ዜና: የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት አንድ ግዜ ከአዲስ አበባ ወደ ኮፐን ሀገን የጭነት በረራ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6/ 2015 ዓ.ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት አንድ ግዜ ከአዲስ አበባ ወደ ኮፐን ሃገን የጭነት በረራ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ። ከመጋቢት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባካሄደው ሳምንታዊ በረራ 45 ቶን የመጫን አቅም ያለው B767-300F የካርጎ ፕሌን መጠቀሙን ገልጿል። አዲሱ የጭነት በረራው በአውሮፓ እና በተቀረው አለም ያለውን የንግድ ትስስር ይበልጥ ለማሳደግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አስታውቋል።
ከጭነት በረራው በተጨማሪ ወደ ኮፐንሀገብ የሚያደርገውን ሳምንታዊ መንገደኛ የማጓጓዝ በረራ ከግንቦት ወር ጀምሮ ወደ አምስት እንደሚያሳድገው ጠቁሟል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና-የኢትዮጵያ-አየር-መንገድ-በሳምንት-አ/?fbclid=IwAR07Rp_JPWLbfBOHX03kayg9oBdOiVjodWjVTx_2hAqCmIAvzxhF6elbkZc

Addis Standard
ዜና: የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት አንድ ግዜ ከአዲስ አበባ ወደ ኮፐን ሀገን የጭነት በረራ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6/ 2015 ዓ.ም - የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሳምንት አንድ ግዜ ከአዲስ አበባ ወደ ኮፐን ሃገን የጭነት በረራ ማድረግ መጀመሩን አስታወቀ። ከመጋቢት 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባካሄደው ሳምንታዊ በረራ 45 ቶን የመጫን አቅም ያለው B767-300F የካርጎ ፕሌን መጠቀሙን ገልጿል። አዲሱ የጭነት በረራው […]
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 6ኛው ክልል አቀፍ የባህል እና ዋዛ ፌስቲቫል በተለያዩ ዝግጅቶች መከበር ጀመረ
የ #ቤኒሻንጉልጉሙዝ ክልል 6ኛው ክልል አቀፍ የባህል እና ዋዛ ፌስቲቫል በተለያዩ ዝግጅቶች መከበር ጀመረ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኮሙኒኬሽን ቢሮ እንደገለጸው፣ "ባህላችን ለአብሮነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ-ቃል መከበር የጀመረው ፌስቲቫል በባህላዊ ሁነቶች፣ በፓናል ውይይት፣ በኤግዚቪሽንና ባዛር በድምቀት ይከበራል።
"ፌስቲቫሉ በዛሬው ዕለት በፓናል ውይይት መከበር የጀመረ ሲሆን፣ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ይሆናል" ሲልም ቢሮው ጨምሮ ገልጿል።
በመድረኩም የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሠር አበባው አያሌውን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዜና ትንታኔ: #አዲስ አበባን የሁከት ማእከል ለማድረግ የተደረጉ ሙከራዎች መክሸፋቸውን ከንቲባ #አዳነች አበቤ አስታወቁ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6/ 2015 ዓ.ም - አዲስ አበባ ከተማን የሁከት ማእከል ለማድረግ በተለያየ ግዜ የተደረጉ የተለያዩ ሙከራዎች መክሸፋቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አበቤ አስታወቁ፡፡
ከንቲባዋ በመካሄድ ላይ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤው ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመለከቱት ባለፉት ስድስት ወራት የከተማ አስተዳደሩ ካስመዘገባቸው ዋና ዋና ተግባራት አንዱ ከተማይቱ የሁከት አውድማ ከመሆን ለመታደግ የተሰራ ስራ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለፉት ወራት መነሻቸውን ከአማራ ክልል የተለያዩ አከባቢዎቸ ያደረጉ ተጓዦች በኦሮምያ ክልል የጸጥታ ሀይሎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ መከልከላቸውን የተመለከተ ዘገባ የክልሉ የቴሌቪዥን ጣቢያ አሚኮ ማሰራጨቱ ይታወሳል።
