በመከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ የተመራ ልዑክ በጂቡቲ የመከላከያ ሠራዊትን 47ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ለመታደም ጂቡቲ ገባ።
ክብረ-በዓሉ ላይ የጂቡቲ የመከላከያ ሚኒስትር ሀሰን ኦመር መሐመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የመከላከያ ሠራዊት አታሼዎች እና ዲፕሎማቶች በተገኙበት በተለያዩ ወታደራዊ ትርዒቶች መከበሩን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አስታውቋል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek

ዜና፡ በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የ #ኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ፍርድ ቤት አለመቀረባቸው ተገለጸ፤ የህዳር 30 ሠልፍ አስተባባሪ አቶ ዘለሌ ጸጋስላሴ ታሰሩ
ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ግንቦት 23 ቀን 2016 በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ፍርድ ቤት አለመቀረባቸው ተገለጸ።
ከአርብ ግንቦት 23 ቀን ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኙት ኅዳር 30 የተጠራው ሠልፍ አስተባባሪና የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ “ #ፋኖን ሊደግፍ የሚችል ጽሁፍ በሚዲያ ጽፈዋል” የሚል ክስ በቃል ከፖሊስ እንደቀረበላቸው የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ይስሀቅ ወልዳይ ገልጸዋል።
“ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” በሚል መሪ ቃል ኅዳር 30 የተጠራው ሰልፍ አስተባባሪ የነበሩት አቶ ዘለሌ ጸጋ ስላሴ ትላንት ግንቦት 28 ቀን 2016 መሳለሚያ አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተይዘው መታሰራቸውን አቶ ይስሀቅ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
ሙሉ ዘገባውን ለመመልከት፡- https://wp.me/pfjhHd-1bb

Addis standard
በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ፍርድ ቤት አለመቀረባቸው ተገለጸ፤ የህዳር 30 ሠልፍ አስተባባሪ አቶ ዘለሌ ጸጋስላሴ ታሰሩ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29/2016 ዓ/ም፦ ባሳለፍነው ሳምንት አርብ ግንቦት 23 ቀን 2016 በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ፍርድ ቤት አለመቀረባቸው ተገለጸ። “ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” በሚል መሪ ቃል ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩት የሰለፉ አስተባባሪዎች መካከል አንዱ ከሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ…
በ #አማራ ክልል ያለው የሰላም እጦት በሴቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች ላይ ጉዳት እያስከተለ ነው- የሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ
የ #አማራ ክልል ሴቶች ሕጻናት ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ንፁህ ሽፈራው በክልሉ ያለው የሰላም እጦት በተለይም በሴቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት የከፋ በመኾኑን ገለጹ።
ኃላፊው ይህንን ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ተግባራት በዘላቂነት መከወን እንደሚገባ አሳስበዋል። ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በሚሠራው ሥራ ሴቶች ግንባር ቀደም መኾን ይኖርባቸዋልም ብለዋል።
ንፁህ ሽፈራው ይህን የገለጹት በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ከሁሉም ክፍለ ከተማ የተውጣጡ ሴቶች በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ባለው መድረክ ነው። በሰላም እጦት ከሚፈተኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች መካከል ሴቶች ቀዳሚዎቹ ናቸው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
የ #አማራ ክልል ሴቶች ሕጻናት ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ንፁህ ሽፈራው በክልሉ ያለው የሰላም እጦት በተለይም በሴቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት የከፋ በመኾኑን ገለጹ።
ኃላፊው ይህንን ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ተግባራት በዘላቂነት መከወን እንደሚገባ አሳስበዋል። ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በሚሠራው ሥራ ሴቶች ግንባር ቀደም መኾን ይኖርባቸዋልም ብለዋል።
ንፁህ ሽፈራው ይህን የገለጹት በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ከሁሉም ክፍለ ከተማ የተውጣጡ ሴቶች በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ባለው መድረክ ነው። በሰላም እጦት ከሚፈተኑ የማኅበረሰብ ክፍሎች መካከል ሴቶች ቀዳሚዎቹ ናቸው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
ዜና፡ ቤተ ክርስቲያኗ በሀገራዊ ምክክር እንድትሳተፍ ኮሚሽኑ ጥሪ ባለማቀረቡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቅር መሰኘቱን ገለጸ
የ #ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንድትሳተፍ ጥሪ ባለማቀረቡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቅር መሰኘቱን ገለጸ። ሲኖዶሱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ መሰየሙንም አስታውቋል።
ምልዓተ ጉባኤው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በመንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙ ተገልጿል።
በመላ ሀገሪቱ በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት መቀጠሉ እንዳሳዘነው የገለጸው ሲኖዶሱ ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት እንዲቆጠቡና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ጥሪ አቅርቧል።
ተጨማሪ ይመልከቱ፡ https://wp.me/pfjhHd-1bh

