ድረስ ፖሊስ ምርመራ መጀመር እንዳለበት፤ ማኅበረሰቡም መጠቆም እንደሚችል፤ ዓቃቤ ሕግም ወንጀል የመመርመርና የመምራት ኃላፊነት ስላለበት በዚህ ሂደት ውስጥም ፖሊስ የወንጀል ምርመራ እንዲጀምርና የተጣራ ምርመራ ካለ ክስ መስርቶ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶ ክርክር ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል። ይህ በተጨባጭ እንደሚከናወንም ነው ያስታወቁት።

ይህን ማድረግ ባለመቻላችን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ሰዎች ከመስመር ሲወጡና እንዲህ አይነት መረጃዎችን ሲያሰራጩ ቆይተዋል ያሉት ዳይሬክተሩ፤ በሐሰተኛ መረጃና ጥላቻ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71665

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጀ
በቀጣዮቹ 10 ዓመታት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን መኖሪያ ቤቶች እንዲገነቡ ይሠራል

👉 በአሁኑ ወቅት 2 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች እጥረት አለ
*****
(ኢ ፕ ድ)
መንግሥት በራሱ ከሚገነባቸው ቤቶች በተጨማሪ ሌሎች አጋር አካላትን በማሳተፍና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በቀጣዮቹ 10 ዓመታት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶች እንዲገነቡ እንደሚሠራ የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ።

ለኑሮ ምቹ ያልሆኑና ፈርሰው መሠራት ያለባቸውን አንድ ሚሊዮን ቤቶችን ሳይጨምር በአሁኑ ወቅት የሁለት ሚሊዮን ቤቶች እጥረት እንዳለም ተገልጿል።

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ታደሰ ከበበ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መንግሥት በራሱ ከሚገነባቸው በተጨማሪ ሌሎች አጋር አካላትን በማሳተፍና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም በቀጣዮቹ 10 ዓመታት 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቤቶችን እንዲገነቡ ይሠራል።

አሁን ባለው ደረጃ በከተሞች ያለው የቤት አቅርቦት እና ፍላጎት መካከል ሰፊ ልዩነት አለ ያሉት የቢሮ ኃላፊው፤ ለዚህም ከተሞች በፈጣን ዕድገት ውስጥ መገኘታቸው እና የሕዝብ ቁጥር ዕድገቱን...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71660

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
«የሩስያና የዩክሬን ግጭት እንደ ሃገር ራስን በምርት ለመቻል ለሚደረገው ጥረት እድል አምጥቷል»አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ
*******
(ኢ ፕ ድ)

የሩስያና የዩክሬን ግጭት ኢትዮጵያን በኢኮኖሚ ቢጎዳትም እራስን ለመቻል አስገድዶም ቢሆን እድል አምጥቷል ሲሉ የፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገለጹ።

አቶ ዘመዴነህ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ የሩሲያ እና የዩክሬን ግጭት የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ተፅዕኖ ቢያሳርፍም አስገድዶም ቢሆን ራስን በምርት ለመቻል እድሉን አምጥቷል። እራስን መቻል ላይ ባሉን አማራጮች ሁሉ አጥብቀን እንድንሠራ ያደርጋል ብለዋል።

የአገራቱ ግጭት ከጀመረ በኋላ ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም ላይ የሸቀጦች ዋጋ ጨምሯል ያሉት አቶ ዘመዴነህ፤ ስንዴንና መሰል ግብዓቶችን ከነሱ ያስገቡ የነበሩ ሃገራትና ኢትዮጵያ ራስን ለመቻል የሚያደርጉትን በሃገር ውስጥ የማምረት ትጋት ሽፋን እንዲሳድጉ ያደርጋል። ግጭቱም በክፉ ቀን የተገኘ መልካም አጋጣሚን ይዞ መጥቷል ብለዋል።

ግጭቱ የኢትዮጵያን የምግብ፣ ኢነርጂና ሌሎችም ቁሳቁሶች የዋጋ ግሽበት ከፍ አድርጎታል። ከውጭ የሚገቡ እቃዎች ቀድሞውኑ ሲገቡም ጭምር ዋጋቸው ስለሚጨምርና የነዳጅ ዋጋም...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71654

