Addis Standard Amharic – Telegram
Addis Standard Amharic
18K subscribers
4.67K photos
121 videos
3 files
3.72K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ዜና፡ #በትግራይ የምግብ እርዳታ በመቋረጡ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች መጨመሩ #አሜሪካ ድጋጤ ፈጥሮብኛል ስትል ገለጸች

በኢትዮጵያ የረድኤት ድርጅቶች የምግብ እርዳታ አቅርቦታቸውን በማቋረጣቸው ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተዘግቧል። አሶሼትድ ፕሬስ በትግራይ የሚገኙ ባለስልጣናት በክልሉ በሚገኙ ሰባት ዞኖች የምግብ እርዳታ ከተቋረጠ ወዲህ #728 ሰዎች መሞታቸውን ገልጸውልኛል ሲል ዘግቧል።

ይህንንም ተከትሎ የአሜሪካ የተራድኦ ድርጅት ለዜና አውታሩ በላከው የኢሜይል መልዕክት በእርዳታው መቋረጥ ሳቢያ የሚሞቱ ሰዎች መጨመሩ ድንጋጤ እንደፈጠረበት አስታውቋል።
እርዳታ ስርጭቱን የማቆም ውሳኔ እጅግ መራራ መሆኑን

የገለጸው ተራድኦ ድርጅቱ በየትኛውም ሀገር ተፈጽሟል ተብሎ የማይገመት መጠን ያለው የምግብ እርዳታ በኢትዮጵያ መሰረቁን አመላክቷል።
በምግብ እጦት ከሚሰቃይ ህዝብ ጉሮሮ ስርቆት መፈጸም ተቀባይነት የሌለው ከመሆኑ ባሻገር ነገሩ ከአይምሮ በላይ ነው ሲል በአጽንኦት ኮንኗል።
https://rb.gy/q8djx
#ኢትዮጵያ: ከ86 ሺ በላይ ሀሰተኛ የአሜሪካን ዶላር ለመመንዘር ይዞ የተገኘው ግለሰብ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

በፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ የኢኮኖሚ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ 86ሺ 600 ሀሰተኛ የአሜሪካን ዶላር እንደ እውነተኛ አስመስሎ ሊመነዝር ሲል እጅ ከፍንጅ በተያዘው ታደሰ ኃ/ማርያም ላይ ክስ መስርቶበት በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ አድርጓል በማለት የፍትሕ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሹ ለጊዜው ካልተያዘው ግለሰብ ጋር በመሆን ህዳር 5 ቀን 2015 ዓ.ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ዲአፍሪክ ሆቴል ተብሎ ከሚታወቀው አካባቢ ኦዚ ካፌ ውስጥ 86ሺ 600 ሀሰተኛ የአሜሪካን ዶላር እንደ እውነተኛ አስመስሎ በመመንዘር እንዲዘዋወሩ ለማድረግ ሲል እጅ ከፍንጅ የተያዘ በመሆኑ ሀሰተኛ ገንዘብ ይዞ መገኘት ወንጀል በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ወንጀል ሕግ አንቀጽ 359 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ክስ የቀረበበት ሲሆን እንዲሁም በዚሁ ቀን በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ፖሊስ መምሪያ ተጠርጥሮ በህግ አግባብ ተይዞ ታስሮ ካለበት የማቆያ ቤቱን በር በመገንጠል ከእስር ቤቱ ያመለጠ በመሆኑ ከእስር ማምለጥ ወንጀል የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 461/2/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ሁለት ተደራራቢ ክሶች ቀርበውበታል። https://www.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid0e8FjgUHxbVRMnPpWznaVpiDZUxncJXpbSSjxUDoc5UNhDNgcvBcSeHT3BzTvcWeKl
ዜና፡ የአርቲስት #ሀጫሉ_ሁንዴሳ ገዳዮች ማንነት እውነት እንዲወጣ ባለቤቱ ፋንቱ ደሚሴ ጠየቀች