ቤተ ክርስቲያኗ በሀገራዊ ምክክር እንድትሳተፍ ኮሚሽኑ ጥሪ ባለማቀረቡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቅር መሰኘቱን ገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29/ 2016 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንድትሳተፍ ጥሪ ባለማቀረቡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቅር መሰኘቱን ገለጸ። ሲኖዶሱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ መሰየሙንም አስታውቋል። ሲኖዶሱ ይህን የገለጸው ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28…
ፍርድ ቤቱ በአቶ ታዬ ደንደአ ላይ የቀረቡ ምስክሮችን ቃል ሰማ
ፍርድ ቤቱ በቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ታዬ ደንደአ ላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረባቸውን የሁለት ምስክሮች ቃል ሰማ።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥት ሥርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮችን የሚመለከተው ችሎት፤ አቶ ታዬ "የጻፍኩት ጽሑፍ ፕሮፖጋንዳ አደለም፣ ወንጀል አልፈጸምኩም" በማለት የዕምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ምስክር እንዲሰማ ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ጥያቄ መነሻ መሰረት ዛሬ የምስክሮችን ቃል አዳምጧል።
ፍርድ ቤቱም የተሰሙ ምስክሮችን ቃልና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጥቱን ፋና ዘግቧል።
አቶ ታዬ የሰላም ሚኒስትር ዴዔታ ሆነው ሲሰሩ የሀገር፣ የመንግሥትና የሕዝብን ደኅንነት ማስጠበቅና ማረጋገጥ ሲገባቸው፤ ይህን ወደጎን በመተው የሽብር ቡድኖችና የፀረ-ሰላም ኃይሎችን የሚደግፉ ፕሮፓጋንዳ መልዕክቶችን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ሲያስተላልፉ ነበር የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ይታወቃል፡፡
በተጨማሪም ፈቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ አዋጁን በመተላለፍ ታኅሣስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም በመኖሪያ ቤታቸው በተደረገ ብርበራ አንድ ታጣፊ ክላሽንኮቭ መሳሪያ፣ 2 የክላሽንኮቭ ካዝና፣ 60 የክላሽንኮቭ ጥይቶች ተገኝተዋል የሚል ክስም መቅረቡ ይታወሳል፡፡

ዜና፡ በ #አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንድ ሳምንት ሁለት አመራሮች 'በታጠቁ አካላት' ተገደሉ
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ትላንት ግንቦት 29፣ 2016 በታጠቁ ሰዎች መገደላቻቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ።
ነፍሰጡር የነበሩት የወረዳው አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊዋ፤ ከተማ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ “በፅንፈኛ አካላት በተተኮሰባቸው ጥይት ተገድለዋል" ሲል አስተዳደሩ ባወጣው መግለጫ ገልጿል።
በተመሳሳይ መልኩ በታጠቁ አካላት በተፈጸመ ጥቃት የዞኑ ኤፍራታ ግድም ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አልብስ አደፍራሽ የተገደሉት በያዝነው ሳምንት ነው።
ተጨማሪ ይመልከቱ፦ https://wp.me/pfjhHd-1bp