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (#አብን) ከንቲባዋ አዳነች አቤቤ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ያቀረቡትን ሪፖርት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ከንቲባዋ ያቀረቡት ሪፖርት ተቃውሞ መንግስት ከንቲባዋን ከስልጣን እንዲያነሳ እና ለፍርድ እንዲያቀርብ አሳስቧል።
ከሳምንት በፊት ወደ አዲስ አበባ መግባት ከአማራ ክልል ነዋሪዎች አስቸጋሪ ሁኗል በሚል ከክልል ምክር ቤት አባላት ለቀረበ ጥያቄ የክልሉ ፕሬዝዳንቱ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ሲመልሱ ዜጎች በሀገራቸው በነጻ መንቀሳቀስ አለባቸው ይህም በህገመንግስቱ ተደንግጓል፤ ይህን ማስከበር አለብን ማለታቸው ይታወሳል።
ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም #ሱዳን በነጻ እየገባን አንዳንድ ሀገሮች ላይ ያለቪዛ በቀጥታ እየገባን በሀገራቸው እዚህ ቁሙ ሊንባል አይገባም ሲሉ ተደምጠዋል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና-አዲስ-አበባን-የሁከት-ማእከል-ለማድረ/

ዜና: አዲስ አበባን የሁከት ማእከል ለማድረግ የተደረጉ ሙከራዎች መክሸፋቸውን ከንቲባ አዳነች አበቤ አስታወቁ
ፎቶ ከአስተዳደሩ የማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6/ 2015 ዓ.ም - አዲስ አበባ ከተማን የሁከት ማእከል ለማድረግ በተለያየ ግዜ የተደረጉ የተለያዩ ሙከራዎች መክሸፋቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አበቤ አስታወቁ፡፡ ከንቲባዋ በመካሄድ ላይ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤው ላይ ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመለከቱት […]
#ኢትዮጵያ እና #አሜሪካ ግንኙነታቸውን "ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ" ተስማሙ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ረፋድ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንን ተቀብለው አነጋግረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፅህፈት ቤት እንደገለው፣ ውይይታቸው በተለያዩ የሀገር ውስጥ፣ ቀጣናዊ እና የሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ተስማምተዋል።
"ኢትዮጵያ በሰላም ስምምነቱ ላይ እያስመዘገበች ያለችው ስኬት ተቀባይነት አግኝቷል" ያለው ፅህፈት ቤት "በኢኮኖሚው፣ በልማት ጥረቶች፣ በተለይም በግብርና እና በቀጣናዊ መረጋጋት ላይ ያሉ ጉዳዮችም ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል" በማለት ጨምሮ ገልጿል።

ዜና: የ #ኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በ #ቦረና እና በ #ሞያሌ አካባቢዎች 28 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ
*በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎችም ቀጣይነት እንዲኖራቸው ስልታዊ እና የተቀናጁ መሆን እነዳለባቸው ማህበሩ አሳስቧል፡፡
የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ቶላ በቦረና ዞን በድርቅ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው አባባቢዎች በሁሉም አቅጣጫ ማለትም በውሀ አቅርቦት፣ የተረፉትን ከብቶች በማከምም ሆነ ህብረተሰቡ ወደ ተለመደ ያኗኗር ዘይቤው እንዲመለስ እና ቀጣይ ህይወቱን እንዲመራ ዘር በማቅረብም ሆነ በሌሎች ማህበራዊ እና ጤናን መሰረት ባደረጉ ድጋፎች በቅንጅት መስራት እነዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡
በተጨማሪም ህብረተሰቡ በማህበራዊ፣በስነልቦናም ሆነ በኢኮኖሚ በመጎዳቱ ከምግብ እና ከገንዘብ ድጋፍ በተጨማሪ የስነ-ልቦና፣ የጤና እና ወደተለመደ ሕይወቱም በቀላሉ እንዲመለስ ጥብቅ የሆነ ክትትል እንደሚያስፈልገው የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር የወጣት በጎፈቃደኞች ተወካይ የቦርድ አባል ዶ/ር አዲስአለም ሙላት አሳስባለች፡፡
https://amharic.addisstandard.com/ዜና-የትዮጲያ-ቀይ-መስቀል-ማህበር-ባለፉት/?fbclid=IwAR1GqaOjHgImIstr-jBzEr_iL9miF7L4RJPAtbJCTGNISKJO0kqHaCcTZ0k

