ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ዛሬ ከሰዓት መወያየታቸውን የጠ/ሚ ፅ/ቤት አስታውቋል::
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን ያደረጉት ከልዑካቸው ጋር በአውሮፓ ያደረጉትን የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ከተመለሱ ከሰዓታት ቆይታ በኋላ ነው።

ዜና፡ ድንበር ጥሰው ወደ ክልሉ የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎችን ገድለው አንድ ሰው ማቁሰላቸው ተገለፀ
ከደቡብ ሱዳን በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ጋምቤላ ክልል የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎችን ገድለው አንድ ሰው ማቁሰላቸውን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ።
ድንበሩ ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተለይም በአኙዋና በኑዌር ዞኖች ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸም መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጓዳኝ ህብረተሰቡ በንቃት አካባቢውን እንዲጠብቅ አቶ ኡቶው አሳስበዋል።
የሙርሌ ታጣቂዎቹ ከዚህ በፊትም በተለይም በበጋው ወራት በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ጥሰው በመግባት የሰው ሕይወት ሲያጠፉ፣ ሕፃናትን አፍነው ሲወስዱና ንብረት ሲዘርፉ እንደነበር ይታወቃል።
ባሳለፍነው አመት ጥር ወር አጋማሽ ላይ ከደቡብ ሱዳን በመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች በክልሉ ኑዌር ዞን አኮቦ ወረዳ ባካንካን ቀበሌ ላይ በከፈቱት ጥቃት ስምንት ሰዎች ሲሞቱ አምስት ሰዎች ቆስለዋል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-ድንበር-ጥሰው-ወደ-ክልሉ-የገቡ-የሙር/?fbclid=IwAR3jWB1QWs0-F2Gp5IznCYfasAtVoaPuVhQ9IiebghNUJllM8_HEinb7PI0

Addis Standard
ዜና፡ ድንበር ጥሰው ወደ ክልሉ የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎችን ገድለው አንድ ሰው ማቁሰላቸው ተገለፀ
የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ኡቶው ኡኮት አዲስ አበባ፣ የካቲት፣2/ 2015 ዓ.ም፡- ከደቡብ ሱዳን በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ጋምቤላ ክልል የገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎችን ገድለው አንድ ሰው ማቁሰላቸውን የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል […]
ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ የትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በመውጫ ፈተና ዙሪያ ከተማሪዎች ህብረት ተወካዮች ጋር የተወያዩ ሲሆን የመውጫ ፈተና በመጪው ሐምሌ ወር በኦንላይን ለሁሉም የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደሚሰጥ ገልጸዋል።
ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ብቁ ለመሆንም ተማሪዎች በየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚሰጠውን የመጨረሻውን ሴሚስተር ፈተና መውሰድና ኮርሶችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
ለፈተናው በሁሉም የትምህርት መስኮች ላይ የተመረጡ ኮርሶች የብቃት ልየታ ተደርጎላቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንዲያውቁት መደረጉን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው በአሁኑ ወቅት የፈተና ንድፈ ማሳያና የፈተና ዝግጅት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በመሆኑም ተማሪዎች በቀሪዎቹ አምስት ወራት ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ራሳቸውን ለፈተናው ብቁ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በመድረኩ የተገኙ የተማሪዎች ህብረት ተወካዮችም ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻቸው ሲመለሱ ተማሪዎች ለፈተናው በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል፡፡
ምንጭ -ዋልታ

