FRESHMAN TIPS – Telegram
FRESHMAN TIPS
1.4K subscribers
636 photos
36 videos
254 files
144 links
For Promotion Dm me @TechnerdGuy

🔴 ውድ የ freshman tips famoch እንኳን ወደ groupachen  በስላም መጣቸሁ  እይልን ።
🔷 ይሄ group create የተደረገው for grade 12 up to university level
በዚ💪 group የሚይገኙት ነገር
🙋Unlimited knowledge
🙋 Educational tips
🙋Info about Campus
Download Telegram
#share #share channel for your friends💪💪💪💪💪💪

@examanswer1
እኛም ግብረሰዶማዊነት እንቃወማለን 💪💪💪💪

#no more 🙅🙅🙅🙅🙅🙅🙅🙅
👍3
📌መጀመሪያ ግቢ ስንደርስ ማን ጋር ነው ምንገናኘው 


📚 ግቢ በር ላይ ከመኪና ኦር ከታክሲ እንደወረዳቹህ በመጀመሪያ የምታገኙት እንኳን ደህና መጣቹህ የሚል ፈገግ ያለ ፊት ነው ። ( like አስጌ ዴንዴሾ ) እዚህ ጋር መርሳት የሌለባቹህን ፤ ላገጠጠላቹህ በሙሉ ሻንጣ እንዳትሰጡ በተለይ መናሀሪያ የምትወርዱ ከሆነ በጣም ተጠንቀቁ አንገታቸው ላይ or ደረታቸው ላይ ባጅ ያጠለቁ እሱንም የዩንቨርሲቲው ማህተም ያለበት መሆኑን ቼክ አርጉ አንዳንድ ከተሞች ላይ በጣም የተደራጁና ረቀቅ ያሉ ሌቦች ስለሚኖሩ be take care. የትኛውም ግቢ አዲስ ተማሪዎች በሚገቡበት ቀን በር ላይ የተለየ ዝግጅት በማድረግ ጥብቅ ፍተሻ ይደረጋል ።

📚 ማንኛውም ተማሪ የያዘውን ሻንጣ ከፍቶ ሳያስፈትሽ እግሩ ወደ ግቢ አይገባም ። ከፍተሻው በተጨማሪ  ግን ሁሉም ተማሪ የዶርምና ብሎክ ቁጥር ማወቅ አለበት እሱም ከግቢ ውጭ ወይም ግቢ ውስጥ ይለጠፋል አንዳንዶች ግቢዎች ደግሞ ዌብሳይት ላይ አስቀድመው ይለቃሉ። የብሎክና ዶርም ቁጥራችሁን ካወቃቹህ ጓዛችሁንም ካስፈተሻቹህ በኋላ ቀጥታ የምትሄዱት ወደ ዶርም ነው ።(ነባር ተማሪዎች ብሎክ ድረስ ይሸኟቹሃል)
ብሎካቹህ ጋር ስትደርሱ ground ላይ የብሎክ ሃላፊው(ፕሮክተር) ቢሮ በመስኮት በኩል ዶርም ቁጥራችሁን፣ ስም፣ phone number እና ፎቶ በመስጠት ፈርማቹህ የዶርም ቁልፍ ትቀበላላቹህ ።( ቁልፍ የሚሰጠው ቀድሞ ለመጣ አንድ የዶርም አባል ብቻ ነው ከተቀደማቹህ ቁልፍ የተሰጠውን ዶርሜት ስልክ ቁጥር ተቀብላቹህ መደወል ነው ።) ዶርም ስትገቡ የመጀመሪያ ሰው ከሆናቹህ ያሻችሁን አልጋና ሎከር መርጣቹህ የመያዝ ሙሉ መብት አላቹህ ። ደስ ካላችሁም ትራስ ምናምን መቀያየር ችቡድ ሰባራ ከሆነ እሱንም መቀየር... ብቻ በዶርሙ ላይ የተመቻችሁን የግል ንብረት ማሽከርከር ትችላላቹህ coz ማንም በቦታው ላይ የለምና ።
ከተቀደማቹህ ግን ከቀደማቹህ ሰው ጋር ሳትጋፉ ያገኛችሁትን ፤ አደራ ግን እንዳትጨቃጨቁ።