ዜና: የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ በቦረና እና በሞያሌ አካባቢዎች 28 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ
የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ አበራ ቶላ፡፡ ፎቶ፣የትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎችም ቀጣይነት እንዲኖራቸው ስልታዊ እና የተቀናጁ መሆን እነዳለባቸው ማህበሩ አሳስቧል፡፡ አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6/ 2015 ዓ.ም - የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር በድርቅ ክፉኛ ለተጎዱ የቦረና እና የሞያሌ አካባቢዎች ወደ […]
ዜና: #የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለሦስት እና አራት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎች ላይ የጣለውን እግድ እንዲያነሳ #ኢሰመኮ ጠየቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7/2015 ዓ.ም - አዲስ አበባ የከተማ አስተዳደሩ ባለሦስት እና አራት እግር (ባጃጅ) አነስተኛ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ላይ ያስቀመጠውን ሙሉ እገዳ በማንሳት ለችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ሊያመቻች ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጠይቋል። በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች ላልተወሰነ ጊዜ ገደብ መጣሉ ሕገ-መንግሥታዊ ጥበቃ የተደረገላቸው መብቶች አደጋ ላይ የጣለ እርምጃ ነው ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።
ኮሚሽኑ ባደረገው ክትትል እገዳው በከተማዋ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ በመሆኑ የባጃጅ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎቹንና ቤተሰባቸውን ብቻ ሳይሆን፣ እጅግ በርካታ ተጠቃሚዎችንም ችግር ላይ እንደጣለ መረዳቱን ያመላከተው የኮሚሽኑ መግለጫ መንግሥት ሰዎች ሥራቸውን እና የመረጡትን መተዳደሪያ ያለአግባብ እንዳያጡ ማድረግን ጨምሮ የመረጡትን እና የተቀበሉትን ሥራ እንዲሠሩ የማስቻል ኃላፊነት አለበት ሲል አሳስቧል።
ኮሚሽኑ እገዳውን ተከትሎ የደረሱትን አቤቱታዎች መሠረት በማድረግ የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችን ማነጋገሩን በመግለጫው አስታውቆ ኃላፊዎቹ በከተማዋ ወደ #10 ሺህ የሚገመቱ “የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በከተማ አስተዳደሩ የሥራ ፈቃድ ያልተሰጣቸው መሆኑን፣ እንደ አንድ አገልግሎት ሰጪ በከተማዋ አሠራር ሥርዓት ያልተዘረጋላቸው መሆኑን፣ እንዲሁም ሌሎችም ተዛማጅ ችግሮች” መኖራቸውን እንደገለጹለት አመላክቷል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና-የአዲስ-አበባ-ከተማ-አስተዳደር-ባለሦ/?fbclid=IwAR0KaHrFqm5WXn_43hYyN7rNH_d4SEV6M2gmEqnxzfT1HxaafMQoyDSqSqs

ዜና: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለሦስት እና አራት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪዎች ላይ የጣለውን እግድ እንዲያነሳ ኢሰመኮ ጠየቀ
ፎቶ ከፋይል አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7/2015 ዓ.ም - አዲስ አበባ የከተማ አስተዳደሩ ባለሦስት እና አራት እግር (ባጃጅ) አነስተኛ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተሽከርካሪዎች ላይ ያስቀመጠውን ሙሉ እገዳ በማንሳት ለችግሮች ዘላቂ መፍትሔ ሊያመቻች ይገባል ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ጠይቋል። በሁሉም የከተማዋ ክፍሎች ላልተወሰነ ጊዜ ገደብ መጣሉ […]
