Advanced Freshman – Telegram
Advanced Freshman
27.4K subscribers
650 photos
9 videos
59 files
206 links
🔔ይህ ቻናል freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::

📩Owner:- @Bekijum
Download Telegram
በቅርቡ ለተመረቃችሁ እንዲሁም 12ኛ ክፍል ለተፈተናችሁ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ማስታወቂያ አውጥቷል ።

✔️ Ethiopian Airlines Group Job Vacancy 31 July 2025

1.Position : SCHOOL OF MARKETING /SOM/ TRAINEE (ET SPONSORED)

How to Apply

https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies#collapsetwo_0

2.Position : TRAINEE CABIN CREW (ET SPONSORED)

How to Apply

https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies#collapsetwo_1

3.POSITION: TRAINEE PILOT (ET SPONSORED)

how to Apply
https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies#collapsetwo_2

Deadline : August 15- 2025

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
20👍3🙏2😱1
2018_Academic Calender_2025_26_FINAL.pdf
1.3 MB
☎️Addis Ababa University's official Academic Calendar for 2018 EC (2025/26)

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መስከረም 6, 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተማሪዎችን ለመቀበል እቅድ ይዟል።

የትምህርት ሚንስትር እና ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት አመቱን ወጥ ለማድረግ አያደረጉት ያለው አካሄድ ደስ የሚያሰኝ ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨረሲቲም ከመስከረም እስከ ሰኔ የሚል እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በዚህ እቅድ መሠረት ትምህርት መስከረም ወር ላይ ተጀምሮ ሰኔ ወር ላይ ይጠናቀቃል።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
22🙏5😍2👍1🔥1🙈1
#የሪሜዲያል_ውጤት_ቅሬታ

የ2017 ዓ.ም የሪሜዲያል ውጤት ላይ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለ ትምህርት ሚኒስቴር በፅሁፍ አቅርበዋል።

ቅሬታቸውም የሚከተሉት ናቸው

1, አብዛኛው ተማሪ ውጤቱ ከጠበቀው በጣም የራቀ መሆኑ ።
2, የተወሰኑ ጥያቄዎች ላይ የምርጫ (የጥያቄ) ስተቶች እንደነበሩ ።
3, ከ50 ጥያቄ ተፈትነን ከ100 መያዙ ።

ይህንን ትምህርት ሚኒስቴር ተገንዝቦልን ከዚህ በፊት ሲሰጥ እንደነበረው 70% በማዕከል እና 30% ደግሞ ከተቋማት ቢያዝልን በማለት የ 2017 ዓ.ም የሪሜዲያል ተማሪዎች ጠይቀዋል ።

ትምህርት ሚኒስቴር ቅሬታቸዉን ይቀበል ይሁንየምናይ ይሆናል ።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN🩵
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
106🙏49👍15💔12🙈8😱5🥰1
እውነተኛ ለውጥ⚠️

🔄አጎንብሰህ ስትለፋ ስትጥር ማንም ላያይህ ይችላል፤ እውነተኛ ለውጥ ጊዜ ይጠይቃል! ብርታት ይጠይቃል! ትዕግስት ይጠይቃል! ፅናት ይጠይቃል! ማንም ባላየህ ጊዜ ከጠነከርክ ሁሉም እያየህ ትሸለማለህ።

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN🩵
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🫡3619👍5👌2🥰1😎1
🛜12ኛ ክፍል ውጤት ሊለቀቅ 1 ወር ብቻ ቀረው!!

🛜የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጳጉሜ ወር ላይ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል ።

🛜ትምህርታቸውን በሰላም እና ፀጥታ ምክንያት ያልወሰዱ 4,966 ተፈታኞች ሲሆኑ ፈተናውን ከነሐሴ 26 - 28/2017 ዓ/ም ድረስ በወረቀት እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ደግሞ መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ/ም ተማሪዎችን መቀበል ይጀመራሉ🙌

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN🩵
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
12🔥6👍5
Forwarded from Remedial Class
በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ እነዚህ ነገሮች ብታረጉ ጥሩ ነው☺️

💡....ዲያሪ መፃፍ .....

🎓 የካንፓስ ቆይታ በጣም የሚገርሙ moment ያሉበት ነው ።በቃ 3 or 5 የደስታ ዘመናት ... የሚገራርም ሰው ታያላችሁ ....የሚወዛገብ ፤ የሚወሳሰብ የሚፈላሰፍ ፤ ምንም ዲጭ የማይልበት  ፤ ተንከሲሲስ ፤ በጣም ጅል ፤ አራዳ ነኝ ባይ ገገማ ....ኧረ ምኑ ቅጡ ....በህይወታችን አዳዲስ ነገሮች ይከሰታሉ ። ነገር ግን እንረሳቸዋለን ቶሎ ቶሎ አዳዲስ ነገር ስለሚፈጠሩ ይረሳል ። እናንተ ደግሞ ከፈለጋችሁ መፃፍ ብታረጉት ፤ ወደፊት ፊልም የመስራት ዕቅድ ካላችሁ ሚገራርሙ ገፀባህራያት ታገኛላቹሁ....ብቻ በላይፋቹ የማታገኙት ዕድል ስለሆነ በርትታቹሁ?...አዳዲስ ነገር ሲኖር በወረቀት (ዲያሪ)  "ወይም ስልካቹም ላይ ቢሆን አስፍሩት ..! ትዝታዎቻቹ ናቸው እንዳትረሱት...ሙድ የተያዘባችሁ ሙድ የያዛችሁትን ...የሚያስቅ ፤ የሚያሳዝን፤ የሚያናድድ ብቻ ....ቸክችኩ ቢያንስ ልጆቻችሁ ትሰጧቹሃላቹ እነሱም ካምፓስ ሊገቡ ሲሉ ....በየቀኑ ሳይሆን የሆነ ነገር ሲፈጠር ፃፉት ...አሁን ምንም ላይመስላቹሁ ይችላል ግን አልፎ ስታዩት  የምርም ትደሰታላቹሁ .....