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንድ ሳምንት ሁለት አመራሮች 'በታጠቁ አካላት' ተገደሉ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30/ 2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በአንድ ሳምንት ሁለት አመራሮች ‘በታጠቁ አካላት’ ተገደሉ። በክልሉ የሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሚሊሹ በቀለ ትላንት ግንቦት 29፣ 2016 በታጠቁ ሰዎች መገደላቻቸውን የወረዳው አስተዳደር አስታውቋል። ነፍሰጡር የነበሩት የወረዳው አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊዋ፤ ከተማ ውስጥ በመንቀሳቀስ ላይ…
በ #ሰሜን_ጎንደር ዞን በአድርቃይ ወረዳ በታጣቂዎች ጥቃት ንጹሃን ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ
በ #አማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን አድርቃይ ወረዳ ዓሊ ጣራ በተባለ ቀበሌ፣ “ከ #ትግራይ ክልል መጡ የተባሉ ታጣቂዎች”፣ ማክሰኞ ግንቦት 27 ቀን በሰነዘሩት ጥቃት፣ የሲቪል ሰዎች ሕይወት መጥፋቱንና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱንና ዘረፋም መፈጸሙን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጹ፡፡
የአድርቃይ ወረዳ አስተዳዳሪም ሆነ አስተያየታቸውን የሰጡ ነዋሪዎች፣ ለጥቃቱ “የህወሓት ታጣቂዎችን” ተጠያቂ ማድረጋቸውን የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል፡፡
በጥቃቱ ጉዳት ደርሶበት በወልቃይት ሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት እንደሚገኝ የተናገረ ወንድሙ ነጋሽ የተባለ ነዋሪ ታጣቂዎቹ በአምስት ጓደኞቹ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን እና እርሱ ብቻ ብህይወት መትፍ መቻሉን ገልጿል።
የአድርቃይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ታደሰ ከአስር በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገለጸዋል። በታጣቂዎቹ ሶስት ነዋሪዎችም ታፍነው መወሳዳቸንና አንዱ በህይወት መመለሱን ተናግረዋል። የቀሩት ሁለቱ እስካሁን ያሉበት እንደማይታወቅ አክለው ገልጸዋል።
በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ከላሊ ሃጋዚ፣ ከትግራይ ክልል ተነሥቶ ጥቃት የፈጸመ እንደሌለና ተፈጸመ ለተባለውም ጥቃት ክልላቸው ኃላፊነቱን እንደማይወስድ ተናግረዋል፡፡ አክለውም ሁሉተኛ ጦርነት የመቀስቀስም አላማ የለንም ሲሉ ተናግረዋል።

#ሶማሊያ ከ50 ዓመታት በኋላ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና ተመረጠች
ሶማሊያ ከ50 ዓመታት በኋላ ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባል ሆና ከ #ዴንማርክ፣ #ግሪክ፣ #ፓኪስታን እና #ፓናማ ጋር ተመርጣለች።
በጦርነት ስትታመስ ለኖረችው ምስራቅ አፍሪካዊቷ አገር የምክር ቤቱ አባል ሆና መመረጧ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል ተደርጎ ተወስዶላታል።
ሶማሊያ የምክር ቤቱ አባል መሆኗ ከአል-ሸባብ ጋር የምታደርገውን ውጊያ በተመለከተ ለተመድ ውሳኔ ግብዓት ትሆናለች መባሉን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።
ሶማሊያ ይህን መቀመጫ ያገኘችው ለምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የተቀመጠውን ወንበር ያለተቀናቃኝ ከወሰደች በኋላ ሲሆን፤ ከ193 አባል አገራት የ179 ድምጽ ማግኘት ችላለች።
ሶማሊያ ያገኘችውን ድል ተከትሎ የልዑካን ቡድንን መርተው ወደ ኒው ዮርክ ያቀኑት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ ፊቅ “በዓለማችን ሰላም እና ደኅንነትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ሶማሊያ የተሰጣትን ሚና ለመውጣት ዝግጁ ነች” ብለዋል።
https://www.facebook.com/AddisstandardAmh

ዜና፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ላይ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ ከሲኖዱሱ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ
የ #ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገራዊ ምክክር ቤተክርስቲያኗ እንድትሳተፍ ጥሪ ባለመቅረቡ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ የሲኖዱሱ ጽ/ቤት ድረስ በመሄድ ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።
ቅዱስ ሲኖዶሱ ትላንት ባወጣው መግለጫ ቤተክርስቲያኒቱ በኮሚሽኑ በኩል በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ እንዳልተደረገላት በመግለጽ በሂደቱ ቅር መሰኘቷን አስታውቋል።
ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ፤ ኮሚሽኑ ገና ሥራውን እንደጀመረ የመግባቢያ ሠነድ የተፈራረመው ከአምስቱ ተባባሪ አካላት አንዱ ከሆነው ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር ነው ብሏል።
ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱ፦ https://wp.me/pfjhHd-1bA

