የጥላቻ ንግግሮች እና ሀሰተኛ መረጃዎች በስራው ላይ ተጽእኖ እንደፈጠሩበት ባለስልጣኑ ገለጸ
👉 መገናኛ ብዙኃን መረጃ የሚከለክሉ ተቋማትና አካላትን ሊያጋልጡ ይገባል
****************
(ኢ ፕ ድ)
የጥላቻ ንግግሮችና ሀሰተኛ መረጃዎች በስራው ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደፈጠሩበት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ገለጸ። መገናኛ ብዙኃን መረጃ የሚከለክሉ ተቋማትና አካላትን ማጋለጥ እንደሚኖርባቸው የሕግ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አሳሰበ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትህ እና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ትናንት ገምግሟል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ እድሪስ የተቋማቸውን የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ የሐሰት መረጃና የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት በኩል አሁንም ፈተና ሆኗል። ሚዲያ የአገር ግንባታ፣ የሕዝብ አብሮነትን የሚያጠናክሩ መሆን ይኖርባቸዋል። ችግር ሲፈጠርም ችግር አመላካች ሊሆኑ ይገባልም ነው ያሉት።
የጥላቻ ንግግርንና ሐሰተኛ መረጃ ይዘትና በአገር ሰላምና ደህንነት ላይ ተጽእኖ የመፍጠር አዝማሚያ ያላቸውን በመለየት የህግ ተጠያቂነታቸው እንዲረጋገጥ መረጃ በማደራጀት ለሚመለከታቸው የሕግ አስፈጻሚ አካላት ማቅረቡንም ጠቁመዋል።
መረጃ በሌለበት ሁኔታ ሚዲያው ሚዛን አልጠበቅክም ማለት አንችልም። ጋዜጠኞች ለተሳሳተ መረጃ ከሚዳርጋቸው መካከል አንዱ የመረጃ እጥረት መሆኑንም አመልክተዋል። መረጃ የሚከለክሉ አካላት ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባና ባለስልጣኑ በዚህ ረገድ ያለውን ችግር ለመፍታት..
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71917
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

"የመቻቻል እሴታችንን ለማስጠበቅ የእምነት አባቶች ተቀራርበው መነጋገር ይጠበቅባቸዋል" -ሙሺድ አስማማው አህመድ
******************
(ኢ ፕ ድ)
በየእምነት ተቋማቱ ያሉ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች የቆየውን የሕዝቡን ተቻችሎ የመኖር እሴት ለማስቀጠል ተቀራርበው መነጋገርና ለሀገር ሰላም በጋራ መስራት እንደሚገባቸው ሙሺድ አስማማው አህመድ አስታወቀ።
ሙሺድ አስማማው አህመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በየእምነት ተቋማቱ እየተፈጠረ ያለውን አለመግባባት ለመቅረፍ እንዲሁም እየጠፋ ያለውን የመከባበርና የመቻቻል እሴት ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ ለመመለስ ያስችል ዘንድ ሁሉም የሃይማኖት መሪዎችና አባቶች ተቀራርበው መነጋገርና በጋራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል።
‹‹በተለይ አሁን ያለንበት ወቅት ብዙ ነገሮች የተበላሹበት ነው›› ያለው ሙሺድ አስማማው፤ ከዚህ ቀደም ግን የእምነት ተቋማቱ የታጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ ወይም ደግሞ ነገሮች ሲበላሹ እንዲያስተካክሉ የእምነት አባቶች ሚና...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71928
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
******************
(ኢ ፕ ድ)
በየእምነት ተቋማቱ ያሉ የሃይማኖት አባቶችና መሪዎች የቆየውን የሕዝቡን ተቻችሎ የመኖር እሴት ለማስቀጠል ተቀራርበው መነጋገርና ለሀገር ሰላም በጋራ መስራት እንደሚገባቸው ሙሺድ አስማማው አህመድ አስታወቀ።
ሙሺድ አስማማው አህመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ በየእምነት ተቋማቱ እየተፈጠረ ያለውን አለመግባባት ለመቅረፍ እንዲሁም እየጠፋ ያለውን የመከባበርና የመቻቻል እሴት ቀድሞ ወደነበረበት ሁኔታ ለመመለስ ያስችል ዘንድ ሁሉም የሃይማኖት መሪዎችና አባቶች ተቀራርበው መነጋገርና በጋራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል።
‹‹በተለይ አሁን ያለንበት ወቅት ብዙ ነገሮች የተበላሹበት ነው›› ያለው ሙሺድ አስማማው፤ ከዚህ ቀደም ግን የእምነት ተቋማቱ የታጣሉ ሰዎችን ለማስታረቅ ወይም ደግሞ ነገሮች ሲበላሹ እንዲያስተካክሉ የእምነት አባቶች ሚና...
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
https://www.press.et/?p=71928
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወልድያ ከተማ የሚገኙትን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ዕዞችን ጎበኙ
************************
(ኢ ፕ ድ)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ የሚገኙትን የሀገር መከላከያ ሠራዊት የተለያዩ ዕዞችን ጎበኙ።
መጪውን የኢድ አልፈጥር በአል ምክንያት በማድረግ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአማራ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እና ከፍተኛ የመንግሥት እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር በመሆን፣ በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ የሚገኙትን የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የደቡብ፣ ምሥራቅ፣ 6ኛ እና 8ኛ ዕዞችን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለመኮንኖች ባደረጉት ንግግር ዝግጁነታቸውን አጠናክረው በመቀጠል 1) የማሸነፍ ዕድላቸውን እንዲያሰፉ፣ 2) ድል አድራጊ ሰብዕናን እንዲገነቡ እና 3) ለስጋት ተጋላጭነትን እንዲቀንሱ አበረታተዋል።
ኃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ማፍራት እና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለማስረከብ መንገዱን መጥረግ አስፈላጊ መሆኑ መግለጻቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