💡አዲስ ቋንቋ መማር ......❗️

📚 ዶርም የምትሰባሰቡት ከየአቅጣጫው ነው ። ብዙ የማታውቁትን የሚያቁ ይሄም አለ...  ያምሃል...!  የሚያስብሉ ዕውቀቶች ታገኛላችሁ ። አንዱ ደሞ ቋንቋ ነው ። በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በርከት ያለ ተናጋሪ ያላቸው እንደ ኦሮሚኛ ፣ሲዳመኛ ፣ትግረኛ፣ ሱማሌኛ ቋንቋዎች የሚችሉ ልጆች ዶርም ካገኛችሁ በቀን 5 ቃልም ቢሆን ቀስ እያላችሁ ተማሩ .....የምር ይጠቅማቹሃል ። ቋንቋ መልመድ ጥሩ ነው ። ሁላቹም ጋር አዲስ ቋንቋ ከሌለ ደሞ ጓደኞቻችሁን የምታስታውሱበት አለ ኣ በቃ ....አዲስ የባህርማዶ አንድ ቋንቋ በጋራ ተለማመዱ ...ስፓንሽ ወይ ደሞ ፈረንች ...የተመቻችሁ በጋራ በቀን ትንሽ ነገር አጥኑ ። ጓደኞቻችሁን ስትለዮዎቸው ማስታወሻ ይሆናቹሃል ። ፈታ እያላችሁ ጠዋት ላይ 5 ቃላት ምናምን ሸምድዱ የምርም ጓደኝነታችሁ ለማጠንከር ያግዛቹሃል ።

💡መክሊታችሁን ማዳበር ......!

📚 የሰው ልጅ በተፈጥሮ የተለያዩ መክሊቶች ተሰጥቶታል ። ታዲያ እናንተም የተፈጥሮ ስጦታችሁን በክበብ በመሳተፍ ማሳደግ አለባቹሁ፣ በገገሙ ትምህርት ብቻ ካንሰር ነው  የሚሆንባቹሁ ...ትወና የምትሞክሩ....ግጥም መጣጥፍ የምትሞክሩ ....ስዕል ....ሃይማኖታዊ ነገሮች የምትሞክሩ  ብቻ ግቢ ላይ ብዙ ክበቦች አሉ ...የሴቶች ...የበጎአድራጎት ...የሌለ የለም ....እና ተሳተፉ ማህበር  አለ ...ዕቁብ፣ ዕድር ሁላ አለ (ቀልዴ ነው ...) ....በቃ በዓል ግዜ ደስ ይላል ። የምትወዱት ከኖርማል ትምህርታቹ ላይ የሚደበል ...ዘፈን ከሆነ ...ስፓርት ከሆነ ...ኳስ ከሆነ .....ብቻ የምትወዱትን አንድ ነገር አዳብሯቹሁ ። ተገኙ .....በገገሙ ትምሮ ብቻ አይነፋም ...!


💡 የተለያዮ EVENT እና TOUR  እንዳትቀሩ ...

በግቢ ቆይታ ፍራንክ ባይኖራቹ ራሱ ተበዳድራቹ  ሀገር መጎብኘት አሪፍ ነው ። በቃ ceremony  ሲኖር ....ይሂዱ ባክህ አትበሉ ዳግም የሚገኝ ነገር አይደለም ጦቢያን የምር የምታውቁበት ነው ። ትምህርተ ጋር ካልተጋጨ በየ ግዜው  በአስተባሪዎች ጉዞ ይኖራል ። ስለዚህ.... አትቅሩ ...የመፅሀፍ ምረቃዎች ....አነቃቂ ንግሮች ...ትያአታራዊ ዝግጅቶች ይደረጋሉ .....አትቅሩ ....ታዋቂ ሰዎች በየግቢ እየመጡ በተለይ ወጣቶች የህይወት ልምዶቻቸውን ስለሚያጋሩ .....የምታደንቋቸው ሰዎች በየትኛው መንገድ ነው የተሳካላቸው ....የሚለው የህይወት ጉዞን ትማሩበታላቹሁ ...የፈታ ኢቨንቶችም አሉ በቃ ....ፈተና ሲያልቅ ምናምን ከች የሚሉ እና ሳትንዘላዘሉ ተሳተፉ ....እነ ሮፍናን ደግሰው መቼስ አይቀርም .....እነ እሸቱ መለሰ እየቀለዱ መቅረት ይከብዳል ....


አዳዲስ ነገሮች ሞክሩ ...አትፍሩ

📚 አዳዲስ ነገሮች የማድረግ ዕድሉ ስለሚኖረን ምንአቧቱ በእናት ሆድ አይለመድ አትፍሩ ሞክሩ ....ታዲያ ሱስ ምናምን ሳይሆን አሪፍ የሚባሉ ነገሮች የፍቅር ህይወትም ቢሆን ትምህርትን በማይነካ መልኩ ቢደረግ አይከፋም ።ግን ብዙ አትንዘላዘሉ ...ቸክሉ ...በቃ የሚያስደስታችሁን አዲስ ነገር ሞክሩ .....ብዙዎች ካንፓስ ሃይማኖተኛ ያረጋቸዋል አንዳንዶች ደሞ ...."ፈላስፈ አንዳነዶች ....ዘልዛላም ይሆናል ....አንዳንዴ ሳታስቡት ሃርድ ውስጥ ትገቡ ይሆናል ....ታዲያ ያን ግዜ አትጨናነቁ ...Normal ነው ። በተረፈ መልካም ካንፓስ!