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ገዳዮች ማንነት እውነት እንዲወጣ ባለቤቱ ፋንቱ ደሚሴ ትላንት ሰኔ 22 ቀን በተካሄደው ሁለተኛው የሀጫሉ ሁንዴሳ አዋርድ መርሃ-ግብር ላይ በደረገችው ንግግር ጠየቀች፡፡

የአርቲስቱ ባለቤትና የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ሰብሳቢ ፋንቱ ሶስት አመት ሙሉ የሀጫሉን ግድያ ፍትህ አላየሁም፣ እውነቱ እስካልወጣ ድረስ ለእኔ ማንም ንፁህ አይደለም ስትል ገልፃለት፡፡

ለአሸናፊ አርቲስቶችና የኪነጥበቡ ባለሙያዎች ሽልማትና እውቅና በተሰጠበት መርሃ-ግብር ባደረገችው ንግግር ፣ “ ጥለሀን ከሄድክ በኋላ እውነት ላይ ተኝተው እኛ እንዳለን አለን፣ የበላህም፣ ያስበላህም ዘመድ ይሁን ጠላት ሳናውቅ አለን፣ የሀገራችን ነገር አለባብሶ ማለፍ ነው” ስትል ተናግራለች፡፡
https://rb.gy/k21hu
ዜና፡ የደንብ ልብስ በለበሱ የጸጥታ ሀይሎች በዘፈቀደ #በአደባባይ የሚፈጸሙ ግድያዎች እየጨመሩ መጥተዋል፤ የድርጊቱ ፈጻሚዎች ተጠያቂ አለመሆን አሳሳቢ ሁኗል

የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በክልሎች አሰቃቂ ግድያ ሲፈጽሙ የሚያሳይ በርካታ ተንቀሳቃሽ ምስሎች በስፋት ተሰራጭተዋል። ባለፈው አመት ሰዎች በህይወት እያሉ ሲቃጠሉ የሚያሳይ ምስል በስፋት ተሰራጭቷል። ይህ አሰቃቂ ድርጊቱ ከተፈጸመ 15 ወራትን ቢያስቆጥርም #የፌደራል መንግስቱም ይሁን #የክልሉ መንግስት ድርጊቱን ፈጻሚዎች በግልጽ ክስ አልመሰረቱባቸውም። በወቅቱ ከድርጊቱ ጋር በተገናኘ የተጠረጠሩ አራት ሰዎች በቁጥጥር ስር ቢውሉም ክስ ይመስረትባቸው ወይም ፍርድ ይሰጣቸው የሚታወቅ ነገር የለም።

በኦሮምያ ክልል በአደባባይ የተገደለው አማኑኤል ወንድሙን ጨምሮ በርከታ የሀገሪቱ ሰዎች ከፍርድ ሂደት ውጭ የጸጥታ ሀይል መለዮ በለበሱ የመንግስት ሀይሎች ተንቀሳቃሽ ምስል በማስደገፍ በግልጽ ግድያ ተፈጽሞባቸዋል። #በጋመቤላ በጸጥታ ሀይሎች የተፈጸመው ጭፍጨፋ 50 ሰዎችን ቀጥፏል።

በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሰቪል እና ፖለቲካ መብቶች ኮሚሽነር #አብዲ ጂቢር (ዶ/ር) ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት ኮሚሽኑ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች የተፈጸሙ እና በተንቀሳቃሽ ምስል የተደገፉ ወንጀሎች ዙሪያ መረጃዎች አሰባስቧል። ኮሚሽኑ ባካሄደው ምርመራ ያገኘውን ውጤት እና ምክረ ሀሳብ ለመንግስት ማቅረቡንም አስታውቀዋል።

https://rb.gy/cr74k
ዜና ትንታኔ፡ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤትና ፌዴሬሽን ምክር ቤትን ጨምሮ በስምነት የፌዴራል እና የክልል መንግስት ተቋማት ላይ ክስ አቀረቡ

