Addis Standard Amharic – Telegram
Addis Standard Amharic
18K subscribers
4.66K photos
121 videos
3 files
3.71K links
አዲስ ስታንዳርድ በጃኬን አሳታሚ ኃ.የተ.የግ.ማ. ባለቤትነት ስር የሚታተም በኢትዮጵያ የሚገኝ ነፃ እና ገለልተኛ ሚዲያ ነው። አዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የአዲስ ስታንዳርድ እንግሊዝኛ ሕትመት አካል ነው።
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
Download Telegram
ዜና፡ "ብልፅግና መራሹ መንግስትም ሆነ ፓርላማው አገራችን ከገባችነት የፖለቲካ ቅርቃብ ማውጣት ስለማይችሉ ጠ/ሚ አብይ ስልጣንዎን ለጊዚያዊ ሲቪል አስተዳደር ያስረክቡ" - ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

“ከለውጡ በኋላ ፈተና በዝቷል ለተባለው እውነት ነው ፈተና በስቷል ግን ደግሞ ተፈናው እያዳከመን ሳይሆን እንደ ወርቅ አጠንክሮ እያወጣን ነው”- ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ መንበረ ስልጣን ከወጡበት ከመጋቢት 2010 ጀምሮ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች አሁን ላይ ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ መሸጋገሩን ገልፀው ብልፅግና መራሹ መንግስትም ሆነ ፓርላማው አገራችን ከገባችነት የፖለቲካ ቅርቃብ ማውጣት ስለማይችሉ ስልጣንዎን ለጊዚያዊ ሲቪል አስተዳደር ያስረክቡ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አክለውም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በምክር ቤቱ ፍቃድ ምክር ቤቱን እንዲበትኑና ለአዲስ ምርጫ መንገዱን እንዲጠርጉ ለጠቅላይ ሚንስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ይህን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ፣ “ከለውጡ በኋላ ፈተና በዝቷል ለተባለው እውነት ነው ፈተና በስቷል ግን ደግሞ ተፈናው እያዳከመን ሳይሆን እንደ ወርቅ አጠንክሮ እያወጣን ነው” ብለዋል፡፡ የችግሩ መንስዔ ፖለቲካዊም ኢኮኖሚያዊም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ፖለቲካዊው ፅንፍ የያዘ ፖለቲካ ነው “ እኔ ብቻ ነኝ የምመራው፣ እኔ ካልመራው ምርጫ ይፍረስ፣ እኔ ካልመራው ፓርላማው ይበተን” የሚል ፅንፍ የወጣ አስተሳሰብ ነው ብለዋል፡፡
https://rb.gy/36irx
ዜና: የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በትግራይ ክልል የነበርው ጦርነት እንዲቆም ጥረት ባለማድረጉ ይቅርታ ጠየቀ፡፡

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በትግራይ ክልል በነበርው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተክርስቲያን ጦርነቱ እንዲቆም መግለጫ ባለመስጠቷ ፣ በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እያለ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ እንደሚጓዝ የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል፡፡
https://rb.gy/9wwz8
ሹፌርና ረዳቱን በመግደል 100 ኩንታል ሰሊጥ የጫነን FSR መኪና ይዘው የተሰወሩ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር አባጀምበር ቀበሌ የጨረቃን ጎጥ ከተባለው ቦታ ፣ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ/ም ፣ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ መቶ ኩንታል ሰሊጥ ጭኖ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረን FSR መኪና ፣ ሌሊት ባልታወቀ ሰዓት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰወች መኪናውን አስቁመው ሾፌርና ረዳቱን በመግደል መኪናውን ይዘው ይሰወራሉ::

የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከአካባቢው ነዋሪዎች የደረሰውን መረጃ መሰረት በማድረግ በሰራው እጅግ ፈጣንና ጥብቅ የሆነ ክትትል ፣ ወንጀለኞቹ መኪናውን ወደኋላ በመመለስ በእነብሴ ሳር ምድር ወረዳ ዲቦ ከተማ ወስደው ማሳደራቸውን መረጃ ይደርሰዋል፡፡

ፖሊስ የወንጀለኞችን ዱካ ይዞ ጠንካራ ክትትል በማድረግና እግር በእግር በመከታተል ላይ እያለ ፣ ወንጀለኞቹ ሰኔ 29/2015 ዓም መኪናውን ይዘው ወደ ግንደወይን ከተማ በመመለስ ላይ ሳሉ ፣ ግንደወይን ከተማ አካባቢ ሲደርሱ በጎንቻ ሲሶ እነሴና በግንደወይን ከተማ ህዝብና የጸጥታ አካላት ብርቱ ጥረት አንዱ ወንጀለኛ ከመኪናው ጋር በቁጥጥር ስር ሲውል ፣ ሌሎች ወንጀለኞችን ለመያዝ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ አስታወቋል፡፡