ዜና፡ የሰላም ጥረቱን ተከትሎ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና ስደተኞች የሚደረገው ድጋፍ እና መፍትሔ እንዲጠናከር የተመድ የስደተኞች ኮሚሽን ጠየቀ
በኢትዮጵያ ከቀያቸው የተፈናቀሉ እና ስደተኞችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን የበለጠ እንደሚያጠናክር ሃላፊው ፍሊፖ ግራንዴ አስታወቁ። በኢትዮጵያ በድርቅ እና የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተፈናቀሉም ሆኑ ስደተኞችን ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ለማስቻል ኮሚሽኑ ጥረቱን እንደሚያጠናክር ገለጸዋል።
የሰላም ስምምነቱ ከተደረሰ ጥቅምት ወር ጀምሮ ከተባባሪ ድርጅቶች ጋር በመሆን በርካታ እገዛወችን ማድረጉን ያሰታወቀው ዩኤንኤችሲአር፣ የህይወት አድን እርዳታዎች በተለይም ደግሞ መድሃኒት፣ የመጠለያ ቁሳቁሶቸ፣ አልባሳት፣ የቤት ቁሳቁሶቸ እና ብርድ ልብሶችን ማድረሱን አመላክቷል።
“የአርዳታ አቅርቦቱ መሬት ላይ ወርዶ የሚታይ ሆኗል፤ ህዝቡ ድጋፍ እያገኘ ነው፤ አንዳንዶች ወደ ቀያቸው እየተመለሱ ነው” ሲሉ የገለጹት ኮሚሽነሩ በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ የሚደረገውን የመልሶ ግንባታ እና ማቋቋም ጥረትን ይበልጥ ማገዝ ይገባል ብለዋል።
በተጨማሪም ኮሚሽነሩ ይህ ተግባር በፍቃዳቸው ወደ ቀያቸው የሚመለሱትን ጨምሮ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት እና ኑሯቸውን ለማሻሻል የሚያስችል ወሳኝ ተግባር ነው ሲሉ ገልጸዋል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-የሰላም-ጥረቱን-ተከትሎ-በኢትዮጵያ/?fbclid=IwAR3F8viQ2T6zkUWRqsq3GrvDLzAlFKMNBv0eI1IO-uCzEFU6QaxQQplYAec

© UNHCR/Samuel Otieno አዲስ አበባ፣ የካቲት 2/ 2015 ዓ.ም፡– በኢትዮጵያ ከቀያቸው የተፈናቀሉ እና ስደተኞችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን የበለጠ እንደሚያጠናክር ሃላፊው ፍሊፖ ግራንዴ አስታወቁ። በኢትዮጵያ በድርቅ እና የአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የተፈናቀሉም ሆኑ ስደተኞችን ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ ለማስቻል ኮሚሽኑ ጥረቱን […]
ዜና፡ መንግስት በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ እና ሃይማኖት አባቶች ላይ እየደረሰ ያለውን ማዋከቦች፣ እስሮች እና ግድያዎችን በአስቸኳይ እንዲያስቆም ኢዜማ አሰሰበ
መንግስት በኦሮሚያ ክልል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ እና በሃይማኖት አባቶች ላይ እየደረሰ ያለው ማዋከቦች፣ እስሮች እና ግድያዎችን በአስቸኳይ ኢንዲያስቆም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አሳሰበ።
ፓርቲው ከመንግስት ሃላፊዎች አባባሽ ንግግሮች ባሻገር የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትና የጸጥታ ኃይሉ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት በተግባር ካሳዩት ወገንተኝነት እና አድሎ በከፋ መልኩ ፈፅሞ የጸጥታ ስጋት ባልሆኑ ምእመናን ላይ ጭካኔ የተሞላበት የኃይል እርምጃ በመውሰዳቸው የንጹሐን ዜጎች ሕይወት እንዲቀጠፍ እና አካል እንዲጎድል ምክንያት ሆኗል ብሏል፡፡
በዛሬ እለት እንኳን በወሊሶ መስመር በወለቴ፣ አለምገና እና ሰበታ ቀውሱ ተባብሶ ቀጥሏል ያለው የድርጅቱ መግለጫ ግልፅ በሆነ መንገድ ጣልቃ እየገባ ያለው መንግሥት ለሀገር ሰላምና ደህንነት ስጋት እየፈጠረ መሆኑን ተገንዝቦ ኃላፊነቱ “ህግን አክብሮ ማስከበር” መሆኑን በመረዳት እንዲንቀሳቀስ አሳስቧል
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-መንግስት-በኦርቶዶክስ-እምነት-ተከ/?fbclid=IwAR3EwPL_RS3iOY7q24Nq1ZRzFBPb3K-FpujKcIAzf7NPQ-SuF8wKOYHJZVM