በብሩክ አለሙ

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባርና ዎላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ከታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም ጀምሮ የዎላይታ ብሄር የራሱን እድል በራሱ የመወሰንና ራሱን የማስተዳደር መብትን በመጠቀም በክልል የመዳራጀት ህግን በመከተል ያቀረበዉን የመብት ጥያቄ ተከትሎ በብሔሩ ግለሰብ አባላትና በቡድን እንዲሁም በብሔሩ ላይ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች ፈፅመዋል ባሏቸው አካላት ላይ ክስ አቀረቡ፡፡

ፓርቲዎቹ ክሱን ያቀረቡት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት( 1ኛ ተከሳሽ) ፣በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግስት( ጠቅላይ ሚንስቴር ጽ/ቤት) (2ኛ ተከሳሽ)፣ በኢትዮዽያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ( 3ኛ ተከሳሽ)፣ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች መንግስት(የፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት) (4ኛ ተከሳሽ) ፣በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ምክር ቤት( 5ኛ ተከሳሽ) ፣ በወላይታ ዞን አስተዳደር(6ኛ ተከሳሽ)፣በወላይታ ዞን ምክር ቤት(7ኛ ተከሳሽ) እና ብልጽግና ፓርቲ ( 8ኛ ተከሳሽ) ላይ ሲሆን ክሱን የመሰረቱት ሰኔ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ነው፡፡

የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባርና ስራ አስፈፃሚ አባልና የወላይታ ወጣቶች አደረጃጀት አመራር የሆኑት አቶ አሸናፊ ከበደ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር በስልክ ባደረጉት ቆይታ ለተከሳሶቹ መጥሪያው እንደደረሳቸው ገልፀው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የመሰረታዊ መብቶችና ነጻነት ችሎት ፍ/ብሄር ምድብ ክስ ችሎት ለሀምሌ 3 የፅሁፍ መልስ እንዲሰጡና ለሀምሌ 7 ደግሞ ለቃል ክርክር ቀጠሮ ሰጥቷል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

https://rb.gy/lh492
አንድን ግለሰብ በመግደል አስከሬኑን ቆራርጠው መጸዳጃ ቤት ውስጥ የጣሉት ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ

678 ሺህ ብር የሚያወጣ በዱቤ የተሸጠን በቆሎ ለግል ጥቅማቸው ለማዋል የንብረቱን ባለቤት በመግደል አስከሬኑን በመቆራረጥ መጸዳጃ ቤት ውስጥ የጣሉት ሁለት ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ፡፡

ድርጊቱ የተፈጸመው በሀዲያ ዞን ዱና ወረዳ መሆኑን የደቡብ ክልል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

ከተከሳሾቹ አንዱ የንብረቱን ባለቤት በጥይት ከገደለ በኋላ አስከሬኑን ሁለቱም ተከሳሾች ቆራርጠው በማዳበሪያ በመጠቅለል መጸዳጃ ቤት ውስጥ መክተታቸው ተገልጿል፡፡

የወረዳው ፖሊስም ለአራት ቀናት ያህል ባደረገው ፍለጋ÷ አገልግሎት መሥጠት ባቆመ አሮጌ መጸዳጃ ቤት ውስጥ የሟችን የተቆራረጠ አስከሬን ማግኘቱን አስታውቋል።

ወንጀሉን የፈጸሙት በድለላ ሥራ የሚተዳደርና በሟች ግቢ ውስጥ ቤት ተከራይቶ የሚኖር አቶ ፈለቀ በቀለና በጫኝና አውራጅ የቀን ሥራ የሚተዳደር አቶ ሳሙኤል አበራ የተባሉ ግለሰቦች መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

በዚህም 1ኛ ተከሳሽ አቶ ፈለቀ በቀለ ከግል ተበዳይ አቶ አባተ ኢቶሬ ጥር 13 ቀን 2015 ዓ.ም ግምቱ 678 ሺህ ብር የሆነ 230 ኩንታል በቆሎ ተቀብሎ በዱቤ ማሻሻጡም ነው የተገለጸው፡፡