📚 ሌላው ዶርም ስትገቡ አንሶላና ትራስ ጨርቅ ምናምን ሳትጠቀሙ ጋደም ማለት ቢያምራቹህ እንኳ እንዳተኙ coz ፎከታም ትሆኑብኛላቹህ(biology ላይ የተማራችሁትን አትርሱ fungus+virus) የዶርም ጣጣችሁን ከጨረሳችሁ ቀጥታ የምትሄዱት ወደ register ይሆናል (በስራ ሰዓት ብቻ) አመሻሽ ላይ ግቢ ከደረሳቹህ ለምዝገባ ስለማትደርሱ የዶርማችሁን ጣጣ ለመጨረስ ሞክሩ ለምዝገባው አታስቡ በነገታው መመዝገብ ትችላላቹህ ።

   ምዝገባ ቦታ ላይ ያለው process 


📚 በመጀመሪያ ክላሰር ወረቀት ትገዙና የሚሰጣችሁን ፎርም ትሞላላቹህ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ኦሪጂናሉንና ኮፒውን ትጠየቁና ኦሪጂናሉ ይመለስላቹሃል ። ፎቶም ትጠየቃላቹህ
በሌላ መስኮት ደግሞ ID ምናምን ታወጣላቹ ከዛ ትንሽ ትንቀዋለሉና ትጨርሳላቹህ ። Above ሁለት ሺህ ተማሪ ምናምን በአንድ መስኮት ስለሚስተናገድ በጣም መጨናነቅ ይኖራል ቻል ማድረግ ነው ።

📚 ምዝገባ ከጨረሳቹህ መታወቂያ ከተቀበላቹ ዶርም ሂዳቹ ደስ ካላቹህ ተገልብጣቹህ ለጥ ማለት ትችላላቹህ ። አንዳንድ ግቢዎች ላይ መጨናነቁ በከፊል ሊቀንስ ይችላል ። አንዳንዶች ጋር ደግሞ ባስ ይላል ። ተማሪዎችም በተመሳሳይ መልኩ ይሆናል register ላይ ግን እንደፍሬሽ አይንከራተቱም ID ማሳደስ ብቻ ሌላው ነገር በሙሉ ተመሳሳይ ነው ።


ይሄ ካወቃችሁ ኮ አቤት በቃ ፍሬሽ ሳትሆኑ ግቢ ገባችሁ ማለት ነው ።

📌 Join and share 👇👇

FRESHMAN TIPS
@examanswer1
Haramaya University Remedial Students Result.pdf
2 MB
#Haramaya University Remedial Result

#SHARE
Share share please 🙏For remedial students
@examanswer1
The Dutchman invented an autonomous device for collecting garbage in the ocean, powered by solar energy. If things continue at this pace, then in 20 years the ocean will be 90% cleaner from garbage.

#General_knowledgeTM
👍2
Adding story to ur telegram is free for all users u can u use it new

Dont forget to update ur tg app🙏🙏
1
Guys now telegram story is available for everyone (Without telegram premium )
So update your app and enjoy it
Serway Physics, 9th edition.pdf
53.1 MB
# ቀጣይ ዩኒቨርስቲ ለምትገቡ የGrade 12 ተማሪዎች ዛሬ ለGeneral physics የሚሆን Guide book recommend ላድርጋቹ

SERWAY PHYSICS 9TH EDITION

ስለ መጸሀፉ እንዴት እንደ ምትጠቀሙበት  እና ፈተና እንዴት እንደ ምሰሩበት ማወቅ ከፈለጋችሁ channelu join belut😉😉

we r stemeducation


Link
@examanswer1
@examanswer1
.
👍2
የጂኒየስነት ሚስጥር .....!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
       ክፍል »1

📚  የአጠናን ዘዴዎች
             
👨‍💻ከራሴ ልምድ በመነሳት ስለ አጠናን ዘዴዎች
               አንዳንድ ነገሮችን ላንሳላችሁ

🅾 በመጀመሪያ ስታጠኑ በተቻላችሁ መጠን ላለመጨናነቅ ሞክሩ። ስለ ውጤት መውረድ ወይም ስለትምህርቱ ክብደት እያሰባችሁ በጭራሽ ለማጥናት አትሞክሩ ምክንያቱም ምንም ትርፍ የለውም። ራሳችሁን ዘና አድርጉ
#motivated ሆናችሁ አጥኑ እመነኝ ትኩረት እስከሰጣችሁት ድረስ የማይሳካ ምንም ነገር የለም። አመናችሁኝ እንቀጥል ..!