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2/ 2015 ዓ.ም፡- መንግስት በኦሮሚያ ክልል በኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ላይ እና በሃይማኖት አባቶች ላይ እየደረሰ ያለው ማዋከቦች፣ እስሮች እና ግድያዎችን በአስቸኳይ ኢንዲያስቆም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አሳሰበ። ኢዜማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተፈጠረውን ችግር መሰረት በማድረግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በተቋሙ […]
ዜና፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ በርካታ ቅርንጫፎቹ የተሟላ የባንክ አገልግሎት ጀመረ፤ በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል የከፈቱ የሂሳብ ደብተሮች መጠቀም ይቻላል ተባለ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል በሽሬ፤ አክሱም፤ ዓድዋ፤ ሰለኽለኻ፤ ማይ ፀብሪ፤ እንዳባጉና፤ ውቕሮማራይ፤ ዓዲግራት፣ ውቕሮ፣ ፍረወይኒ፣ ሓውዜን፣ ዓዲጉዶም፣ ሒዋነ፣ ዓዲሽሁ፣ መኾኒ፣ ማይጨውና አካባቢው በሚገኙ በርካታ ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡
ባንኩ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እደገለጸው፥ አገልግሎት መስጠት በጀመረባቸው ቅርንጫፎች ለደንበኞች የተሟላ የባንክ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ “የባንኩ ደንበኛ የሆነ ማንኛውም ሰው በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል የከፈተውን የሂሳብ ደብተር ይዞ በመቅረብ አገልግሎት ማግኘት ይችላል” ሲልም ጨምሮ ገልጿል፡፡
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-የኢትዮጵያ-ንግድ-ባንክ-በትግራይ-በ/?fbclid=IwAR0TMb29k98SRVSkOgvVuF7r6hr13_or7rvFFIz8zMEVAm79shWHULAHg44

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2/ 2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትግራይ ክልል በሽሬ፤ አክሱም፤ ዓድዋ፤ ሰለኽለኻ፤ ማይ ፀብሪ፤ እንዳባጉና፤ ውቕሮማራይ፤ ዓዲግራት፣ ውቕሮ፣ ፍረወይኒ፣ ሓውዜን፣ ዓዲጉዶም፣ ሒዋነ፣ ዓዲሽሁ፣ መኾኒ፣ ማይጨውና አካባቢው በሚገኙ በርካታ ቅርንጫፎች የተሟላ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡ ባንኩ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት እደገለጸው፥ አገልግሎት መስጠት […]
በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ዝግ ተደረጉ
በአዲስ አበባ ከተማ በዛሬው እለት በትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደት እየተከናወነ አለመሆኑን አዲስ ስታነንዳርድ አረጋግጣለች፡፡
አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረቻቸው መምህር በስብሰባ ምክኒያት በዛሬው እለት ትምህርት ቤት ዝግ መደረጋቸውን ገልፀውልናል፡፡
ዝግ የተደረጉት ትምህርት ቤቶች የመንግስት ብቻ ሳይሆኑ የግል ትምህርት ቤቶች ጭምር መሆኑን አዲስ ስታነዳርድ ማረጋገጥ ችላለች፡፡
ትላንት አመሻሽ ላይ ትምህርት ቤቶች በዛሬው እለት ትምህርት አለመኖሩን የሚገልፅ አጭር መልዕክት ለወላጆች የተላከ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ትምህርት ዝግ የተደረገበት ምክኒያት የሰራተኞችና የኮሚቴ ስብሰባ ለማድረግ ነው በሚል መሆኑን ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ ምንጫችን ገልፀዋል፡፡
ፎቶ- የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

ዜና፡ በመንግስትና በቅዱስ ሲኖደስ መካከል የቃላት ጦርነት ተባብሶ ቀጥሏል፤ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ–ኃይል ሰልፍ እናዳይካሄድ ቢያስጠነቅቅም ሲኖዶሱ ሰላማዊ ሰልፉ ተፈጻሚ እንደሚሆን ገልጧል
በመንግሥትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየተባባሰ በሄደበት ወቅት ሁለቱም ተቋማት ትላንት ከስዓት በኋላ የራሳቸውን አቋም የሚያንጸባርቅ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ መንግስት በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው "መንግስትን በትጥቅ ሃይል ለመነቅነቅ" እየሰሩ ያሉ እና “ለዚህ አላማ ወጣቶችን የሚመለምሉ” አካላት መኖራቸውን መረጃ ማግኘቱን አስታውቋል።
ቅዱስ ሲኖዶሱ ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ–ኃይል የተፈቀደ ሰልፍ የለም በማለት መግለጫ ቢሰጥም ፣ ሰላማዊ ሰልፉ በሀገራ አቀፍ ደረጃ በተያዘለት መርሃ-ግብር እንደሚከናወን ቅዱስ ሲኖዶሱ አስታውቋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ አክሎም የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ–ኃይል የተሰጠው የሰልፍ ክልከላ መግለጫ መንግሥት አሁንም ችግሩን ለመፍታት ሳይሆን ቤተክርስቲያኒቱን ለአንዴና ለመጨረሻ ለማውደምና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማጥፋት የታወጀ አዋጅ መሆኑን “በጽኑ እንድናምን” አድርጎናል ብሏል፡፡
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-በመንግስትና-በቅዱስ-ሲኖደስ-መካከ/?fbclid=IwAR0U8at9Bs-HPvrvlY10uUYpCCZvpfmd9uX87Op-MlyKQioczGmBVL8_3zc