ዜና: #በኢትዮጵያ ጦርነቱ ያደረሰውን ጉዳት እና የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ #ብሊንከን በጥንቃቄ ሲመልሱ በሰላም ስምምነቱ ላይ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7/ 2015 ዓ.ም - ትላንት ረቡዕ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት #የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጥንቃቄ በተሞላበት፣ ላለማስቀየም ጥረት በታከለበት መንገድ በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አመታት በተካሄደው ጦርነት የተፈጸመውን ግፍ እና ጥፋት አስመልክተው ምላሽ ሰጥተዋል። ትኩረት ማስቀየሻ በሚመስል መልኩ አጽንኦት ሰጥተው #ከፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት በኋላ ግፉ እና ጥፋቱ መቀነሱ ላይ አተኩረዋል። በተጨማሪም የሰላም ስምምነቱን የፈረሙት ሁለቱም አካላት፣ #ፌደራል መንግስቱ እና #የህወሓት ሀይሎች የተፈጸመውን ሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ያስከተለውን ጉዳት አምነዋል፣ ተቀብለዋል ሲሉ ተደምጠዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት #በትግራይ የተፈጸመውን ከጦርነት ጋር የተያያዘ ሰብአዊ መብት ጥሰት የዘር ፍጅት ወይንም ጀኖሳይድ መሆኑን የሚያትተውን በ2021 የተደረሰውን ሪፖርት መደርደሪያው ላይ እንዲቀመጥ እና እንዳይቀርብ አድርጎታል ሲል ብሊንከን ወደ አዲስ አበባ ከመምጣታቸው ጥቂት ቀደም ብሎ #ፎሬን ፖሊሲ መጽሔት ይፋ አድርጓል። ይህንንም ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ሶስት ዲፕሎማት መስማቱን መጽሔቱ በዘገባው አስታውቋል።
#አዲስ ስታንዳርድ ብሊንከን በአዲስ አበባ #ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገኝቶ ይህንኑ ጉዳይ ጠይቋቸው ነበር፤ ለምን ሪፖርቱ ይፋ አልተደረገም? ሲል። ጥያቄውን በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ በጦርነቱ ወቅት በንጹሃን ላይ የተፈጸሙ ሰብአዊ መብት ጥሰቶች ሀገራችው በተደጋጋሚ በግልጽ ስትኮንን እንደነበር እና በሁሉም ጎራ ያሉ ጥቃቱን የፈጸሙ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማቅረቧን አውስተው ይህንን ጉዳይ ከአንድ አመት በፊት እኔ እራሴ ገልጨው ነበር ብለዋል።
https://amharic.addisstandard.com/ዜና-በኢትዮጵያ-ጦርነቱ-ያደረሰውን-ጉዳት/?fbclid=IwAR2Xx9qTDDo7cYc5PX9R8uigJDUUIXSycdPpqNgWVzVOP6Q7U-7JEOd_Eu4

ዜና: በኢትዮጵያ ጦርነቱ ያደረሰውን ጉዳት እና የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ በጥንቃቄ ምላሽ የሰጡት ብሊንከን በሰላም ስምምነቱ ላይ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል
ፎቶ ከብሊንከን የትዊተር ገጽ አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7/ 2015 ዓ.ም - ትላንት ረቡዕ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ጥንቃቄ በተሞላበት፣ ላለማስቀየም ጥረት በታከለበት መንገድ በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት አመታት በተካሄደው ጦርነት የተፈጸመውን ግፍ እና ጥፋት አስመልክተው ምላሽ […]
የ #አማራ ባንክ #መርሀባ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን መጋቢት 9 በይፋ የሚመረቅ መኾኑን ገለጸ
የአማራ ባንክ መርሀባ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎቱን መጋቢት 9 በይፋ የሚመረቅ መኾኑን ገልጿል።
ባንኩ የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት በተለያዩ የአገልግሎት አማራጮች ለደንበኞቹ ቅርብ በመኾን ላይ መኾኑን ተገልጿል። በአፍሪካ መሪ እና ጨዋታ ቀያሪ እንዲሁም ተወዳዳሪ የመኾን አላማን አንግቦ መነሳቱን ባንኩ ገልጿል።
እስካሁን በተጓዘባቸው መንገዶች ከፍተኛ የካፒታል አቅምን በማጎልበት ተወዳዳሪ ለመኾን የሚያስችል ቁመና በመገንባት ላይ ሲሆን ተወዳዳሪ ለመኾንና አላማውን ለማሳካት ቀልጣፋ፣ በሁሉም ተደራሽ ፣ ጊዜውን ያማከለ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ተብሏል።
በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን በባንክ ወለድ ምክንያት ከባንክ የራቁ ደንበኞችን ፍላጎት ለማርካት በወለድ ከሚሰጡት መደበኛ የባንክ አገልግሎት በኅብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት በማግኘቱ በከፍተኛ ኹኔታ በማስፋት እና በማደግ ላይ እንደሚግርኝ ባንኩ ገልጿል ።
ባንኩ በአሁኑ ጊዜ በሁሉም የመደበኛ የባንክ አገልግሎት በሚሰጡ ከ230 ቅርንጫፎች በላይ በመስኮት በኩል የተሟላ የመርሀባ ከወለድ ነፃ የባንክ አገለግሎት በመስጠት ላይ መገኘቱን ባንኩ አመላክቷል።
እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ ድረስ 30 ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችን ለመክፈት በዝግጅት ላይ መኾኑን ባንኩ ገልጿል።
https://www.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02HWzstL2BYijczMBUPFrpka5ovx8PBo9ATYzJhtbvoYqdmZKt5mJdbbmSdp5rGYF1l

በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ ከ47 ሺህ ሊትር በላይ ቤንዚን በቁጥጥር ስር ዋለ
መነሻውን #ጅቡቲ ያደረገ የነዳጅ ማመላለሻ ቦቲ ከተመደበለት መዳረሻ ውጪ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያለው 47 ሺህ ሊትር ቤንዚን በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
የአዲስ አበባ #ቃሊቲ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትል ተሽከርካሪው ስምሪት ከተሰጠው ቦታ ውጪ ወደ ደቡብ የሀገሪቱ ክፍል በመጓዝ ላይ እያለ #ሞጆ ከተማ አቅራቢያ በቁጥጥር ስር ውሏል።
ይህን ህገወጥ ድርጊት የፈጸመው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን የተያዘው ቤንዚንም በነዳጅ አቅራቢው ድርጅት ማደያ ተራግፏል፡፡
የኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡
ኢ.ፕ.ድ

በ #አዲስአበባ የኃይል መቆራረጥ በውሃ ምርት እና ስርጭት ላይ ችግር እንደፈጠረበት የከተማዋ ውኃና ፍሳሽ ባለስልጣን ገለጸ
ከመጋቢት 1 ቀን 2015ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ ስምንት ቀናት በባለሥልጣኑ የውሃ ጉድጓዶች እና የግፊት ጣቢያዎች ላይ በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ማጋጠሙን በባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ሠርካለም ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
ይህም በባለስልጣኑ የውሃ ምርት እና ስርጭት ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩን ነው ዳይሬክተሯ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡
በኃይል መቆራረጡ ምክንያት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣ 2፣3፣ 5፣ 12፣ 13 እና 14፤ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣2፣3፣4፣5፣6 እና 10 እንዲሁም በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2፣3፣4፣5፣6፣9፣10፣11፣12፣13 እና 14 የውሃ አቅርቦቱ ተቋርጧል ነው ያሉት፡፡
እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣9 እና 10፤ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 13፤ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 6 እና ከወረዳ 9 እስከ 11 የውሃ አቅርቦቱ መቋረጡን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ከወረዳ 1 እስከ 15፤ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣ 2፣ 11 እና 12፤ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 እና 5 በከፊል እና ወረዳ 9 በሙሉ እንዲሁም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እና 5 በኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ምክንያት የውሃ አገልግሎቱ መቋረጡን ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