ይህንኑ ገንዘብ ለግል ጥቅሙ ለማዋል በማሰብም በመጠጥ ተገፋፍቶ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 4 ሠዓት እስከ 8 ሠዓት ባለው ጊዜ የግል ተበዳይን ወደ ቤቱ በመጥራት በጥይት መግደሉ ተረጋግጧል፡፡

ከ2ኛ ተከሳሽ አቶ ሳሙኤል አበራ ጋር በመሆንም የሟችን አስከሬን ቆራርጠው በሦስት ማዳበሪያ በማድረግ መጸዳጃ ቤት ውስጥ መክተታቸውን 1ኛ ተከሳሽ አረጋግጧል፡፡

የሀድያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሁለቱም ተከሳሾ በሞት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡

ፋና
በዲማ ወረዳ ለግዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ የሁለት የአካባቢ ሚሊሻዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገለፀ።

በጋምቤላ ክልል በአኙዋ ብሔረሰብ ዞን በዲማ ወረዳ ለግዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ የሁለት የአካባቢ ሚሊሻዎች ሕይወት ሲያልፍ አንድ ሚሊሻ መቁሰሉን የዲማ ወረዳ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ኡኬሎ ኡጁሉ ገልፀዋል።

እንደ ሃላፊው ገለፃ ሰኔ 24 ዕለት ከጥዋቱ 2 :00 ላይ ለግዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂዎች በካችና ቀበሌ አካባቢ ገብተው በከፈቱት ተኩስ በሰዓቱ ፀጥታ በማስከበር ላይ የነበሩ ሁለት የአካባቢ ሚሊሻዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ አንድ ሚሊሻ ደሞ ቆስሎ በህክምና ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ ኡኬሎ አያይዘውም ሰኔ 23 ዕለትም ከቀኑ 3:00 አካባቢ ከካችና ቀበሌ ወደ ናምካዶ ቀበሌ በመጓዝ ላይ የነበረው አንድ ሞተረኛ በጥይት ተመትቶ ጉዳት እንደደረሰ ገልፀዋል።

ሃላፊው አክለውም በወረዳው ላይ የተሻለ ሰላም ቢኖርም ከቅርብ ግዜ ወዲህ በመንገድ ላይ ዝርፊያ የተሠማሩ ሽፍቶች በተደጋጋሚ ጥቃት እየፈፀሙ መሆኑን ገልፀው የወረዳው መንግስት ጥቃቱን ለማስቆም ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት የአቅሙን ያህል እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል።


ምንጭ- ዲማ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት
እለታዊ ዜና፡ የ #አማራ_ክልል የገጠመው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ለዘመናት የተሰበከው የልዩነት ሃሳብ ውጤት መሆኑን አቶ ደሳለኝ ጣሰው ገለፁ

የአማራ ክልል የገጠመው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር በድንገት የተከሰተ ሳይሆን ለዘመናት የተሰበከው የልዩነት ሃሳብ ውጤት በመሆኑ ችግሮችን ገምግሞ እና አርሞ መውጫ በሮችን ማዘጋጀት ተገቢ ነው ሲሉ የክልሉ ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኅላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ገለፁ፡፡

ኃላፊው ለክልሉ አሁንም ድረስ አጀንዳዎችን በመወርወር አካባቢውን ሠላም የራቀው ቀጣና ለማድረግ የሚሰሩ መኖራቸውን ጠቅሰው የተለያየ ፍላጎት ያላቸው እና በውስጥም በውጭም ያሉ ኃይሎች የክልሉን ሠላም ለማወክ ቀን ከለሊት እየሰሩ ነው ብለዋል።
https://rb.gy/7vdjh
ዜና ትንታኔ፡ በኮንደሚኒየም ቤቶች ላይ የወጣው አዲስ የግብር ተመን የህዝቡን አቅም ያላገናዘበ፣ የህግ ክፍተት ያለበት እና ማህበራዊ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል የህግ ሙሁራንና የቤት ባለንብረቶች ገለጹ