አዲስ አበባ፣ የካቲት፣3/ 2015 ዓ.ም ፡- በመንግሥትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መካከል የተፈጠረው አለመግባባት እየተባባሰ በሄደበት ወቅት ሁለቱም ተቋማት ትላንት ከስዓት በኋላ የራሳቸውን አቋም የሚያንጸባርቅ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ መንግስት በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው "መንግስትን በትጥቅ ሃይል ለመነቅነቅ"…
ዜና፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ እየተወያየ መሆኑን አስታወቀ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፓትሪያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር በጠቅላይ ሚንስትሩ ጵ/ቤት እየተወያዩ መሆኑን አስታወቀ፡፡
ወይይቱ እየተደረገ ያለው የኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ትላንት ባወጣው መግለጫ ላይ የቤተ ክስቲያኒቱን ሃይማኖት ቀኖና እና አስተዳራዊ ሕግጋትን ባልጣሰ መልኩ ከመንግስት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመወያየት መንፈሳዊ በሯ ክፍት መሆኑን በገለፀችው መሰረት ጠቅላይ ሚንስትሩ ለውይይት ጥሪ በማቅረባቸው መሆኑንን የሲኖዶሱ መግለጫ ገልጧል፡፡
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-የኢትዮጵያ-ኦርቶዶክስ-ተዋሕዶ-ቤተ/?fbclid=IwAR2EFyR8Y_sw0iQjHtNJ7m6-yJFcZC6NrygJGb9qGH-kCJKKb87xVoBf4VU

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3/ 2015 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፓትሪያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ ከጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጋር በጠቅላይ ሚንስትሩ ጵ/ቤት እየተወያዩ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ወይይቱ እየተደረገ ያለው የኢትዮጵያ ኦርትዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ትላንት ባወጣው […]
ዜና፡ አዲስ “ቤተ ክህነት” አቋቁመናል በማለት ያሳወቁ ጳጳሳትን የተቃወሙ ሰዎችና የሃይማኖት መሪዎች ላይ የሰበዓዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን ኢሰመኮ አስታወቀ
አዲስ “ቤተ ክህነት” አቋቁመናል በማለት ያሳወቁ ጳጳሳት በአንዳንድ ቦታዎች በኃላፊዎች ድጋፍ ጭምር በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሚገኙ ሀገረ ስብከቶችን መያዛቸውን ተከትሎ ይህን ድርጊት በተቃወሙ ሰዎችና የሃይማኖት መሪዎች ላይ በመንግሥት የጸጥታ አባሎች በርካታ የሰበዓዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ፡፡
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-አዲስ-ቤተ-ክህነት-አቋቁመናል-በ/?fbclid=IwAR3cSF-J5UXPa8vR9Ur6xlZxTbPqY9zoKqE4WCFGRjr8_ViguptEiyHFmU0
አክሎም ሲኖዶሱ ያቀረበውን የጥቁር መልበስ ጥሪ የተቀበሉ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ እስሮች፣ ከአገልግሎት እና ከሥራ ቦታ ማግለልና ማንገላታት ፍጹም ተገቢ ያልሆኑ እና የዜጎችን በሕይወት የመኖር፣ በነጻነት ሃይማኖታቸውን እና ሐሳባቸውን የመግለጽ ሕገ መንግሥታዊ መብቶችን የሚፃረሩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፈፀማቸውን አረጋግጫለው” ብሏል፡፡
መንግሥት የተሟላና ተገቢውን ማጣራት አድርጎ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ ሊወስድ እና የተጎዱትንም ሊክስ ይገባል ሲል ኮሚሽኑ ገልጧል። በተጨማሪም የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ተቃውሞ በሚያደርጉ ሰዎች ላይ ኃይል ከመጠቀም፣ ከማንገላታት፣ ከሕገ ወጥ እስር እና የሰዎችን እንቅስቃሴ ያለበቂ ምክንያት ከመገደብ መቆጠብ ይኖርባቸዋል ሲል አሳስቧል፡፡

