Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ – Telegram
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/
25.8K subscribers
40K photos
304 videos
7 files
5.76K links
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.
Download Telegram
"የከፍታ ማማ ላይ ወጥተው የምናያቸው ሀገራት ለኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ በሰጡት ትኩረት ነው"
- ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ
***************
(ኢ ፕ ድ)

የከፍታ ማማ ላይ ወጥተው የምናያቸው ሀገራት መነሻቸው ለኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ በሰጡት ትኩረት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።

የአምራች ኢንደስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ "ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል መሪ ቃል የንቅናቄ መድረክ ተጀምሯል።

ንቅናቄው 10 ሺህ 500 አምራች ኢንዱስትሪዎችን ቁጥር ወደ 22 ሺህ ለማሳደግም ያግዛል ተብሏል።

እድገት ያለ ጥረትና ድካም ከቶውንም አይታሰብም፤ የዕድገት ራዕያችን ማጥራት፣ ለሥራ ያለንን ፍቅርና ትጋት ማሳደግ፣ ጊዜያችንንና ሀብታችንን በአግባቡ መጠቀም ይገባል ብለዋል።

በከተሞች ለስራ ፈላጊዎች የተለያዩ አማራጮችን ለማመቻቸት የስራ እድል ማጠናከርና የተቀናጀ የኢንዱስትሪ ድጋፍን ማከናወን ዋና አጀንዳችን ሊሆን ይገባል ያሉት ከንቲባዋ፣ የከፍታ ማማ ላይ ወጥተው የምናያቸው ሀገራት መነሻ ለኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ የሰጡት ከፍተኛ ትኩረት ነው።

የስራ መዳረሻ አላማው የስራ ክቡርነትን ባህል በማድረግ ፤ የማምረትና ሃገር ውስጥ ፍጆታን ከመሸፈን ባሻገር በአለም ገበያ ውስጥ በብቃት መግባትን መሰረት ያደረገ መሆን ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የስራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው የሚሰሩ እጆችን ከስራ ጋር በማገናኘት ከተለመደው መንፏቀቅ ለመውጣት የተለየ ንቅናቄ አስፈልጓል ብለዋል፡፡

በአቅራቄ መድረኩ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ አቶ መላኩ አለበል የኢንደስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር፣ የፌደራልና የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የኢንደስትሪ ባለቤቶች መገኘታቸውን የአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ መጪውን የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ማእድ አጋሩ
******
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ መጪውን የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ከ101 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ማእድ አጋሩ።

ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ማእድ ባጋሩበት ወቅት እንደገለጹት፣ የኑሮ ውድነቱ ጫና ለፈጠረባቸው ዜጎች ማእድ የማጋራት ስራ እየተሰራ ነው። ካለን ማካፈል አያጎልም በማለት የተለያዩ ድርጅቶች ድጋፍ እያደረጉ ነው ብለዋል።

ይህን ጊዜ በመደጋገፍ ማለፍ አለብን ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰብ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አስፋው ተክሌ እንደተናገሩት፣ የኑሮ ውድነቱን ለመቅረፍ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ካልን ማካፈል የማይዳሰስ ሀብታችን ነው። በዚህም በየደረጃው የሚገኙ የህብረተስብ ክፍሎችን በማስተባበር ድጋፍ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዛሬው ዕለት ከአንድ መቶ አንድ ሺ በላይ ለሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ማእድ ማጋራት ተችሏልም ብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ሳምንታት ለ240 ሺ ዜጎች ማእድ ያጋራ ሲሆን ለቀጣይ ሶስት ወራት የሚቆይ ተግባር ነው ተብሏል።

በሞገስ ተስፋ

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ከመኖሪያ ቤት ጀርባ በድብቅ የተቀመጠ 10 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፖሊስ አሰታወቀ
******
(ኢ ፕ ድ)

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በጋራ ባደረጉት ክትትል በቦሌ ክፍለ ከተማ ከመኖሪያ ቤት ጀርባ በማገዶ እንጨት ተሸፍኖ በድብቅ የተቀመጠ 10 ክላሽንኮቭ ጠብመንጃ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለፀ፡፡

ከህብረተሰቡ በተገኘው ጥቆማ መነሻነት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር የዋለው 7 ባለሰደፍ እና 3 ታጣፊ ክላሽን-ኮቭ ጠብመንጃ ነው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳስታወቀው የጦር መሳሪያው የተያዘው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አቦ መሻገሪያ መቃብር ጀርባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሚገኝ መኖሪያ ቤት ጀርባ ማገዶ ማስቀመጫ ስፍራ ላይ በሸራ ተጠቅልሎ በእንጨት ተሸፍኖ በድብቅ የተቀመጠ ነበር፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ ሲሆን ህብረተሰቡ ህገ ወጥ የጦር መሳሪ ዝውውር በህዝብ እና በሃገር ላይ የሚያመጣውን የደህንነት አደጋ ተገንዝቦ ወንጀሉን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ ጥቆማ እና መረጃ በመስጠት እያበረከተ ያለውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል፡፡
ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