በሞላ ምትኩ

በአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎቸ ቢሮ የተላለፈውና በትግበራ ላይ ያልው የቤት ጣራና ግድግዳ ግብር አዲስ የክፊያ ተመን በአሁኑ ወቅት ያለውን ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበ እና አሁን ያለውን የኑሮ ውድነት በህዝቡ ላይ የፈጠረውን አሉታዊ ጫና በከፋ ደረጃ የሚያባብስ ከመሆኑም በላይ የህግ ክፍተት እንዳለበት በጋራ መኖሪያ ህንጻዎች የቤቶች ባለንብረቶች እና የህግ ሙሁራን ተናገሩ።

በአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ በቂሊንጦ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ባለንብረቶች ለአዲስ ስታንዳርድ አንደገለጹት የከተማ አስተዳደሩ ህዝቡ በአስጭናቂ የኑሮ ሁኔታ ላይ እንዳለ እያወቀ አንዳንድ ማስተካከያዎች ቀድመን አንዳናደርግ አስቀድሞ ሳያሳውቀን ድንገተኛ የግብር ክፍያ አስገዳጅ ማምጣቱ አግባብነት የለውም ይላሉ።

https://rb.gy/e4wm0
ዜና፡ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ ሁለት የፖሊስ አዛዦች በጥይት ተገደሉ

በአማራ ክልል፣ ምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለ እና የወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ም/ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ወርቁ ሽመልስ ትላንት ሰኔ 26፣ 2015 ለስራ በወጡበት ለጊዜው ማንነቱ ባልታወቀ አካል በተከፈተባቸው ጥቃት ህይወታቸው ማለፉን የወረዳው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አስታወቀ፡፡

የፖሊስ አዛዦቹ ላይ ጥቃቱ የተከፈተባቸው ትላንት ከቀኑ 8፡ዐዐ ሰዓት አካባቢ በደጀን ወረዳ ኩራር ቀበሌ ደምበዛ ጎጥ የሚሰጠውን የ8ኛ ክልላዊ ፈተና የጸጥታ ስራ ለመከታተል በወጡበት መሆኑን የወረዳው አስተዳደር ገልጧል፡፡ አብሯቸው መኪና በማሽከርከር ላይ የነበረ አንድ የፖሊስ አባል ቆስሎ ህክምና እየተደርገለት እነደሚገኝ ገልጧል፡፡
https://rb.gy/v8em2
የፀጥታ ኃይል ልብስ በለበሱ ሰዎች ታግቼ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ተዘርፍኩ ያለው አሽከርካሪ ንብረቱን ሸጦ የሀሰት ክስ መመስረቱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

አሽከርካሪው ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ/ም የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-35747 ኢ/ት በሆነ ተሽከርካሪ አዳማ ከሚገኝ ድርጅት ግምቱ 2 ሚሊዬን 7መቶ ሰላሳ ሺ 240 ብር የሚያወጣ የፌሮ ብረት መርካቶ ከሚገኝ የግል ተበዳይ ሱቅ ለማራገፍ ይጭናል።

የፀጥታ ኃይል ልብስ የለበሱ አካላት ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ አግተው ንበረቱን እንደዘረፉት በአቃቂ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለቃሊቲ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ያመለክታል፡፡

ፖሊስ ጣቢያው ለጉዳዩ ልዮ ትኩረት በመስጠት ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ንብረቱን ለማስመለስ ባደረገው በርቱ ክትትልና ባሰባሰበው መረጃ አሽከርካሪው ብረቱን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 አካባቢ ሸጦ ተሽከርካሪውን ጀሞ አካባቢ ማቆሙን ይደርስበታል፡፡

በግለሰቡ ላይ ምርመራው ቀጥሎ ከተሰረቀው ንብረት መካከል ግምቱ 648ሺ 432 ብር የሚያወጣ ብረት ማስመለሱን ፖሊስ ጣቢያው አስታውቋል። የተጣለበትን እምነት ወደኋላ በማለት ንብረቱን ሸጦ ሳይታገት ታግቻለሁ በማለት ፖሊስን ለማሳሳት ሀሰተኛ ክስ የመሰረተው አሽከርካሪ እና የተሰረቀውን ንብረት የገዛውን ጨምሮ በአጠቃላይ ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን መቀጠሉን ፖሊስ አስታውቋል።