የተወሰኑ እኔን የጠቀሙኝን የጥናት ዘዴዎች ልንገራች ፤ ተከተሉኝ ፦

💥 ጥያቄ አውጡ 🤔

እስካሁን ከብዙ ሰዎች እንደሰማችሁት ጥያቄዎችን መስራት ውጤታማ የሆነ የጥናት ዘዴ ነው። የ
#worksheet , #አጋዥ መፅሐፍት ፣ እንዲሁም #text book  ጥያቄ መስራት ጠቃሚ እንደሆነ ታውቃላችሁ ብዬ አስባለሁ። ዛሬ እኔ ሌላ ቴክኒክ ላሳያችሁ....ምን በሉኛ     በራሳችሁ ጥያቄ አውጡ።

❇️ እኔ አስተማሪ ብሆን ኖሮ ምን ጥያቄ ነበር ልጆቼን የምፈትናቸው ብላችሁ አስቡ። ይሄንኑ ጥያቄ ራሳችሁን መልሳችሁ ፈትኑ። ከጓደኞቻችሁ ጋር ስሩት ። ለምን ይጠቅማል ያላችሁ እንደሆነ ከማንበብ በተጨማሪ የጥያቄ አወጣጥ (exam question concept) ታገኙበታላችሁ ።

ላውጋችሁማ

እኔ የማልረሳው አንድ ታሪክ አለ። የ elementary ተማሪ እያለሁ ሳይንስ አስተማሪያችን ፈተና ሲቃረብ አካባቢ አሳይመንት ሰጠን። አሳይመንቱ እኛ በራሳችን ጥያቄ አውጥተን ከነመልሱ ሰርተን ማስገባት ነው።  የሚገርመው ነገር እኔ ያወጣሁአቸውን ጥያቄዎች ፋይናል ፈተና ላይ በብዛት አገኘሁአቸው። የመምህራንን exam question psychology ስታገኙ ትምህርቱ ልክ እንደ ውሀ ቀላል ነው ሚሆንላችሁ። ፡አገኛቹኝ😉?

    📛concept ያዙ

በጣም ብዙ ተማሪዎች በደንብ እያጠኑ ግን ውጤታማ ሳይሆኑ ሲቀሩ ይታያል።
ለምን ከተባለ የሚያነቡት መፅሐፉ ላይ ያለውን ፅሁፍ እንጂ Conceptun አይደለም። የምናነበው ነገር ስለምንድነው  እያወራ ያለው ምን እንድንይዝ ነው የተፈለገው ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን።

⛔️ቆይ ጥናታችን ውጤታማ እንዲሆን ምን እናድርግ

💥 ክላስ አትቅጣ /ጪ

ይብዛም ይነስም teacherሩ የሚነግረን concept ዋጋ አላት። ጂኒየስም ይሁን አይሁን የሚያስረዳበት መንገድ ይጣፍጥም አይጣፍጥ ክላስ ተከሰት/ቺ ።

🟥 ከጓደኞቻችሁ ጋር ተጠያየቁ። 

አሪፍ ጀማ ሰርታችሁ ጥያቄ ፍለጡ ፤ ጥሩ እና መልካም ጓደኞች ጋር የሚደረግ ጥረት ትልቅ effect አለው ።

💥 informal way ተጠቀሙ።

በጨዋታ (በቀልድ) አስታካችሁ የያዛችሁትን ዕውቀት ልትረሱ ብትፈልጉ ራሱ አትችሉም ፣ በፌዝ መልክ አውሩት።በወሬ መሀል ጣል ጣል ማረግን ልመዱ:: ገቢቶ😊😉

እንደ ጉርሻ

🚧 ከformal ጥናት ውጪ በሆናችሁ ጊዜ በማያጨናንቃችሁ መልኩ meditate አድርጉት ። ተመስዕጦ ራስን ለማግኘት ምርጥዬ መንገድ ነው ። (የግል ምክር )

‼️ በተለየ መልኩ ደግሞ 💭

አልችልም የሚል ሀሳብን አስወግዱ😎። ትችላላችሁ 💪...! መቻልን ተሸክሞ የመጣ የለም ሁሉም በምድር በጥረቱ አበጅቶት ነው ። 

📪 በሚመቻችሁ ጊዜና ቦታ አጥኑ። ቀን or ማታ  ላይብረሪ ወይም ከሰው ጋር  ብቻ እናንተ በለመዳችሁት setting ( የምታውቁትን ጎበዝ ተማሪ ሳይሆን የራሳችሁን መንገድ ፍጠሩ ..!)

👉👉ፈታ በሉ ፤ ግን ከትምሮ መቼም አትራቁ። because
#ርቆ_መመለስ_ከባድ_ነው‼️ ሚያረግባችሁ ...ስትኖሩ ተማሪ መሆናችሁን አትርሱ ...!

👨‍💻እንግዲህ ካለኝ ልምድ በመነሳት ይህንን
          ፃፍኩላችሁ ...

