Advanced Freshman
ትናንት ህዳር 11/2018 ዓ.ም ጠዋት ላይ በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ተማሪዎች "የምግብ እጥረት አለ ይስተካካከል" ብለው ሰላማዊ ሰልፍ በወጡበት የግቢው ዘበኞች ተኩስ ከፍተው የ2 ተማሪዎች ህይወት እንዳለፈ እና ሌሎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የደረሰን መረጃ ያመላክታል። ምንጭ :- (አዩዘሀበሻ) 🌟 JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN✅
" በምግብ በአቅርቦቱ ላነሷቸው ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ ሊሰጥ፣ እነርሱም ጥያቄዎቻቸውን በነጻነት አንስተው መግባባት ተደርሷል " - ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አለ ?
ለጉዳዩ ምላሽ እንዲሰጡና ችግሩን ለመቅረፍ ምን እየተሰራ እንደሆነ የጠየቃቸው የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ እና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ ተበጀ፣ ተማሪዎች ቅሬታ የማቅረብ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን አምነዋል።
" ጥያቄዎች አንስተው ነበር ችግሩን ለመፍታት በተፈጠረ መድረክ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ተማሪዎችም በተገኙበት ተወያይተው መግባባት ላይ ተደርሷል " ሲሉ ተናግረዋል።
ተማሪዎቹ፣ " የምግብ ችግር አለብን " በማለት ጭምር ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፤ መግባባት ላይ የተደረሰው በምን መልኩ ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበው ጥያቄ፣ " ከዚህ ጋር በተገናኘ በአቅርቦቱ ላነሷቸው ጥያቄዎች ተገቢው ምላሽ እንደሚሰጥ፣ እነርሱም ጥያቄዎቻቸውን በነጻነት አንስተው ይሄ መግባባት ተደርሷል " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም፣ በደፈናው መግባባት ላይ ተደርሷል ሳይሆን ላነሱት ቅሬታ ምን ማስተካከያ ልታደርጉ ነው መግባባት ላይ የተደረሰው ? ሲል በድጋሚ የጠየቃቸው አቶ አምሳሉ፣ መስተካከል ያለባቸው የጠየቋቸው የቀን ሽፍት ማድረግና መሰል ጉዳዮች እንዳሉ ገልጸዋል።
" ለምሳሌ 'ረቡዕ የሆነው የሩዝ ምግብ ቅዳሜ ይሁንልን' " እንዳሉ ተናግረው፣ " ከዚህ በፊት ይቅር ብለው የነበረውን ፓስታ ይዘጋጅልን ብለዋል፤ በመጠንም ያነሱት ጥያቄ አለ " ሲሉ ያከሉ ሲሆን፣ የተግባቡት ይህን ሊያስተካክሉ መሆኑን ገልጸዋል።
" የሞቱና የቆሰሉ ተማሪዎች አሉ " ስለመባሉ ስንጠይቃቸው ደግሞ፣ " መረጃው የለኝም " ያሉ ሲሆን፣ ስለጉዳዩ እያብራሩልን አይደል እንዴ እንዴት መረጃው የለኝም ይላሉ ? ስንላቸው፣ " ያለኝን መረጃ ነው የምናገረው፤ ስለዛኛው (ግድያው) መረጃ የለኝም " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ ለጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጥ የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ቢጠይቅም ጉዳይ እንደማይመለከተው በመግለጽ፣ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል። የተማሪዎች ኀብረት መረጃው በፕሬዚዳንት ደረጃ ይሰጥ ተብሏል ቢልም፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ግን ስልክ ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆኑም።
" በጥይት ቆሰሉና ተገደሉ " ስለተባሉ ተማሪዎች መረጃው ደርሶት እንደሆን የጠየቅነው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ኀብረት ግን፣ " የሞተም ሆነ የቆሰለ የት፣ በማን? " የሚለውን መረጃ እያጠናቀረ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
ውይይት በተደረገበት ወቅት አንድ ተማሪ ምን አለ?
" ዩኒቨርሲቲው ጊዜ ስጡኝ ብሎን ነበር። ግን አመት ከርመን ስንመጣ ያቆየን ረሃብ ነው። ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መስከረም 5 ነው የገቡት። እኛ የሁለተኛ አመት ተማሪዎች ጥቅምት 17 ነው የገባነው። ግን መስከረም 5 ከገባ ተማሪ ጋር ነገ የመውጫ ፈተና የምንፈተነው። ለምን ?