ቅዱስ ሲኖዶሱ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ላይ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ ከሲኖዱሱ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30/ 2016 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገራዊ ምክክር ቤተክርስቲያኗ እንድትሳተፍ ጥሪ ባለመቅረቡ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ የሲኖዱሱ ጽ/ቤት ድረስ በመሄድ ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። ቅዱስ ሲኖዶሱ ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ሲያካሄድ የቆየውን የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ማጥናቀቁን ተከትሎ…
እነ #ዮሐንስ_ቧያለው ቅሬታ እና የክስ መቃወሚያ ለፍርድ ቤት አቀረቡ
በእነ አቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ የተከሰሱ 52 ተከሳሾች ትላንት ሐሙስ ግንቦት 29/2016 ዓ.ም. የክስ መቃወሚያቸውን ለፍርድ ቤት በጽሁፍ አቅርበዋል።
ተከሳሾች ጉዳያቸውን እየተመለከተ ከሚገኘው ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣን ጋር የተያያዘ መቃወሚያም አቅርበዋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀዳሚው የተከሳሾች መቃወሚያ፤ “ፍርድ ቤቱ አማራዊ ማንነትን ለመዳኘት ሥልጣን [የለውም]” የሚል ነው።
በተጨማሪም ፍርድ ቤቱ በተወሰኑ ተከሳሾች ላይ “የአስተዳደር አካባቢ የዳኝነት ሥልጣን የለውም” የሚል መቃወሚያ ቀርቧል።
ወንጀሉ ተፈጸመ የተባለው በ #አማራ ክልል መሆኑን ያስታወሱት ተከሳሾች፤ “ይህን ጉዳይ ለማየት ሥልጣን ያለው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ነው በማለት ጉዳዩን ወደ አማራ ክልል እንዲልከው በማክበር እንጠይቀለን” ብለዋል።
በመቃወሚያ አቶ ዮሐንስ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል በመሆናቸው ያላቸው ያለመከከስ መብት አለመነሳቱ በመቃወሚያው ላይ ተጠቅሷል። በዚህም መሰረት “በ1ኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበው የወንጀል ክስ ተቋርጦ ከእስር እንዲፈቱ” የሚል ጥያቄ አቅርቧል።
https://www.bbc.com/amharic/articles/c100qz32e0mo