https://www.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid02Zzv31WrbQaDLESbRttmrHHyK3uRjY9WyDcLcGCto85vcAnmfVN5ZM6oWwnT7oKUul

ዜና፡ #በሱማሌ ክልል የተከሰተው ድርቅ የበርካቶችን ህይወት ቀጥፏል፤ የወረዳው አመራር “ከአቅማቸው በላይ” መሆኑን ቢያምኑም የሟቾችን ብዛት ግን ውድቅ አድርጓል
በመድኃኔ እቁባሚካኤል እና በብሩክ አለሙ
በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ዞኖች አንዱ በሆነው በዳዋ ዞን፣ ከተለያዩ ወረዳዎች ተፈናቅለው በሞያሌ ወረዳ በሚገኙ ሁለት የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች የተጠለሉ ከ18 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ተፈናቃዮች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ። ተፈናቃዮቹ ያልተለመዱ ነገሮችን ለመመገብ እየተገደዱ ነው። የወረዳው ኃላፊዎች የችግሩን አሳሳቢነት በማመን “ከአቅማችን በላይ ሆኗል” ብለዋል።
አዲስ ስታንዳርድ በሞያሌ አቅራቢያ መለብ ቀበሌ በሚገኘው ሃርቦር ተፈናቃይ መጠለያ ባደረገው ጉብኝት በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያገኛቸው አንድ ተፈናቃይ አፋጣኝ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልፀው በማዕከሉ አካባቢ እሳቸው የሚያውቁት ከስምንት በላይ ሰዎች መሞታቸውን ተናግሯል።
ቤተሰቦቹን ለመርዳት የ12ኛ ክፍል ትምህርቱን አቋርጦ ከሞያሌ ከተማ ወደ ኤል ጎፋ መጠለያ ጣቢያ የገባው ወጣት አሊ እንደሚናገረው በስፍራው እርዳታ እየደረሰ አይደለም፡፡
https://amharic.addisstandard.com/ዜና፡-በሱማሌ-ክልል-የተከሰተው-ድርቅ-የበ/?fbclid=IwAR0mJCEkrfpl97RPj5SnUkxhhn6hPKNFnD4kimjQHnjJJGZCPexqu2x53qI

ዜና፡ በሱማሌ ክልል የተከሰተው ድርቅ የበርካቶችን ህይወት ቀጥፏል፤ የወረዳው አመራር “ከአቅማቸው በላይ” መሆኑን ቢያምኑም የሟቾችን ብዛት ግን ውድቅ አድርጓል
ሞያሌ ወረዳ ኤል ጎፋ መጠለያ በመድኃኔ እቁባሚካኤል @Medihane እና በብሩክ አለሙ @Birukalemu21 ሞያሌ፣ መጋቢት 8/ 2015 ዓ.ም፡- በሶማሌ ክልል በተከሰተው ድርቅ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ዞኖች አንዱ በሆነው በዳዋ ዞን፣ ከተለያዩ ወረዳዎች ተፈናቅለው በሞያሌ ወረዳ በሚገኙ ሁለት የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች የተጠለሉ ከ18 በላይ ሰዎች መሞታቸውን ተፈናቃዮች […]
በ #አዲስአበባ ከተማ ተቋርጦ የቆየው የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ከነገ ጀመሮ ይጀመራል
በመዲናዋ ተቋርጦ የቆየው የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ከነገ ጀመሮ በ138 የስምሪት መሥመሮች እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ አሰታወቀ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎትን አሰመልክቶ ዛሬ ለሀገር ውስጥ ሚዲያ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫው ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ቢሮ ሀላፊ አቶ ምትኩ አስማረ እንደተናገሩት፤ በከተማ ውስጥ እየሰሩ ያሉት ሁሉም የባጃጅ አሽከርካሪዎች የትራንስፖርት ቢሮው በሚያወጣቸው መመሪያ መሠረት በ123 ማህበራት ሥር አገልግሎት ይሠጣሉ።
በከተማዋ መደበኛ ትራንስፖርት በማይገኝበት አካባቢዎች ውስጥ ከ 0.9 እስከ 2.45 ኪሎ ሜትሪ ራዲየስ ብቻ በ5 ብር ታሪፍ አገልግሎት እንዲሰጡም ተወስኗል ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በስምንት ክፍለ ከተሞች ስር በሚገኙ 123 ማህበራት ስር የሚገኙ 9ሺህ 550 ባጃጅ አሽከርካሪዎች ጊዜያዊ ታፔላ ተሰጥቷቸዋል በማለትም አብራርተዋል።
አቶ ምትኩ እንደሚሉት ከ2001 ጀምሮ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት ታርጋቸውን በከተማዋ ያላወጡ ናቸው።
ቢሮው ባለፈው ሳምንት የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎቶቹን ያቋረጠው በተደጋጋሚ የሚከሰቱ አደጋዎችንና ወንጀሎችን ለመከላከል አሠራርና ሕግ በማስፈለጉ መሆኑን ሀላፊው ጨምረው ገልጸዋል።