 

‼️.... part V  ይቀጥላል....
                      ‼️  ....to be continued.
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
      For more  Join us 👇👇👇
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
🅾 For Fast and Reliable info..⬇️
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
         ⬇️ Join and Share ⤴️👇
      ╔═══════════╗
      ❇️      @examanswe1     ❇️
      ❇️      @examanswer1    ❇️
      ╚═══════════╝
👍1
👨‍💻ለተማሪዎች👩‍💻
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ለተማሪዎች የሚጠቅሙ 4 የአንድሮይድ አፕሊኬሽኖች ልንገራቹ፡

❇️ተማሪዎች፤ የሃይ ስኩል እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደራራቢ አሳይመንቶች ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡
ተደራራቢ የቤት ስራዎች፣የግሩፕ አሳይመንቶች፣ፕሮጀክቶች፣ ተደራራቢ ጥናቶች ተማሪዎች ላይ ጫና ሊያበዛ ይችላል፡፡ ይሄ ጫና ደሞ ጭንቀት ሊፈጥር ይችላል፡፡   

⛔️በትምህርት ወቅት ጫና እንዳይፈጠርባችሁ ዋናውና ቁልፍ መፍትሔ ለየአንዳንዱ ነገር ፕሮግራም ማዘጋጀት ነው፡፡

⭕️ቀጥሎ የምነግራችሁ 4 አፕሊኬሽኖች ተማሪዎች በትምህርት ወቅት ጫና ሳይፈጠርባቸው ትምህርታቸውን ባግባቡ በመከታተል በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ የሚረዱ አፕሊኬሽኖች ናቸው፡፡ ዓለም ዓቀፍ እውቅናም የተሰጣቸው አፕልኬሽኖች ናቸው።

1️⃣ School Planner Application 🧲
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ይህ አፕሊኬሽን የቤት ስራዎችን፣ የግሩፕና የግል አሳይመንቶችን፣ፕሮጀክቶችን፣የእያንዳንዱን ክላስ ሰዓትና ቀን…ማንኛውም ትምህርት ነክ አክቲቪቲዎቻችሁን ኦርጋናይዝ ያደርግላችኋል፡፡ ፕሮግራም ያወጣላችኋል።

ይህ አፕሊኬሽን በየቀኑ በፕሮግራማችሁ መመሰረት በየቀኑ መስራት ያለባችሁን ለምሳሌ ጥናት ወይም የቤት ስራ፣የግሩፕ አሳይመንት፣ የላብራቶሪ ሙከራ ….ባጠቃላይ  ጠዋት ምን ማድረግ እነዳለባችሁ፡፡ ከሰዓት ምን መስራት እንዳለባችሁ ማታ ምን መፃፍ እንዳለባችሁ ያስታውሳችኋል….

የምታስረክቡት አሳይመንት ወይም ፕሮጀክት ካለባችሁ የምታስረኩብበት ቀን "በዚህ ቀን ነው፡፡ ቀኑ እየደረሰ ነው…" እያለ ያስታውሳችኋል፡፡

2️⃣Brilliant 🧲
▬▬▬▬▬
❇️ ይህ አፕሊኬሽን ደሞ በተለይ በሂሳብ፣ በሳይንስና በኮምፒውተር ሳይንስ ጥሩ ውጤት ለማምጣት በጣም የሚጠቅም አፕ ነው፡፡

❇️ይህ አፕሊኬሽን እየሸመደዳችሁ እንዳታጠኑና በተለይ ረጃጅም ቃላት የሚበዙባቸው የትምህርት አይነቶችን ዘርዘር ያሉ ገለፃዎችን በመጠቀም ሳትሰለቹ  ትምህርቶቹን በቀላሉ እንድታጠኗቸውና እንዲገባችሁ ይረዳል ።

3️⃣Grammarly  🧲
▬▬▬▬▬▬▬
ይህ አፕሊኬሽን ደሞ በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ያሳድጋል፡፡

የተለያዩ ESSAY በእንግሊዘኛ ስትፅፉ  የግራመር ስህተታችሁን ያርማል፣ትክክለኛ ቃላት እንድትመርጡ ይረዳል፡፡ ረጃጅም አረፍተ ነገሮችን ስትፅፉ የሲንታክስ ስህተታችሁን ያርማል፡፡

በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ቀስበቀስ ያሳድጋል፡፡

4️⃣Mendeley  🧲
▬▬▬▬▬▬
Research በምትሰሩበት ግዜ ለጥናታችሁ  የሚሆኑ የተለያዩ ሪሶርሶች እንዴት እንደምታገኙ ይረዳችሃል፡፡