እናንተ ናችሁ ፓለቲካን የምንትሰብኩብን እንጅ እኛ ለመማር ነው የመጣነው። እኛ ጥያቄያችን ርቦናል የሚል ነው። ከተለያዬ ቦታ ነው የመጣነው፤ ስልካችንን እየተዘረፍን፤ በሬ እያሸጥን ነው ለመማር የመጣነው።
በዓለማችን ትልቁ መሳሪያ ትምህርት ነው። ስለዚህ አስተምሩን፤ መግቡን ኢትዮጵያን እናሳድጋት ነው ያልነው። ሌላ የፓለቲካ አጀንዳ የለንም። ሞትማ በነበርንበት ቦታ ሞልቷል። ምግባችንን አስተካክሉልን፣ እንማር " ብሏል።
Via:- TIKVAH
🌟 JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN✅

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤40😢35👍16👏5💔2
Forwarded from Remedial Class
1. ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ:- ህዳር 2 እና 3
2. ቦረና ዩኒቨርሲቲ:- ህዳር 8 እና 9
3. ቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ:- ህዳር 4 - 7
4. ጅግጅጋ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 5-8
5. ባህርዳር ዩንቨርስቲ:- ህዳር 11 እና 12
6. ጋምቤላ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 15 እና 16
7. ራያ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 22 እና 23
8. ጅንካ ዩንቨርስቲ:- ተራዝሟል
9. ደባርቅ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
10.ኦዳ ቡልቱም ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
11.ድሬ ደዋ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 20 እና 21
12.አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
13. መቱ ዩንቨርስቲ :- ታህሳስ 1 እና 2
14. መቅደላ አምባ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
15. አምቦ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 29 እና 30
16. ቡሌ ሆራ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 29 እና 30
17. ወሎ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
18. አሶሳ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 2 እና 3
19.ደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ :- ህዳር 25 እና 26
20. ወልድያ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 6 እና 7
21. ሰመራ ዩንቨርስቲ:- ህዳር 25 እና 26
22. ጎንደር ዩንቨርስቲ:- ህዳር 29 እና 30
23. ወራቤ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 2 እና 3
24. ደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲ:- ታህሳስ 2 እና 3
.
JOIN: @Remedial2018batch
JOIN: @Remedial2018batch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤39🙏7👍3🆒2
#BahirDarUniversity
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ የኒቨርሲቲነት ለመሸጋገር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡
ራስ ገዝ እንዲሆኑ በመንግሥት ከተለዩ አስር ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
በዚህም ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን የሚያስችለውን የተሟላ ዝግጅት ማድረጉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው የሰው ኃይል ስምሪት፣ ሃብት የማመንጨት አቅም፣ አስተዳደራዊ መዋቅር እና ሌሎች ተግባራትን በማካተት የደረሰበትን ውጤት ለትምህርት ሚኒስቴር መላኩን ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በሚሰጠው ፈቃድ መሰረት ዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት አሰራሩን ተቀብሎ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል።

❤34👍7🆒1
ሰላም ቤተሰብ 😊የተለያዩ ሚጠቅሟችሁን material እያዘጋጀን ስለሆነ ይበልጥ ብዛታችሁን ለማወቅ ከታች vote አድርጉ
Anonymous Poll
64%
Freshman ተማሪ ነኝ
13%
Remedial ተማሪ ነኝ
19%
>2nd year ተማሪ ነኝ
4%
Highschool ተማሪ ነኝ
❤40👍11
Forwarded from Campus ተማሪ
JU 2017 MidExam Collections.pdf
2.2 MB
ቻናላችንን ለሌሎች share ያድርጉ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤12🙏7👍5
#MoE
➡️ አምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ራስገዝ ለመሆን ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
🔺 ባሕር ዳር፣ ጅማ፣ ጎንደር፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ራስገዝ ለመሆን ጥያቄ ያቀረቡ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።
🔺 ዩኒቨርሲቲዎች በአስተዳደር፣ በፋይናንስ፣ በሰው ሃብት፣ በአካዳሚክ ጉዳዮች እና በምርምር ዘርፍ ባላቸው ቁመና እና በሚያስመዘግቡት ውጤት መሰረት ወደ ራስገዝነት እንደሚሸጋገሩ ጠቁመዋል፡፡
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከሁለት ዓመት በፊት ቀድሞ ራስ ገዝ መሆኑ ይታወሳል ።
➡️ በመሆኑም እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ከሆኑ በኋላ ከ Entrance በተጨማሪ ሌላ ፈተና ተፈትነው ተማሪዎችን የሚቀበሉ ይሆናል!