💬በመጨረሻም ካንፓስ ላይ ቆይታቹሁ ልትደሰቱበት የሚችሉበትን የማትፀፀቱበትን ነገር ብቻ ከውኑ ። በቃ ያማረ የግቢ ቆይታ እንዲሆንላቹ ምኞቴ ነው ። ጥሩ ጥሩ ነገሮች ሊያውም የማይደገሙ ሲያጋጥማቹሁ አትለፉ እርግጥ ዋናው ጉዳያቹሁ ትምህርት ቢሆንም ...መደሰቱ መሳተፉ አይከፋም ። አይዞን በቆንጆ ሁኔታ ይታለፋል ።

📱Telegram: @EthioUniversity3 ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
57👍9🥰8🔥4👏2🙈1
🎓ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ቀጣይ ግቢ ምትገቡ ሊኖራችሁ የሚገባ ምርጥ የዩንቨርስቲ ቻናል 🦋🦋

Join us
👇👇
https://news.1rj.ru/str/EthioUniversity3
https://news.1rj.ru/str/EthioUniversity3
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5👍2👏2
❗️አንዱን ምረጥ!

ህይወት በምርጫ የተሞላች ናት!
➡️ ወይ አጥንተህ ውጤታማ ትሆናለህ ወይ የሌሎች ስኬት ተመልካች ትሆናለህ፤
➡️ ወይ የሚያኮራህን ነገር ታደርጋለህ ወይ ግድየለሽ ሆነህ ትቀራለህ፤
➡️ ወይ ተኝተህ ትቀራለህ ወይ ተነስተህ ህልምህን ታሮጣለህ፤

🔵ምርጫህ የህይወትህን አቅጣጫ ይወስነዋል። አብዛኛው ሰው ደስ የማይል ህይወት የሚኖረው ምርጫው ደካማ ስለሆነ ነው።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN🩵
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍166🫡6❤‍🔥3💯3😎1
Forwarded from Remedial Class
😁 እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው🤔?

💠 አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ።

አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ።

አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው።

ስለዚህ እንዴት እናብብ🤔

💛 የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም🤷‍♂️

➡️ ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ

🛡 የሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው።

🛡 መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ።

🔄 የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው።

🔄 ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን።

     የጊዜ አጠቃቀም

🔵ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው።

      👋 አለመሰልቸት

🔎ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል።

   🎙ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን።

🌗ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ።

  🔰  Google

🔺 ለ ግቢ Google በጣም ወሳኝ ነገር ነው። Assignment መስራት ብትፈልጉ ፡ practical education በ video  ማየት ብትፈልጉ ፡ የተለያዩ መፅሀፎችን እና የመፅሀፍ solution ማውረድ ብትፈልጉ ፡ ምናልባት መምህሩ የሰጣችሁ ኖት ካልገባችሁ እና ሳይንሱን መረዳት ብትፈልጉ ፡ Google ለነዚህ ሁሉ በቂ መፍትሔ አለው። ስለዚህ Google ን የቅርብ ወዳጅ አድርጋችሁ ወጤት መስራት ትችላላችሁ ፡ ሳይንሱን መረዳት ትችላላችሁ። በዚሁ አጋጣሚ ለ Google ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ😘

          ☺️ The End

  📱Telegram: @EthioUniversity3 ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
25🙏22👍7
ቤተሰብ እንዴት ናችሁ 😊ክረምቱ እንዴት እያለፈ ነው 🤔እስቲ ያላችሁበትን ሁኔታ በሚገልፃችሁ reaction ግለፁ 🙈
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2😴66🥰42🤯35🙏32😭31💔16😇13😐86😱6😘4
#AksumUniversity

🛜በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሐግብር የምትማሩ #የሁለተኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች ወደ ተቋሙ የመግቢያ ቀናት ነሐሴ 06 እና 07/20217 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN🩵
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍107👏3🥰2
💻ምዝገባ በቅርቡ ይጠናቀቃል!!

💥የ UAT Exam የአንድ የ 12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ወሳኝ ምእራፍ ነው። ለምን ከተባለ የሚፈልገውን ዩኒቨርሲቲ ለማግኘት የግድ የ University Admission Test ተፈትኖ ማለፍ ይጠበቅበታል።

📣ይህን ፈተና ደግሞ AAU, ASTU, AASTU እንዲሁም SPHMC በመስጠት ይታወቃሉ።

📊ታዲያ ለዚህ ፈተና የት ልዘጋጅ ካላቹ ምርጫቹ UAT Preparation መሆን አለበት። ልምድ ባላቸው አስተማሪዎች በተደራጁ አጋዥ ፈተናዎች አዘጋጅቶ ብቁ ያደርጋቹሀል

ከ UAT Preparation ጋር የትም መግባት ይቻላል💥

መመዝገብ ምትችሉት ከታች ካሉት ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ ቀጣይ ዓመት ትምህርታችሁን መከታተል ምትፈልጉ ብቻ ናችሁ🔄

🔵AAU

🔵AASTU

🔵ASTU እና

🔵SPHMMC

🤳ለመመዝገብ ይህን⬇️
     @UATpreparationbot ይጠቀሙ ::

🎙ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት🔽
             @UATRegistration

JOIN US👇
@UATpreparation
@UATpreparation
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
19👍4🔥4🥰3
የSenior ተማሪዎች ምክር ጤና ዲፓርትመንት መግባት ለምትፈልጉ ተማሪዎች

ጤና የምትፈልጉ ማለትም Medicine, pharmacy, Anesthesia, Veterinary medicine, Dentist, Optometry እና አሁን ያልጠቀስኳቸውን የጤና Fieldoch መግባት የምትፈልጉ ልጆች 