ወንጀለኞችን ለመያዝ በተደረገው ጥረትም የጎንቻ ሲሶ እነሴና የግንዶይን ከተማ አስተዳደር ህዝብና የፀጥታ አካላትን ፣ እንዲሁም መረጃ በመስጠት ለተባበሩት ሁሉ የደብረወርቅ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል ።

ምንጭ- ምስራቅ ጎጃም ፖሊስ
ዜና፡ በ #ሸዋሮቢት ከተማ እንድ የፖሊስ አባል ተደገለ፤ ግድያው በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ የተገደሉ የአካባቢ ባላስልጣንና የፀጥታ አካልን ብዛት ወደ አራት ከፍ አድርጎታል

ምክትል ሳጅን ያለለት ደጉ ትላንት ሰኔ 29 ቀን ማታ በሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር 08 ቀበሌ ከምሽቱ 4 ስዓት በስራ ላይ እያሉ ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት መገደላቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ፡፡

የአሁኑ ግድያ በአማራ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ የተገደሉ የአካባቢ ባላስልጣንና የፀጥታ አካልን ብዛት ወደ አራት ከፍ አድርጎታል፡፡
https://rb.gy/5uzd6
#ትግራይ ክልል የግብር መክፈያ ጊዜ ለሶስት ወር ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2015- የትግራይ ክልል ግዚያዊ መስተዳድር ካቢኔ ትናንት ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በክልሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል።

ከውሳኔዎቹ መካከል የ2015 በጀት ዓመት ግብር መክፈያ ጊዜ ማራዘም አንዱ ሲሆን በውሳኔው መሰረት በክልሉ ግብር የሚከፈልበት ጊዜ እስከ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም መወሰኑ ተገልጿል።

የንግድ ፈቃድ የሚታደስበት ወቅትም በተመሳሳይ እስከ መስከረም 30 2016 ዓ.ም ተራዝሟል።

በትግራይ በነበረው ጦርነት ምክንያት የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ውል ገብተው ግዴታቸውን ያልተወጡ ኮንትራክተሮች ውላቸው እንዲያሳድሱም ውሳኔ መሰጠቱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።
ዜና ትንታኔ፡ “የዛፍ አንበጣ የእንስሳ መኖ፣ አትክልት እና ፍራፍሬ ሳይቀር አውድሞ ባዶ ነው አስቀረን፤ ከፌደራልም ይሁን ከለጋሾች የተደረገልን ምንም አይነት ድጋፍ የለም”- የትግራይ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ

በሚሊዮን በየነ

በኢትዮጵያ በዘንድሮ የክረምት ወቅት የዛፍ አንበጣ ስጋት ሊኖር እንደሚችል በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መከላከያ ድርጅት የኢትዮጵያ ቁጥጥር ቅርንጫፍ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቀ፡፡

በምስራቅ አፍሪካ የበረሃ አንበጣ መከላከያ ድርጅት የኢትዮጵያ ቁጥጥር ቅርንጫፍ ቢሮ ሃላፊ ሒወት ለማ በተለይ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ የዛፍ አንበጣ ስጋት ሊኖር እንደሚችል ጠቁመው የበረሃ አንበጣ ስጋት ግን የለም ብለዋል።

የትግራይ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ የእጽዋት ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መብራህቶም ገብረኪዳን ወልዱ በትግራይ የተባይ ወረርሽኝ ፈታኝ መሆኑን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልፀዋል፡፡ በክልሉ ተከስቶ የነበረው የዛፍ አንበጣ እና ተምች ያስከተለው ጉዳት ለመግለጽ አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጸው፣ ክልሉ ካለበት ወቅታዊ ችግር ጋር ተደማምሮ ሁኔታው ተስፋ አስቆራጭ መሆኑን አመላክተዋል።

https://rb.gy/3kgob
#ሶማሊ ክልል ርእሰ መዲና #ጅግጅጋ ከተማ በንግድ ቦታ የተከሰተው የእሳት አደጋ እንዳይዛመት ርብርብ እየተደረገ ነው።

በጅግጅጋ ከተማ አዲሱ ታይዋን ገበያ ተብሎ በሚጠራው የመገበያያ ስፍራ ለጊዜው መነሻው ያልተወቀ ከባድ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል።

የድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ቡድን፣ የፀጥታ አካላት እና የህክምና ባለሙያዎች ቡድን በአደጋው ስፍራ በመሰማራት የእሳት አደጋው ወደሌሎች አከባቢዎች እንዳይዛመት በጋራ እየተረባረቡ እንደሚገኙ ሶማሊ ፈጣን መረጃ ዘግቧል።
#ሶማሊ ክልል #ጅግጅጋ ከተማ የተነሳው የእሳት አደጋ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሳይዛመት በቁጥጥር ስር ውሏል