የብላቴናው ራስን «ሰው» የማድረግ ትግል
.....መልካሙ ጠዋት ጠዋት ከተማሪዎች ቀድሞ በመግባትና ማታም አርፍዶ በመውጣት እንዲሁም እሁድና ቅዳሜ ሳይቀር ግቢውን እያጸዳና ችግኞችን እየተንከባከበ መማር ይጀምራል።
...ትምህርት ቤቱን የተቀላቀለው ከግምሽ ሴሚስተር በኋላ ስለነበር ለነገሮችም አዲስ እንደመሆኑ የሶስተኛው ኳርተር (ሶስተኛው ሩብ አመት) ውጤት ሲገለፅ ከአስራ አራት ተማሪዎች አስራ ሁለተኛ ደረጃ ይወጣል። ትምህርት ቤቱ በአራተኛው ኳርተር ካላሻሻለ እንደሚያባርረው ነግሮት አንድ እድል ይሰጠዋል።
መልካሙ ሰነፍ ሆኖ አልነበረም፤ ለጥናት የሚሰጠው ጊዜ ስላልነበረው ነው። ኋላ ግን ከሥራው ውጭ ያለውን ጊዜ በሙሉ ለትምህርቱ በመስጠት ጠንክሮ በማጥናት በአራተኛው ሩብ ዓመት ከክፍሉ ሶስተኛ ይወጣል።
በቀጣይ ዓመትም ሰባተኛ ክፍልን እዚያው ተምሮ በመጀመሪያው ኳርተር አንደኛ ደረጃ ይወጣል። አብዛኛውን ጊዜውን ለትምህርቱ መስጠቱን ተከትሎ እንደቀድሞው ተሯሩጦ በመሥራት ገቢውን ማሳደግ ስላልቻለ ኑሮ ይከብደው ጀመር።
https://www.press.et/?p=71967

"የዒድ አል ፈጥርን ዋዜማ ከወልድያ ከተማ ሕዝብና በአካባቢው ካለው ሠራዊታችን ጋር በማክበሬ ደስታ ተሰምቶኛል። ጀግናው ሠራዊታችን የሕዝቡን ደኅንነትና ልማት በደሙ ለማስከበር ወትሮ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል። ይህንን ሕዝብና ሠራዊት በዓላማ አንድነት ያጸናውን ግንብ፣ እንኳን ሊደፍሩት ሲጠጉት አስፈሪ ነው"
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ
"የከፍታ ማማ ላይ ወጥተው የምናያቸው ሀገራት ለኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ በሰጡት ትኩረት ነው"
- ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
***************
(ኢ ፕ ድ)
የከፍታ ማማ ላይ ወጥተው የምናያቸው ሀገራት መነሻቸው ለኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ በሰጡት ትኩረት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
የአምራች ኢንደስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ "ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ ተጀምሯል።
ንቅናቄው 10 ሺህ 500 አምራች ኢንዱስትሪዎችን ቁጥር ወደ 22 ሺህ ለማሳደግም ያግዛል ተብሏል።
እድገት ያለ ጥረትና ድካም ከቶውንም አይታሰብም፤ የዕድገት ራዕያችን ማጥራት፣ ለሥራ ያለንን ፍቅርና ትጋት ማሳደግ፣ ጊዜያችንንና ሀብታችንን በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል።
በከተሞች ለስራ ፈላጊዎች የተለያዩ አማራጮችን ለማመቻቸት የስራ እድል ማጠናከርና የተቀናጀ የኢንዱስትሪ ድጋፍን ማከናወን ዋና አጀንዳችን ሊሆን ይገባል ያሉት ከንቲባዋ፣ የከፍታ ማማ ላይ ወጥተው የምናያቸው ሀገራት መነሻ ለኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ የሰጡት ከፍተኛ ትኩረት ነው።
የስራ መዳረሻ አላማው የስራ ክቡርነትን ባህል በማድረግ ፤ የማምረትና ሃገር ውስጥ ፍጆታን ከመሸፈን ባሻገር በአለም ገበያ ውስጥ በብቃት መግባትን መሰረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው የሚሰሩ እጆችን ከስራ ጋር በማገናኘት ከተለመደው መንፏቀቅ ለመውጣት የተለየ ንቅናቄ አስፈልጓል ብለዋል፡፡
በአቅራቄ መድረኩ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ አቶ መላኩ አለበል የኢንደስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ የፌደራልና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የኢንደስትሪ ባለቤቶች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።