በጤና ዠርፍ እየተማሩ ያሉ ልጆች እነርሱ ካሳለፋቸው ነገሮች አንፃር በይበልጥ በ 3 ነገሮች ትኩረት እንድታደርጉ ይመክሯቿል


1️⃣ውጤት መስቀል አለባቹ

#️⃣ውጤት በተለይ ደግሞ ጤና ለመግባት ፍላጎት ያላቹ ልጆች የ First semester ውጤታቹ አሪፍ ሊሆን ይገባል ብቻ ባጭሩ ጤናን ካለ ውጤት ማግኘት ይከብዳል አሁን ላይ ባለው ሁኔታ እንደውም ሁሉም ግቢዎች ከነርስ ጀምሮ እስከ Medicine ድረስ ከፍተኛ ውጤት ይጠይቃሉ ውጤቱም በትንሹ 3.2 በላይ ሊሆን ይችላል Medicine እና ሌሎች የሚፈለጉ ዲፖርትመንቶች ደግሞ የሚጠይቁት ውጤት 3.8 በላይ ሊሆን ይችላል ይሄ ግቢ ከገባቹ በኃላ የምትሰሩት ውጤት ብቻ ነው የ Entrance ውጤታቹ ብዙም ላይረዳቹ ይችላል ቢበዛ ከ 30% ቢይዙት ነው አንዳንድ ግቢዎች ደግሞ እንደውም ላይዙትም ይችላሉ ስለዚህ ጤናን የምትፈልጉ ልጆች ካሁኑ ውጤት መስራት እንዳለባቹ አውቃቹ ትኩረታቹን ትምህርታቹ ላይ ብቻ አድርጉ፤ ይሄን ስንል ደግሞ ተጨናነቁ ማለታችን እንዳልሆነ መቼም ትረዱናላቹ::

🥈በደንብ አስቡበት

#️⃣ለምን ጤና መግባት ፈለጋቹ ቤተሰብ ስላላቹ ነው ወይስ ጥሩ ገንዘብ አገኝበታለሁ ብላቹ ?? ይሄ ጉዳይ በደንብ ሊታሰብበት ይገባል ያው እንደምታውቁት ከሌሎቹ ፊልዶች አንፃር የጤና ፊልድ ጥረት የሚፈልጉና ብዙ ረዘም ያለ ጊዜ የሚውስዱ ስለሆኑ በግለትና በስሜት እንድትመርጧቸው አይመከርም ምክንያቱም በኃላ ላይ ፍላጎትና ጥረት ከሌላቹ ማማረራቹ አይቀርም ከባሰባቹ ደግሞ ትምህርቱን ጥሎ መውጣትም አለ::

🥉ማንንም አትስሙ
 
#️⃣አንዳንድ ለጤና ፍላጎት የሌላቸው እና ውጤት መስራት የማይችሉ ጀለሶቻቹ እነርሱ ጤና መግባት ስለማይችሉ ብቻ እናንተ የምትፈልጉትን ጤና የተለያዩ የወረዱ ሀሳቦችን እያነሱ ፍላጎታቹን ሊያጣጥሉባቹ ይችላል ስለዚህ be Wise 😎 አትስሟቸው።

ይቀጥላል ...

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍2713🥰4🙏4🔥2
🔄 የዶርም ህይወት በጥቂቱ እናጋራቹ

🛡ግቢ ውስጥ ከምንም በላይ ደስ የሚልና የማይረሱ ብዙ ክስተቶችን የምናሳልፈው በዶርም ህይወታችን ውስጥ ሲሆን በቆይታችንም እጅግ በጣም ብዙ አይነት ትምህርቶችን እንማራለን ።(የቀለም ትምህርት አላልኩም)

በብዙ ግቢዎች የሎከር በተወሰነ መልኩ አለ ፡ እናም በሎከር እጥረት ምክንያት አንድ ሎከር ለሁለትና ከዛም በላይ በመጠቀም ደስ የሚል መተሳሰብም አለ ፤ ባንፃሩ ደግሞ የዶርም ጭቅጭቅም በብዙ ነገራቶች ይፈጠራል ገና ከጅምሩ በሎከርና በአልጋ ምርጫ የሚጨቃጨቅ ተማሪ አይጠፋም ።

ሎከር ላይ ያለው ንትርክ ቀድሞ የያዘው ተማሪ ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ አልደበልም በማለት ሲሆን የአልጋው ግን ብዙ ጊዜ ከታች ያሉትን አልጋዎች ፍለጋ የሚፈጠር ሹኩቻ ነው ። ከላይ ያሉት አልጋዎች የመብራት ብርሃን💡 ስለሚያስቸግርና አንዳንድ ተማሪዎችም ስለማይፈልጉ or ስለማይመቻቸው ይመስለኛል (ሎከር ላይ ያለው ነገር በስምምነት ይፈታል ከቻላቹ ለመቅደም ሞክሩ ከተቀደማቹ ደግሞ አምባጓሮ ሳትፈጥሩ በpeace....)

🔅ዶርም ውስጥ በምትኖሩበት ጊዜ ከተለያዩ ተማሪዎች ጋር ስለምትኖሩ ፀባያችሁን በጣም መግራት ይጠበቅባቹሃል ። ለምሳሌ በአንድ ዶርም ውስጥ 8 ተማሪ ቢኖር ከሰባቱም ተማሪ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፀባይ ላይኖረን ይችላል ።
ያንተ ፀባይ የቱንም ያህል አሪፍ ቢሆን ምንም ደስተኛ የማይሆን የዶርም አባል ሊኖር ይችላል ። በዚህ ጊዜ ከኛ የሚጠበቀው እንደዛ አይነት ተማሪዎችን ለማስደሰት መፍጨርጨር አልያም በንዴት እነሱን ፊት መንሳት ሳይሆን ባለንበት ጥሩ ፀባይ ለመፅናት መሞከር ነው ።

👋ተመልከቱ እንግዲህ ከሰባት ተማሪ ጋር ሆኖ ሰባት አይነት ፀባይ መቻል እንዴት እንደሚከብድ ? ዋናው love❤️ ነው ብላቹህ የምታምኑ ከሆነ ግን ለሀያ ምናምን መኖርም አይከብዳችሁም ።

ዶርም ላይ

🌗በጣም ሀይማኖተኛ
🌗በጣም ነጭናጫ
🌗በጣም ሱሳም
🌗ከፊል ዘረኛ
🌗በጣም ዝርክርክ
🌗በጣም ተጠራጣሪ
🌗መቼም የማያወራ (ልጉም)
🌗ለሰከንድ ዝም ማለት የማይችል (BBC).....