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN✅
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከሁለት ዓመት በፊት ቀድሞ ራስ ገዝ መሆኑ ይታወሳል ።
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤17👍10🔥1
ይህንን ያውቃሉ?
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ተማሪዎች በቀን የተማሩትን ነገር ሲተኙ አንጎላቸው መረጃውን ያጠናክራል። ስለዚህ ከረዥም ትምህርት በኋላ ትንሽ እንቅልፍ መውሰድ ከሌላ ሰዓት ትምህርት የበለጠ ውጤታማ መሆን ያስችላል።
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN✅
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ተማሪዎች በቀን የተማሩትን ነገር ሲተኙ አንጎላቸው መረጃውን ያጠናክራል። ስለዚህ ከረዥም ትምህርት በኋላ ትንሽ እንቅልፍ መውሰድ ከሌላ ሰዓት ትምህርት የበለጠ ውጤታማ መሆን ያስችላል።
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😇29❤18👍10🙏8😎6🫡2🔥1🕊1
Forwarded from Campus ተማሪ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤7🙏5👍2
University grading system
#️⃣ A+ --------> ብርቄ ነሽ
Range ፡ ከ90 በላይ
Multiplied by: 4
#️⃣ A -------> አስቤሽ አላውቅም
Range : 85-90
Multiplied by:4
#️⃣ A- ----->አለም 9 ናት
Range : 80-85
Multiplied by:3.75
#️⃣ B+ ------>ጌጤ ነሽ
Range: 75-80
Multiplied by:3.5
#️⃣ B -------> ነይልኝ በሞቴ
Range : 70-75
Multiplied by:3
#️⃣ B- ----->አንቺን ከሚከፋሽ
Range :65-70
Multiplied by:2.75
#️⃣ C+ -----> የኔ ማር
Range : 60-65
Multiplied by:2.5
#️⃣ C --------> አንለያይም
Range : 50-60
Multiplied by:2
#️⃣ C- -------> በቴስታ ማለት ነበር
Range:45-50
Multiplied by:1.75
#️⃣ D -------> የኔው ጉድ
Range: 40-45
Multiplied by:1
#️⃣ FX -------> አንቺ ባትኖሪ እኮ
Range : 30-40
Multiplied by:tempo 0 ኮርሱን በድጋሚ የመፈተን እድል ይፈጥራል፤ በድጋሚው ፈተና ግን ከ40 በላይ ካላመጡ F ይሆናል
#️⃣ F --------> ጥሎብኝ
Range ከ30 በታች
Multiplied by: 0 ኮርሱን እንደገና መማር ያስገድዳል በቀጣዩ ዓመት ማለት ነው።
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN✅
Range ፡ ከ90 በላይ
Multiplied by: 4
Range : 85-90
Multiplied by:4
Range : 80-85
Multiplied by:3.75
Range: 75-80
Multiplied by:3.5
Range : 70-75