በእሳት አደጋው ሳቢያ #932 ሱቆች ወድመዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ የተመራ ልዑክ ከፌዴራል እና ክልል ሃላፊዎች ጋር በመሆን ዛሬ ጠዋት የደረሰውን ውድመት ለመመልከት በቦታው ተገኝተዋል፡፡

ዛሬ ጠዋት ከጎረቤት #ሶማሊላንድ ዋና ከተማ #ሀርጌሳ ከንቲባ የተመራ የእሳት አደጋ አጥፊ ቡድን ወደ ስፍራው አምርቷል። ባለፈው አመት በሚያዝያ ወር በሀርጌሳ ከተማ #ዋሄን ገበያ ላይ ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በደረሰበት ወቅት የሶማሊ ክልል የነፍስ አድን ቡድን ወደ ስፍራው መላኩ ይታወሳል።

አዲሱ ታይዋን ተብሎ በሚጠራው የገበያ ማእከል ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ መንስዔውእስካሁን አልታወቀም፡፡ በእሳት አደጋው ሳቢያ #932 ሱቆች ሲወድሙ የደረሰውን ጉዳት የሚያጣራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ተገልጧል። SRTV_Somali ያጋራው ምስል ከባድ ውድመት መድረሱን ያመላክታል፡፡
ዜና፡ በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል ያሉ የማንነትና የወሰን ውዝግቦች በሕዝበ ውሳኔ እንዲፈቱ እንቅስቃሴ መጀመሩን የአማራ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ

ለ30 ዓመታት የአማራና የትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱባቸው አካባቢዎች ጉዳይ በህዝበ ውሳኔ እንዲፈታና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የአማራ ክልል መንግስት ጥረት እያደረገ መሆኑን የክልሉ የኮሙዩኒኬስን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የማንነትና የወሰን ጥያቄ ቢያንስ ከ30 አመታት በኋላ በህዝበ ውሳኔ እንዲፈጣ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ሕገ መንግስት ለማሻሻል ጥረቶች መጀመራቸውን አስታውሰው ጥያቄ ማቅረብ መቀጠላቸውንና በጥሩ ሁኔታ እየሄዱ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ጥያቄዎቻቸው እንዲመለሱም ዝግጁነት ስለሚያስፈልግ ክልሉን ሰላም ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አክለው ገልፀዋል፡፡

አቶ ግዛቸው በነፃነት በመዘዋወር በተመለከተ በአንዳንድ አካባቢ ችግር መኖሩን ጠቅሰው የመንገድ መዘጋት፣ የመታገት አደጋዎች፣ ግድያ፣ ውድመትና ዘረፋ የክልሉን ሰላም በመደፍረስ አሉታዊ ተጽዕኖ እያደረሱ ነው ብለዋል፡፡
https://rb.gy/ccnel
በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ ልዑካን ቡድን መቐለ ከተማ ገባ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በቅዱስ ፓትርያርክ የሚመራ ልዑካን ቡድን በትግራይ ክልል ከሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጋር የሰላም ውይይት ለማድረግና የሰብዐዊ ድጋፍ ለማድረስ መቐለ ከተማ መግባቱን የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታወቀ።

ቀደም ሲል የተቋቋመው ኮሚቴው ወደ ክልሉ ከመጓዙ አስቀድሞ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ ልዑካን ቡድን ወደ መቐለ እንዲጓዝና የሰብዐዊ ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ በክልሉ ከሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ውይይት አድርጎ እንዲመለስ በቋሚ ሲኖዶስ መወሰኑና ይኸው በመቐለ ሊካሔድ የታሰበው መርሐ ግብርም አስቀድሞ ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲደርስ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ ሐምሌ 3ቀን 2015 ዓ.ም ማለዳ ወደ ክልል ትግራይ መቐለ ከተማ አምርቷል።

ልዑካን ቡድኑ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በመገኘት የሰብዐዊ ድጋፉን የሚያበረክት ሲሆን በክልሉ ጊዜያዊ መንግስት በኩል በሚመቻቸው መሠረት ተፈናቃይ ወገኖችን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በመርሐ ግብሩ መሰረትም ቅዱስ ፓትርያርኩና የልዑካን ቡድኑ አባላት በትግራይ ከሚገኙ ብፁዓን አባቶች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ባስተላለፈው ውሳኔ መሠረት የትግራይን ሕዝብ ይቅርታ መጠየቁ ይታወሳል።