👋እና ሌሎችንም የመሳሰሉትን አይነት ተማሪዎች ያጋጥሙሃል/ሻል የናንተም የሆነ type of ፀባይ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው ።

🎧እናም ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎችንም አይነት ፀባይ ያላቸውን ተማሪዎች እንደ አመጣጣቸው ማስተናገድ ይኖርባቹሃል ማለት ነው ።

🔵አንዳንዴ ደግሞ ደባሪ ነገሮችንም ልታስተናግድ ትችላላችሁ ። ለምሳሌ አንድ የዶርም አባል ቅዳሜን አክባሪ ከሆነ ጨብሶ በመምጣት ቁም ስቅላችሁን ያሳያቹሃል (ቅዳሜ የመጠጥ 🍻ቀን ናት ብለው ስለሚያስቡ ነው) እናም የጨበሰው ወይም የጨበሰችው ተማሪ ዶርም ውስጥ በብዙ አይነት መልኩ አዛ ያደርጓቹሃል ።

🤮ሻታ በርግደው የዶርሙን ንፅህና በማስዋብ (ምን ማድረግ ይሻላል🥹? ማልቀስም አይሻልም😭 ...ማለት ከዚህ ላይ ነው)

🍆በተኛችሁበት ብርድ ልብስ በመግፈፍ
ከአልጋ ለማስወረድ በመታገል

😡ሳትፈልጉ በስካር ቅላፄ ዘፈን መጋበዝ (ወይኔ በላቸው ...እስክትሉ)

❗️ሌሎችንም like this የመሳሰሉትን የስካር  አመሎችን ሊያሳዩ ስለሚችሉ በተቻላቹ አቅም ስካራቸው እስኪለቃቸው በትዕግስት በመቻል እንዴትም ጊዜዋን ማሳለፍ ይጠበቅባችዋል ።

👱‍♂👱‍♀ከላይ የተጠቀሱ ነገሮች ወንዶችን ብቻ የሚመለከቱ አይደለም ከወንዶች ባልተናነሰ መልኩ የሴቶች በሽታ ነው ።

📱JOIN:@campus_communityEt ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
31👍8🔥2🤗2🥰1
#AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን በተቋሙ ለመማር ፍላጎት ያላቸው አዲስ ተማሪዎች መረጃ የሚያገኙበት ሳምንት አዘጋጅቷል።

ራስገዝ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ የራሱን የቅበላ ፖሊሲ በማውጣት በ2017 ዓ.ም የመጀመሪያዎቹን ተማሪዎች ባዘጋጀው መስፈርትና ፈተና መቀበሉ ይታወቃል።

በተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲው በ2018 የትምህርት ዘመን ባሉት ሰባት ኮሌጆች እና የህግ ትምህርት ቤት ስር በሚገኙ 353 የድኅረ-ምረቃ እና 66 የቅድ-ምረቃ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር መዘጋጀቱን ገልጿል።

በዚህም ዕጩ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ዩኒቨርሲቲው ስለሚሰጣቸው የትምህርት ፕሮግራሞች እንዲሁም የተማሪዎች አገልግሎት መረጃ የሚያገኙበት ሳምንት ከነሐሴ 05-09/2017 ዓ.ም አዘጋጅቷል።

መረጃውን ለማግኘት በተገለፁት ቀናት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ ልደት አዳራሽ ይገኙ።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
14👍2🔥1
የ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መግባት የምታስቡ ልጆች Don't Miss this event. አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለጥያቄዎቻቹ መልስ ለመስጠት መረጃ እንድታገኙ ፕሮግራም አዘጋጅቷል።

ይህም ፕሮግራም ከ ነሀሴ አምስት እስከ ዘጠኝ ስለሚቆይ በነዚህ ቀናት ሄዳቹ መረጃ ማግኘት ትችላላቹ።

መረጃው ስለፈተናው ስለምትማሯቸው የትምህርት ዘርፎች ስለሚሆን ከወዲሁ ለፈተና እራሳቹን ማዘጋጀታቹ አትርሱ።

👍ይህ መረጃ የመስጠት ፕሮግራም የሚያመላክተው የፈተና ቀኑ እንደደረሰ ስለሆነ ለፈተና የቀራቹ ጊዜ ከአንድ ወር ያነሰ ነው።

🟢እኛንም በውስጥ መስመር መዝግቡን እባካችሁን ላላቹን በጥያቄያቹ መሰረት ሶስተኛ ዙር ምዝገባ ከዛሬ ማታ ጀምሮ ለጥቂት ቀናት ክፍት አድርገናል።

ይህን እድል ተጠቀሙበት በተደራጁ Materials በምስል፣ በ Note እንዲሁም ከዚህ በፊት የነበሩትን ጥያቄዎችን በመስራት ቀድመው ከተቀላቀሉን ልጆች ጋር ጥሩ ቆይታ እያደረግን እንገኛለን።

አስታውሱ ሁላቹም ተሳክቶላቹ ማየት ስለምንፈልግ ነው በርካሽ ዋጋ በ 250 ብር እያዘጋጀን ያለነው። ስለዚህ ይህን እድል አሁን ተጠቀሙበት

መመዝገብ ምትችሉት ከታች ካሉት ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ ቀጣይ ዓመት ትምህርታችሁን መከታተል ምትፈልጉ ብቻ ናችሁ🔄

🔵AAU

🔵AASTU

🔵ASTU እና

🔵SPHMMC

🤳ለመመዝገብ ይህን⬇️
     @UATpreparationbot ይጠቀሙ ::

🎙ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት🔽
             @UATRegistration

JOIN US👇
@UATpreparation
@UATpreparation
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
15😴3👍1🥰1
ግቢ ላይ በበሶ ቀልድ የለም 😁

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🤣112😁159💯8👌4😎3🙈2🎉1
Forwarded from Remedial Class
🎓 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ሂደት

💻የኢትዮጵያ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎች የምደባ ሂደት የሚካሄደው በትምህርት ሚኒስቴር ነው።

How it works

✈️Submission of Choices: After passing the university entrance exam, students fill out a placement form where they list their preferred universities and programs in order of preference.