Multiplied by:3
Range :65-70
Multiplied by:2.75
Range : 60-65
Multiplied by:2.5
Range : 50-60
Multiplied by:2
Range:45-50
Multiplied by:1.75
Range: 40-45
Multiplied by:1
Range : 30-40
Multiplied by:tempo 0 ኮርሱን በድጋሚ የመፈተን እድል ይፈጥራል፤ በድጋሚው ፈተና ግን ከ40 በላይ ካላመጡ F ይሆናል
Range ከ30 በታች
Multiplied by: 0 ኮርሱን እንደገና መማር ያስገድዳል በቀጣዩ ዓመት ማለት ነው።
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤56👍29😘7🫡4🙏3🤗3👌2🤝2🕊1
🧑🔬ስለ ህክምና ማወቅ ያለባችሁ 10 ነገሮች ❗️
«
🟢 ብዙውን ጊዜ ስለ ሙያው ሳያውቅ መድሃኒትን ለመቀላቀል ውሳኔዎች እየተደረጉ ናቸው:: ከዚህ በታች ወደ ህክምና ከመቀላቀል በፊት ባገኛቸው የምመኘውን ከልምዶቼ እውነቶችን ዘርዝሬአለሁ። ይህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን እንዲሁም የህክምና ትምህርትን በተገቢው እና በመረጃ በተደገፈ የቅጥር ሂደት ለማሻሻል የበኩሉን እንደሚረዳ ተስፋ አደርጋለሁ።
➖ ➖ ➖ ➖ ➖ ➖ ➖ ➖
1⃣ . የሕክምና ሙያ የታሰበው ጽንፍ መቋቋም ለሚችሉ ግለሰቦች ብቻ ነው:: መድሃኒት ለስላሳ መንገድ አይደለም::ብዙ ውጣ ውረዶች አሉት።
🔻 🔹 🔹
2⃣ . ይህ ሙያ እንደ ቤተሰብ ባህል መወሰድ የለበትም:: አያቴ ሐኪም ነው፣ አባቴ ሐኪም ነው፣ እናም ዶክተር መሆን አለብኝ። ይሄ አይሰራም!!!
🔺 🔺 🔺
3⃣ . የሕክምና ሙያ የሚጠብቀውን ዋጋ ለሚገነዘቡ ሰዎች ነው:: በአንድ ቀን ውስጥ ምንም ነገር አይከሰትም:: ወይም በአንድ ወር ውስጥ ወይም በዓመት ውስጥ እንኳን ለመመስረት በአጠቃላይ አመታትን ይወስዳል። ስሜት የሚጫወተው እዚያ ነው። ለምታደርጉት ነገር በጣም የምትጓጉ ከሆነ, መጠበቅ የጊዜ ጉዳይ ነው::
🔻 🔹 🔹
4⃣ . የሕክምና ሙያው ለማይነጻጸር ነው:: ጓደኛዬ ውጭ ሀገር እየሰራ ነው, መሄድ አለብኝ ወይም የአክስቴ ሴት ልጅ እያገባች ነው... አሁንም ኮሌጅ ነኝ። አንድ ሰው ራሱን ከሌላ ሰው ጋር ባነጻጸረበት ቅጽበት፣ ሁሉንም ዓይነት የመንፈስ ጭንቀት ውስጥ የሚያስገባ ባዶነት ይፈጥራል።
🔹 🔻 🔸
5⃣ . የሕክምና ሙያ የመንፈስ ጭንቀትን ለመዋጋት በቂ ጥንካሬ ላላቸው ነው:: ትምህርቱ ከባድ እና ብዙ ፈተናዎች አሉት።
🔺 🔺 🔺
6⃣ . አንድ ሰው ለጥናት ጊዜ እና አስደሳች ጊዜ ግልጽ የሆኑ ድንበሮችን ማዘጋጀት ያስፈልገዋል:: በህክምና ውስጥ ለፈተናዎች ብቻ አይሰለጥኑም, በአብዛኛው በታመሙ እና በሞት መካከል ለሚቆሙበት ቀን ነው::
🔻 🔹 🔹
7⃣ . በሕክምና ትምህርት ትምህርቱ አያልቅም:: የመጀመሪያ ዲግሪ የሚፈጀው 'ሰባት አመት ብቻ' ነው፣ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያውቋቸው ሁሉ የመጀመሪያ ዲግሪዎን እየሰሩ ነው የሚመረቁት። ከዚያም በመረጡት መስክ ላይ በመመስረት ከ3-5 ዓመታት ልዩ ሙያ ይመጣል:: ከዚያ ከ2-3 ዓመታት ንዑስ-ስፔሻላይዜሽን ይከተላል....