ከፍተኛ የካርበን ልቀት ያላቸው መኪኖች በመዲናዋ እንዳይነዱ የሚያግድ መመሪያ ስራ ላይ ሊውል ነው ተባለ
በተሽከርካሪዎች የበካይ ጋዝ ወይም ካርበን ልቀት የሚፈጠርን የአየር ብክለት ለመቆጣጠር ከፍተኛ የካርበን ልቀት ያላቸው መኪኖች ከአዱስ አበባ እንዳይነዱ የሚያስችል አስገዳጅ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለፀ።
በአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተዘጋጀው አስገዳጅ መመሪያው በከተማዋ ያለው የአየር ብክለት መጠን ከአለም አቀፍ ብሎም እንደ ሀገር ከወጣው ስታንዳርድ ወይም መለኪያ በማለፉና አስጊ ደረጃ በመድረሱ መሆኑም ተነግሯል፡፡
በከተማዋ ከሚከሰተው የአየር ብክለት ውስጥ 27 በመቶው ከተሽከርካሪዎች የጭስ እና የጋዝ ብናኝ ምክንያት እየተከሰተ መሆኑንም ተገልጿል፡፡
በተሽከርካሪዎች ላይ በሚደረግ ፍተሻ ከጭስ እና ከጋዝ ልቀት አልፈው ከተገኙ ለጊዜወ አገልግሎት እንዳይሰጡ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡
ሆኖም ግን ተሽከርካሪዎች የተሻለ ቴክኖሎጂዎች እንዲገጠምላቸው እና የብክለት መጠኑ እንዲቀንስ አስፈላጊውን የጥገና ስራ እንዲደረግላቸው ይደረጋልም ተብሏል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
በተሽከርካሪዎች የበካይ ጋዝ ወይም ካርበን ልቀት የሚፈጠርን የአየር ብክለት ለመቆጣጠር ከፍተኛ የካርበን ልቀት ያላቸው መኪኖች ከአዱስ አበባ እንዳይነዱ የሚያስችል አስገዳጅ መመሪያ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ ተገለፀ።
በአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተዘጋጀው አስገዳጅ መመሪያው በከተማዋ ያለው የአየር ብክለት መጠን ከአለም አቀፍ ብሎም እንደ ሀገር ከወጣው ስታንዳርድ ወይም መለኪያ በማለፉና አስጊ ደረጃ በመድረሱ መሆኑም ተነግሯል፡፡
በከተማዋ ከሚከሰተው የአየር ብክለት ውስጥ 27 በመቶው ከተሽከርካሪዎች የጭስ እና የጋዝ ብናኝ ምክንያት እየተከሰተ መሆኑንም ተገልጿል፡፡
በተሽከርካሪዎች ላይ በሚደረግ ፍተሻ ከጭስ እና ከጋዝ ልቀት አልፈው ከተገኙ ለጊዜወ አገልግሎት እንዳይሰጡ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡
ሆኖም ግን ተሽከርካሪዎች የተሻለ ቴክኖሎጂዎች እንዲገጠምላቸው እና የብክለት መጠኑ እንዲቀንስ አስፈላጊውን የጥገና ስራ እንዲደረግላቸው ይደረጋልም ተብሏል፡፡
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡https://rb.gy/3bghek
በአዲስ አበባ የአከራይና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ዛሬ ይጀመራል
በአዲስ አበባ የአከራይና ተከራይ ህጋዊ ውል ምዝገባ ዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጀመር የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።
የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ በሀገሪቱ ያለውን የቤት ኪራይ ችግር ለመፍታት እንዲሁም ፍትሃዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማህበረሰቡ ኑሮና በአጠቃላይ ሀገራዊ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚፈጥረውን ጫና ከግምት በማስገባት ተዘጋጅቶ መጽደቁ ይታወሳል፡፡
ከሰኔ 1 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የግል ቤት አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር ህጋዊ ሰነዶቻቸውን ይዘው በመቅረብ ምዝገባ ማድረግ እንደሚችሉ አስገንዝቧል።
በስራ ሰዓት መመዘግብ የማይችሉ አከራይና ተከራዮች ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም በስራ ቀን ማታ ከ12 ሰዓት በኋላ ህጋዊ የውል ምዝገባውን መፈጸም እንደሚችሉም ተገልጿል።
በምዝገባውና አዋጁን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ቅሬታዎችን በመቀበል ማስተናገድ የሚያስችል አሰራር መዘርጋቱም ተነግሯል።
(ፋና)

በ #ኦሮሚያ ክልል አሙሩ ወረዳ በታጣቂዎች በደረሰ ጥቃት ሶስት ሰዎች ተገደሉ
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ ረቡ ዕለት ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡ በጥቃቱ የተገደሉ ሰዎች በሞተር ሳይክል ወደ አጋምሳ ከተማ ሲጓዙ እንደነበር ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ከሞቱት መካከል አንድ መምህር እንደሚገኝበትም የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ አሙሩ እና ምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ሀሮ በሚባል አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶችን ሲያደርሱ እንደነበር ጠቁመዋል፡፡
የአሙሩ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ቂጠሳ በአሙሩ ወረዳና ኪረሙ ወረዳ መካከል በሚገኘው ጎንካ በሚባል ቦታ በደረሰው ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን ማረጋገጣውን ዶቼ ቬለ ዘግቧል፡፡
"ታጣቂዎቹ በአዋሳኝ አካባቢዎች እየገቡ ነው ጥቃት አድርሰው የሚመለሱት" ያሉት አቶ ቂጠሳ በጸጥታ ጉዳይ ኦፕሬሽን የሚፈልጉ ቦታዎች አሉ፤ እንደ አሙሩ በዚህ ጉዳ ላይ እየተሰራ ነው” ብለዋል።
በአሙሩ ወረዳ ለ3 ዓመታት በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ከ40ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው መቆየታቸውን እና በአሁኑ ወቅት ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን ይታወቃል።
================
የአዲስ ስታንዳርድ አማርኛ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ፡
ቴሌግራም: https://rb.gy/rekjr
ፌስቡክ: https://rb.gy/xwxb3
ትዊተር (X)፡ https://rb.gy/34uh4
ዩቲዩብ፡ https://rb.gy/bjcbg
ድረገጽ: https://rb.gy/5td6n
ቲክቶክ፡ https://rb.gy/3bghek