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
"ፍቼ ጨምበላላ የቱሪስት መስህብ ከመሆኑ ባሻገር የፍቅርና የይቅርታ በዓል ነው" -መምህርና ደራሲ አለሙ ኪርባ
*****
(ኢ ፕ ድ)
የሲዳማ ብሔር የዘመን መለወጫ የፍቼ ጨምበላላ በዓል የቱሪስት መስህብ ከመሆኑ ባለፈ የፍቅርና የይቅርታ በዓል ነው ሲሉ መምህርና ደራሲው አለሙ ኪርባ ገለጹ።

መምህሩ የዘመን መለወጫ በዓሉን ትውፊትና ዕሴቱን በጠበቀ መንገድ ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባም አሳስበዋል።

መምህርና ደራሲ አለሙ ኪርባ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ፍቼ ጨምበላላ ብዙዎች ሊታደሙበት የሚመኙት የፍቅር፣ የሰላም፣ የመረዳዳትና የይቅርታ በዓል ነው።

በዓሉ የአንድነትና የመተሳሰብ በመሆኑ ፍቼ ጨምበላላን የሚያከብር ሁሉ የበዓሉን ዕሴት በጠበቀ መልኩ ችግረኞችን በመርዳትና በመደጋገፍ ሊሆን እንደሚገባውም መምህር አለሙ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፍቼ ጨምበላላ ስለ ሃገር ሰላም፣ ስለ አዝመራው ደህንነት እንዲሁም ስለእንስሳቱ ጤንነት እንዲሁም ስለ መላው ሃገር ወደ ፈጣሪ የሚለመንበት ክብረ በዓል ነው ብለዋል።

በዓሉ ኢትዮጵያውያን ሰላማቸውን፣ ፍቅር አንድነትና ወዳጅነታቸውን የሚያጠናክሩበት ነው ያሉት መምህሩ፤ በመሆኑም በዓሉን ስናከብር በመዋደድና ሰላምን በመፈለግ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71651

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የውስጥና የድንበር ዘለል የጸጥታ ችግሮችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሊሠሩ እንደሚገባ ክልሉ አሳሰበ
*****
(ኢ ፕ ድ)

በክልሉ የሚከሰቱ የውስጥና የድንበር ዘለል የጸጥታ ችግሮችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሠሩ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል አሳሰበ።

የጋምቤላ ክልል መንግሥት የፀጥታ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ትናንትና በጋምቤላ ከተማ አካሂዷል።

በወቅቱ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ፤ በክልሉ የውስጥና የድንበር ዘለል የጸጥታ ችግሮችን ለመከላከል ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሠሩ ይገባል ብለዋል።

የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚዋሰነው የጋምቤላ ክልል ውስጥ በመግባት በነዋሪዎች ላይ ከሚፈጸሙት ጥቃት በተጨማሪ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቀንድ ከብቶች በተደጋጋሚ ዘርፈው ሲወስዱ እንደነበር አስታውሰዋል።

የጥፋት ኃይሎች በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ሊያደርሱ የሚችሉትን ጥፋት ለመከላከል መንግሥት በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ራሱን የጋምቤላ ነፃነት ግንባር /ጋነግ/ ብሎ የሚጠራው የአሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ ተላላኪ እኩይ ሴራውን ለማምከን የተለያዩ የጸጥታና ደህንነት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስታውቀዋል።

በተያያዘ የሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውርን ጨምሮ በክልሉ ጠረፋማ አካባቢዎች....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71648

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ዶክተር ፍጹም አሰፋ ከጃፓን የልማት ትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ልዑክ ጋር ተወያዩ
****
(ኢ ፕ ድ)

የኢፌዴሪ ፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ከጃፓን ልማት የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዶክተር ፍጹም በፕሮፌሰር ኬኒቺ ኦህኖ ከተመራው የኤጀንሲው ልዑክ ጋር የአስር ዓመት የልማት ዕቅድ አተገባበር ያለበት ደረጃ፣ ውጤትና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ መክረዋል።

የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አተገባበርና የታለመላቸውን ውጤት ያመጣ ስለመሆኑ ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበ የሦስት ዓመት ዕቅድ ተግባራዊነት ውጤታማነት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ዶክተር ፍጹም ይህ እቅድ የተሳካ እንዲሆን በዋነኝነት በአገር በቀል እውቀትና ክህሎትን ለማጎልበት እንደሚሠራ የጠቆሙ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን ከውጭ አገራት የሚገኙ ድጋፎችን አስፈላጊነት አንስተው አብራርተዋል፡፡

እንደ ጃፓን ዐይነት የዓላማችን አገራት ያለፉበትን ሂደት ማየት እጅግ ጠቃሚ እንደሆነ የገለጹት ዶክተር ፍጹም፣ ኢትዮጵያ በቀጣይ ይፋ ከምታደርገው የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ጋር በተገናኘም ምርትን በማሳደግ፣ በሰው ሃብት፣ በተቋም ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲሁም በተሳካ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ትግበራ ዙርያ ከጃፓን ጋር በትብብር ሊሠራባቸው እንደሚችል ጠቅሰዋል፡፡

በፕሮፌሰር ኬኒቺ ኦህኖ በበኩላቸው ጃፓን ከኢትዮጵያ ጋር ከኢንዱስትሪ ፖሊሲ ትግበራ ጋር በተገናኘ በትብብር ለመስራት ያላትን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
"ከኢድ እስከ ኢድ መርሐ ግብር ዲያስፖራው ከሃገሩ ጎን መቆሙን የሚያሳይበት ዕድል ነው" - ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ
******
(ኢ ፕ ድ)
ከኢድ እስከ ኢድ ሃገራዊ ጥሪ መርሐ ግብር ዲያስፖራው በደስታም ሆነ በኃዘን ወቅት ከሃገሩ ጎን መቆሙን የሚያሳይበትን ዕድል ፈጥሯል ሲሉ የመርሐግብሩ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ገለጹ።

ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ የከኢድ እስከ ኢድ ሃገራዊ ጥሪ መርሐግብር ዲያስፖራ ማኅበረሰብ ወደሃገሩ ገብቶ ከሕዝቡ ጎን መቆሙን የሚያሳይበት ዕድል መፍጠር ይችላል።

ሃገራዊ ጥሪውን ተከትሎ በመርሐ ግብሩ ለመታደም በርካታ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደኢትዮጵያ እየመጡ መሆኑን የጠቆሙት ኡስታዝ አቡበከር፤ ዲያስፖራዎቹም ወደትውልድ ሃገራቸው ሲመጡም በደስታና በጥሩ መንፈስ መሆኑን ገልጸዋል።

ሃገራዊ ጥሪውን መሠረት አድርገው የተሰናዱት መርሐግብሮችም ዲያስፖራውን ማኅበረሰብ ያማከሉ...