አንዳንድ ግለሰቦች ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማቀድ ሳይታገቱ ታግተናል በማለት ሀሰተኛ መረጃ የሚያሰራጬ እና ሳይዘረፋ ተዘርፈናል በማለት የግል ጥቅማቸውን በህገወጥ መንገድ ለሟሟላት የሚሯሯጡ መኖራቸውን ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ የተለያዩ ሚዲያዎች የእነዚህ ህገወጦች መጠቀሚያ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ መልእክቱን አስተላልፏል ።
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች ተገደሉ

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች መገደላቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር በማህበራዊ ትስስር ገፁ፣ አቶ አብዱ የመንግስት ኃላፊነታቸው ለመወጣት ሲሰሩ መገደላቸውን ጠቅሶ የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

በተመሳሳይ ሁኔታ በትላንትናው እለት በምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዘውዱ ታደለ እና የወንጀል መከላከል ክፍል ኃላፊ ም/ኢንስፔክተር ወርቁ ሽመልስ ወርቁ ሽመልስ ለስራ በወጡበት ለጊዜው ማንነቱ ባልታወቀ አካል በተከፈተባቸው ጥቃት ህይወታቸው አልፏል።
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች መገደላቸውን ተከትሎ በከተማዋ ገደቦች ተቀመጡ

የጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፓስት በከተማዋና በአካባቢዉ የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ እንዲሆን እና ዜጎች ያለ ስጋት ወጥተው የሚገቡበት ለማድረግ ብዙ ጥረት የተደረገ ቢሆንም አሁንም ከተማዋን ሰው አልባ እንድትሆንና ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንዲከሰት ጥረቶች እየተደረጉ በመሆኑ ክልከላዎች አድርጊያለሁ ብሏል።

በዚህም መሰረት ከነገ ማለትም ከሰኔ 28/2015 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ከምሽቱ 12 ስዓት ጀምሮ
ማንኛውም ተሽከርካሪ ይሁን የሰው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ተገድቧል።

በተጨማሪም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የምሽት ክለቦችን ጨምሮ ከምሽቱ 12 ስዓት በኃላ ምንም አይነት አገልግሎት አንዳይሰጡ ክልከላ አድርጓል።

እንዲሁም የከተማው ነዋሪ ለጸጥታ መዋቅሩ እገዛውንና ድጋፍ በማድረግ ከተማዋን ካለባት ከፍተኛ የጸጥታ ችግር ልንታደጋት ይገባል ሲል ዛሬ ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል።
ዜና፡ ምክር ቤቱ “የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል” በሚል ስያሜ 12ኛ ክልል እንዲደራጅ ውሳኔ አሳለፈ

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የተካተቱበት “የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል” በሚል ስያሜ አዲስ 12ኛ ክልል ሆኖ እንዲደራጅ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬው እለት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ባካሄደበት ወቅት ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ጌዲዮ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ ዞኖችና ደራሼ፣ ቡርጂ፣ አማሮ፣ ኧሌና ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች “የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል” በሚል አዲስ ክልል ስር እንዲደራጉ ውስኗል፡፡
https://rb.gy/kdsy1
ዜና፡ በፋኖ ታጣቂ ሀይሎች ከቀያቸው የተፈናቀሉ የምስራቅ ወላጋና የሆሮ ጉዱሩ ነዋሪዎች ለረሃብ፣ ለበሽታና ለተጨማሪ ሰብዓዊ ቀውስ መጋለጣቸውን ገለፁ