#ኢትዮጵያ በ #ሩሲያ በመካሄድ ላይ ባለው 3ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ተወካዮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈች ነው
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ እና በብሪክስ የኢትዮጵያ ዋና ተወካይ አቶ ማሞ እስመልዓለም ምህረቱ የሚመራ የልዑካን ቡድን ዛሬ በሩሲያ በተጀመረው 3ኛው የብሪክስ የአባል ሀገራት ተወካዮች ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።
አቶ ማሞ በብሪክስ አባል አገራት መካከል በንግድ፣ ኢንቨስትመንት ፣ ቱሪስት ፍሰትና ሌሎች መስኮች ያለውን የኢኮኖሚ ግንኙነት ማሳደግ እንደሚገባና የልማት ፋይናንስን በመጨመር የአካታች እና ዘላቂ ልማትን መደገፍ አስፈላጊ መሆኑን በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል።
በተለዋዋጭና ሊተነበይ በማይቻል የአለም ኢኮኖሚና ፖለቲካ ምኅዳር ዉስጥ ብሪክስ ሀገራትን እና ሃብቶችን በማሰባሰብ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶችን በአጋርነት መንፈስ ለመቅረፍ አረጋጊ ኃይል ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ጠቅሰዋል።
አክለውም፣ ኢትዮጵያ የብሪክስ ብሔራዊ ተሳትፎ ስትራቴጂን በብሔራዊ የሚኒስትሮች አስተባባሪ ኮሚቴ ማፅደቋን መግለጻቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ዜና፡ የቀድሞ የ #ኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከእስር ተፈቱ፤ አዋሽ አርባ የነበሩ ሰባት ፖለቲከኞች ወደ አዲስ አበባ ተዘዋወሩ
“ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” በሚል መሪ ቃል ህዳር 30 ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ ትላንት ሰኔ 1/ 2016 ከእስር መፈታታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሙሉ ብርሃን ገለጹ።
"አቶ የሺዋስ ታመው ስለነበር እንደተፈቱ ካሳንችስ አካባቢ ወደሚገኘው መቅረዝ ሆስፒታል በማምራት ህክምና ተደርጎላቸው ማታ ወደ ቢቤታቸው ገብለዋል ሲሉ" ወ/ሮ ሙሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እያለ ከሰልፍ ጋር ተያይዞ ከሁለት ወራት በላይ #አፋር በሚገኘው አዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ ታስረው የነበሩ ሰባት ፖለቲከኞች እርብ ዕለት ወደ አዲስ አበባ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ መዘዋወራቸውን የ #ኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቢ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ይመልከቱ፦ https://wp.me/pfjhHd-1bI

የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ ከእስር ተፈቱ - Addis standard
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2/ 2016 ዓ/ም፡– “ጦርነት ይቁም! ሰላም ይስፈን!” በሚል መሪ ቃል ህዳር 30 ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ አስተባባሪ የሆኑት የቀድሞ የኢዜማ ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ከአንድ ሳምንት እስር በኋላ ትላንት ሰኔ 1/ 2016 ከእስር መፈታታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሙሉ ብርሃን ገለጹ። አቶ የሺዋስ ታመው ስለነበር እንደተፈቱ ካሳንችስ አካባቢ ወደሚገኘው መቅረዝ ሆስፒታል በማምራት ህክምና…
የ #ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአራት አመታት በኋላ ወደ አክሱም ከተማ ዳግም በረራ ጀምሯል።
በ #ትግራይ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት አጼ ዮሐንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ የተደረገለት ጥገና ተጠናቆ ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2016 መደበኛ ስራ ጀምራል።
ዛሬ በተደረገ የመጀመሪያ በረራም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ መስፍን ጣሰውን፣ የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ 140 ተጓዦች የያዘው አውሮፕላን አክሱም ሃፀይ ዮሐንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጓል።
በአቀባበል ስነ ስርዓቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
በረራውም በየቀኑ 1 ጊዜ የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቀን ወደ 3 ጊዜ ለማሳደግ እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