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71668

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መመሪያ በምስራቅ ጉጂ ዞን የመልካ ጉባ ወረዳን ከሸኔ ታጣቂ ቡድን ነፃ ማውጣቱን አስታወቀ
***********************
(ኢ ፕ ድ)
የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ጉጂ ዞን መልካ ጉባ ወረዳ ባደረገው ዘመቻ አካባቢውን ከሸኔ ታጣቂ ቡድን ነፃ ማድረጉን አስታወቀ።
በዚህ ዘመቻ በአካባቢው ለ4 አመታት ያህል በህዝቡ ላይ ስቃይ ሲያደርሱ ከነበሩ የቡድኑ ታጣቂዎች መካከል በርካታዎቹ መደምሰሳቸው ታውቋል።
የዕዙ የኋላ ደጀን አስተባባሪና የኦፕሬሽኑ መሪ ኮሎኔል ግርማ አየለ በዚህ ውጊያ ከ200 በላይ የሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን፣ ከ100 በላይ መቁሰላቸውንና 22 መማረካቸውን የገለፁ ሲሆን ከተደመሠሡት ውስጥም የአሸባሪው ህወሀት ታጣቂዎች እንደሚገኙበት ተናግረዋል።
መልካ ጉባ በተፈጥሮው በአስቸጋሪ የመሬት ገፅና ከፍተኛ የውሃ ሙላት ባለው ዳዋ ወንዝ መከበቡ፣ ሸኔን የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች በአካባቢው መገኘታቸው፣ ታጣቂ ቡድኑ ለአመታት በአካባቢው በመንቀሳቀስ ይዞታውን ማስፋቱ በዘመቻው የነበሩ ፈታኝ ሁኔታዎች ነበሩ ያሉት ኮሎኔል ግርማ ሰራዊቱ ሁሉንም ችግሮች እንደአመጣጣቸው በመመከት ድል ማስመዝገብ ችሏልም ብለዋል።
የዳዋ ወንዝ ከፍተኛ የውሃ ሙላትን እንደምሽግ በመጠቀም ለማጥቃት ሙከራ ያደረገውን የሸኔ ቡድንን ለመደምሰስ የሰራዊቱ ተነሳሽነት ከፍተኛ ነበር ያሉት ኮሎኔል ግርማ ዘመቻው የህይወት መስዋዕትነት ያልተከፈለበትና በጥንቃቄ የተመራ ተልዕኮ እንደነበርም ገልፀዋል።
ዘመቻው የጠላትን አንገት ያስደፋ፣ በርካታ የተዘረፉ ንብረቶችን ይዞ እንዳይወጣ ያደረገና ለአመታት ሰላም የጠማቸውን ህዝቦች የሰላም አየር የመለሰ ዘመቻ እንደነበርም ተናግረዋል።
ሽብርተኛው ሸኔ በቦታው በርካታ ዜጎችን በመግደል በጅምላ ቀብሯል ያሉት ኮሎኔል ግርማ መላው ህዝባችን የዚህን አረምኔ ቡድን መጥፎ ተግባር በመረዳት ልጆቹን ከዚህ ሽብርተኛ ቡድን ጥሪ እንዲጠብቅና መከላከያ ኃይሉን እንዲያግዝ ጥሪ አቅርበዋል።
ሶስት ቀናትን በፈጀው ውጊያ ተማርከው እጃቸውን ከሰጡ የሸኔ አባላት መካከል ወጣት ጉዮ አዲ፣ ወጣት መሃመድ ረሽድ እና ወጣት ሰለሞን አምቢሳ እንዳሉት የሸኔ ታጣቂ ቡድን በተለያዩ የማደናገሪያ ስልቶች በመጠቀም ወጣቱን እየመለመለ የቡድኑ መጠቀሚያ ማድረጉን ይናገራሉ።
ቡድኑ የኦሮሞን ህዝብ ከመጨቆንና የኦሮሞን ህዝብ ከመግደል ያለፈ ምንም ፋይዳ የሌለው ስብስብ መሆኑን የተናገሩት ምርኮኞቹ የኦሮሞ ወጣት የዚህ ሽብርተኛ ቡድን መሰረተቢስ ዓላማ ተጋሪና ፈፃሚ መሆን የለበትም ሲሉ መናገራቸውን ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ማህብራዊ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ አካላት እንዲጠየቁ ዩኒቨርሲቲው አሳሰበ
*****************
(ኢ ፕ ድ)
በወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈፀሙ አካላትን በሕግ ተጠያቂ ማድረግና ለቀጣይም ትምህርት በሚሆን መልኩ ጉዳዩን የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እንዲያውቀው መሥራት እንደሚገባ የጎንደር ዩኒቨርስቲ አሳሰበ።
በጎንደር ዩኒቨርስቲ የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ላይ የተካሄደውን ጅምላ ጭፍጨፋዎችና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አስመልክቶ ጥናት ያደረገው የጎንደር ዩኒቨርስቲ የጥናት ቡድን መሪ ረዳት ፕሮፌሰር ጌታ አስራደ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ ሕወሓት አካባቢውን መቆጣጠር ከጀመረበት ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ ከፍተኛ ኢ-ሰብዓዊና ስነልቦናዊ ግፎች ተፈጽመዋል።
ረዳት ፕሮፌሰሩ እንደገለፁት፤ ሕወሓት በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ በፈፀመው ግፍ የተነሳ ከእያንዳንዱ ቤተሰብ 26 ነጥብ 5 ከመቶ ለስደት ተዳርጓል፤ 19ነጥብ5 ከመቶ ታፍኖ የት እንደገባ አይታወቅም፣ እንዲሁም 29 ከመቶ
https://www.press.et/?p=71786