✈️የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ካለፉ በኋላ ተማሪዎች የሚመርጧቸውን ዩኒቨርሲቲዎች እና ፕሮግራሞች እንደየፍላጎታቸው የሚዘረዝሩበትን የምደባ ቅጽ ይሞላሉ።

👤 Data Collection: The MoE collects all the placement forms and compiles the data. This includes the students' exam scores, their preferred universities.

👤MoE ሁሉንም የምደባ ቅጾችን ይሰበስባል እና መረጃውን ያጠናቅራል። ይህም የተማሪዎቹን የፈተና ውጤቶች፣ የሚወዷቸውን ዩኒቨርሲቲዎች ያካትታል።

Placement Algorithm: The MoE uses a placement algorithm to assign students to universities. This algorithm considers several factors:

MoE ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለመመደብ የምደባ algorithm ይጠቀማል። ይህ algorithm  በርካታ መረጃዎችን ግምት ውስጥ ያስገባል

Exam Scores(ያገኛችሁት ውጤት): Higher scores increase the likelihood of getting into more competitive programs and universities.

Preferences(የ ዩኒቨርስቲ ምርጫችሁ): The order of preferences listed by the students is taken into account.

Quota Systems(የ ዩኒቨርሲቲው የመቀበል አቅም): Some universities and programs may have quotas based on regional representation, gender, or other criteria.

Assignment: Based on the algorithm, students are assigned to universities and programs.

በመጨረሻም algorithmሙ ከላይ የተዘረዘሩትን በተቀበለው የእናንተ መረጃ መሠረት ይመድባችኋል።

ዋና ዓላማቸው በተቻለ መጠን  የ እናንተን ምርጫ ማስጠበቅ ነው።

ከተመቻችሁ ❤️👍

📱Telegram: @EthioUniversity3 ⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
28👍7🙏1
  ⚖️ Law department  


🔨 ትምህርቱ ሽምደዳ ሲሆን ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ከመጀመሪያ አመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ውጭ ያሉት የኮርሶች ፈተና open book ነው።

😄open book ማለት መምህሩ የሚፈቅድላችሁን ማንኛውም መፅሀፍ ይዛችሁ መግባት ትችላላችሁ።

🔨 ከዚህ በተጨማሪ የምትማሩዋቸውን ኮርሶች ማቴሪያል መፅሀፎች ከ መፅሀፍት ቤቱ ይሠጡዋችኃል።

🧑‍🎓ወደ ፈተናዎቹ ስንመለስ ከላይ እንዳልኳችሁ ከመጀመሪያ አመት ሁለተኛው ሴሚስተር ጀምሮ case  ይሆናል የምትፈተኑት። ይህም ማለት የሆነ የፍርድ ቤት ክርክር አይነት ይሰጣችሁና ውሳኔውን እናንተው የምትሰጡት ይሆናል።

😏እዚህ ጋር የማልደብቃችሁ ነገር English language ሞካሪ መሆን ይጠበቅባችኃል። ምክንያቱም ውሳኔያችሁን ከ civil code አንቀፅ ጠቅሳችሁ ማብራራት ስለሚጠበቅባችሁ።ስለዚህ law መግባት ምትፍልጉ ልጆች የኢንግሊዘኛዋን ነገር አደራ 🫡

⚖️Law department ለመግባት በመጀመሪያ ፍሬሽማን course 1st semester ትወስዱና then law and other social science ተብሎ 2nd semester ላይ ይከፈላል :: እዚህ ጋር ግን law መግባት ሚፈልጉ ተማሪዎች በCOC or በGPA ዉጤታችሁ ነዉ እንዲህ ሲባል አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በGPA እና በentrance result ሲሆን ሌሎቹ ደሞ በentrance result እና በCOC ይሆናል :: ለምሳሌ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ COC የለም, entrance result 30% እና GPA 70% ተይዞ ከ50 ማይበልጡ ተማሪዎችን law ያስተምራል::


🧑‍⚖️በመጨረሻም ከተመረቃችሁ በኋላ  ለ 6 ወር ያክል የደሞዛችሁን ግማሽ እየተከፈላችሁ ለ 6 ወር ያክል ስልጠና ትወስዳላችሁ። ለምሳሌ አማራ ክልል ከሆናችሁ ባህር ዳር ትሰለጥናላችሁ። በመጨረሻም ዳኛ😎
ከቆይታዎች በኋላ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚያወጣውን የጠበቆች ፈተና ተፈትናችሁ ጠበቃ መሆን ትችላላችሁ።
 
ይቀጥላል.....በቀጣይ ስለ ምን ይሰራ?

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
25👍23🥰6🙏3
💡 ካንፓስ tip 😅✌️
    
💳 ገንዘብ ና ካንፓስ ....!  


💡 በምድር የትኛውም ስፍራ ብትሆን ፔሳ (pisa) ገንዘብ ወሳኝ ጉዳይ ነው ግቢ ደሞ ትቸግራለች ። በአማካኝ 700 ብር በወር በቂ ነው ። ግን ቤተሰብ ከማስቸገር ሌላ መንገዶችን በት በት ማለት ያስፈልጋል ። እስቲ መንገዶቹን በ2 ከፍለን እንመልከት ....!

😭 አስጠሊ የሆኑ ገንዘብ መስሪያ መንገዶች ....!

🎓 አንድ አባባል አለ ..."የሰው ልጅ ሀብት ንብረቱን ከሸጠ ቸግሮታል : ህሊናውን ከሸጠ ግን በጠና ተቸግሯል ማለት ነው ይባላል😔 ። በግቢ ህሊናቸውን ሸጠው የሚማሩ አሉ ....ምክንያቱ አንዳንዱ ምክንያታዊም ነው ፤  አንዳንዱ ደሞ እዚ ግባ የሚባል አይደለም ። እስቲ አሳፋሪ የሆነ መንገዶችን እንመልከት ...!

  💡 ሹገር ዳዲ / ማሚ....!