አዲስ አበባ፣ ጥር 3/ 2015 ዓ.ም፡- አዲስ “ቤተ ክህነት” አቋቁመናል በማለት ያሳወቁ ጳጳሳት በአንዳንድ ቦታዎች በኃላፊዎች ድጋፍ ጭምር በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሚገኙ ሀገረ ስብከቶችን መያዛቸውን ተከትሎ ይህን ድርጊት በተቃወሙ ሰዎችና የሃይማኖት መሪዎች ላይ በመንግሥት የጸጥታ አባሎች በርካታ የሰበዓዊ መብት ጥሰት መፈፀሙን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች […]
በ #አፋር ክልል በግጭቱ ትምህርት አቋርጠው የነበሩ 368 ትምህርት ቤቶች ስራ ጀምረዋል
በአፋር ክልል በግጭት ምክንያት ትምህርት አቋርጠው የነበሩ 368 ትምህርት ቤቶች ዳግም ትምህርት እየሰጡ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ዳግም ትምህርት መስጠት ከጀመሩት ትምህር ቤቶች ውስጥ 358ቱ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲሆኑ፥ አስር የሚሆኑት ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በአፋር ክልል ዞን 2 ውስጥ የሚገኙ 6 ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና 202 አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች አስፈላጊው እገዛ ተደርጎላቸው ትምህርት እየሰጡ መሆኑን በሚኒስቴሩ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አመለውርቅ ሕዝቅኤል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በዞን አራት ውስጥ የሚገኙ 4 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና 156 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ዳግም ተቀብለው ትምህርት እየሰጡ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በክልሉ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርት አቋርጠው ስራ ያልጀመሩ ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለማስጀመርም የዳሳሳ ጥናት በማድረግ በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ምንጭ- ፋና

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን (ኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ) ለየካቲት 05/2015 የጠራችው አገር አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ መራዘሙን ቅዱስ ሲኖዶስ አስታውቋል፡፡
ቅዱስ ሲኖዶሱ መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ ሰልፉ መራዘሙን ገልጿል።

ዜና፡ በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከ50 በመቶ በታች ላመጡ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ
በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከ50 በመቶ በታች ላመጡ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በዚህም መሰረት በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የአቅም ማሻሻያ (Remedial ፕሮግራም) ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣ 180 ከ 600 እና 150 ከ 500) በመሆን የተቆረጠ መሆኑ ተገልጧል።
የተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 263 ፣ የተፈጥሮ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ700 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 227 ፣ የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 220 ፣ የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች ፤ ከ600 በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለመማር የረሜዲያል መቁረጫ ነጥብ 190 እንዲሆን ተወስኗል፡፡
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-በዩኒቨርሲቲ-መግቢያ-ፈተና-ከ50-በመቶ/?fbclid=IwAR2nesx4GeDjMjLO7zX9_jN2uDOeAJ6MeG_UelQKO1o3REj2MUij1wgddiU

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6/2015 ዓ.ም፡- በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከ50 በመቶ በታች ላመጡ ተማሪዎች የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ይፋ መደረጉን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው 50 ከመቶ እና […]
ዜና፡ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ጦር ጋር አንድ ሁነን ተባብረን በመዋጋታችን ትልቅ ልምድ እና ትምህርት ቀስመናል ሲሉ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ገለጹ
ከኢትዮጵያ ፌዴራል ጦር ጋር አንድ ሁነን ተባብረን በመዋጋታችን ትልቅ ልምድ እና ትምህርት ቀስመንበታል እንዲሁም በቀጠናው ሰላም ለማስፈን ጥሩ ተሞክሮዎችን ተለዋውጠናል ሲሉ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተናገሩ።
የፌደራል መንግስቱ እና ህወሓት የሰላም ስምምነት በመፈጸማቸው ለእኛ የሚያሳስበን ነገር የለም፤ መፈራረማቸው ጥሩ ነው፤ ስምምነቱ ወደ ተግባር ተለውጦ ሳናይ የምንሰጠው አስተያየት የለም ብለዋል። ስምምነቱን ተግባራዊ ከማድረግ ይልቅ የተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ዘመቻ በማካሄድ ህወሓቶች እና ተላኪዎቻቸው ተጠምደዋል ሲሉ አስታውቀዋል።
ጦርነቱ ምንም አይነት አላማ ሳይኖረው በህወሓት እና ዘዋሪዎቹ የዋሽንግተን አካላት የተለኮሰ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንቱ በተደጋጋሚ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል የሚፈጠር ሰላም ለዋሽንግተን ትልቅ ራስ ምታት ነው ሲሉም ተናግረዋል። ህወሓቶች አቅማቸውን አያውቁም፤ እነሱን የሚይዟቸው እና የሚያሽከረክሯቸው የዋሽንግተን ቡድንም ከነሱ የባሱ ናቸው ሲሉ የተደመጡት ፕሬዝዳንቱ የዋሽንግተን የተሳሳተ ስሌት ለህወሓት የልብ ልብ ሰጥቶታል ብለዋል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-ከኢትዮጵያ-ፌዴራል-ጦር-ጋር-አንድ-ሁ/?fbclid=IwAR2TBoNV4a9f9EF0vvnrUrV3bVEOWJoOFC8tIg_uhKhtf29AQ9REOLazV5o