ፎቶ: አዲስ ፎርቹን

ዜና፡ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳዳርን እንዲመሩ መረጠ
የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮምቴ ትላንት ማምሻውን የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳን የክልሉ ግዜያዊ አስተዳደር እንዲመሩ መምረጣቸውን ሶስት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።
አቶ ጌታቸው ረዳ ከ41 የማዕከላዊ ኮምቴ አባላት 18 የድምጽ ብልጫ አግኝተው መመረጣቸውን ምንጮቹ አክለው ገልጸዋል።
ነገር ግን የፌደራል መንግስት ይሁኝታ ይሰጠው እንደሆነ ገና የሚታይ ነው።
የተቋቋመው ግዜያዊ አስተዳደር ጥቅምት 23 ቀን 2013 ዓ/ም የተመረጠውን የትግራይ ክልላዊ መንግስትን የሚተካ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ጥቅምት 23 ቀን 2015ዓ/ም ከፌደራል መንግስት ጋር በተደረገው ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ዋና ከሆኑ ክፍሎች አንዱ ነው፡፡ የሰላም ስምምነቱ ሰነድ አንቀጽ 10 አካታች ግዜያዊ አስተዳደር መመስረት አንዳለበት ይደነግጋል።
https://amharic.addisstandard.com/%E1%8B%9C%E1%8A%93%E1%8D%A1-%E1%8B%A8%E1%88%85%E1%8B%88%E1%88%93%E1%89%B5-%E1%88%9B%E1%8A%A5%E1%8A%A8%E1%88%8B%E1%8B%8A-%E1%8A%AE%E1%88%9A%E1%89%B4-%E1%8A%A0%E1%89%B6-%E1%8C%8C%E1%89%B3%E1%89%B8/

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9/ 2015 ዓ.ም:- የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ማዕከላዊ ኮምቴ ትላንት ማምሻውን የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮምቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳን የክልሉ ግዜያዊ አስተዳደር እንዲመሩ መምረጣቸውን ሶስት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። አቶ ጌታቸው ረዳ ከ41 የማዕከላዊ ኮምቴ አባላት 18 […]
አገልግሎት ያቆሙ 18 የአዲስ አበባ ቀላል ባቡሮች ወደ አገልግሎት ሊመለሱ ነው
#ቻይና ባቀረበችው የመለዋወጫ ድጋፍ አገልግሎት መስጠት ያቆሙ 18 ባቡሮች ወደ አገልግሎት እንደሚመለሱ የ #አዲስአበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ድርጅት አስታወቀ፡፡
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሙሉ ቀን አሰፋ እንደገለጹት፤ ቻይና የአንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር የመለዋወጫ ድጋፍ በማድረጓ አገልግሎት መስጠት ያቆሙ 18 ባቡሮችን ሥራ ለማስጀመር እየተሠራ ይገኛል።
የአዲስ አበባ ቀላል ባቡሮች በመለዋወጫ እጥረት፣ በኃይል መቆራረጥና በተለያዩ ችግሮች ሥራ ሲያቆሙ መለዋወጫቸው ከውጭ ሃገራት ተገዝቶ የሚገባ በመሆኑ ለተወሰኑ ጊዜያት መዘግየት ተፈጥሮ እንደነበር አስታውሰዋል።
የኃይል መቆራረጥ ችግሮች እንዳይከሰቱ እንዲሁም በጥራት ጉድለት ምክንያት ለረጅም ጊዜ የቆዩ ኬብሎችን የመቀየር ሥራ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ጋር በመሆን እየተሠራ መሆኑን ኢንጂነር ሙሉቀን ጠቁመዋል፡፡
እንደ ኢንጂነር ሙሉቀን ገለጻ፤ ለባቡር የሚውለውን የኃይል ማቀባበያ ሲስተሞችን በየጊዜው መፈተሽ እንዲሁም የባቡር ሀዲዶችን ንቅለ ተከላ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በአሁኑ ወቅት በሚሠሩት ባቡሮች አማካኝነት በርካታ ሕዝብ በአዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎት እያገኘ ነው፡፡ አሁን ላይ በመዲናዋ ያሉት ባቡሮች በቀን 60ሺ እንዲሁም በዓመት 41 ሚሊዮን ሰዎችን ያጓጉዛሉ፡፡
ከፍተኛ የባቡር ትራንስፖርት ፍላጎት የሚስተዋልበት መስመር ከሃያት ተነስቶ ጦር ኃይሎች የሚደርሰው መስመር መሆኑን ገልጸው፤...
https://www.facebook.com/AddisstandardAmh/posts/pfbid023mDioYbqL6rSBQjzRAi3S9sCMeZZCkEjdF3qvCQkTF4YxCEPK482GJTyGMvi3Qd6l