🎓 ወንዶችም ሆኑ ሴቶች  ከአሮጊት እና ሼቦች ጋር በመውጣት ጨላ ያገኛሉ ። ይህ በጣም አስጠሊ ነገር ነው🤢 ...ያሳፍራልም ሁሉም ግን ዝም ብለው አይደለም የምር ቸግሯቸው እንዲ አይነት ነገር ውስጥ የሚገቡ አሉ ። በተቻላችሁ አቅም ለመረዳት ሞክሩ ጓደኞቻችሁን ....እዚ ነገር ውስጥ እንዳይገቡ በምትችሉት እርዷቸው ...ኤጀንቶች አሉ ሼባ እና አሮጊቶቹን የሚያገናኙ ገንዘብ አያጡም  .....ኮሚሽን ይቀበላሉ እንዲሁም ሹገሮች ጋር የሚወጡትም ገንዘብ በአዳር እስከ 3ሺ ድረስ ይበላሉ ። እንዲ አይነት ነገር ውስጥ እንዳትገቡ ጓደኞችም ቢኖራቹሁ ራቋቸው ።ገንዘብ ሲቸግሯቹ ጠብቀው በአንድ ቀን 5ሺ እፈሺ ...ምናምን ብለው ይገፋፋቹሃል ..የነሱን ኑሮ የመረጡትን በልተው ..ገዝተው....ስታዩ ትታለሉ ይሆናል ።ግን የውስጥ ሰላም የላቸውም በምንም ተኣምር እዚ ውስጥ ገብታችሁ አትንቦራጨቁ 😡

🤨 ሌብነት ....!


💻 ብዙ ግዜ ስልክ አንዳንዴ PC ፤ አሪፍ ልብሶች ፤ውድ ዕቃዎች ካላቹሁ በተለይ ጫማዎች ....በቃ የማይሰረቅ የለም ። ስርቆት ግቢ አሪፍ መላ መስሪያ ነው ። በጣም ብዙ ተማሪ ስላለ በዚሁ ስራ የሚተዳደሩ ..በተለይ ሱሰኞች /ወልፋሞች እጃቸው አያርፍም .....ከዶርም ጓደኞቻቸውም ጭምር  ይሰርቃሉ ...ብታሳውቁም ከተሰረቃችሁ ወዲህ ምንም የሚመጣ ነገር....አይያዙም ... በተቻላችሁ አቅም ሱስ ውስጥ እንዳትገቡ ...በቃ ሱስ ያዛቹሁ ማለት ...ገንዘብ ስትሉ ወልፉ ያስገድዳቹሃል ቀስቴ ግድ ነው ። ከያዛቹሁ ደግሞ ትጫራላችሁ ....ገንዘብ ባታጡም ሌሎችን አሰቃይቶ ገንዘብ መግኘት ፥ ህሊናን መሸጥ ከባድ ነገር ነው ።  አትዝረፉ ...ከተቸገራቹ ዶርም ጓደኞች ለምኑ ....እንጂ No ሌብነት ውዶቼ🫡...!

💡 ግርግር .....!


🎓 ካንፓስ ለማበጣበጥ የሚገቡ ተከፍሏቸው አሉ ። በቃ ሽብር መንዛት ነው ስራቸው ...ከነዚ ይሰውሯቹሁ ....ስለሚከፈላቸው አምርረው እንደ WORk ነው የሚሰሩት .....ረጭ ሲል አይወዱም ...ጫጫታ መፍጠር ...ማናቆር ነው ስራቸው ። ዘር ነገር እያነሱ ...አናታችሁን ነው የሚበጠብጡላቹሁ ....እናንተ ከበሶ ያለፈ ነገር መበጥበጥ ውስጥ እንዳትገቡ ...ዋ 🤨

💡 ...ቱጀር መጥበስ .....!


🎓 የልጥጥ ልጆች LIFE ን  እንየው ብለው ይከሰታሉ.....2nd year ባይመለሱም ....ጨላ እነሱም ማግኘት ይቻላል አለ ኣ በፍቅር ሙድ በጓደኛ ምናምን ...በትበት ብሎ ...በተገኘው ቀዳዳ ሾልኮ መመረቅ ነው ። ኖ ወደ  ኃላ ..!

🤌 መልካም የሚባሉ  ፍራንካ መቀፈያ መንገዶች .....!

💡  ንግድ .....!..


🎓 በየግዜው EVENT ስለሚዘጋጅ የተለያዩ ነገሮች በመሸጥ ኮኔክሽ ካለህ ዘና ብለህ ነው የምትማረው ። ቲሸርቶችን ፤ ቲኬቶችን (የኮንሰርት ምናምን .. )... ለመጀመር ትንሽ ገንዘብ ቢጠይቅም (2ሺ አከባቢ) ከጀመራችሁት አሪፍ ገንዘብ ይዛችሁ ትወጣላችሁ ..... በቃ ዝግጅት በተካሄደ ቁጥር እናንተ አሰብ አሰብ እያረጋቹሁ....መወረክ ነው ። GC ሲሆን አበባ ምናምን ......ለበኣላት ፓስት ካርድ .....ከዘቡሌዎቹ ጋር ከተስማማቹ ደግሞ ነገሮች በጎን እያስገባቹሁ .... መሸጥ ትችላላቹሁ ። ፓፍ ምናምን የሚሸጡ .....አሉ .....ያው ከተያዛቹሁ ግን .....(ለካ ከዘቡሌው ጋር ፒስ ናችሁ😏 ...) .....!

💡 ቸካይ ነሽ /ህ 


📚 ትምሮ ላይ ቀለሜ ከሆንክ አሳይመንት ምናምን ትሰራለህ በጨላ .....ካንፓስ አምርረው የሚማሩ 20% አይበልጡም ....አዝጎቹ መጨናነቅ ስለማይፈልጉ ጭንቄ ካላቹሁ ...ወረክ ወረክ አርጋቹሁ ....ጨላ በጨላ ነው ።በተለይ ደሞ GC መመረቂያ ፁሁፍ ላይ ....ይሸቀላል ....! ሰጋጭ ቸካይ ከሆንክ ለመኮረጅ ጀለሶችም ይንከባከቡሃል ....አንቺ ፀባይ አሳምሪ እንጂ አያሳስብም ገንዘቡ እህት አለም ።

💡 ዝግጅቶችን ማዘጋጀት .....!