በጌታሁን ለገሰ

በኦሮሚያ ክልል የሆሮ ጉዱሩና የምስራቅ ወለጋ ዞን ነዋሪዎች በፋኖ ታጣቂ ሀይሎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ለሰብዓዊ ቀውስ መዳረጋቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ አፋን ኦሮሞ ተናገሩ፡፡ ተፈናቃዮቹ ምንም አይነት ሰብዓዊ እርዳታ እያገኙ እንዳልሆነ ገልፀው ለደህንነት ስጋት፣ ለረሃብ፣ ለመኖሪያ ቤትና ህክምና እጦት መጋለጣቸውን ገልፀዋል፡፡

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ከሆሮ ጉዱሩ ዞን አሙሩ ወረዳ ከሲደን ባርክሌቲ ቀበሌ ተፈናቅሎ ወደ ጊዳ አያና ወረዳ መሸሻቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ የገለፁ አንድ አርሶ አደር፣ ሲኖሩበት በነበረው ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት ባለቤታቸው እና አንድ ልጃቸው እንደተገሉባቸው ተናግረዋል፡፡

አቶ ዳባ 11 የቤተሰባቸውን አባላት ይዘው በጊዳ አያና ከተማ እየኖሩ መሆኑን ገልፀው መንግስት ለአንድ ቤተሰብ እያደረገ ያለው እርዳታ ለአንድ ሰውም የሚበቃ አይደለም ብለዋል፡፡ በርካታ ሰዎች ከአንድ ቤት እየሞቱ መሆኑንም አክለው ገልፀዋል፡፡

https://rb.gy/2knvx
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አስደሳች ዜና ከአዲስ ስታንዳርድ !
ዜና፡ "ብልፅግና መራሹ መንግስትም ሆነ ፓርላማው አገራችን ከገባችነት የፖለቲካ ቅርቃብ ማውጣት ስለማይችሉ ጠ/ሚ አብይ ስልጣንዎን ለጊዚያዊ ሲቪል አስተዳደር ያስረክቡ" - ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

“ከለውጡ በኋላ ፈተና በዝቷል ለተባለው እውነት ነው ፈተና በስቷል ግን ደግሞ ተፈናው እያዳከመን ሳይሆን እንደ ወርቅ አጠንክሮ እያወጣን ነው”- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ መንበረ ስልጣን ከወጡበት ከመጋቢት 2010 ጀምሮ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች አሁን ላይ ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ መሸጋገሩን ገልፀው ብልፅግና መራሹ መንግስትም ሆነ ፓርላማው አገራችን ከገባችነት የፖለቲካ ቅርቃብ ማውጣት ስለማይችሉ ስልጣንዎን ለጊዚያዊ ሲቪል አስተዳደር ያስረክቡ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አክለውም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በምክር ቤቱ ፍቃድ ምክር ቤቱን እንዲበትኑና ለአዲስ ምርጫ መንገዱን እንዲጠርጉ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ይህን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ፣ “ከለውጡ በኋላ ፈተና በዝቷል ለተባለው እውነት ነው ፈተና በስቷል ግን ደግሞ ተፈናው እያዳከመን ሳይሆን እንደ ወርቅ አጠንክሮ እያወጣን ነው” ብለዋል፡፡ የችግሩ መንስዔ ፖለቲካዊም ኢኮኖሚያዊም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ፖለቲካዊው ፅንፍ የያዘ ፖለቲካ ነው “ እኔ ብቻ ነኝ የምመራው፣ እኔ ካልመራው ምርጫ ይፍረስ፣ እኔ ካልመራው ፓርላማው ይበተን” የሚል ፅንፍ የወጣ አስተሳሰብ ነው ብለዋል፡፡
https://rb.gy/36irx
ዜና: የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ ክልል የነበርው ጦርነት እንዲቆም ጥረት ባለማድረጉ ይቅርታ ጠየቀ፡፡

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በትግራይ ክልል በነበርው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተክርስቲያን ጦርነቱ እንዲቆም መግለጫ ባለመስጠቷ ፣ በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ እንደሚጓዝ የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል፡፡
https://rb.gy/9wwz8