🔹 🔻 🔸
8⃣ . ማህበራዊ ህይወት ይከፈላል:: ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጡ ጓደኞችህ እና ዘመዶችህ ከሜድ ተማሪነትህ በኋላ በትዕቢት ምክንያት የምትርቃቸው አድርገው ያስባሉ። ትክክለኛ ምክንያቶችዎን የሚረዳ ሌላ የህክምና ተማሪ ብቻ ነው። ተማሪው ሁልጊዜ የሚያጠናው ነገር አለ::
🔺 🔺 🔺
9⃣ . የሥርዓተ-ሥርዓት ተዋረድ፣ በመሠረቱ የሕክምና መሰላልን መነሳት ማለት ከሥሩ መጀመርን ይጨምራል፣ ከእርስዎ ለሚበልጡ ሁሉ መልስ ይስጡ። በመጨረሻ ደረጃውን እስክትወጣ ድረስ ይህን ታደርጋለህ.
🔻 🔹 🔹
1⃣ 0️⃣ . ህይወታችሁን በሙሉ ታቆማላችሁ:: ህይወታችሁን ለመተው ተዘጋጁ፣ ምክንያቱም የጊዜ ቁርጠኝነት ከምታስቡት በላይ ነው። ቅዳሜና እሁድ እና ምሽቶችዎን ደህና ሁን ይበሉ። ትዳር፣ ልጆች፣ ቤት፣ መኪና... እነዚህ ነገሮች ዘግይተው ይመጣሉ። ለዚያ ምቾት ሊሰማዎት ይገባል:: »
✍️ ዶክተር ቤተልሄም👩🔬
✅ ስለ medicine ተጨማሪ መረጃዎችን ከፈለጋችሁ ከዶክተር አንደበት በvoice🎙 አጠር ያለ ማብራሪያ አዘጋጅተን ፖስት እናደርጋለን:: comment ላይ አሳዉቁን👇
ይቀጥላል.....ከተመቻቹ 🥺👍❤️
JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️
«
ይቀጥላል.....ከተመቻቹ 🥺👍❤️
JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤49👍13🙏7🥰4
Computer science ምን አይነት Department ነው
አብዛኛው ጊዜ ኮምፒውተር ሳይንስ ስትማሩ የምትወስዱት ኮርስ እነዚህ ናቸው
እና ሌሎችንም ጨምሮ ከኮምፒዩተር ጋር የተያያዙ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮች አሉ::
በቀላሉ አማርኛ COMPUTER
የሚገባበት ቦታ ሁሉ ላይ የComputer science ተመራቂ ይገባል
ምሩቅ በአሁን ሰዓት በ ወር ከ10,000 እስከ 15,000ብር እና ከዛ በላይ ያገኛል ግን በየመስሪያ ቤት ወይም በየ ደርጅት ይለያያል: በዛ ላይ ከ መደበኛ ስራ ውጪ በግል የራሳችሁን ስራ ለመስራት ስለሚመች በጣም አሪፍ ገቢ ይኖራችኋል።
ይቀጥላል.....
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤43👍11🥰5
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤
ስሙንም፦ ‘አማኑኤል፡’ ይሉታል፤”
የተባለው ይፈጸም ዘንድ ነው፤ ትርጓሜውም፦ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር፡” ነው።
ማቴ 1፥23
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤69🥰7🙏6👍5😱1
ከቆይታዎች በኋላ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚያወጣውን የጠበቆች ፈተና ተፈትናችሁ ጠበቃ መሆን ትችላላችሁ።
ይቀጥላል.....በቀጣይ ስለ ምን ይሰራ?
JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤39🙏15👍6🔥2
አሳዛኝ ዜና😭
ተወዳጁ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ከዚህ አለም በሞት ተለዬ።
ነፃነት በአጋጠመው ድንገተኛ ህመም ነው ዛሬ ረፋድ ላይ ከዚህ አለም የተለየው።
በቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢነት፣ በተዋናይነትና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ውስጥ ስመጥር እና ተወዳጅ ከሆኑ የጥበብ ሰዎች አንዱ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባደረበት ህመም በድንገት ከዚህ ዓለም ተለይቷል፡፡
ለበርካታ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን የሚተላለፈው የቤተሰብ ጨዋታ ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ የሆነው ነጻነት ወርቅነህ ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ነበር፡፡
የኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማኔጅመንትና ሰራተኞች ለቤተሰቦቹ፣ ለሙያ ባልደረቦቹ እንዲሁም አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል በማለት መግለጫ አውጥቷል።

😭206💔41😨23❤16👍1🕊1🆒1