📚የተለያዮ TOUR የሚያዘጋጁ ፓሪ ምናምን ...ልጆች አሉ እና ይሸቃቅላሉ ። ወደ ገዳም ....ንግስ ...ወይ ደሞ ቅርብ የሚጎበኝ ነገር ካለ እዛ በፓኬጅ ይወስዳሉ RIsk በመውሰድ ገንዘብ ይሰራሉ ...እነዚ አይነት ፕሮግራሞች በተቻለ መጠን  በትንሽ ገንዘብ ስለሆነ ...ተማሪዎች ይሳተፋሉ .....

💡 ስልጣንሼ🍸 .......!


🎓 የተማሪዎች ህብረት ወይ ደግሞ ...ሚኒ ሚዲያ ተቆጣጠሪ በመሆን ጥቅማጥቅም ማግኘት ይቻላል ። ስብሰባ ምናምን ሲኖር አበል ....ችግሮች ቢኖሩትም ጥቅሞችም አለው ...ለኢንፎ ሩቅ አትሆኑም...... መረጃዎች ቶሎ ይደርሰናል አንዳንዴም ኪሳችሁም ብዙም አይደርቅም ...ሸጎጥ ይደረጋል ።

💡 Normal Work.....


📚 ማስጠናት ሊሆን ይችላል ፥ ሊስትሮ ሊሆን ይችላል .....ወይ ስዕል ምናም የሚችሉ ልጆች ...ሙያ ያላቸው ልጆች ግቢ ውስጥ ወይም ውጪ አንዳንዴ ይወርካሉ ....ያው ይሄ ከባሰብን ነው ። እንጂ እዛ የሚያደስ ነገር የለም ....!

💡 businesses ideas......!


💡 ትንታግ ከሆናችሁ የራሳችሁ ቢዝነስ ሀሳብ ፈጥራቹሁ ....መስራት ትችላላችሁ ....አንድ አይነት ፍላጎት ያለው ፤ በተመሳሳይ የዕድሜ ደረጃ፤  በሙሉ የተማረ ብዙ ሺ ግለሰብ ነው ካንፓስ ሚጠብቃቹሁ  ። ታዲያ እናንተም ....ፍላጎቱን ተረደድታቹሁ ..ችግሩን አይታቹሁ ሸቀጥ መስጠት ከቻላችሁ ባለሃብት መሆን ትችላላችሁ ...ግቢ ስትደርሱ  የሆነ ችግር አለ እሱን solve የሚያረግ አሪፍ ነገር ካመጣችሁ ሚለየነር ነው የምትሆኑት ።

💡 አንድ  ምሳሌ እንይ ....ድሬ ዮኒቨርስቲ አንዱ ምን አረገ ...ሽንት ቤት በጣም ነው የሚያስቸግረው ስለዚህ ......አይመችም ...ልጁ አነስተኛ ሽንት ቤት ሰርቶ በአንድ ብር ያስጠቅም ነበር ከዮኒቨርስቲው ጋ በመተባበር በር አከባባቢ   ...ከዛ ታገደ ነገሩ 2ተኛ እና 1ኛ ዜጋ ይፈጥራል በሚል ......ግቢ የሆነ ነገር ....አሰብ አሰብ አርጉና  ፍጠሩ ........ቢዝነስ ተማሪ ከሆናቹ አይከብዳቹሁም...እኔም የቻልኩት በዚ እፅፋለሁ ..!

🎓 በመጨረሻም  ካንፓስ ላይ ገንዘብ ቆይታችሁን ያቀለዋል ....ግን ለእሱ ብላቹሁ አይሆን ሙድ ውስጥ እንዳትገቡ .... መላ አይጠረርባቹ🙏 ...ዘመደ ብዙ ያርግላቹሁ🙏 ...አትቸገሩ🦋 ....ውብ የካንፓስ ቆይታ ለሁላችሁም ተመኘው🥰 ...!

⚠️ማሳሰቢያ 🤨
የምትሄዱት ለትምህርት ነው ፤ ሚሊየር እሆናለሁ ብላችሁ ትምሮውን እንዳትረሱት  ...ዋ...!🙏


ከተመቻቹ 👍

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
87👍23🙏8🔥5🥰3😇1
Forwarded from Ravini Digital Solutions
#MoE

🎓ትምህርት ሚኒስቴር ተቀራራቢ ይዘት ባላቸው የከፍተኛ ትምህርት ፕሮግራሞች ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ክለሳ በማድረግ ወደ ትግበራ ገብቷል።

✈️ሚኒስቴሩ ከሰኔ 2014 ዓ.ም እስከ ግንቦት 2017 ዓ.ም ድረስ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ተቀራራቢ ይዘት እና ስያሜ የነበራቸው ፕሮግራሞችን በመለየት ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ኢንዱስትሪዎች ከተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር በመሆን በፕሮግራሞቹ ስያሜ እና ስርዓተ ትምህርት ላይ ማስተካከያ አድርጓል፡፡

🔄ተቀራራቢ ይዘት ያላቸው ፕሮግራሞችን በማጠፍ/በማዋሃድ አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜዎች መሰጠቱን በአካዳሚክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ያሳያል።

🔵በዚህም 147 ፕሮግራሞችን ወደ 54 በመጠቅለል አዳዲስ የፕሮግራሞች ስያሜ መሠጠቱ ተገልጿል። በተወሰኑ ፕሮግራሞች ላይ ማስተካከያ የተደረጉ ሲሆን የታጠፉ ፕሮግራሞች እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል።

📎ይህም በሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተግባራዊ እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

(የፕሮግራሞቹ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።)
©tikvahuniversity

✈️ለተጨማሪ መረጃ ይቀላቀሉን 👇
https://news.1rj.ru/str/+GHYjUHHHcdQ5MzA0
https://news.1rj.ru/str/+GHYjUHHHcdQ5MzA0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
14👍5🥰1