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6/ 2015 ዓ.ም፡- ከኢትዮጵያ ፌዴራል ጦር ጋር አንድ ሁነን ተባብረን በመዋጋታችን ትልቅ ልምድ እና ትምህርት ቀስመንበታል እንዲሁም በቀጠናው ሰላም ለማስፈን ጥሩ ተሞክሮችን ተለዋውጠናል ሲሉ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ተናገሩ። የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ይህን ያሉት በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል በተለይም በትግራይ ላይ ስለተካሄደው […]
#ደብረታቦር ዩኒቨርስቲ "ከክርስቲያን ሪሊፍ ሰርቪስ" ጋር በመተባባር ለደብረታቦር አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና እና የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ።
14 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገባቸው በአይነት 35 ብዛታቸው ደግሞ 689 የህክምና እና የመማሪያ ቁሳቁሶች ለተቋማቱ ያለባቸውን የህክምና እና የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ለመቅረፍ ለደብረታቦር ሆስፒታል እና ለቀጨን መስክ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተበርክቷል።
"ደብረ ታቦር ዩኒቨርስቲ ከመማር ማስተማሩ በተጨማሪ በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎት ስራዎችን እየሰራ ያለ ተቋም ሲሆን በዞኑ የህክምና እና የመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ያለባቸውን ተቋማት በመለየትና ከአለም አቀፍ ርዳታ ድርጅቶች ጋር ልዩ ስምምነት በማድረግ ድጋፉን አበርክቷል" በማለት የአማራ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

ዜና፡ ፕሬዘደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጋር ተወያዩ ፤ “ዘር እና ሃይማኖትን” ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል “ቀይ መስመርን መተላለፍ ነው” አሉ
ፕሬዘደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ማትያስን ጨምሮ የቤተክርስቲያኒቷን መሪዎችን ካነጋገሩ በኋላ ሰኞ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም በማኅበራዊ ትስስር ገጾቸው ባሰፈሩት መግለጫ “ዘር እና ሃይማኖትን ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል ቀይ መስመርን መተላለፍ ነው” አሉ።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-ፕሬዘደንት-ሳህለወርቅ-ዘውዴ-ከኦር/?fbclid=IwAR0STAnpKHeueRjHNvYUzTmMxnFyoyqgWqyam3TYIz-KfxNpye-sBedVzuk
“የሰው ልጅ በህይወቱ፣ በስራው፣ በማህበራዊ ኑሮው ድንበር ከሌለው እራሱ የአደጋ ምንጫ ነው” ሲሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከገጠማት ወቅታዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ሀሳባቸውን ገልፀዋል፡፡
ፕረዝዳንቷ በምእመናን እና በፀጥታ አካላት መካከል በጠፈጠረው ግጭት ለጠፋው ሕይወት ሀዘናቸውን ሲገልፁም “እምነቶች ለእኛ አማኞች የመጨረሻ ምሽጎቻችን ናቸው፡፡ ብርታት፣ተስፋና ፅናት ይሰጣሉ” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7/ 2015 ዓ.ም፡- ፕሬዘደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አቡነ ማትያስን ጨምሮ የቤተክርስቲያኒቷን መሪዎችን ካነጋገሩ በኋላ ሰኞ የካቲት 6 ቀን 2015 ዓ.ም በማኅበራዊ ትስስር ገጾቸው ባሰፈሩት መግለጫ “ዘር እና ሃይማኖትን ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል ቀይ መስመርን መተላለፍ […]