❇️ለጥናታችሁ ወይም ለሪሰርቻችሁ የሚጠቅሙ መፅሃፎችን፣ጥናታዊ ፅሁፎችን፣ ምክረ ሃሳቦችን እንዴት እንደምታዘጋጁ ያስተምራቸኋል፡፡

❇️ለሪሰርቻችሁ የተጠቀማችሁባቸውን የተለያዩ የጥናታዊ ፁሁፎች ፃሃፊዎችን፣የመፅሐፍት ደራስያን ፣ምሁራንን ስማቸውን በመጥቀስ ጥናታችሁ ላይ በማካተት እንዴት ወይም ክሬዲት እንደምትሰጧቸው ያስተምራችኋል፡፡

   🛑Share to Your Friends kindly 🛑  
Hurley - A Concise Introduction To Logic 13th ed 2018.pdf
10.6 MB
ለ ''logic and cirtical thinking'' የሚጠቅም መጸሀፍ ነው።ብዙ የጊቢ መምህራን ፈተና ለማውጣት ይጠቀሙታል።

File=10.6 Mb👆👆👆
👍1
✌️ጩባው እስታይል

ሰው ሁሉ
#UNIVERSITY ገብተህ ተመረቅ ይለኛል ኛል ኛል ኛል
እኔ ግን ዴች ብወድቅ ይሻለኛል ኛል ኛል
ምክንያቱም ደግሞ at least ስራ ይገኛል ኛል ኛል
#ተመርቆ መቀመጥ በጣም ያስጠላኛል ኛል ኛል

እርግጠኛ ነኝ ከነ
#ዜማው ነው ያላችሁት ሁት ሁት ሁት
😂😂😂😂😂😁😁
‌‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
😁7👍1
#anyone try this exercise
#AAU
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን በውድድር ብቻ እንደሚሆን አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው ክፍያ የሚፈጽሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን “በልዩ” ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል።

ተቋሙ ይህን ያለው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን አስመልክቶ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዛሬ ነሐሴ 16/2015 በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።

ተቋሙ ራስ ገዝ ለመሆን ላለፉት ሁለት ዓመታት ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን መግለጫውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ፕ/ር ጣሰው ወልደሃና ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ወደ ራስ ገዝነት የሚያደርገውን ሽግግር “ሁለት ዓመት ባልሞላ” ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ማቀዱን ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ መሆኑን ተከትሎ የሥራ ነፃነትን የሚያጎናጽፉ የሕግ ማሻሻያዎች እያደረገ እንደሚገኝ መግለጡ ይታወሳል፡፡ (ተጨማሪ ይኖረናል)

Share Share👆👆👆🙏🙏
@examanswer1
👍1
#AAU
Addis Ababa University has announced that starting from 2016, it will accept undergraduate students only through competition.

The university said it plans to teach fee-paying undergraduates under "special" conditions.

The president of the university said this in a press conference today, August 16, 2015, regarding the fact that the institution is the first autonomous university in Ethiopia.

The president of the university Prof. Tase Woldehana said that the institution has been making preparations for the past two years to become autonomous.

The president indicated that the university plans to complete its transition to autonomy in "less than two years".

It is recalled that Addis Ababa University has announced that it is making legal reforms to increase freedom of work following its independence. (we'll have more)
በ2016 የትምህርት ዘመን አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ይተገበራል፡፡ -ትምህርት ሚኒስቴር

በ2016 ዓ.ም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በሁሉም የመንግሥት እና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ከዓለም አቀፍና ከውጭ የማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች በስተቀር ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሚያስተምሩ ሁሉም የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች እንደሚተገበር በሚኒስቴሩ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ሥራ አስፈጻሚ ቴዎድሮስ ሸዋርገጥ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ስርዓተ ትምህርቱ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እንዲሁም በትግራይ ክልል በ9ኛ እና 10ኛ ክፍል እንደሚተገበር ተናግረዋል።

ስርዓተ ትምህርቱ ከሥራና የተግባር የትምህርት አይነቶች በስተቀር በሁሉም የቀለም ትምህርት ዓይነቶች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ እንደሚተገበር ጠቁመዋል፡፡ በሥራና የተግባር ትምህርት አይነቶች ላይ ከ2017 ዓ.ም ጀምሮ ይተገበራል ብለዋል።

አዲሱ ስርዓተ ትምህርት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከ2015 ዓ. ም ጀምሮ መተግበር መጀመሩ ይታወቃል። #MoE